Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
Ethiopia is deeply honoured to receive the torch and assume the responsibility of hosting the fifth P4G Summit in 2027. We embrace this opportunity with determination and an unwavering commitment
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። አጀንዳዎቹም ፦
1ኛ. ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል።
2ኛ. የብርሃን አይሰውራን፣ የመነን እና የገላን ቦርዲንግ ት/ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበዉን ደንብ መርምሮ አጽድቋል ::
3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ተገቢነት ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ አጽድቋል::
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት እና በተጠሪ ተቋማት የትንሳኤ በአል ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ዝርዝር ዘገባን ከፕራይም ቲቪ ይመልከቱ
መጪው የትንሳዔ በዓል ባማረ እና በደመቀ መልኩ እንዲከበር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወናቸውን አስታወቁ::
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የከተማው የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ ቤት በቀጣይ የሚከበረው የትንሣኤ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የተሻለ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ፅ/ቤቱ ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በዛሬዉ እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለፁት በቀጣይ የሚከበረው የትንሣኤ በዓል ህብረተሰቡ በዓሉን በሰላምና ከአደጋ ስጋት ተጠብቆ፣ጽዱ እና ማራኪ በሆነች ከተማ እንዲያሳልፍ በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ደረጃና በተጠሪ ተቋማቱ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ ለመስጠት የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን በዝርዝር አስረድተዋል።
ለዚህም ጽ/ ቤቱ ከማእከል እስከ ታችኛው መዋቅሩ፣ከተጠሪ ተቋማት ጋርና ከከተማው የተለያዩ ተቋማት ጋር የቅንጅት ስራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን ገልፀው ለሚያጋጥሙ የአገልግሎት መቆራረጥ ፈጣን የሆነ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረሀይል መቋቋሙን ገልፀዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮማንደር አህመድ መሀመድ መጪዉ በዓል ከአደጋ ነፃ ሆኖ በሰላም እንዲያልፍ በተለያዩ አማራጮች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዉ ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታዉቀዋል።
የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ እንዳሳወቁት ከበአል ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመነጨዉ ቆሻሻ የከተማችንን ጽዳት እንዳያጓድል ስለቆሻሻ አወጋገድ ለህብረተሰቡ ሰፋፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሠራቱን ተናግረዋል።
ከበአሉ አከባበር ጋር ተያይዞ የሚኖረው የእርድ ተረፈ ምርቶችን አካባቢን እንዳያቆሽሽ ህብረተሰቡ በተዘጋጁ የቆሻሻ ማስወገጃዎች ቦታዎች በአግባቡ ማስወገድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስተቢበሪያ ጽ/ ቤት ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጂሳ ካሳ እንደገለፁት በበዓሉ ወቅት ሰፊ የሆነ የሀይል ፍላጎት ስለሚኖር ይህንን ከግምት ዉስጥ በማስገባት በተቋሙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸዉን ተናግረዉ ከሀይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ ክፍል እንደተዘጋጀም ጠቅሰዋል። ለቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የበዓል ቀን ጨምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥም አሳዉቀዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የተቋማትን አሰራርን ለማዘመን እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልየተጠኑጥናቶች ሰነድ ርክክብ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የጥናት እና ልማት ትግበራ ዘርፍ ከዚህ በፊት ለፅ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የነበሩት ማለትም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትና የህዝብ መዝናኛና ፖርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የአገልግሎት አሰጣጥን እና አሰራራቸውን ለማዘመን የተጠኑ የ10 አመት ፍኖተ ካርታ ሁለት ጥናቶች በዛሬው እለት የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ከፍተኛ አመራሮች የከተማው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለስልጣን፣ የቄራዎች ድርጅት እና የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት የሰነድ ርክክብ ተካሂዷል።
በዚሁ መድረክ በሁለቱም ተቋማት በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡን ስርዓት ከማሻሻል፣የሚሰጠዉን አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ከማገዝ እና ከማዘመን አንፃር መፍትሄ ሰጪ የሚሆን የጥናቱ ግኝት ለተሳታፊዎች ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተካሂዶበታል።
በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለፁት የተጠኑት ሁለቱም ጥናቶች በቀጣይ ለሁለቱም ተቋማት ተግባራዊ የሚያደረጓቸው ስራዎች የሚስተዋሉ ክፍተቶችን የሚሞሉና የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ብሎም የአገልግሎት አሰጣጡን ከማዘመን አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።
አክለዉም የተጠኑት ጥናቶች በቀጣይ ተቋማቱ ለነዋሪው የሚሰጡትን አገልግሎት እርካታ ከመጨመርና ለከተማችን የእድገት ጉዞም ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ሚያዝያ 8 / 2017
“ዘላቂ እና ሕዝብን ማዕከል ያደረገ አረንጓዴ ሽግግር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው የ2025 ፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ የአየር ንብረት ጥበቃን ለማራመድ አስፈላጊ የሆኑ ሶስት ቁልፍ የተግባር ነጥቦችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት “ዘላቂ እና ሕዝብን ማዕከል ያደረገ አረንጓዴ ሽግግር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው የ2025 ፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ የአየር ንብረት ጥበቃን ለማራመድ አስፈላጊ የሆኑ ሶስት ቁልፍ የተግባር ነጥቦችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ ብለዋል፡፡
