Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን መካከለኛ አመራርና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረዉ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ልዩ ልዩ የሰራ ክፍሎች ለተዉጣጡ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በስሜት ልህቀት ፣ በሙያዊ ስነምግባር ፣ በተግባቦትና በቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያተኮረ ለሶስት ቀናት ሲሰጥ የቆየዉ የአሰልጠኞች ስልጠና ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠናቋል።
በስልጠናዉ ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ላይ በኮሚሽኑ የሰዉ ሀይል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘዉዱ ተፈራ እንደተናገሩት የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የስልጠና ማኑዋል በማዘጋጀት በዘርፉ ልምድና ዕዉቀት ባላቸዉ አሰልጣኞች ስልጠናዉ እንደሰጥ እንደዚሁም ለስልጠናዉ የሚያስጠይቀዉን ወጪ በመሸፈን ጽ/ቤቱ ላደረገዉ ከፍተኛ ድጋፍ አመስግነዉ በስልጠናዉ የተሳተፉ ሰልጣኞች በስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀትና መረጃ ለሌሎች የኮሚሽኑ ሰራተኞች ስልጠናዉን በልዩ ትኩረትና ዝግጅት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
የስልጠናዉ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ለሶስት ቀናት በነበራቸዉ የስልጠና ቆይታ ሰፊ ዕዉቀትና መረጃ እንዳገኙ ጠቅሰዉ በስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀት በቀጣይ በሚዘጋጀዉ የስልጠና መድረክ ለኮሚሽኑ ሰራተኞች ስልጠናዉን እንደሚያጋሩ ተናግረዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲደሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
የከተማዋን ጽዳት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተመላከተ
ግንቦት 1/2017 ዓ.ም
******************
የከተማዋን ጽዳት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ሚናቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አሳሰቡ፡፡
"ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ መንሰኤ ሊሆን አይገባም" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ለቀጣይ አምስት ወራት የሚካሄድ የጽዳት ንቅናቄ ተጀምሯል::
ንቅናቄው ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ድረስ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተመላከተው፡፡
በንቅናቄውም የዉሃ መውረጃ ቦዮች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች እና ወንዞች ላይ ትኩረት ተደርጎ የፅዳት ስራው ይከናወናል ተብሏል::
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የከተማዋን ጽዳት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ::
አንዱ ለጎርፍ መንሰኤ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ነዉ ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፅዳትን ከዘመቻ ባለፈ የዘወትር ተግባር ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳዳር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ለማ (ዶ/ር) ለጎርፍ የሚያጋልጡ ቦታዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል::
የግንባታ ተረፈ ምርቶችን እና ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከጎርፍ አደጋ የፀዳ አካባቢ መፍጠር ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
በመዲናችን እየተገነቡ የሚገኙት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው ተገለጸ
AMN - ሚያዝያ 30/2017
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ለተጠሪ ተቋማት የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ሰጥቷል።
በመዲናዋ እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የቀጣዩን ትውልድ ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉን የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ግዛቸው አይካ ገልጸዋል፡፡
በኮሪደር በለሙ የመንገድ ዳርቻዎች እና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባም ሰብሳቢው ገልጸዋል።
መጪው ጊዜ ክረምት እንደመሆኑ መጠን የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት የቅድመ መከላከል ስራ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው፣ የቋሚ ኮሚቴው ግብረ መልስ ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ እና የማህበረሰባችን ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
በቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ የተደረገባቸው ተቋማትም የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ፣ የሲቪል እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና በስሩ የሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
በዳንኤል መላኩ
