Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የከተማ እና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በመርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ እንደገለፁት ኮሚሽኑ በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ሰአት የሰውን ህይወት እና ንብረት ለማዳን ለሊት ከቀን መስዋእትነት እስከመክፈል እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው ዛሬ ክፍት የተደረገው ለከተማዋ 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ለህብረተሰቡ ይበልጥ ቅርብ እና ተደራሽ ለመሆን እንጂ ስራውን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ እንዲከፈት ለአገዙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ በተለያዩ ምቹ ባልሆኑ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በክፍለ ከተማው እሳትና ጎርፍ አደጋ ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን አንስተው ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲሰጥ አስቻይ ሁኔታ መፈጠሩን ገልፀው በቀጣይም የራሱን ህንፃ ገንብቶ ይበልጥ የተጠናከረ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ሊያግዝ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኒቆዲሞስ ቡቹ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ በ2016 ነሃሴ 21 መቋቋሙን አንስተው የተመደቡ ሰራተኞች በቦታ እጥረት ምክንያት ተበታትነው ሲሰሩ እንደነበር በማንሳት ኮሙሽኑ ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የራሱ ቢሮ እና ማቴሪያል ተሟልቶለት የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻላቸው ምስጋና አቅርበው በቀጣይም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙ እንጀሚሰራ ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ፣የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላናን ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ተቋሙ በተሟላ መልኩ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ላገዙ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።
Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት በማካሔድ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተጠሪ ተቋማት እውቅና ሰጠ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እዉቅናና የ2018 በጀት አመት እቅድ ኦረንቴሽን ከተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደዋል።
በመድረኩም የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም በክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ሀላፊ በአቶ ዳኛቸው አበበ ዝርዝር ሪፖርቶች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ ከተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤታማ ስራዎች መከናወኑን ገልፀዋል።
አክለዉ በተለይ በውሀና ፍሳሽ፣ ከመብራት ፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት እና እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር እና ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አግልግሎት ጽህፈት ቤት አበረታች ተግባር መፈጸማቸውን አብራርተዋል።
በቀጣይ የሚታዩ ጉድለቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በ2018 በጀት አመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና በመረባረብ የህዝቡን ችግር መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል።
በተቋማቶቹ መካከል የሚነሱ ያለመናበብ ችግሮች በማረም እና ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ተግባራዊ በማድረግ በምንሰጣቸው አገልግሎቶች የህዝቡን እርካታ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉም አስታዉቀዋል።
