Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
ለኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ደህንነት ተገቢውን ትኩረት እንስጥ!!!
በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ ከሚከሰቱ ጉዳቶች መካከል ምሰሶዎች በተሽከርካሪ መገጨት፣ ከፍተኛ ጭነት በጫኑ ተሽከርካሪዎች መስመሮች መቆረጥ፣ በመንገድ ዳር በሚገነቡ ግንባታዎች ምክንያት መስመሮች ላይ ጉዳት መድረስ፣ የመሬት ውስጥ መስመሮች በዘራፊዎች መሰረቅ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
እነዚህ ጉዳቶች ለህብረተሰቡ የሚቀርበው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረግ በከተማዋ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር ላይ ይገኛሉ፡፡
የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን ደህንነት ለማስጠበቅ የተለያዩ አዋጆችና መመሪያዎች ስራ የዋሉ ቢሆንም በመሰረተ ልማቱ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችንና ስርቆቶችን ማስቀረት አልተቻለም፡፡ በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት - የከተማው ነዋሪ፣ ልዩ ልዩ የአስተዳደር አካላት፣ የከተማው ፖሊስ እና ሌሎች ችግሩን በመከላከል ረገድ ከዚህ በፊት ያደርጉት ከነበረው ጥረት በላቀ ደረጃ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል፡፡
በከተማችን የተሳለጠ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን እውን ማድረግ የሚቻለው የኤሌትሪክ መሰረተ ልማት ደህንነት ሲረጋገጥ ነውና ሁላችንም ለኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ደህንነት ተገቢውን ትኩረት እንስጥ!!!
#የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ሰኔ 21/ 2016 አ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+4
ዛሬ የከተማ ግንባታ ሥራችን አንድ ስኬት የሆነውን ከሜክሲኮ እስከ ሳር ቤት ያለውን ሁለተኛውን የኮሪደር ልማት ስራ መርቀናል። መሰረተ ልማት ማጎልበት፣ የሥራ ባህል እና ታታሪነት፣ የእግረኛ መንገዶች፣ በቂ የተሽከርካሪ መንገዶች ለከተማ እድገት ወሳኝ ናቸው።
ያረጁ እና የተጎዱ የከተሞቻችንን ክፍሎች ማስወገድ ለትውልድ የተሻለ ከባቢን እና መፃዒ እድልን ለመተለም አስፈላጊ ርምጃ ነው። ከተጎዱ እና የጤና ጠንቅ በሆነ ከባቢ መኖርን ልንለማመደው አይገባም። የከተማችን የእድገት መንገድ ገና መጀመሩ እንደመሆኑ የለውጡን እድገት ቀጣይ ማድረግ ቁልፍ ነው። በጋራ ጥረታችን የተሻለ ነገን እናሳካለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
+7
በክረምቱ ወራት ከሚዘንበው ዝናብ ጋር ተያይዞ በዋና ዋና እና ውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ የተዘረጉ የፍሳሽ መውረጃ መስመሮች፣ ቱቦዎች፣ ማንሆሎች እና ክፍት የሆኑ ቦታዎች ሁሉ በቆሻሻዎች እንዳይደፈኑ ሁላችንም የመዲናችን ነዋሪዎች አካባቢያችንን ከወትሮው በበለጠ ፅዱ ማድረግ ይጠበቅብናል!
" እኛ ሁላችንም የከተማችን የጽዳት አምባሳደሮች ነን!"
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በክረምት ወቅት ለምን የኃይል መቆራረጥ ችግር ይከሰታል?
የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው በማሰራጫ መስመሮች እረጅና፣ በመሰረተ ልማት የጥራት ማነስ፣ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስ የመኪና፣ የእሳት እንዲሁም የስርቆት አደጋዎች እና የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ ነው፡፡
ከእነዚህ ምክንያቶች በተጨማሪ የኤሌክትሪክ መሰራጫ መስመሮች በዝናብና በነፋስ ሲነካኩ፣ ዛፎች በኤሌክተሪክ ገመድ ላይ ሲወድቁ ወይም ዛፎቹ ከኤሌክትሪክ መስመሩ ጋር ንኪኪ ሲፈጥሩ ብሎም የመብረቅ አደጋ ሲከሰት የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡
ዛፎች ከከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመሮች ጋር ሲነካኩ ወይም በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ሲወድቁ፣ በኤሌክትሪክ መስመሮች አቅራቢያ ግንባታዎች ሲከናወኑ፣ በመሬት ስር የሚቀበሩ የኤሌክትሪክ መስመሮች ሲጎዱ፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የኃይል ፍሰት ሲፈጠር፣ የሃይል ፍሰቱ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ መሬት ሲገባ በሳይንሳዊ አጠራሩ «ኧርዝ ፎልት» የተሰኘ የኃይል መቋረጥ ችግር ያጋጥማል፡፡
በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች መሰል ችግሮችን መመልከት የተለመደ ቢሆንም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የኃይል አስተላላፊ መስመሮች ያሉበት ከመሆኑ ጋር ተያዞ መስመሮቹ በሚያልፉበት አካባቢ በርካታ ዛፎች ስላሉ በዝናብ እና በነፋስ ወቅት የኤሌክትሪክ ገመዶች ከዛፎች ጋር በሚፈጥሩት ንክኪ ብሎም የዛፍ ቅርንጫፎች ገመዶች ላይ በሚያርፉበት ወቅት የገመድ መበጠስ ያጋጥማል፡፡
በዚህ ሁኔታ ኃይል ሲቋረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ መሬት ስለሚገባና የአደጋውን ትክክለኛ ቦታ በቀላሉ ለማወቅ አዳጋች ስለሚሆን የቴክኒክ ባለሙያዎች ችግሩን ፈልገው ደተጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ በርካታ ሰዓታትን ይጠይቃል፡፡
ተቋሙ የክረምቱን ወቅት ታሳቢ በማድረግ ክፍት የነበሩ የኃይል ገመዶችን በሽፍን የኤሌክትሪክ ገመዶች የመቀየር፣ መስመር ላይ ያረፉ ዛፎችን የማፅዳት፣ ያረጁ የእንጨት ምሰሶችን በአዲስ የመቀየር ስራዎችን በማከናዎን ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በመጪው የክረምት ወራት ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ እንዳይከሰት የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት የመንገድ ዳር የኤሌክትሪክ ፖሎችን እንዳይጎዱ ጥንቃቄ በማድረግ እንዳሽከረክሩ፣ ዛፍ የሚቆርጡ ብሎም የሚተክሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ መስመሮች እንዳያስጠጉ ብሎም ህገወጦችን እንዲከላከሉ አገልግሎቱ ከወዲሁ ጥሪውን ያስተላልፋል።
Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የህፃናት ተማሪዎችን የልደት ምዝገባን አስመልከቶ ለወለጆች የሚከተለውን መልእክት አስተላልፏል።
