ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለፅ/ቤቱ ሰራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለፅ/ቤቱ ሰራተኞች በሚኒስትሪሚንግ እና የመንግስት የሀብት አጠቃቀምና የዉስጥ ኦዲት አሰራር ዙሪያ ላይ ያለመ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዛሬዉ እለት ሰጥቷል። በስልጠናው ላይ ጥምር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ተግባራት፣ዉስጣዊ እና ዉጫዊ የሜንስትሪሚንግ ተግባራዊ ከማድረግ፣ተቋም ተኮር የተፅዕኖ ዳሠሳ ከማድረግ፣የተሞክሮ አዘገጃጀት፣የዉስጥ ኦዲት ምንነት፣በኦዲት ግኝት ላይ እርምጃ ከመዉሰድ፣የዉስጥ ቁጥጥር ስርዓት ምንነት፣የቁጥጥር አይነቶችና አመዳደባቸዉ፣የዉስጥ ኦዲትን ከማጠናከር አንፃር በእነዚህ እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የፅ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያና የሜንስትሪም ፎካል ኘርሰን የሆኑት ወ/ሪት አስረስ ተረፈ በበኩላቸው እንደገለፁት ስልጠናው የተቋሙ ሰራተኛ በሚንስትሪሚንግ እንዲሁም  በኤች አይቪ ኤድስ በሽታ ምንነትን ለሰራተኛዉ በቂ የሆነ ግንዛቤ ለመስጠትና የበሽታዉን አስከፊነት ለተቋሙ ባለሙያዎች ከማሳወቅ አንፃር ከፍተኛ የግንዛቤ አቅምን ለማሳደግ እና የተሻለ እዉቀትን ከማስጨበጥ ረገድ የስልጠናዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። ስልጠናውን በመስጠት ሂደት የተሳተፉት የአዲስ አበባ የፋይናንስ ቢሮ ቡድን መሪ አቶ እሸቱ ላቀዉ ስልጠናዉ በሰራተኛዉ ዘንድ ያለዉን የዉስጥ ኦዲት አሰራርና ደንብ ላይ ያለዉን ክፍተት ከመሙላት እንዲሁም ግልፅነትን የሚፈጥር በተጨማሪም ስልጠናው በተቋሙ ያለዉን ባለሙያ ብቁ የሆነ ባለሙያ ለማድረግና በእውቀት የተመራ እንዲሆን አቅም የሚፈጥር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም በስልጠናው ላይ ሀሳብ አስተያየት ከሰልጣኞች ተነስተዉ የጋራ ምላሽ በመስጠትና መግባት በመፍጠር ስልጠናዉ ተጠናቋል።

አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው! ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+4

በከተማ የተጀመሩ የክረምት በጎ ፍቃድ ልማት ስራዎች ከገጠሩ ክፍል ጋር የማስተሳሰር አካል በሆነው የገጠር የኮሪደር ልማት ስራ እያስጀመርን ነው። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ዱባንቾ ቀበሌ በገጠር ኮሪደር ሞዴል የአርሶ አደሮች መኖሪያ መንደር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። እነዚህ ማሳያ መንደሮች መገንባታቸው አርሶ አደሩ የግብርና ስራ እያከናወነ የተሻለ ሕይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

photo content
+4

የኮሪደር ስራ ጉብኝትና ቅኝት! በዛሬው እለት በምክትል ከንቲባ ማዕርግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በተገኙበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ እየተሰራ የሚገኘው ኮሪደር ልማት ተጎብኝቷል:: በአዲስ አበባ ከተማ በሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ከሚለሙ መካከል አንዱ 7ኛ ኮሪደር በመባል የሚጠራው (ከሳርቤት - መካኒሳ- ፉሪ አደባባይ) የሚዘልቀው መሆኑ ይታወቃል:: ከነዚህም መካከል ዛሬ አመሻሹን ሲጎበኝ የነበረው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኘው ከመከኒሳ እስከ ፉሪ ያለው ነው:: በጉብኝቱ ላይ የኮሪደር ስራው አስተባባሪና በምክትል ከንቲባ ማዕርግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንዲሁም የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የስራ ሀላፊዎች: ኮንትራክተሮችና የፕሮጀክቱ አማካሪዎች ተገኝተዋል:: በጉብኝቱም በመገባደድ ላይ የሚገኘው የኮሪደር ስራዎችን አንድ በአንድ በመቃኘት ቀሪ ስራዎች ከክረምት ወራት በፊት ፈጥኖ እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል ግንቦት 25/2017

