Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አንፃር ከከተማዋ ነዋሪዎች ምን ይጠበቃል? በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ …
See more
አዲስ አበባ በአለም አደባባይ ሌላኛዋ የኩራታችን ምንጭ !
ባለፉት የለዉጥ አመታት ከተማችን አዲስ አበባን በሁለንተናዊ መልኩ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ፣ ለጎብኚዎቿ የተመረጠችና እንደ ስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን ብለን ከነዋሪዎቻችን ጋር ሌት ተቀን የሰራናቸዉ ስራዎች ይኸዉ ዛሬ ፍሬ አፍርተዉ በአለም አደባባይ አሸናፊ እያደረጉን ይገኛል ።
በተለያዩ መወዳደሪያ መስፈርቶች እየመዘነ እዉቅና እና ደረጃ የሚሰጠዉ የብሉምበርግ ፍላንተሮፒስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቻችንን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስና ለመቆጣጠር በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ በአጭር ጊዜ የሰራነዉን ስራና በተጨባጭ ያስመዘገብነዉን ዉጤት በመገምገም በአለም አቀፍ የከተምች የዘርፉ ዉድድር ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርጎናል ።
ይህንን እዉቅናና ክብር የሰጠንን ብሉምበርግ ፍላንተሮፒስን በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ እያመሰገንኩ በቀጣይም መዲናችንን በሁሉም መመዘኛዎች የተሻለች አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የበለጠ መትጋታችን ይቀጥላል ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
The Addis Ababa City Administration is sincerely grateful to Bloomberg Philanthropies for the worldwide recognition of our dedication to improving road safety and speed control. This honor is a great motivator for our future efforts and a clear testament to the success of our initiatives.
On behalf of the city administration and its residents, I want to express my profound thanks once more.
#Bloomberg #Philanthropies.#AddisAbaba.#RoadSafety.
የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አንፃር ከከተማዋ ነዋሪዎች ምን ይጠበቃል? በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከEBC ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ያነሷቸዉን ዋና ዋና ነጥቦች ይከታተሉ።
See less
የኤሌክትሪክ አገልግሎትን በማዘመን፤ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ሪፎርም ተግባራዊ በመደረጉ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚያስችል የሪፎርም ትግበራ ለከተማው የሚሰጠውን አገልግሎት ማዘመን አስችሏል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቀደም ብሎ ከአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ የደንበኞች መንገላታት፣ አገልግሎት መስጪያ ዴስኮች ምቹ አለመሆን፣ በተገልጋዩ ይነሱ የነበሩ እንግልቶችን ተግባራዊ ባደረገው ሪፎርም መቀረፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
አክለውም በአገልግሎቱ ላይ የሚስተዋሉ የነበሩ አሰራሮችን ወደ ወረቀት አልባ አሰራር በመተካት፣ የደንበኞች የጥሪ ማዕከላትን አውቶሜትድ በማድረግ ከጥገና ስምሪት ጋር አብሮ በማስተሳሰር የቀላጠፈና ውጤታማ ስራ መከናወኑ፣ ከደንበኞች በአገልግሎቱ ላይ ግብረ መልስ የመቀበል ስርዓት መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ አያይዘውም እንዲሁም የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቱንና ሀይል ስርጭት ጋር ተያይዞ ያለውን አሰራር በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በማዕከል ማስተዳደር አስተማማኝ ስርዓት መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ደንበኞች በየትኛውም ሰዓትና ቦታ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መምጣት ሳያስፈልጋቸው በሚኖሩ የክፍያ አማራጮች ሀይል መሙላት የሚችሉበት ስርዓት መፍጠር መቻሉንና በፓይለት ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ቀጣይ ደንበኞችን የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ከእንግልት እንደሚያስቀር አስታውቀዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን ሁለቱም ተቋማት ለከተማው ነዋሪዎች ከሀይልና ከመሰረተ ልማት አቅርቦት ጋር ተያይዞ በቅንጅት የሚሰሩ በመሆናቸው በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ግብዓት