በከተማችን አዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ ስርዓት እንዲዳብር ፣ የህፃናት መብት ጥብቃን ለማጠናከር፣ ዘመናዊ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት ይቻል ዘንድ እንዲሁም ያልተመዘገበ ልደት ክምችትን ሙሉ ለሙሉ ለማቅለል የልደት ምዝገባ ሰርተፍኬትን በከተማዋ ላሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ቅበላ የምዝገባ ቅድመ ሁኔታ አሰራር ስርዓት ሆኖ በአስገዳጅነት ተቀምጧል።
ስለሆነም እስካሁን የልደት ምዝገባ ያላከናወኑ ህፃናት እና ተማሪዎች በወረዳ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ቀርበው ከወዲሁ እንዲመዘገቡ ከከተማው የትምህርት ቢሮ ጋር ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን ከመደበኛ ቀናት በተጨማሪ ከሰኔ 22 ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ሙሉ ቀን የዚህ ምዝገባ አገልግሎት ቀን መሆኑን አውቃችሁ ወላጆች እንድትገለገሉ በአክብሮት እንገልፃለን።
በኢ.ፌ. ዲ. ሪ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈፃፀም መመርያ ቁጥር 7/2010 መሰረት የምዝገባ ህግጋት የሚከተሉት ናቸው:
1. የምዝገባ ቦታን በተመለከተ:
* ወላጆች ነዋሪ የሆኑበት የወረዳ የሲቩል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት።
2. መታወቂያን በተመለከተ:
* የወላጆች ማንነትን የሚገልፅ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ከወረዳው አስተዳደር መደበኛ ነዋሪነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ወይም ከሚሰራበትመስሪያ ቤት ባልደረባነቱን እና ዜግነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤና የመስሪያ ቤቱን መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3. የወላጆችን በአካል መገኘት በተመለከተ:
ህፃናት ትክክለኛ ወላጆቻቸውን የማወቅ እንዲሁም ዜግነት የማግኘት መብታቸውን ጥበቃ ለማድረግ የሚከተሉት ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል:
* የህፃኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት እና እናት ሁለቱም በአካል መቅረብ ያለባቸው ሲሆን ልደቱን ለማስመዝገብከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሁለት አንዳቸው ያልቻሉ ሲሆን አንዳቸው ለሌላቸው ልዩ የልደት ውክልና በመስጠት ማስመዝገብ ይቻላሉ።
* ከወላጆቹ አንዱ በህይወት የሌለ እንደሆነ በህይወት ያለው ወላጅ የሟች ወላጅን ህጋዊ የሞትማስረጃ ሲያቀርብ ልደቱ ይመዘገባል፡፡
* ችሎታ የሌላቸው ሰዎች በተንከባካቢዎቻቸው ወይም በአሳዳሪዎቻቸው አማካይነትመመዝገብ ይችላሉ፡፡
* ዕድሜው 18 ዓመት እና በላይ የሆኑ ልደቱን ራሳቸውማስመዝገብ አለበት፡፡
4. ህጻኑ የተወለደው በጤና ተቋም ከሆነ የጤና ተቋም ማሳወቂያ መቅረብ ይኖርበታል።
5. ስም፣ የአባት ስም እና የአያት ስም በተመለከተ
* ለህፃኑ የተሰጠው የግል ስም፣ የወላጅ አባት ስም እና የአያት ስም ይመዘገባል፡፡ልደቱ ሲመዘገብ የህፃኑ አባት ያልታወቀ እንደሆነ የእናትየዋ አባት ስም የልጁ አባት ስም ሲሆንየእናትየዋ አያት ስም ደግሞ የልጁ አያት ስም ሆኖ ይመዘገባል፡፡
6. ዜግነትን በተመለከተ
* የህፃኑ ዜግነት ከወላጆቹ ተጠይቆ ይመዘገባል፡፡ከወላጆቹ አንዱ የውጪ አገር ዜጋ ከሆነ የህፃኑ ዜግነት በኢትዮጵያዊ ወላጅ ውሳኔ መሰረትይመዘገባል፡፡
የልደት ምዝገባ የህፃናት መብት ነው!
