ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+4

የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም ገመገመ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የኤጀንሲውን የ9 ወራት ሪፖርት ግምገማ በዛሬው እለት ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ባካሄደበት ወቅት በተለይም በሪፎርም ሰራዎች ትግበራ፣ በመደበኛ የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ፣ በቴክኖሎጅ ትግበራ በሰው ሀብት ልማት: ብልሹ አሰራርን በመታገል እና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ከአፈፃፀም ንፅፅር ጋር በሰነድ ቀርቦ ተገምግሟል:: መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንደገለፁት ኤጀንሲው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ያከናወናቸው ተግባራትና፣ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ የተጠያቂነት ሰርአትን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ሰራዎችና እየተገኙ ያሉ ውጤቶች ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው መሆኑን ገልፀዋል:: አክለውም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ከማሳደግና ከማዘመን አንፃር እየተከናወኑ የሚገኙ ሰራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው የተቋም ግንባታ ሰራዎች ወጥ እና ተናባቢ በሆነ መንገድ ከማአከል እስከ ወረዳ መተግበር እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል:: ባለፉት ዘጠኝ ወራት ታቅደው ያልተፈፀሙ ተግባራትን በቀሪ ወራት በትኩረት ሰርቶ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን አሳሰበው በቀጣይም ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጉዳይ ትኩረት በመስጠት: ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ለህብረተሰቡ ግልፅነት የመፍጠር ስራም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል:: በማጠቃለያም የ2017 በጀት አመት እቅድ ላይ ከወዲሁ አዳዲስ አሰራሮችን የመዘርጋትና የመተግባር ጉዳይን ትኩረት በመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ አቅጣጫ አሰቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እና የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደጋን በመከላከል ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባ
+6
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እና የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደጋን በመከላከል ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባና አካባቢዉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ዘርፍ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በትብብር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸዉን ዉይይት ዛሬ ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም አካሄዱ። በመርሀ ግብሩ ላይ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ሁለቱም ተቋማት ተመሳሳይ ተልዕኮ ያላቸዉ ከመሆኑ አንጻር አደጋን ለመቀነስ በሚደረገዉ ጥረት መተጋገዝ እንደሚገባ ጠቅሰዉ ይኸንንም እዉን ለማድረግ በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ተግባር ያስፈልጋል ብለዋል። አቶ ፍቅሬ ግዛዉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ሁለቱ አንጋፋ ተቋማት የአካበቱት ልምድና እዉቀትን በማቀናጀት የአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ስራችንን በተደራጀና በዘመነ መንገድ ማከናወን የምንችልበትን እድል እንፈጥራለን ብለዋል። በመርሀ-ግብሩ ላይ ሁለቱም ተቋማት ከምስረታቸዉ ጀምሮ አሁን የደረሱበት ደረጃ በተቋማቱ በኩል የቀረበ ሲሆን ተቋማቱ በጋራ የሚሰሩበት የመጀመሪያ ደረጃ የመግባቢያ ሰነድ ረቂቅ ቀረቦ አስተያየት ተሰጥቶበታል። ይኸዉ ሰነድ መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎበት በቀጣይ ሳምንት የስምምነት ሰነዱ በመፈራረም ወደ ተግባር እንደሚገባ ተመላክቷል።