አንደኛ የአየር ንብረት ጥበቃ የገንዘብ አቅርቦትን የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት በቂ፣ ተገማች እና ዘላቂ በሆኑ ምንጮች ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ሁለተኛ ዘላቂ ልማትን ለመደገፍ እና የአኅጉሩን ወሳኝ ሥነምኅዳር ጥበቃ ለማድረግ በአለም የኃይል ምንጭ ኢንቬስትመንት ሽፋን ውስጥ የአፍሪካን ድርሻ በአሁኑ ወቅት ካለበት ሁለት ከመቶ በ2030 ወደ ሃያ ከመቶ ማሳደግ ይገባናል።
ሶስተኛ የብዝኀ ሕይወት ጥፋትን እና የምድር መራቆትን በመዋጋት ተፈጥሮን ለመጠበቅ አፋጣኝ ርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ብለዋል፡፡ይኽም እንደ አረንጓዴ አሻራ ያሉ ሕዝባዊ ሥራዎችን በገንዘብ መደገፍን በዚህም ለየአካባቢው ኅብረተሰብ ከአድልዎ የፀዳና ፍትኀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን ያካትታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልእክታቸዉ፡፡
ዛሬ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች 200 ሺህ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸውና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተናል።
ማዕድ ማጋራት ለነዋሪዎቻችን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን የምንገልፅበት እዲሁም እርስበርስ መተሳሰብን የምናዳብርበት የሰዉ ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነዉ።
እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ዛሬም ‘መስጠት አያጎድልም’ ብለው ከጎናችን የቆሙ የከተማችን ባለሃብቶችን፣ ተቋማትን እና ወጣት በጐ ፍቃደኞችን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
መልካም በዓል !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መንገድ ላይ ሽንት በመሽናት ደንብ የተላለፉ ግለሰቦች አንድ መቶ ሺህ ብር ተቀጡ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ እና በመሳለሚያ አካባቢ በመንገድ ላይ ሽንት በመሽናት አካባቢ በማቆሸሽ ደንብ የተላለፉ 50 ግለሰቦች እያንዳንዳቸውን 2000 ብር በድምሩ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱን የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በከተማው በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ክንውን 64,075 የተወለዱ ህፃናትን በ90 ቀን ውስጥ የልደት ምዝገባ ማደረግ መቻሉ ተገለፀ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጠቅላላ ካውንስል የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የስራ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡
በዘጠኝ ወራቱ አፈፃፀም:
ከሲቪል ምዝገባ ዘርፍ አኳያ
* ከኩነት ምዝገባ እኳያ በጥቅሉ የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋን 109.63 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበ ሲሆን የልደት ምዝገባ የፍቺ ምዝገባ እንዲሁም የጉዲፈቻ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን ይህም በከተማው የተዘረጋው የጤና ማዕከላት እና የፍርድ ቤቶች የአንድ ማዕከል የኩነት ምዝገባ አገልግሎት ስርዓት ውጤት መሆኑ ታይቷል።
* በከተማችን 58,342 ህፃናትን በተወለዱ በ90 ቀናት ውስጥ በወቅቱ የልደት ምዝገባ ለማድረግ ታቅዶ 64,075 ምዝገባ በማድረግ ከ100% በላይ መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር 71.15% ብልጫ አሳይቷል።
* በድምሩ 341,674 ወሳኝ ኩነቶችን ( የልደት፣ ጉዲፈቻ፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ) በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደቡ ባለፈ መዝግቦ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 308,289 በመመዘገብ የእቀዱን 90.23 በመቶ ማከናወን የተቻለ ቢሆንም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1.52% ቅናሽ ያሳይል። ቅናሽ ካሳዩ ምዝገባዎች ጋብቻ ሲሆን ፍቺ በንፅፅር ብልጫ አሳይቷል።
የፍቺ እና ጉዲፈቻ ምዝገባ ከአምናው የምዝገባ ስርዓት ለውጥ የተደረገበት ሲሆን ልክ እንደ ጤና ተቋማት ሁሉ በፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት በመቻሉ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአሁኑ ወቅት ጤና ተቋማት ፣ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በድምሩ 170 ማዕከላት ከመደበኛ ቢሮ ውጭ የወሳኝ ኩነት የአንድ ማዕከል ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላት ናቸው።
ከነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ አንፃር:
* 509,938 ነዋሪዎችን ወደ ዲጂታል ምዝገባ ለማስገባት ታቅዶ ክንውን 528,495 (104%) ሲሆን ከአምናው 22.54% ብልጫ አለው፡፡ ይህም በዋናነት በ2016ዓ.ም በማንዋል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 14 ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል በመሸጋገራቸው የመጣ አብላጫ ነው።
* 473, 924 የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በአዲስ ፣ በእድሳት፣ በእርማት እና በምትክ ለመስጠት ታቅዶ 339,048 በመስጠት የእቅዱ 71.54 በመቶ ተከናውኗል። ከዚህም ውስጥ 97.03 በመቶ ዲጅታል መታወቂያ የተሰጣቸው ሲሆን ቀሪው ለአቅመ ደካሞች እና ታማሚዎች የቤት ለቤት አገልግሎት ፣ የጣት አሻራቸው ለተጓዳ እንዲሁም አሻራ መስጠት ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የተሰጠ ነው።
ተጠያቂነትን በተመለከተ:
* 188 የአሰራር ጥሰት የፈፀሙ፣ አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ የሞከሩ፣ የስራ ቦታ ስነ- ምግረር ያላከበሩ እና በሃሰተኛ መረጃ አገልግሎት ለማግኘት ጥረት ያደረጉ አመራር፣ ፈፃፀሚ እና ባለጉዳይ ተጠያቂ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከተጠቀሰው ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር 33 መሆኑ ተነግሯል።
በዕለቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክቶሬት አቶ ዮናስ አለማየሁ በጥሩ አፈፃፀም የታዩት እንደተጠበቀ ሆኖ በጉድለቶች ላይ መስራት እንዲቻል የቀጣይ ቀሪ ወራት አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ከተሰጠው አግልግሎት ቁጥር ባሻገር የተገልጋይ እርካታ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስብዋል።
ለበለጠ መረጃ በነፃ መስመር 7533 ወይም 9779 ይደውሉ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