ለመውሰድ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያካሄደው ሪፎርም የከተማውንና የህብረተሰቡን የአሁንና መጪውን እድገት ታሳቢ ያደረገና የከተማዋን እድገት ጋር በሚመጥን ደረጃ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዘላቂ የሀይልና የመሰረተ ልማት አቅርቦት በቴክሎጂ የተደገፈ ስርዓት መተግበሩን ማየት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በጋራ ጥምረትና ትብብር ለከተማው የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉ ስራዎች ከማዕከል አገልግሎት መስጪያ፣ በመሰረተ ልማት ማዘመን በተለይም በኮሪደር ልማት መሰረተ-ልማቱን ከመሬት በታች በመዘርጋት፣ የሀይል አቅርቦቱን በአንድ ማዕከል ለማስተዳደርና ስርጭቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመፍታት የሚያስችል በሲስተም የተደገፈ ስራ መሰራቱን፣ የደንበኞችና የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሪፎርም መተግበሩን በመልካም ተሞክሮ ሊወሰዱ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኔትወርክ መሠረተ-ልማት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ በበኩላቸው በከተማዋ የሚከሰተውን የሀይል መቆራረጥ ለመፍታት የአጭር፣ የመካከለኛና ረጅም ጊዜ ዕቅድ በመያዝ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቱን ለማሻሻልና አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፉ ብዙ የመሰረተ ልማት ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
በመሰረተ-ልማቱ በኮሪደር ልማቱ ላይ ከመሬት በታች በመቅበር የተገኙ መልካም እድሎችን በማስፋትና የተዳከሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በማልማትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ የተሰሩ ስራዎች ይከሰቱ የነበሩ የሀይል መቆራረጦችን በመቀነስና በቀጣይ ወደ ዜሮ ለማድረስ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተለይም በአዲስ አበባ ጥራት ያለዉ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ ቁመና ላይ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ።
ከተማዋን ከእሳትና ከሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በመጠበቅ ረገድ የሚደረጉ ጥረቶችን የማገዝ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ም/ቤት መሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ ተናገሩ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ክንውን ላይ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዘርፎችና ስራ ክፍሎች እንዲሁም ባለሞያዎች ዛሬ ነሀሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ዕውቅና ሰጥቷል።
በዕውቅና መርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ም/ቤት መሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ እንደተናገሩት በአደጋ ጊዜ ሰዎች ከአደጋ ስፍራ ሲሸሹ የአደጋው ጊዜ ሠራተኞች የሠውን ህይወትና ንብረት ለማዳ ን ወደ አደጋ ውስጥ የሚገቡ ጀግኖች መሆናቸውን አስታውሰው ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተረድቶ እራሱን ከአደጋ እንዲከለከል አሳስበዋል ።
ዶ/ር ግዛቸው አያይዘው አደጋን ቀድሞ በመከላከል ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቅሰው በዚህ ሂደት ኮሚሽኑ እሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ም/ቤታቸው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በበኩላቸው እንደተናገሩት ኮሚሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአሳየው ከፍተኛ አፈጻጸም የአርንጓዴ ሠርተፍኬት ተሽላሚ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የከተማውን ነዋሪ እና የከተማውን ዕድገት ከአደጋ በመጠበቅ ረገድ የላቀ አፈጻጸም እንደሚመዘገብ እምነታቸው ገልጸዋል::
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከሚሸነር አህመድ መሀመድ በዕውቅና መድረኩ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ 2018 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በ 2017ዓ.