ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+9

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ክላስተር የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅድ ያለፉት 45 ቀናት የስራ አፈፃፀምን በዛሬው እለት ገምግመዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ክላስተር የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅድ የ45 ቀናት እቅድ አፈፃፀምን የገመገሙት የ13 ሴክተር ተቋማት ሃላፊዎች እና የ11ዱ ክፍለከተሞች አስተባባሪዎች በተገኙበት ነው። በግምገማ መድረኩ ባለፉት 45 ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊና በጎ ፈቃድ ስራዎች ክላስተር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የወንዝ ዳርቻ ብክለትን እና የጎርፍ አደጋ ስጋትን ከመከላከል፣ከከተማ ፅዳትና ውበት፣ከአረንጓዴ ልማት፣ ከክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች ፣የቤት ግንባታ፣ የደም ልገሳ፣ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ እና የፋይዳ ምዝገባ ስራዎች አንፃር የተከናወኑ ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የ90 ቀናት ልዩ የንቅናቄ እቅዱን መተግበር ከጀመርን 45 ቀናት ያህል ያስቆጠርን ከመሆኑ አንፃር በከተማችን በሁሉም መስክ እየተፈጠረ ያለው ውብ ገፅታን ወደ ከፍታ ለማድረስ እየተከናወኑ ባሉ የመሠረተ ልማት ግንባታና ጥበቃ ስራዎች፣የፅዳት፣ የውበትና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ ህብረተሰባችንን በማሳተፍ የተመዘገቡ ውጤቶች አበረታች ቢሆንም አብዛኛውን የመዲናችንን ነዋሪዎች በበጎ ፈቃድ ስራዎች በስፋት ማሳተፍ ላይ አሁንም በልዪ ትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አስገንዝበዋል። አክለውም ፣ የአደጋ ስጋት እና የጎርፍ መከላከል ስራዎች፣ ከአካባቢ ጥበቃና ወንዞችን ከብክለት ሙሉ በሙሉ ከመታደግ ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችም ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በአፅንኦት ገልፀዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በቀሪ 45 ቀናት ሊጠናቀቁ የሚገባቸው በሚል ካቀረቧቸው ዋነኞቹ በተቀናጀ የሞዴል ብሎክ መስፈርት የተለዩ እና የተመረጡ ብሎኮችን ከአመራሮች ጋር በቅርበት በመስራት የተሟላ ሞዴል ብሎክ በማድረግ ረገድ ቀሪ ስራዎችን የማጠናቀቅ፣በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ አጋርነታቸውን የማጎልበት ፣ ደም ልገሳ የህብረተሰቡ ባህል እንዲሆን የማድረግ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ተጠቃሚ የማህብረሰብ ክፍል በትክክለኛ ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል መሆኑን በሚገባ የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እንዲፈፀም አቅጣጫ አስቀምጠዋል። አክለውም የወንዝ ዳርቻ ፅዳትን በማጠናከር ወንዞቻችን ከብክለት የፀዱ ማድረግ፣የፍሳሽ መስመሮችን የማፅዳት ስራ በአጠቃላይ የከተማዋን ጽዳት የመጠበቅ፣ውብና አረንጓዴ መሠረተ ልማቶችን የመጠበቅና የመንከባከብ ስራ ህብረተሰቡ ባለቤት ሆኖ እንዲይዘውና ፅዳትን ባህል እንዲያደርግ የሚሰሩ ስራዎችም መጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። የ90 ቀናት የልዩ ንቅናቄ እቅድ የቀሪ ቀናት ስራዎች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በስፋት እንዲሳተፍ ማድረግ ይገባል ያሉት ኢንጅነር ወንድሙ በተለይም ከክረምቱ ጋር ተያይዞ የፍሳሽ መሠረተ ልማትን የሚጎዱና ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችንና የግንባታ ተረፈ ምርት ፅዳት ስራን አሁንም በትኩረት ማከናወን ይገባል ሲሉም አሳስበዋል። በአረንጓዴ አሻራ፣ በመንገድ ዳር መብራት መሠረተ ልማት የተመዘገቡ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና የኮሪደር ልማት የማጠናቀቂያ ስራዎች፣የማእድ ማጋራት፣ የመጪዎቹን በአላት ህብረብሔራዊነት በጠበቀ መልኩ እንዲከናወኑ የማድረግ፣ የፋይዳ ምዝገባ እና እንዲሁም ሁሉንም ስራዎች በተገቢው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ፕላትፎርም ለህዝብ በማድረስ ተሳትፎውን ማጠናከር በቀጣይም አጠናክረን የምንፈፅማቸው መሆን ይኖርበታል ሲሉም አመልክተዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+7