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙ
የአደጋ ጊዜ ልምምድ ማድረግ እዉነተኛ አደጋ በሚያጋጥም ጊዜ አደጋን ፈጥኖ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ገለጹ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክፍለ -ከተማው ወረዳ 5 ቱሪስት የጋራ መኖሪያ ቤት ሳይት ላይ ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የአደጋ ጊዜ ልምምድ አካሂዷል።
የልምምዱ ዋና ዓላማም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የእሳት አደጋዎችን ፈጣን ምላሽ በመስጠት በሰውና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ መታደግ እንደሆነ የልምምዱ አስተባባሪና በኮሚሽኑ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብቴ አማረ አስታዉቀዋል።
በልምምዱ ሂደት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጋር በትብበር ሲሰሩ ያገኛናቸው የቱሪስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስተባባሪ አቶ ባህሩ ሀጎስ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የተካሄደዉ የአደጋ ጊዜ ልምምድ በጋራ መኖሪያ ማህበሩ የሚኖሩ ነዋሪዎች አደጋን አስቀድሞ በመከላከልና በድንገት አደጋ ቢያጋጥም መወሰድ ሰለሚገባቸው እርምጃዎች ሰፊ ግንዛቤ እንደጨበጡ ጠቅሰዉ በአደጋ ጊዜ ድንጋጤን በማስወገድ እንዴት ተቀናጅቶ መስራት እንደሚቻልተገንዝቤያለሁ ብለዋል፡፡
በአደጋ ጊዜ ልመምዱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የአደጋ ምላሽ ባለሞያዎች ፣ የማዕከል የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ቡድን ፣ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፣ የፖሊስ አባላት ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቱ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ምንነትና ባህሪያት እና በማዘጋጃ ቤታዊ ኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂክ ሰነድ ላይ ያተኰረ ስልጠና ለሚዲያ እና ለኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች እና አመራሮች ተሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ምንነትና ባህሪያት፣ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚዲያ ሚና፣እንዲሁም የማዘጋጃ ቤታዊ የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂ ቀርቦ ከተለያዩ የመደበኛ እና የዲጂታል ሚዲያ እና ከኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች እና አመራሮች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን አስመልክቶ ትክክለኛ፣ ተአማኒና ወቅተታዊ ተጨባጭ መረጃዎችን ለነዋሪዎች በማድረስ የአሳታፊነት፣ የግልጽነት እና የተጠያቂነት ስርአትን በማጠናከር ረገድ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የሚጫወተው ሚና የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።
በመድረኩ ላይ የዘርፉ ምሁራንም በሚዲያ እና የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የተሰማሩ በየደረጃው ያሉ አመራሮችም ሆነ ባለሙያዎች የሙያ ብቃትን የተላበሱ፣ ሚዛናዊ እና ሞጋች የሆኑ መረጃዎችን ከትክክለኛው ምንጭ በመውሰድ ለህብረተሰቡ የማድረስ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲሰ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ በ2016 አ.ም አፈፃፀም ማጠቃለያ ምእራፍን የሚያይበት በ2017 አ.ም በጀት አመት የዝግጅት ምእራፍ አቅም የሚፈጥር ግምገማዊ ሰልጠና ለሰራተኞቹ በ2 ዙር መሰጠት ጀመረ።
የስልጠናው አላማም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰኪያጅ አጠቃላይ ሰራተኞች በ2016 በጀት አመት በነበረው የእቅድ አፈጻጸም የነበሩ ጥንካሬና ውስንነቶችን በመገምገም በቀጣይ 2017 በጀት አመት የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ማረጋገጥ የሚያስችል አቅም እንዲፈጥሩ ለማድረግ መሆኑን የአገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ መሰለ ሀጎሰ ገልፀዋል።
በሁለት ዙር ለሰራተኛው የሚሰጡ የስልጠና ርእሶች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ምንነት፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ማንዋል፣ ሙያዊ ስነምግባር፣ የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የእቅድ አዘገጃጀት በሚመለከት መሆኑ ተገልጿል።
ሰልጠናውም በየዙሩ ለ3 ቀናት ለገዳዲ በሚገኘው የአዲሰ አበባ ውሀ እና ፍሳሸ ባለሰልጣን የማሰልጠኛ ማአከል እየተሰጠ ይገኛል ።
17/10/2016
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
"የማንተገብረውን ቃል አንገባም ፤ ቃል የገባነውን እንተገብራለን!"
