ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የጥበብ ስራ በአዳራሽ ብቻ የተወሰነ ባለመሆኑ እና ወደ ማህበረሰቡ ቀረብ እንዲል በከተማችን በተገበርነዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ የተለያዩ የዉጭ የኪነ ጥበብ ስራ የሚከወንባቸዉ ከ 160 በላይ አንፊ ቲአትርና ፕላዛዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አዉለናል :: ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኪነጥበብ ቤተሰቦችና ከያኒያን እንኳን ደስ አላችሁ…

የደመራና የመስቀል በዓል ያለ ምንም አደጋ ክስተት በሠላም ተከብሮ አልፏል። በአዲስ አበባ በደመራና በመስቀል በአል በዋዜማውም ሆነ በበአሉ ዕለት ምንም ዓይነት አደጋ ሳያጋጥም በሠላም ተከብሮ አልፏል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በዓሉ ያለ አደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ በተለያዩ አማራጮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ ሲተላለፉ የነበሩ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበሩ በዓሉ በሠላም ተከብሮ አልፏል። መላው የከተማው ነዋሪ እንዲሁም የሚዲያ አካላት በዓሉ ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ እንዲያልፍ ላደረጉት አስተዋጾ ኮሚሽኑ ምስጋውን እያቀረበ በበዓላት ጊዜ ሲደረጉ የነበሩ የጥንቃቄ ተግባራት በመደበኛ እንቅስቃሴዎች እና በቀጣይ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይም ጥንቃቄዎች ተጠናከረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽኑ ያሳስባል። ለእሳትና ስሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ ! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር መዘርጋት መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በያዝነው ሳምንት የሚከበረው የኢሬቻ በአል በተሟላ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንዳስታወቁት በመስከረም ወር ላይ በመዲናችን በርካታ እንግዶችና ነዋሪዎች የሚታደሙባቸው ሁለት ታላላቅ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በአላት ባማረ መልኩ እንዲከበሩ በጽ/ቤቱ ከማእከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ስራዎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። በዚህም ያለፈው መስከረም 16 እና 17 የተከበረው የደመራና የመስቀል በአል በመዲናዋ ነዋሪው በአሉን ባማረና በደመቀ ሁኔታ ማክበር እንዲችል መደረጉን ኢንጅነር ወንድሙ አክለው ገልፀዋል። በደመራና የመስቀል በአል እለት ከቅድመ አደጋ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ በተከናወኑ የመከላከልና ተገቢውን ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች በሁሉም አካባቢዎች የደመራ ማብራት ስርአት ምንም አይነት አደጋ ሳያስከትሉ በአሉ ባማረና በደመቀ መልኩ መከበሩን ኢንጅነር ወንድሙ አመልክተዋል። ከከተማ ፅዳት ጋር በተያያዘም በሁሉም የከተማችን ክፍሎች በየወረዳው እና ብሎኮች ከበአሉ አስቀድሞና በደመራ ዋዜማ ደግሞ የእምነት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሰፊ የጵዳት ንቅናቄ በማካሄድ ከተማዋን ፅዱና ውበ የማድረግ ስራ መከናወኑን ገልፀው የመስቀል በአል ማግስትም 1537 በላይ የደመራ ስፍራዎችን እና በየአካባቢው ያሉ ተረፈ ምርቶችን በፍጥነት የማንሳትና የማስወገድ ተግባር መከናወኑን አስገንዝበዋል። የኢሬቻ በአልም የአደባባይ በአል እንደመሆኑና በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አገራት ቱሪስቶችና እንግዶች የሚታደሙበት እንደመሆኑ ባማረና ከአደጋ ስጋት ነፃ በሆነ መንገድ እንዲከበር የከተማ ፅዳት እና ውበት፣ የቅድመ አደጋ መከላከል እና የመብራት አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን የተቀናጀና ተናባቢ በሆነ መልኩ ለየማጠናከር ጽ/ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በአፅንኦት ገልፀዋል።

በመዲናዋ የመጀመሪያው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ! በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የመጀመሪያውና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፣ በከንቲባ አዳነች አበቤ በይፋ ተመርቋል፡፡ አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ምን አካቷል? ባለ14 ወለል ህንፃ 2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶች የቲያትር አዳራሽ 3 የተለያዩ አዳራሾች ሆቴል እና ሪስቶራንት ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችና የፓርኪንግ አገልግሎት

ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉን የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን መርቀን ስራ አስጀምረናል ። የከተማችን አስተዳደር በሚሰራቸዉ የልማት ስራዎች ሁሉ ኪነ ጥበብን አበይት የትኩረት አቅጣጫዉ አድርጎ እየተገበረ ይገኛል ።በዚህም ባለፉት ጥቂት አመታት ነባሮቹን በማደስ እና ዘመናዊ እና ደረጃቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም አዳዲስ እና ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸዉ የቲያትርና የሲኒማ ኮምፕሌክሶች ገንብተን ለኪነ ጥበብ ዘርፉ እድገት አስተዋፆ እያበረከትን እንገኛለን ። ዛሬ ያስመረቅነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ፦ ባለ14 ወለል ህንፃ ፣2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶችን ፣የቲያትር አዳራሽ ፣ 3 የተለያዩ አዳራሾችን ፣ የሆቴል እና ሪስቶ ራት ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችን እና ፓርኪንግ አገልግሎት ይዟል ። የጥበብ ስራ በአዳራሽ ብቻ የተወሰነ ባለመሆኑ እና ወደ ማህበረሰቡ ቀረብ እንዲል በከተማችን በተገበርነዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ የተለያዩ የዉጭ የኪነ ጥበብ ስራ የሚከወንባቸዉ ከ 160 በላይ አንፊ ቲአትርና ፕላዛዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አዉለናል ። የኪነ ጥበብ ዘርፉ በፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ የዉስጥ ቁጭትን በመፍጠር ትዉልድን በመልካም ስራ እንድናንፅ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለዉ ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናችን አዲስ አበባ የደመራ በዓል የተከበረባቸውን ቦታዎች በሙሉ የማፅዳት ስራ ተካሄደ በመዲናችን አዲስ አበባ በትናንትናው እለት ባማረና በደመቀ ሁኔታ የተካሄደውን የመስቀል ደመራ በአል የተከናወነበትን የመስቀል አደባባይ ስፍራዎች ጨምሮ ከ1ሺህ 547 በላይ ደመራ የተደመረባቸውን ስፍራዎች በሙሉ የማፅዳት፣ የማጠብ እና ተረፈ ምርቱን የማሰነሳት ተግባር በዛሬው እለት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጠዋት መከናወኑን ከአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የመስቀል/ ደመራ በዓል ፅዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ከማድረግ ጀምሮ ዝግጅቱ የተደረገባቸውን ቦታዎች ሁሉ ፅዱ እንዲሆኑ የድርሻቸውን ለተወጡ የከተማችን የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎችና በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል። በመጪው ሳምንት በመዲናችን ባማረና ደማቅ በሆነ ሁኔታ ለሚከበረው እና የአደባባይ በአል ለሆነው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአልም በፅዱ፣ውብና ከአደጋ ስጋት በተጠበቀች መዲናችን እንዲከበር በሚከናወኑ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስራዎች ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጽ/ቤቱ ጥሪውን አቅርቧል። መስከረም 17/ 2018 ዓ.ም ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳሚ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ኃይማኖት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የእምነቱ አባቶች፣ የኃይማኖቱ ተከታዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የታደሙበት እና በመስቀል አደባባይ የተከናወነው የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ የፀጥታ አካላት በዓሉ በሠላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግና የበዓሉ አከባባር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት በመሰራቱ በስኬት ማክበር እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ህዝብ በስፋት ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው በዓላትና ኩነቶች በሠላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወሶ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም እያደረገ ላለው ቀና ትብብር እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የፀጥታና ደህንነት ተቋማት አባላት እና አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በፀጥታና ደህንነት ተቋማት ስም ምስጋናውን እያቀረበ የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ Addis Ababa Police ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የዘንድሮዉ የመስቀል ደመራ በዓል በርካታ ህዝብና ቱሪስቶች በተገኙበት እጅግ ባማረ እና በደመቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ ተከብሯል ! በዓሉ በደምቀት፣ እሴቱን ጠብቆ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ምስጋና ይገባችሁል። መልካም በዓል