photo content
+9

የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣንና ከአዲስ ሚዲያ ኔት ወርክ ጋር በመተባበር 'ጽዱና ምቹ አዲስ አበባ ለመፍጠር የተቋማት ቅንጅታዊ ስምሪት ያለው ፋይዳ' በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት አካሄደ። አቶ ካሳሁን ጎንፋ የአዲስ ሚዲያ ኔት ወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የከተማዋን ጽዳት ማስጠበቅ የሁሉም ሰው ኃላፊነት እንደመሆኑና ከተማዋ ጽዱና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን ቅንጅታዊ አሰራር በማስፈለጉ ይህ መድረክ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አዱስ አበባ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማት መቀመጫ: የአፍሪካ መዲናና የአገራችን ዋና መዲና እንደመሆኗ እንደነ ኪጋሊ በጽዳትዋ የተመሰከረላት እንድትሆን ቅንጅታዊ አሰራር በማስፈለጉ ይህ የፓናል ውይይቱ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ዶክተር እሸቱ ለማ የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው በከተማዋ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ እያንዳንዱ ነዋሪ በአግባቡ እንዲያስወግድ ከሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት በርካታ የግንዛቤ ስራዎች ተሰርተዋል። ኃላፊው አክለውም ከዚህ ባለፈ ለሚከሰት ህገ ወጥ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ የደንብ ቁጥር 150/2015 ተፈጻሚ እንዲሆን ከደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ለከተማዋ ጽዳት የእያንዳንዱ ሰው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ይህ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል። ለውይይት መነሻ የሚሆነውን ሰነድ ያቀረቡት የደንብ ማስከበር ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ናቸው። ከአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለውይይት የሚሆነውን ሰነድ ያቀረቡት አቶ ምትኩ ሄርዻ የግንዛቤ ስርጸትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ ምንም እንኳን ደንቡን ለማስከበር የሚታትሩ በርካታ የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ቢኖሩም በጣም ጥቂት የሚባሉ ባለሙያዎች ግን ለህጉ ተፈጻሚነት ቸልተኝነት እንዳለ ጠቁመዋል። በመቀጠል በቀረቡ ሰነዶች ላይ ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱን ያወያዩት ዶ/ር እሸቱ ለማ; ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና አቶ ካሳሁን ጎንፋ ሲሆኑ በውይይቱ ከተሳታፊዎች እንደ አዲስ አበባ የከተማዋ ጽዳት የተፈለገበት ደረጃ እንዲደርስ የተቋማት ሚና ብቻ በቂ አይደለም። ነዋሪው የከተማዋ ጽዳት የኔ ነው ብሎ መውሰድ ላይ ችግር አለበት። ስለዚህ ደንቡን የተላለፉ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል። አወያዮቹ በተነሱ ሐሳብና አስተያየቶች ላይ ምላሽ ሰጥተው የፓናል ውይይቱ ተጠናቋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በአዲስ አበባ ከተማ የቅድመ አደጋ መከላከልና የከተማዋ ፅዳት ጉዳይ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ምን ይላሉ? ኢቢሲ ኤፍኤም 97.1 "አዲስ ፎረም" ፕሮግራምን በፌስቡክ ገፃችን እንዲከታተሉ እነሆ ብለናል :: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የፕላስቲክ እና የቆሻሻ ብክለት ሥነ ምኅዳራችንን እና ጤናችንን አደጋ ላይ ይጥላል። በኃላፊነት ስሜት ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ እና ዘላቂ አማራጮችን በመምረጥ ተፈጥሮን ለትውልድ ማቆየት እንችላለን። ከተሞቻችን እና አካባቢያችን ጽዱ ለማድረግ እንተባበር። Faalamni pilaastikiifi balfaa naannawaa keenyaafi fayyaa keenya balaarra buusa. Akkaataa ittigaafatamummaa qabuun balfa karaa sirrii ta'een dhabamsiisuudhaan akkasumas filannoo fulla'a ta'etti fayyadamuudhaan uumama dhalootaaf tursuu ni dandeenya. Magaalotiifi naannawaa keenya qulqulluu gochuudhaaf haa tumsinu. Plastic and waste pollution threatens our environment, ecosystems, and health. By consuming consciously, disposing responsibly, and choosing sustainable alternatives, we can preserve our natural world for generations to come. Let's unite to keep our cities and environment clean.

ቅድሚያ ለደህንነትዎ ይስጡ! ከጥንቃቄ ጉድለት በኤሌክትሪክ አደጋ የሚደርስ የህይወትም ሆነ የንብረት ጉዳትን መከላከል ይችላሉ፡፡ እንዴት አይሉም? ኤሌክትሪክ እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም፤ ከአጠቃቀ
ቅድሚያ ለደህንነትዎ ይስጡ! ከጥንቃቄ ጉድለት በኤሌክትሪክ አደጋ የሚደርስ የህይወትም ሆነ የንብረት ጉዳትን መከላከል ይችላሉ፡፡ እንዴት አይሉም? ኤሌክትሪክ እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም፤ ከአጠቃቀም ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ አደጋ ያስከትላል፡፡ እባክዎ በቅጽበት ህይወታችንን እና ንብረታችንን ሊያሳጣን ስለሚችል፤ ሁልጊዜ ጥንቃቄ ማድረጉን አይዘንጉ! በቤት ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚገለገሉባቸው ቁሳቁሶች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ኃይል የማያባክኑና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብዎ! ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ጋር ያለዎትን ግንኙነትም ጥንቃቄውን የጠበቀ ያድርጉት! በየአካባቢው የሚገኙትን የኤሌክትሪክ ማሰራጫ አውታሮች ማለትም ምሰሶዎች፣ ማስተላለፊያ ሽቦዎች እና ሌሎችንም ከመነካካት ይቆጠቡ! በመስመሮቹ ዙሪያ ልጆች ጨዋታ እንዲጫወቱ አይፍቀዱ! በጣም ተጠግተውም የንግድ ሥራዎች አያከናውኑ! ጥንቃቄ ማድረግ ለራስ ነውና ቅድሚያ ለደህንነትዎ ይስጡ! #ኤሌክትሪክአገልግሎት ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+4

ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ውጤታማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው" አቶ ጫሊ ቤኛ የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የ2016 በጀት አመት የቅንጅታዊ አሰራር 9 ወራት አፈፃፀምን በዛሬው እለት ገምግሟል። በክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት አስተባባሪነት የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የ9 ወራት የቅንጅታዊ አሰራር የዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል። በግምገማ መድረኩ ባለፉት 9 ወራት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ፣ የሲቪል ምዝገባ አገልግሎት እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ የቅንጅታዊ አሰራር ሪፖርት የቀበረ ሲሆን በሪፖርቱም በሶስቱ ተቋማት በቅንጅታዊ አሰራር የተሰሩ ተግባራት አፈፃፀም ቀርቧል። በግምገማ መድረኩን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጫሊ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ውጤታማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተው የዘጠኝ ወር የተቋማቱ ቅንጅታዊ አሰራር አፈፃፀም ከተሰጣቸው ተልእኮ አንፃር ውጤታማ እንደነበር በመግለፅ በቀጣይ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ክፍተቶችን ማረም ለተሻለ ስራ መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዩ ጌታቸው በበኩላቸው አስተዳደሩ ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች በተለየ መንገድ ቅንጅታዊ አሰራርን የሚፈልጉ በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። በግምገማው ባለፉት 9ወራት በሶስቱ ዘርፎች በቅንጅት በተሰሩ ተግባራት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍኤም 97.1 ጋር በመተባበር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከሆኑ የፅዳት አምባሳደሮች (ሻምበል አርቲስት ስዩም ዘለቀ: አርቲስት ሙሉነህ ዘለቀ እና የፅዳት አምባሳደር ሰለሞን ፀሐይ) እና የማህብረሰብ ተወካዮች ጋር በከተማው ፅዳት ላይ የተካሄደ ውይይት ላይ ያተኮረ የሬድዮ ፕሮግራም እንዲከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!

አካባቢዬን አፀዳለሁ ፅዳትን ባህል አደርጋለሁ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በኮሪደር ልማት ተነስተው በወረዳ 05 ተገጣጣሚ ቤቶች እጣ ከወጣላቸው ነዋሪዎች ጋር ''አካባቢዬን አፀዳለሁ፤ ፅዳትን
+7
አካባቢዬን አፀዳለሁ ፅዳትን ባህል አደርጋለሁ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በኮሪደር ልማት ተነስተው በወረዳ 05 ተገጣጣሚ ቤቶች እጣ ከወጣላቸው ነዋሪዎች ጋር ''አካባቢዬን አፀዳለሁ፤ ፅዳትን ባህል አደርጋለሁ'' በሚል መሪ ቃል የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የፅዳት ሰራተኞች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የፅዳት መርሀ-ግብር አካሄዷል ። የብልፅግና ፓርቲ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መዝገቡ ይስማው ባስተላለፉት መልዕክት ከልማት ተነሺዎቹ ጋር በሁሉም ጉዳዮች ከጎናቸው መሆናችንን ለማሳየት ያለመ መርሐግብር መሆኑን ጠቅሰው ክ/ከተማው ነዋሪው የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ነዋሪው የራሱንም ሆነ የአካባቢውን ንፅህና ሊጠብቅ እንደሚገባም አሳስበዋል። Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