የክፍለ ከተማዉ የጽዳት አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሀረግ አብረሃ በበኩላቸው የህዳሴ ግድባችንን መርቀን እያጣጣምን በመሆናችን ይህንን የእዉቅና ፕሮግራም ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዉ በ2017 በጀት አመት በተለይም በማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶች የተሻለው ስራዎች በመከናወናቸውን ከከተማ እውቅና የተገኙ መሆኑን ገልፀው በ2018 በጀት አመት በተሻለ ሁኔታ በመስራት የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ አለብን በማለት ተናግረዋል።
በውይይቱ የሁሉም ወረዳዎች ተጠሪ ተቋማት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ የውሃና ፍሳሽ፣ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣የኤሌክትሪክ ዲስትሪክት፣ የትራንስፖርት እና ትራፊክ ማናጅመንት ኮልፌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮችና ተወካዮች ተገኝተዋል።
መጨረሻም በ2017 በጀት አመት ዓመት የላቀ ዕቅድ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለቁልፍ ባለድርሻ ሴክተሮች፣ ለቅንጅታዊ ተቋማት፣ለጽህፈት ባለሙያዎችና በድን መሪዎች ተበርክቶላቸዋል።
ከተጠሪ ተቋማት ከ1 እስከ 3 በመዉጣት የዋንጫ ተሸላሚ የሆኑት:
1ኛ ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ ቤት
2ኛ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አግልግሎት ጽ/ቤት
3ኛ፣ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ኮልፌ ቅርንጫፍ
ከወረዳ ተጠሪ ተቋማት (ከወረዳ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት) የሰርተፍኬት ተሸላሚ
1ኛ፣ ወረዳ 04 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት
2ኛ፣ ወረዳ 01 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት
3ኛ፣ ወረዳ 2 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት
ከወረዳ ተጠሪ ተቋማት (ከወረዳ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አግልግሎት ጽ/ቤት) የሰርተፍኬት ተሸላሚ:-
1ኛ፣ ወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አግልግሎት ጽ/ቤት
2ኛ፣ ወረዳ 03 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አግልግሎት ጽ/ቤት
3ኛ፣ ወረዳ 06 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አግልግሎት ጽ/ቤት በመሆን እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በ9101 ነፃ ስልክ ጥሪ የመጡ የህዝብ ጥቆማዎችን ምላሽ እየሰጠ ነው
ባለስልጣኑ የከተማዋን የመንገድ መብራት ተደራሽነትና ሽፋን ለማሳደግ የአዳዲስ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታና ተከላ እንዲሁም የተለያዩ የመብራት መሰረተ-ልማት ጥገና ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በባለስልጣኑ የኦፕሬሽንና ጥገና ዘርፍ ተለይተው በዕቅድ ከሚከናወኑ የጥገና ስራዎች በተጨማሪ ህብረተሰቡ ከመንገድ መብራት ጋር ተያይዞ በየአካባቢው ያጋጠመውን ችግር በ9101 ነፃ የስልክ ጥሪ በሚሰጠው ጥቆማና አስተያየት መሰረት አስፈላጊውን ጥገና በማከናወን የመንገድ መብራቶቹን ወደ አገልግሎት በማስገባት ፈጣን ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የቀረቡ ቅሬታዎችን መሰረት አድርጎ ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች ውስጥ አያት አደባባይ ደራርቱ መንገድ 7፣ አየር ጤና በተለምዶ ንጉሴ ጭድ አከባቢና ጀሞ አንበሳ ጋራጅ ጀርባ በተለምዶ ጅግጂጋ ሰፈር የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነባናቸውን 1 ሺህ 671 ያህል ቤቶች ለአገር ባለውለታዎች ፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበናል።
የቤት ግንባታዎቹ አብሮነትን እና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ፣ የህፃናት መጫዎችን ፣ የስፓርት ማዘዉተሪዎችን የያዙ፣ በአጠቃላይ ንፁህና ሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው።