በመዲናዋ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 30/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
''ወቅታዊ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ለዘላቂ ደህንነታችንና ዋስትና'' በሚል መሪ ሀሳብ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሒዷል።
ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ ከ378 በላይ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች በጥናት ተለይተዋል።
ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ አደጋ ያመጣሉ ተብሎ የተለዩ ከ170 በላይ ለሚሆኑት ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ቀሪዎችን የማጠናቀቅ ስራ ይከናወናል ነው ያሉት።
በዋናነትም የተደፈኑ የፍሳሽ መሰረተ ልማቶችን የማጽዳትና የማስተካከል ስራዎችን ማከናወን ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ አስረድተዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ጎርፍና ሌሎች ተያያዥ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በትኩረት በመስራት በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት መረባረብ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
በመዲናዋ የተካሔደው የኮሪደር ልማት የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን በእጅጉ የቀነሰ ነው ብለዋል።
የመንገድ፣ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታዎች የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው መገንባታቸውን ለአብነት አንስተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሀመድ በበኩላቸው፤ የምክክር መድረኩ ባለድርሻ አካላት በመዲናዋ የተለዩ የአደጋ ስጋት ቦታዎችን ለማሳወቅና በቅንጅት መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሕም አስቀድሞ ለመከላከልና አደጋ ሲከሰት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን የሚቻልበትን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል።
ኮሚሽኑ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየት የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ መርክነሕ ያእቆብ በበኩላቸው፤ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ እስካሁን በትብብር ሲሰሩ የቆዩ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛቸው አበበ የተቋማት በትብብር መስራት ማህበረሰቡ ጉዳት ሳይደርስበት አደጋን መከላከል ያስችላል ነው ያሉት።
በዚሁ ጎን ለጎንም ተቋማት አካባቢ የተጠያቂነት ስርዓትም ሊኖር እንደሚገባ ነው ያመለከቱት።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የሰው ተኮር ስራዎች መሰራታቸዉን እና እየተሰሩ መሆናቸዉን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል፡፡
ከንቲባዋ እንደገለፁት ምንም ገቢ የሌላቸዉ የከተማችን ነዋሪዎች በቀን 1 ጊዜ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ የከተማችን ነዋሪዎች አሁን 36 ሺ የሚሆኑ ወገኖቻችን ትኩስ እና ንፁህ ምግብ በቀን 1 ጊዜ መመገብ የቻሉበት እና በዚህም ምግብ ብቻ ሳይሆን ክብርም፤ፍቅርም ያገኙበት ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል::
በተጨማሪም ትዉልድ ላይ ትኩረት በማድረግ በተማሪዎች ምገባ በየትቤ/ቱ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን 2 ጊዜ እንዲመገቡ ማድረግ የተቻለበትና የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓት በሟሟላት የወላጆችን ጫናን ለማቃለል መንግስት ሃላፊነት ወስዶ እየሰራበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፤
ከንቲባዋ አክለዉም በሰዉ ተኮር ስራወች ሰፋፊ እና በሚሊዮን የሚቆጠር የስራ እድል መፍጠር የተቻለበት እና በመሰረታዊነት የሰዉ ህይወት የተቀየረበት መሆኑን ገልፀዉ በሴፍቲኔት ብቻ ወደ 100ሺ የሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ባለፉት ዓመታት ወደ ተሻለ ህይወት በተጨባጭ ማሻገር የተቻለበት ነዉ ብለዋል፡፡
ለመዲናችን የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በሙሉ እንኳን ለአለም ዓቀፉ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ቀን (International Fire Fighters day) አደረሳችሁ!
የዘንድሮው ዓለም ዓቀፉ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ቀን "ህዝባቸውን ከአደጋ ለመታደግ በጀግንነት፣በቆራጥነት እና በመሥዋእትነት ስራቸውን ለሚያከናውኑት የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞቻችን ክብር እንስጣቸው!" በሚል መሪ ቃል በመላዉ ዓለም እየተከበረ ይገኛል።
እለቱ በመላው አለም የሚከበረው የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በስራቸው የሚያጋጥማቸውን አደጋ ተጋፍጠው የሰው ልጅ ህይወትንና ንብረትን ለመታደግ ለሚከፍሉት ዋጋና ለህዝብ ለሚሰጡት ክቡር አገልግሎት እውቅና ለመስጠት በማለም የሚከበር ቀን ነው።
በመሆኑም በመዲናችን አዲስ አበባም እለቱን በተለያዬ ዝግጅቶች በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለመዲናችን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እንኳን አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