"በመትከል ማንሰራራት "በሚል መሪ ቃል ዛሬ ማለዳ ከኮሙኒኬሽን እና ከሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ከስፖርቱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በቀበና ወንዝ ዳርቻ ችግኝ ተክለናል። የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች፣ የስፖርት ቤተሰብ በኢትዮጵያውያን በጎ የሆነን ሀሳብ የምታሰርፁ ናችሁና እና አሁንም ስራችሁን እንድታጠናክሩ እላለሁ ። ዛፍ መትከል የዛሬ ብቻ ሳይሆን የነገም ተስፋችን እንዲሁም የምግብ ዋስትናችንን ለነገው ትውልድ የምናረጋግጥበት በመሆኑ በዛሬው መረሀ ግብር የተሳተፋችሁ ከመትከል ባሻገር መልካም ሀሳብ የምታሰርፁ ናችሁና ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ትውልድን የማነፅ ስራ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Since the first Food Systems Summit in 2021, Ethiopia launched a comprehensive Roadmap for Food Systems Transformation. This roadmap is a key part of our economic transformation, supported by macroeconomic reforms, the Homegrown Economic Reform agenda, and improved business conditions. It advances, policies on land reform, agricultural development, and rural finance to build inclusive and productive food systems.

photo content
+7

በተያዘው በጀት አመት በስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ስር ካሉት ተጠሪ ተቋማት በሁለቱ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥ የጥራት መስፈርት ያሟሉ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እንደሚፈፀም በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬዉ እለት ከተቋሙ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና አጠቃላይ ሠራተኞች ጋር የ2018 በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለመወያየት በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ነዉ። በመድረኩ ላይ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘው እንደገለፁት በ2017 በጀት አመት በነበረው አፈፃፀም ለስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ተጠሪ ከሆኑትና ስትራቴጂክ አመራር ከሚሰጥባቸው፣ ከሚደገፋቸውና ከሚያስተባብራቸው ተቋማት ሁለቱ ማለትም የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እንዲሁም የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከፍተኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ እውቅና የተሰጣቸው ተቋም ከመሆናቸውም በላይ በአገልግሎት አሰጣጣቸወም ሞዴልና በከተማችን ነዋሪዎች ዘንድ ተአማኒነት ያተረፉ ተቋማት መፍጠር መቻሉም ተጨማሪ ስኬት ነው ሲሉም አመልክተዋል። በተያዘው በጀት አመት ስሉጥ፣ ቀልጣፋና እንዲሁም የላቀ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማረጋገጥ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲና የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ያሟላ ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራም ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት አረጋግጠዋል። አክለውም ፅ/ቤቱ በያዝነው በጀት አመት ይህንን የተገኘውን ዉጤት በሁሉም ተቋማት በተቀራረበ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም በአፅንኦት ገልፀዋል። የስራ አሰኪያጅ ፅ/ቤት በራሱ እንደ ተቋም በከተማዋ ካሉት 27 የካቢኔ አባላት ከሆኑ ሴክተር ተቋማት ከፍተኛ ዉጤት በማምጣት የአረንጓዴ ሰርተፊኬት ማግኘቱ አበረታች ቢሆንም ነገር ግን በቀጣይ ከዚህ የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ ሁሉንም አቅሞች በመጠቀም የተቀናጀ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+3

የአፍሪካ የፖለቲካ ርዕሰ መዲና እና የአለም ሶስተኛዋ የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው ከተማችን አዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ሁለተኛውን የተመድ የምግብ ስርዓት ጉባኤ +4 (UNFSS+4) በታላቅ ድምቀት ታስተናግዳለች። ጉባኤዉ ስኬታማ እና ውጤታማ እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ ! Addis Ababa, the political capital of Africa and the third-largest diplomatic hub in the world, will host the Second UN Food Systems Summit +4 (UNFSS+4) from July 27 to 29, 2025. On behalf of the City Administration and the entire residents of Addis Ababa, I would like to extend my warmest wishes for a successful and productive undertakings of the Summit. ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+8