photo content
+3

የከተማችን ፅዳት በዘላቂነት መጠበቅ ሁላችንንም ይመለከተናል! ደረቅ ቆሻሻን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያለው ሕግ ምን ይላል? የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 92 ዜጎች በንፁህና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል፡፡ ይህንንም ድንጋጌ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ አዋጆች በአስፈጻሚው አካል የወጡ ሲሆን ከነዚህም አዋጆች መካከል የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አዋጅ አንዱ ነው፡፡ በደረቅ ቆሻሻ አያያያዝ አዋጅ ቁጥር 513/1999 ከቆሻሻ ሊከተል የሚችልን አሉታዊ ተፅዕኖ እየተከላከሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳውን ማጎልበት የሚያስችል አቅምን በመገንባት ዜጎች በህገ መንግስቱ ያገኙትን በንፁህና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት ማረጋገጥ እንደሚገባ በግልፅ ተመላክቷል ፡፡ ለመሆኑ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት መዘርጋት ለምን ያስፈልጋል? ቆሻሻ በአካባቢና በሰው ልጅ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተጽዕኖና የሚፈጥረውን ሁለንተናዊ ችግር በመቅረፍ ተስማሚና የሰው ልጅ የመኖሪያ አካባቢ እንዲኖር ማድረግ ስለሚያስፈልግ፣ የተፈጥሮ ሀብት በዘላቂነት እንዲጠበቅና እንድንጠቀም ስለሚያግዝ ፣ የንፁህ ውሃ መገኛ አካባቢዎችን እንዳይበክሉ ስለሚያደርግ ፣ የአካባቢ አየር መበከልን ስለሚቀንስ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም እንደ አንድ ሀብት ተደርጎ እንዲቆጠር ግንዛቤ ይፈጠርበታል:: አካባቢያችን ፅዱ ለማድረግ ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል? የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርአትን መዘርጋትና የግል ዘርፍና የባለድርሻ አካላት ግንዛቤና ተሳትፎ በድጋፍ ረገድ ማሳደግ በዘርፉ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸው ሃገሮች ልምድ መቀመር እና ማስፋፋት ፣ወጥ የሆነ ስታንዳርድ ማዘጋጀት፣ቆሻሻ እንደ ሀብት በመቁጠር ጠቃሚ ክፍሉን በመለየት ጥቅም ላይ ማዋል ቆሻሻን በተገኘው ቦታ ሁሉ አለመጣል፣ቆሻሻን በየቦታው የሚጥሉ ግለሰቦችን በዝምታ አለማለፍና አፀያፊ ተግባርም መሆኑን መናገር፣ ቆሻሻን አለአግባብ በየቦታው መጣል አፀያፊና ነውር ነው ብሎ መውሰድ፣ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት በየቦታው ማስቀመጥ፣ በየቦታው የሚሰበሰቡና የሚጠራቀሙ ቆሻሻዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ማስነሳት፣ በተለይ ወረቀቶች ፣ ብረታ ብረቶች፣ ኘላስቲኮች፣ ብርጭቆዎችና ጠርሙሶች እየለዩ በማስቀመጥ ለሚፈልጋቸው አካላት መስጠት፣ በሁሉም ህብረተሰብ ላይ ግንዛቤ መፍጠር በማይማሩና በሚያጠፋ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሠድ ያስፈልጋል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+9

የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ፅ/ቤት በተጠሪ ተቋማት እየተካሄዱ ባሉ የቴክኖሎጂ ዝርጋታዎች ተግባራዊ አፈፃፀም ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያየ:: በከተማ ሰራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት በተጠሪ ተቋማት ላይ ተግባራዊ የተደረጉ የቴክኖሎጂ ዝርጋታ ኘሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል ውይይት በዛሬው እለት ከተካሄደ በሁዋላ በላቀ ደረጃ ለማጠናቀቅ ከተቋማቱ፣ ከከተማው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ቢሮ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስራዎችን በጋራ ተመልክቷል። በዚሁ ወቅት በተለይም በእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ኘሮጀክት የቅድመ አደጋ ጥንቃቄ የማንቂያ መረጃ መስጠት መጀመሩ ስራዉ ሲጠናቀቅ በከተማው የአደጋ መከላከል ላይ ትልቅ ለዉጥ እንደሚያመጣ አመላካች መሆኑ በዉይይቱ ወቅት ተገልጿል። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለፁት የተጀመሩት ኘሮጀክቶች ግዙፍ እንደመሆናቸው የሁሉም ተቋማትን ተሳትፎ የሚጠይቁ በመሆናቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኘሮጀክቶቹን በተያዘላቸዉ ግዜ ተጠናቀዉ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል::በሂደቱ የታዩ ክፍተቶችን በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ በመውሰድ ኘሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚገባም አሳስበዋል:: አክለውም በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ኘሮጀክቶቹ ተግባራዊ የተደረገባቸው ከተጠሪ ተቋማት ማለትም በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ :- የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና በፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በኩል ኘሮጀክቶቹ እንዲጠናቀቁ በጋራና በትብብር የመስራት ጉዳይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም በአጽንኦት ገልጸዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚከናወነው ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሚያዚያ 05/2016 ዓ.ም በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወነው ብሎክን መሠረ
+9
በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚከናወነው ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሚያዚያ 05/2016 ዓ.ም በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወነው ብሎክን መሠረት ያደረገው ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው 40/60 አካባቢ ከማለዳው 12:30 ጀምሮ በድምቀት ተካሂዷል:: በዚሁ ስፍራ በተደረገው ፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አማካሪ አቶ ይብሬ እስማኤል የከተማዋን ፅዳት ለማረጋገጥ በፅዳት ስራው ላይ ህ/ሰቡ ባለቤት እንዲሆን በርካታ ተግባራት መከናወኑን አስታውሰው በተሰራው ቅንጅታዊ ተሳትፎ በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ ለውጥ መምጣቱን ገልፀዋል። የመጣውን ለውጥም ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማስቀጠል የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ እያንዳንዱ አካል በአካባቢ ፅዳት ላይ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባው አሳስበዋል። በንቅናቄው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች : የፀጥታ አካላት : የደንብ ማስከበር አካላት : የስፖርት ቤተሰቦች : የተለያዩ አደረጃጀቶች እና የአካባባው ነዋሪ ህብረተሰብ ተሳትፈዋል።