ም ኮሚሽኑ ላስ መዘገበው ከፍተኛ ውጤት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ላደረጉ የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች ፣ ለአዲስ አበባ ም/ቤት መሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ለከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና ለባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመዲናችን አዲስ አበባ የነዋሪዎችን ህይወት የቀየሩ በርካታ የሰው ተኮር ስራዎች መከናወናቸው በይበልጥ የከተማችንን ገፅታ ለሚቀይር ስራ የሚያነሳሳን እንጅ የሚያኩራራን አይደለም ሲሉ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት በማዘጋጃ ቤታዊ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ክላስተር የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ እቅድ ያለፉት 75 ቀናት አፈፃፀም ሪፖርት በመስክ ምልከታና በሱፐርቪዥን በተደገፈ ሪፖርት ቀርቦ በተገመገመበት ወቅት ነው።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በ90 ቀን የልዩ ንቅናቄ አጀንዳ ትኩረት የተሰጠባቸው የተቀናጀ የሞዴል ብሎክ ፈጠራ፣የማእድ ማጋራት፣ የቤት እድሳት፣ የከተማ ፅዳትና ውበት ስራዎቻችን በእስካሁኑ የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበባቸው ቢሆንም ቀሪ ስራዎች በአመራር ቁርጠኝነት፣ በልዩ ተነሳሺነትና ትጋት አጠናክሮ በማስቀጠል በተያዘለት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አክለውም በማዘጋጃ ቤታዊ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ክላስተር በ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ የተያዙ የማእድ ማጋራት፣ የቤት እድሳት፣ የደም ልገሳ እና መሰል የንቅናቄ ስራዎች እንደ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት የመደጋገፍ ትስስራችን ያጎለበትንበት፣ የወገን አለኝታነታችን በተግባር ያረጋገጥንበት እንደመሆኑ በዚህ ረገድ እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች በመጪው አዲስ አመት ዋዜማም ይበልጥ የምናጠናክርበት ሊሆን ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።
በፅዳትና ከተማ ማስዋብ ስራዎቻችን ወንዞችን ከብክለት ነፃ የማድረግ እንዲሁም የሞዴል ብሎክና ሞዴል ወረዳዎች ፈጠራ ስራ በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነት ህብረተሰቡ ተረክቦ ራሱ እንዲያስተዳድራቸውና እንዲያለማቸው ታቅደው የተከናወኑ ከመሆኑ አንፃር በቀሩት ጥቂት ቀናት ለርክክብ ዝግጁ የሚሆኑትን የማጠናቀቂያ ስራዎች በአፋጣኝ በመጨረስ ለርክክብ ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎትን ይበልጥ የሚያዘምን የቴክኖሎጂ ሥርዓት በቅርቡ ይተገበራል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2017(ኢዜአ)፦ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎትን ይበልጥ የሚያዘምን የቴክኖሎጂ ሥርዓት በቅርቡ እንደሚተገበር የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ከሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት መካከል የነዋሪነት አዲስ መታወቂያ ማውጣትና ማደስ፣ የልደት ፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እንዲሁም የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት ማግኘት ይጠቀሳሉ፡፡
የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለኢዜአ እንደገለጹት ተቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ባካሄደው ሪፎርም ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል።
ሪፎርሙ በዋናነት በዘርፉ የነበረውን ብልሹ አሰራር መቅረፍ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ፣ አደረጃጀቶችን መቀየርና ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቅሰዋል።
ኤጀንሲው በከተማዋ በ11ም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 119 ወረዳዎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ ለነዋሪዎች ፈጣንና ቀልጣፋ መስተንግዶ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የተፈጠረው አሰራር ህገ ወጥ አካሄድን ከማስቀረቱ ባለፈ ቀደም ሲል በተቋሙ ይታይ የነበረውን የሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅትና ስርጭት ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ለማስፈን ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ነው ያሉት።
በቴክኖሎጂ የታገዘው ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር ዜጎች ሳይጉላሉ የሚፈልጉትን አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉንም ተናግረዋል።
በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶች በርካታ በመሆናቸው የማህበረሰቡን ፍላጎት በፍጥነት በመመለስ ረገድ ውስንነቶች መኖራቸውን ሃላፊው ጠቅሰዋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከርና ጉድለቶቹን ለመሙላት አሰራሩን ይበልጥ ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን ነው ያስታወቁት።
