ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+9

ዛሬ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካንዚም አዳራሽ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ባማረና በደመቀ ሁኔታ አክብረናል። በበዓሉ ላይ የተከበሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና የሁሉም ክልሎች አፈ ጉባኤዎች የተገኙ ሲሆን፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ቤት፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መናገሻ፣ የአፍሪካ ህብረት መዲና እና ሶስተኛዋ የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባችን የህብረብሄራዊ አንድነታችን ተምሳሌት መሆኗን በሚመጥን ልክ ተከብሯል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+4

"ውብ አዲስ" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+9

photo content

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር በሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመራ የሠራዊቱ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንኳን ወደ ሰላም መንገድ መጣችሁ ብለው ተቀብለዋቸዋል:: የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለው እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን በመረዳት መንግስት ላደረገው ጥሪ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስምምነቱ የፖለቲካ እና የሃሳብ ልዩነቶችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በውይይትና በሰላም መፍታት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል:: የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የህዝብን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው እንደሆነ ገልጸዋል:: በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን፣ አንድነት ፓርክን እንዲሁም በአዲስ አበባ የተገነቡ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል::

photo content
+3

photo content
+9

የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ውብና ፅዱ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ገለፀ ጽ/ቤቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክቶ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርቶችንና የወዳደቁ ፖሎችን በንቅናቄ ማንሳት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈ እንደተናገሩት የአፍሪካ መዲና የሆነችው ከተማችን አዲስ አበባን ውብ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለው ለአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ የወዳደቁ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርቶችንና ፖሎችን በ7 ቀናት ውስጥ በቅንጅት ማንሳት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ስንታየሁ አክለውም ክ/ከተማችንን ለማፅዳት በቅንጅት መስራት አለብን ብለው በቀጣይ ቀናት ተረፈ ምርቶችን ማንሳት ከሁሉም ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል። የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በፍቃዱ ሀይሌ በበኩላቸው ከዛሬ ጀምሮ ባሉ 7 ቀናት የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርቶችንና የወዳደቁ ፖሎችን በቅንጅት ተሳስረን ማንሳት አለብን ብለው ለዚህም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ተረፈ ምርቶችንና ፖሎችን ለማንሳት በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል። Lideta sub-city communication office ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+1

photo content
+9

መረጃ እንደየ ሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አሁን በምንገኝበት የድህረ እውነት ዘመን ሚዛናዊነታችንን ጠብቀን መረጃዎችን ከምንጫቸው በመውሰድና ትክክለኝነታቸውን በማረጋገጥ ለሕዝብ ተደራሽ ልናደርግ ይገባል ::"የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅር የቀጣይ የመረጃ እና የኮሙኒኬሽን እስትራቴጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የኮሙኒኬሽን የቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ እንደተናገሩት መረጃ እንደየሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አሁን በምንገኝበት የድህረ-እውነት ዘመን ተቋማዊ ሚዛናዊነትን ጠብቀን መረጃዎችን ከምንጫቸው በመውሰድና ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥም ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ የሕዝቡን የመንግሥት መረጃ ፍላጎት ማርካት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል ። ጥንካሬያችንን በማጉላት ሀገራዊ ሪፎርሙን ተዋህደን በጋራ ልንመራ ይገባልም አክለው ያሉት ቢሮ ኃላፊዋ ሌሎችንም ተቋማት ተቀናጅተን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ የመደገፍ ነባር ልማዳችንን አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባልም ብለዋል ። ቢሮ ሃላፊዋ አክለውም በቀጣይ በትኩረት አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን የመጀመሪያው የመንግስትን የፖሊሲ ማዕቀፍ መነሻ አድርገን የኮሪደር ልማት ፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች የግንባታ እንቅስቃሴ ፤ብልሹ አሰራርን መታገል ፤ህግና ስርዓትን ማረጋገጥ ፤የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መሬት እንዲነካ ለማስቻል የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ፤መልካም አስተዳደርን ማስፈን ፤ገበያ ማረጋጋት ፤ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴ መጎልበት ፣ገቢን በሚፈለገው አግባብ መሰብሰብ መቻል ፤ሥራ ዕድል ፈጠራ፤የፋብሪካና የግብርና ምርት ሕጋዊ የገበያ ሰንሰለት ጠብቆ ለሕዝብ እንዲደርስ ማስቻል የሚሉት የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት ስራዎች ናቸው ብለዋል። በመጨረሻ በመድረኩ የተናገሩት የኮሙኒኬሽን መዋቅር አመራር እና ዳይሬክቶረች የተቋም ሁለንተናዊ ግንባታና ልዕልናን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል:: ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+6

የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ በጥራት እና በፍጥነት ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የተገኙ ልምዶችን ቀምረን የጀመርነው 2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች አገልግሎት ክፍት ማድረግ በምንችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት፣ ከኮንትራክተሮች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተወያይተናል። በውይይታችን የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከመጀመሪያ ዙር አንጻር ሰፊ እና የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትብብር፣ በተያዘለት ጊዜ፣ በጥራት እና ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲያጠናቅቁ ተግባብተናል። በትራፊክ መጨናነቅ እና አንዳንድ ምቾት በማይሰጡ ጊዜያዊ ሁኔታዎች የተንገላታችሁ የከተማችን ነዎሪዎችን ይቅርታ እየጠየቅኩ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በውጤቱ እንደምንክሳችሁ ቃል ለመግባት እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+4

photo content
+9

በከተማችን የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንስ እና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊና የተሟላ ዲጂታል የሲቪል ምዝገባ ስርዓት የሚተካ ፣ ለነዋሪዎች ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ለሀገራችን ሞዴል የሆነ ስራ እየሰራን እንገኛለን። የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ ምዝገባን፤ የነዋሪነት መታወቂያ አሰጣጥን፤ ሰነድ ማመሳከር እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ ዲጂታል አገልግሎት በመተካትና ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ 132 የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በካሜራ ቁጥጥር ስርዓት የተሸፈኑ በማድረግ የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የመታወቂያ፣ ሰነድ ማመሳከር እና ተያያዥ የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች በየእለቱ በየወረዳው በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት፣ ከማዕከል አገልግሎት አሰጣጡን መከታተል እና በየሰአቱ እና በየዕለቱ ምን ያህል አገልግሎት እንደተሰጠ ወዲያዉ ያለምንም ሪፓርት ማወቅ የተቻለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። የተቋሙን ሰራተኞች የተቋሙ ሰራተኛ በመምሰል ከሚያጭበረብሩ እና ከደላላዎች መለየት እንዲቻል ሁሉም የደንብ ልብስ እና መለያ ባጅ እንዲኖራቸው በማድረግ ከአሰራር በተጨማሪ ሰራተኛዉን መለየት እንዲቻል ግልፅነትን ጨምረናል። ለነዋሪዎቻችን በማዕከሉ ከሚሰጡ አገልግሎቶች በተጨማሪ የሰርግና የልደት ፕሮግራሞቻቸውን በጊቢው ውስጥ እንዲያከናውኑ የቀድሞው ሸገር መናፈሻ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጓል። በትላልቅ ፓርኮች እና የመዝናኛ ቦታዎች ከፍለው ይህን አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ ነዋሪዎቻችን በዚህ ጊቢ እና በቅርንጫፎቹ በተዘጋጁ የሰርግና የልደት ማክበሪያ ቦታዎች ፣ የቁሳቁሶች እና የፎቶግራፍ ግልጋሎት ጭምር እንዲያገኙ በማድረግ ፍትሃዊነትን እያረጋገጥን እንገኛለን። በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎትን በዋና መስሪያ ቤትም ሆነ በየቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ እና ሰፋፊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ተቋማት ነዋሪዎችን በመመዝገብ ላይ እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሁላችሁም ምዝገባችሁን እንድታጠናክሩ ጥሪ አቀርባለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+2

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ቀድሞ ከነበሩት ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ጋር በዛሬው እለት የስራ ርክክብ አድርገዋል። ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ (የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ) ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ቀደም ሲል በዚሁ ሃላፊነት ላይ የነበሩት ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የከተማው ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል። ጽ/ቤታችን ለአመራሮቹ አዲስ በተሰጣቸው ሹመትና የስራ ሃላፊነት መልካምና ውጤታማ የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et