photo content

የኮሪደር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተቀናጀ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ ነው በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ስራ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተቀናጀ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። የአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ገበየሁ ሊካሳ፤ በመዲናዋ ከኮሪደር ልማቱ ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይቋረጥ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ስራ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሃይል አቅርቦት እንዳይቋረጥ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።በመሆኑም የኮሪደር ልማት ስራ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተቀናጀ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ከኮሪደር ልማቱ በተጓዳኝ ዘላቂ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት።በቀጣይ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቱ የሚዘረጋበት ቋሚ ቦታ እንዲኖር ያደርጋል፤ይህም በእቅድ ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት ያስችላል ብለዋል። ከዚህ በፊት የተቀናጀና ቋሚ ቦታ ባለመኖሩ የተሰራው ስራ ተመልሶ ሲፈርስ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ በተጠና መልኩ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።የኮሪደር ልማቱ ዘላቂና የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ስራን መሰረት ያደረገ አዲስ የልማት ክንውን ስለመሆኑም ገልጸዋል። በቀጣይ የእግረኛ መንገድን መቆፈር ሳያስፈልግ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን ከመሬት ስር ለመዘርጋት ያስችላል ሲሉም ተናግረዋል።ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የመስመር መቀየርና አቅም የማሳደግ ስራ በመከናወኑ ሃይል መቆራረጡ እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው ዘላቂ ለማድረግ ደግሞ የቅንጅት ስራ ያስፈልጋል ብለዋል። በከተማዋ አሁንም የእንጨት ምሶሶዎችን በኮንክሪት የመቀየር፣ ከዚህ በፊት የነበረውን ገመድ በፕላስቲክ በተሸፈነ የመቀየር ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በአራት ምዕራፍ የተከፈለ የኤሌክሪቲሪክ አገልግሎት የዲስትሪቢዩሽን ስራ እየተከናወነ ስለመሆኑም አንስተዋል። በሁለት ምዕራፍ የተሰሩት ሲጠናቀቁ የሶስተኛው ምእራፍ አፈፃፀም 73 በመቶ መድረሱን ጠቅሰው አራተኛው ምእራፍ ደግሞ በ2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል ብለዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ

ህብረተሰቡ በክረምት ወቅት ሊከሰቱ ለሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች እንዳይጋለጥ የቅድመ-መከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማው የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ
+7
ህብረተሰቡ በክረምት ወቅት ሊከሰቱ ለሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች እንዳይጋለጥ የቅድመ-መከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማው የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ውይይት አድርገዋል። የክፍለ ከተማው አስተዳደር የክረምት ወቅት ሳይገባ በፊት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታሰዎችን በመለት የቅድመ-መከላከል ስራ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ከነዚህም ስራዎች መካከል ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑትን ነዋሪዎችን ምትክ የማመቻቸት ስራ በመሰራት ላይ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ህብረተሰቡ ለጎርፍ አደጋ መከሰት ምክኒያት የሆኑ ደረቅ ቆሻሻዎችን፣ የግንግባታ ተረፈ-ምርቶች እና መሰል የአደጋ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በማስወገድ መከላከል እንደሚገባው ወ/ሮ አይዳ አሳስበው ሁሉም የባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ በበኩላቸው ድንገተኛ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት ቀድሞ መከላከል ላይ በትኩረት መስራቱ ተገቢ በመሆኑ የቅድመ መከላከል ስራውን ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!