ለዚህ የሚረዳ ዘመናዊና ዜጎች በቀላሉ የሚገለገሉበት ቴክኖሎጂ መልማቱን በመጠቆም ቴክኖሎጂው ተገልጋዮች የሚፈልጉትን አገልግሎት ባሉበት ቦታ ሆነው የሚያገኙበትን አሰራር የሚዘረጋና በዘርፉ የሚሰጠውን የዲጂታል አገልግሎት ከፍ የሚያደርግ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ያገኙ ተገልጋዮች በበኩላቸው በዲጂታል የታገዘ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል ብለዋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት የልደት ካርድ ዲጂታል ለማድረግ የመጣችው ወጣት ዮርዳኖስ ኤርሚያስ አገልግሎት አሰጣጡ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዳገኝ ረድቶኛል ስትል ገልጻለች።
በዚሁ ወረዳ የነዋሪነት ማረጋገጫ ሰነድ ለማውጣት የመጣው ወጣት ከተማ መርጊያ በበኩሉ ቀደም ሲል በወረዳው ይሰጥ የነበረው አገልግሎት የተንዛዛና የአሰራር ስርዓት ያልተበጀለት እንደነበር አስታውሷል።
ወረዳው አሁን ላይ አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ በማዋሉ ቀልጣፋና ፍትሃዊ መስተግዶ ለማግኘት አንዳስቻላቸው ነዋሪዎቹ አስታወቀዋል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ መታወቂያ ለማሳደስ የመጡት ወይዘሮ አልማዝ ወልደሰንበት እና አቶ ኑሩ አብዱራህማን የጽህፈት ቤቱ ሙያተኞቸ ያደረጉላቸው ትብብር የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ
#Ethiopia
አገልግሎቶችን ያለ አግባብ ሲሰጡ የነበሩ ባለሙያዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው በዛሬው እለት እንዳስታወቀው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የነዋሪዎች ቡድን መሪን ጨምሮ አገልግሎቶችን ያለ አግባብ ሲሰጡ የነበሩ ባለሙያዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተካሄባቸው እንደሆነ አመልክቷል፡፡
ኤጀንሲው በደረሰው የተገልጋይ ጥቆማ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የነዋሪዎች አገልግሎት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ክብረት ቦጋለ እንዲሁም የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሞላ ልንገረዉን ያለአግባብ ለማይገባቸዉ ባለጉዳዮች የመታወቂያ እና ያላገባ ሰርቲፊኬት አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ሲታወቅባቸዉ ከህግ ለማምለጥ ጥረት ቢያደርጉም የተቋሙ የህግ ክፍል ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ክትትል በማድረግ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ማድረግ ችሏል ሲል ገልጿል፡፡
ኤጀንሲው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ህዝብን ሲያማርሩ የነበሩ ቡድን መሪና ባለሙያ ተቋሙ ለረጅም ጊዜ ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ስር በማዋል ከ26 በላይ የተለያዩ አላግባብ የተሰጡ መረጃዎችን በማስረጃነት ለፖሊስ ያስረከበ ሲሆን በተጨማሪም በወረዳዉ ሁለት የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛልም ብሏል፡፡
በተያያዘም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሁለት የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ ሁለት የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች ምንም መረጃ ለሌላቸዉ ተገልጋዮች የመታወቂያና የልደት ሰርተፊኬት ያለአግባብ በመስጠታቸው ከስራ ታግደው ክስ እንዲመሰረትባቸው ተደርጓል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኤጀንሲው ለከተማችን ነዋሪዎች ያስተላለፈው መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል።
ውድ ነዋሪዎቻችን
ተቋማችን እራሱን ከህገ-ወጥነት ለመከላከል የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና የስራ ክፍል እንዲሁም የህግ ክፍል በማደራጀት የመረጃ አቅምን እያጠናከረ ያለና የዲጂታል አገልግሎቱም ኦዲት የሚደረግበት ስርዓት የዘረጋ በመሆኑ ይህንን ተቋማዊ ቆራጥ አቋም በመረዳት ከህገ-ወጥ ደላሎች እና አገልግሎትን በገንዘብ ከሚሸጡ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እንዲሁም እራሳችሁም ተባባሪ ከመሆን እንድትቆጠቡ እያሳሰበ መሰል ሁኔታዎች በአገልግሎታችን ላይ ሲገጥማችሁ በ7533 የነፃ የስልክ መስመር ወይም ከታች ባለው የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ጥቆማ እንድትሰጡን ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን!!
ሌብነትን በፅኑ እንታገላለን!
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ መስመር 7533 ይደውሉ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