ከሜክሲኮ እስከ ሳርቤት ያለው የኮሪደር ልማት ስራችንን አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገምግመናል:: ከጥቂት የእርማት ስራዎች በስተቀር የተጠናቀቀ ሌላኛው የኮሪደር ልማት ስራች መሆንም ችሏል::
የኮሪደር ልማት ስራችን ትልቅ የመፈጸም ብቃት የታየበት ፣ ለየት ያለ የስራ ባህል የተተገበረበት ፣ ትብብር እና የመሰረተ ልማት ቅንጅት የተሻሻለበት ፣ በርካታ በከተማችን ውስጥ ያልነበሩ አዳዲስ የመሰረተ ልማት አገልግሎት እና ስታንዳርዶችን በአይነት ፣ በጥራት እና በውበት ለከተማችን ያስተዋወቅንበት
ለከተማችንና ለሃገራችን ትልቅ ብስራት ነው::
የከተማዋን ስታንዳርድ ለማስጠበቅ እና ለእግረኛ መተላለፊያነት እንዲውል ህንጻችሁን በማፍረስ እና በሰጠናችሁ ስታንዳርድ መሰረት እድሳት ያደረጋችሁ ተቋማት፣ የቤትና ህንጻ ባለቤቶችእንዲሁም በተለያየ መንገድ በስራው ላይ ለተሳተፋችሁ እና ለተባበራችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ::
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች መንገዶቹን በምንሰራባቸው ጊዜያት ለነበረው የትራፊክ መጨናነቅ እና ለተፈጠሩ መጠነኛ ውጣውረዶች ቅር ሳትሰኙ ላሳያችሁን ትዕግስትና ማበረታቻ ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ይህንን እና ሌሎቹንም ኮሪደሮች በቀሪ ጊዜያት ውስጥ አጠናቅቀን ለህዝባችንን አገልግሎት እንዲውሉ የምናደርግ ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"የማንተገብረውን ቃል አንገባም ፤ ቃል የገባነውን እንተገብራለን!"
ከሜክሲኮ እስከ ሳርቤት ያለው የኮሪደር ልማት ስራችንን አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገምግመናል:: ከጥቂት የእርማት ስራዎች በስተቀር የተጠናቀቀ ሌላኛው የኮሪደር ልማት ስራች መሆንም ችሏል::
የኮሪደር ልማት ስራችን ትልቅ የመፈጸም ብቃት የታየበት ፣ ለየት ያለ የስራ ባህል የተተገበረበት ፣ ትብብር እና የመሰረተ ልማት ቅንጅት የተሻሻለበት ፣ በርካታ በከተማችን ውስጥ ያልነበሩ አዳዲስ የመሰረተ ልማት አገልግሎት እና ስታንዳርዶችን በአይነት ፣ በጥራት እና በውበት ለከተማችን ያስተዋወቅንበት
ለከተማችንና ለሃገራችን ትልቅ ብስራት ነው::
የከተማዋን ስታንዳርድ ለማስጠበቅ እና ለእግረኛ መተላለፊያነት እንዲውል ህንጻችሁን በማፍረስ እና በሰጠናችሁ ስታንዳርድ መሰረት እድሳት ያደረጋችሁ ተቋማት፣ የቤትና ህንጻ ባለቤቶችእንዲሁም በተለያየ መንገድ በስራው ላይ ለተሳተፋችሁ እና ለተባበራችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ::
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች መንገዶቹን በምንሰራባቸው ጊዜያት ለነበረው የትራፊክ መጨናነቅ እና ለተፈጠሩ መጠነኛ ውጣውረዶች ቅር ሳትሰኙ ላሳያችሁን ትዕግስትና ማበረታቻ ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ይህንን እና ሌሎቹንም ኮሪደሮች በቀሪ ጊዜያት ውስጥ አጠናቅቀን ለህዝባችንን አገልግሎት እንዲውሉ የምናደርግ ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