የ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ በተገነቡ የልማት ስራዎች ላይ ያደረጉት ጉብኝት በምስል፡-

photo content
+1

የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሚኒስትሮች ምክርቤት ፕሬዝደንት ጂኦርጂያ ሜሎኒን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ እላለሁ። ሁለቱ ሀገሮቻችን በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚካሄደውን ሁለተኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ በጋራ በመሆን አዘጋጅተዋል። Ministira Muummeefi Pirezdaantii Mana Maree Ministirootaa Rippabiliika Xaaliyaanii, Joorjiyaa Meeloonii baga nagaan Itoophiyaa dhuftani. Biyyoonni keenya lachan guyyoota sadan dhufaniif waliin dhaabatanii akka michootaatti Yaa'ii Sirna Nyaataa Mootummoota Gamtoomanii isa 2ffaa waliin kan kessumsiisan ta'a. It is my pleasure to welcome to #Ethiopia Giorgia Meloni, Prime Minister and President of the Council of Ministers of the Italian Republic. Our two nations stand together over the next three days, as partners in co-hosting the Second United Nations Food Systems Summit.

photo content
+2

ወንድሜ ሀሰን ሼህ መሃሙድ ኢትዮጵያ በክብር በምታስተናግደው የሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ አስቀድሞ እንኳን በደህና መጡ። ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጥልቅ መሠረት ያለው ታሪካዊ፣ ባሕላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትስስርን ይጋራሉ። ይኽን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር መሥራታቻንን እንቀጥላለን። Obboleessaakoo Hasan Sheek Mohaammud Yaa'ii Sirna Nyaataa Mootummoota Gamtoomanii isa 2ffaa Itoophiyaan kabajaan keessumsiiftuuf dursitanii baga nagaan dhuftani. Itoophiyaafi Somaaliyaan hidhata seenaa, aadaafi dippiloomaasii bu'ura gadi fagoo qabu waliin qabu. Hidhata kana caalaatti cimsuuf hojjechuu ittifufna. Welcome to #Ethiopia, my brother Hassan Sheikh Mohamud, ahead of the Second United Nations Food Systems Summit, which we are proud to host. Ethiopia and Somalia share deep-rooted historical, cultural, and diplomatic ties, and we remain committed to strengthening our brotherly relations.

photo content
+3

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና ሙሀመድ ዶ/ር) እና የምግብ ሥረዓተ ጉባኤ ታሳታፊ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ጎበኙ የተባበሩት የምግብ ሥረዓተ ጉባኤ ለመሳተፍ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የተመድ የምግብ ስርዓት ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንና ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው። ለ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና የሀገራት ተወካዮች የጉለሌ የተቀናጀ ልማት ፣ ለሚ ኩራ የግብርና መሽጫ የገበያ ማዕከል፣ ጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት :የምገባ ተቋማትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ጉብኝቱ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሠራችው ያለውን ሂደት በአካል እንዲመለከቱ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በጉብኝት የተለያዩ ሀገራት ተወካዮችና የዓለም ተቋማት የሥራ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በመጨረሻም የአረንጏዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር አከናውነዋል ::

photo content
+5

ዛሬ የህፃናትን የፈጠራ እና የማሰላሰል አቅም የሚጨምሩ በጨዋታ መልክ ለማስተማር የሚያግዙ በርካታ መጫወቻዎች ከሎጎ ፋዉንዴሽን በክሊቲን ሐልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ በኩል ተበርክቶልናል ። በከተማችን የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን ዋነኛ የትዉልድና የአገር ግንባታ ምሶሶ አድርገን በስፋት እየሰራንበት እንገኛለን ። ይህ ፕሮግራም በክህሎት የዳበረ፣ በፈጠራ የጎለበተ አካባቢዉን በሚገባ የተረዳና ለሚገጥሙት ፈተናዎች አስቀድም ሳይንሳዊ መፍትሔ የሚያበጅ ጠንካራና አገር ወዳድ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል ። ፕሮግራሙ ተግባራዊ ማድረግ ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ አገራት ከወዲሁ ውጤቱን በመረዳት ልምድ እየቀሰሙበት እና እየደገፉት ይገኛል ። ስጦታዎቹ የአዕምሮ እድገት ውስንነትና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናት ጭምር ያማከለ በመሆኑ አስተባባሪዎቹን ከልብ አመሰግናለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content