የመዲናዋን የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት ስጋት ለመቅረፍ እየተሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የሰጡትን ማብራሪያ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ

የመዲናዋን የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት ስጋት ለመቅረፍ እየተሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የሰጡትን ማብራሪያ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉

photo content
+6

የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረው የገጠር ኮሪደር በሁሉም አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው። በዛሬው እለትም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሲንቢጣ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆኑ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታን አስጀምረናል። ሞዴል የገጠር መንደሮቹ ቀላል ወጪ የሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ሲሆኑ አርሶ አደሩም ጤናማና ክብር ያለው ህይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው። በአካባቢው ከ2 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጎርፍና ድርቅ አደጋ ይታወቅ የነበረውን አካባቢ የልማት ተምሳሌት ያደርገዋል"። ጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር ዓብይ አሕመድ

photo content
+9

photo content

በአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት  የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ  ለፅ/ቤቱ ባለሙያዎች፣ለክፍለ ከተማ የጥናት ቡድን መሪዎች፣ለተጠሪ ተቋማት የጥናት ቡድን መሪዎች በማዘጋጀት ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥና በመረጃ መሰብሰብ ዙሪያ ላይ ያለመ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናዉን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አማረ ሙላዉ በስልጠናው እንደገለፁት ስልጠናው በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥና በመረጃ አሰባሰብ ዙሪያ አቅም ለመፍጠርና ባለሙያዉን ብቁ  ለማድረግና የሚሰጠዉን አገልግሎት በእውቀት የተመራ ለማድረግ አቅም የሚፈጥር ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። ስልጠናው ላይ የመረጃ  መሰብሰቢያ መንገዶች ፣የመረጃ መሰብሰብ ስነ ምግባር፣የዳታና የመረጃ ምንነትና ልዩነት፣መረጃ የመሰብረብ አላማ፣መረጃን ከጊዜ ጋር ከማጣጣም፣የሚሰጡ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ቀጣይነት ከማረጋገጥ አንፃር፣ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎትን ከማዘመን፣የዘመነ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ከመስጠት፣በእነዚህ እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ስልጠናውን በመስጠት ሂደት የተሳተፉት የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር መሀሪ እንደተናገሩት ስልጠናዉ በሰራተኛዉ ዘንድ ያለዉን የማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥና የመረጃ አሰባሰብ ዘዴን ከማዘመን አንፃር ግልፅነትን የሚፈጥር እንደሆነ አስገንዝበዋል። የፅ/ቤቱ የጥናት ልማት ትግበራ ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት አቶ መገስ ቶማ በበኩላቸው ስልጠናው ተቋሙ የሚሰጠዉን አገልግሎት ከማዘመን አኳያ በሚያደርገው ጥረት የባለሙያውን የመፈፀም ክህሎትን ለማጎልበት የሚያግዝ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም በስልጠናው ላይ ሀሳብ አስተያየት ከሰልጣኞች ተነስተዉ የጋራ መግባት በመፍጠር ስልጠናዉ ተጠናቋል።

photo content
+5

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተከማዋ ዕድገት እየሰጡ ላሉት በሳል አመራር እውቅና ሰጠ የጋራ ምክር ቤቱ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናውን የሰጠው የአዲስ አበባን ህዝብ ኑሮ በተጨባጭ የለወጡ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ከጎበኙ በኋላ በዛሬው ዕለት ከከንቲባዋ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ነው። የጋራ ምክር ቤቱ መሪዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና መላው አመራራቸው የከተማዋን ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ ግዙፍ ፕሮጄክቶችን በፍጥነት እና በጥራት በማከናወን ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ በመቻላቸው ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ስሆን፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ልዩነቶቻቸውን በማክበር ለሀገር ሰላምና ልማት በጋራ መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

photo content
+4

photo content
+9