ይህን በጎ ተግባር በእውቀታቸው፣ በሃብታቸው፣ በጉልበታቸው የደገፉ ልበ ቀና ባለሀብቶችን እና ያስተባበሩ አመራሮቻችንን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ጥያቄዎች ቅድሚያ ሰጥቶ በመመለስ የመዲናዋን መሠረተ ልማቶች የማስፋትና የማዘመን ስራ እየሰራ ይገኛል ሲሉ በም/ከን…
See more
የአለም የፅዳት ቀንን ምክንያት በማድረግ "ቆሻሻ ሀብት ነው " በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአለም የፅዳት ቀንን ምክንያት በማድረግ "ቆሻሻ ሀብት ነው " በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
የአለም የጽዳት ቀን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መከበሩ በርካታ ቆሻሻ ቦታዎችን በመቀየር በራስ አቅም የኮሪደር ልማት በማከናወን ለነዋሪዎች ምቹ አካባቢን መፍጠር በመቻሉ መሆኑ ተመላክቷል።
በዕለቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የተቋማት ክትትል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ ንጉስ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ፣ የዩናይትድ ኔሽን ሀቢታት ፕሮግራም ማናጀር ሴሎ ፓጉዌ ጨምሮ ሌሎች የከተማ፣ የክፍለ ከተማ፣ የወረዳ እንዲሁም ፀጥታ አካላት፣ የፅዳት ማህበራትና አርቲስቶች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ፣ የፅዳት ቀን ስናከብር በማንሰራራት ዘመን ላይ የህዳሴ ግድብ ያጠናቀቅንበት ከድህነት ለመላቀቅ የመጀመሪያ ደውል የደወልንበት ነው ብለዋል።
የአለም የጽዳት ቀን ስናከብር በአለማችን የሚገኘውን 5 ፐርሰንት ቆሻሻ ክምችት በማስወገድ ለአለም ዜጎች ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ አላማ ያደረገ ነው ብለዋል።
የዩናይትድ ኔሸን ሀቢታት ፕሮግራም ማናጀር አቶ ሴሎ ፓጉዌ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ፅዱ በማድረግ ረገድ እየተሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ቆሻሻን መልሶ መጠቀም ከተቻለ ወደ ሀብትነት መቀየር እንደሚቻል ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
#LaftoCommunication
ለረጅም ዓመታት የመንገድ መብራት መሰረተ-ልማት ባለመሟላቱ ይነሱ የነበሩ የህዝብ ቅሬታዎችን እየተፈታ መሆኑ ተገለፀ
በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመዲናችን ከመንገድ መሰረተ-ልማቱ ጋር አብሮ የመብራት አገልግሎቱ ባለመሟላቱ ምክንያት ይነሱ የነበሩ የህዝብ ቅሬታዎችን መፍታት የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ትናንት ምሽት ከመንዲዳ እስከ የሺ ደበሌ ባለው መንገድ ላይ የተሰራውን የመንገድ መብራት መሠረተ ልማት የሟማላትና የጥገና ስራ በጎበኙበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ በጉብኝታቸውም ወቅት መንገዱ ከፍተኛ የሆነ የእግረኛና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዲሁም ሰፊ ንግድ የሚከናወንበት ቢሆንም መንገዱ ተገንብቶ ለህብረተሰቡ ክፍት ከተደረገ ከ7 ዓመታት በላይ አገልግሎት ባለመስጠቱ ምክንያት ሰዎች በማታ በእግር መንቀሳቀስ የማይችሉበት፣ ለአደጋ የሚጋለጡበትና የቢዝነስ ስራዎችን አምሽቶ ለመስራት አዳጋች በመሆኑ አከባቢው በጊዜ ጭር የሚልበት ሁኔታ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ምክንያት የህዝብ ቅሬታዎች በተለያየ አግባቦች ይቀርብ እንደነበር ገልፀው ይህን ከመፍታት አኳያ ባለስልጣኑ መሰረተ-ልማቱን በመጠገንና በአዲስ በመገንባት ወደ አገልግሎት በማስገባት ቅሬታዎቹን መፍታት እንደተቻለ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አንስተዋል፡፡
አያይዘውም ባለስልጣኑ ተቋቁሞ ወደ ስራ ሲገባ ከተረከባቸው የመንገድ መብራቶች ውስጥ 56 በመቶ የሚሆኑት ብቻ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ሲሆን የቀሩትን ወደ አገልግሎት ለማስገባት የወንጀል ተጋላጭነት፣ የትራፊክ አደጋና የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወንባቸውን አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት በዕቅድ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ በገለፃቸው በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ መብራት ተሟልቶ ወደ ስራ ማስገባት በመቻሉ ሰዎች የንግድ ስራቸውን እስከ ምሽት የተመቸ በማድረግ ያለውን የንግድ አቅም በማሳደግ ከተማውም የተሻላ ገቢ መሰብሰብ የሚችልበትን አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል ፡፡
የተከናወነው ስራ አስመልክቶ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን እንደተናገሩት ለረጅም ዓመታት ከመንገድ መሰረተ-ልማቱ ግንባታ ጋር አብሮ ወደ አገልግሎት ባልገቡ የመንገድ መብራት ምክንያት የህዝብ ቅሬታ ሆነው የቆዩ መንገዶችን ወደ አገልግሎት ባለስልጣኑ ካስገባቸው ውስጥ አንዱ የመንዲዳ- የሺ ደበሌ መንገድ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አቶ ሰብስብ በመንገዱ ላይ የመብራት ምሰሶዉቹ የተተከሉ ቢሆንም የመብራት አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ለመስጠት የመብራት መሰረተ-ልማቱ ባለመሟላቱ ምክንያት የነበሩ ችግሮችን ባለስልጣኑ እንደ አዲስ የኤል.ኢ.ዲ ገጠማ፣ ተጨማሪ ምሰሰዎችን በመትከልና የኬብል ዝርጋታና ጥገና ስራዎችን በማከናወን ለማህበረተሰቡ ለአገልግሎት ማብቃቱን ተናግረዋል፡፡
አቶ ሰብስብ ባለስልጣኑ የህብረተሰቡን ቅሬታ ከመፍታት አኳያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ባከናወናቸው ስራዎች የህብረተሰቡን ሰፊ ድጋፍና ትብብር ማግኘት መቻሉን ጠቅሰው በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት የማይሰጡትን ወደ ስራ የማስገባቱ ስራ በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በአካባቢው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎችና የመንገዱ ተጠቃሚዎች ለረጅም ዓመታት መንገዱ ጭለማ በመሆኑ ምክንያት ይደርስባቸው የነበሩ የወንጀልና የአደጋ ተጋላጭነትና ጫና መቃለሉንና አሁን ላይ አካባቢው በብርሀን በመለወጡ ለእግረኛውም ሆነ ለተሽከርካሪ እንዲሁም በአካባቢው ላለው ንግድ ጤናማና ሰለማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር አድርጓል ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
በእምርታና በማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናክብር በሚል መሪ ቃል ዉይይት ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት
"በእመርታና በማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር"በሚል መሪ ሀሳብ በቀጣይ የሚከበሩትን ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ የበዓል አከባበር ዙሪያ ከፅ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በዚሁ መድረክ በቀጣይ የሚከበሩት የመስቀል እና ኢሬቻ በአል አከባበር ታሪካዊ የሆነ መነሻ እንዳላቸዉ ተገልጾ ሁለቱም በዓላት የምስጋና፣ የመታደስ እና የጥንካሬ ማሳያ ምልክቶች መሆናቸዉን በዚሁ ወቅት ተገልጾ የበአላቶቹን የአከባበር ሁኔታን የሚያሳይ ሰነድ ቀርቦ በጋራ ዉይይት ተደርጎበታል።
የከተማዋ በቀጣይ ሳምንት የሚከበሩት ሁለቱ የአደባባይ በዓላት ከሌላዉ ጊዜ ለየት የሚያደርጋቸዉ ታለቁን የህዳሴ ግድባችንን በጋራ ጀምረን በጋራ ጨረስን ባስመረቅንበት ማግስት መሆኑና ለዓለም እንደምንችል ያሳየንበት ነዉ ሲሉ በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥናትና ልማት ግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሠ በዚሁ ወቅት ገልፀዋል።
እነዚህ የአደባባይ በዓላት ኢትዮጵያዊያንን ባህልና እሴት እና ትዉፊታቸዉን በጠበቀና በተላበሰ መልኩ እንዲከበሩ በማድረግ ረገድ እሴቶቹን ለሀገር ግንባታ ከፍታ ለማዋል እዚህ ያለዉ ሰራተኛው ድርሻው ከፍተኛ ነዉ ሲሉም ተናግረዋል።
የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ባህላቸዉንና እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በማድረግ እሴቶቹን ለሀገር ግንባታ ማዋል፤ በዓላቱ ለከተማችንና ለሀገራችን የኢኮኖሚና ቱሪዝም ዕድገት ምንጭ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ማበርከት እንደሚጠበቅበት ገልፀው እዚህ ያለነዉ ሰራተኞች በዓላቱን በሰላም ተከብረዉ እንዲጠናቀቁ ሀላፊነታችንን በወንድማማችነትና እህትማማችነትን ባጠናከረ መንፈስ ልንወጣ ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ለረጅም ዓመታት የመንገድ መብራት መሰረተ-ልማት ባለመሟላቱ ይነሱ የነበሩ የህዝብ ቅሬታዎችን እየተፈታ መሆኑ ተገለፀ
በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሚኪሊላንድ ኮንደምንየም ተብሎ በሚጠራው እና በአካባቢው ያጋጠመ የመሬት መሰንጠቅ ነዋሪዎችን የአደጋ ስጋት ላይ እንዳይጥል የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለፁ።
