Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የኮሪደር ልማቱ ካስገኛቸው ዋና ዋና ፋይዳዎች መካከል፣
👉የሥራ ባህል ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል፣
👉ፕሮጀክቶችን ፍጥነት እና በከፍተኛ ሁኔታ በማሻሻል መጨረስ እንደሚቻል ማሳያ ነው፡፡
👉ከተማችንንና ሀገራችንን ለመለወጥ የይቻላል አስተሳሰብ እያደገ መምጣቱ፣
👉የሕዝባችን ድጋፍ እየጎለበተ እንዲመጣ ማስቻሉ፣
👉የከተማችን ደረጃ መሻሻልና ተወዳዳሪ መሆን ያሳደገ፣
👉ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ውብና ማራኪ በማድረግ ገጽታዋን የቀየረ፣ የአገራዊ አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ ስራ መሰራቱ፣
👉የሕዝብ የጋራ መዝናኛ ቦታዎች፣ እና በርካታ የሕጻናት መጫወቻዎችና ፋውንቴኖችን በመገንባት ገንዘብ መክፈል የማይችሉ የከተማችን ነዋሪዎች የሚዝናኑባቸው ሰው ተኮር ተግባራት ተሰርተዋል፡፡
👉በተጎሳቆለና ለመኖር በማይመቹ ቤቶች እና ንግድ ቤቶች ውስጥ የነበሩ በርካታ የልማት ተነሺ የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ እና መስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ተደርጓል፣
👉የህዝብ ሮሮ የሚሰማበትን የትራንስፖርት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የአውቶብስና ታክሲ ተርሚናሎች፣ በተለይም ምድር ውስጥ ፓርኪንግ፣ የታክሲ መውረጃና መጫኛ ቦታዎችን በመግንባት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ መሰራቱ፣
👉የመሮጫ ትራኮች፣ የእግረኛ መሿለኪያ፣ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች፣ የሳይክል መንገድ መሰራተቸው፣
👉በኮሪደር ልማት ስራው ለወጣቶች ሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑ፤
👉በአገልግሎትና በአቅርቦት ላይ ለተሰማሩ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሰፊ የገበያ ትስስር በመፍጠር ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ማረጋገጥ ያስቻለ መሆኑ፤፡፡
👉የከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ገቢ እና የቱሪዝም መዳረሻ የሚያሳድጉ በርካታ ልማት ስራዎች መሰራታቸው፤
+2
የሪፎርም ስራዎችና የአገልግሎት አሠጣጥ በተመለከተ
የበጀት ዓመቱ ቁልፍ ተግባር የነበረው የተቋም ግንባታ ሲሆን በተመረጡ ተቋማት ሪፎርም በ16 ተቋማት በአደረጃጀት፣ በአሠራር፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሃይልና ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር ሪፎርም ተከናውነዋል።በቀጣይም በአገልግሎት አሰጣጥከ የሕዝብ ቅሬታ የሚበዛባቸውን ተቋማት አሰራራቸውን በመፈተሽ ሪፎርም ማድረጉ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በተለያዩ ተቋማት የተከናወኑ ሲሆን ለአብነትም የከተማችንን በገቢዎች በሆስፒታሎችና በጤና ጣቢያዎች፣ በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሬት አስተዳደርና በትምህርት ዘርፍ ቀልጣፋና ግልጽ ዘመናዊ ሥርዓት በመገንባት የተገልጋዮችን እንግልት መቀነስ ተችሏል።
+4
የሲቨል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ
👉በ2016 በጀት ዓመት በቴክኖሎጂ በመታገዝ መረጃዎችን ለሕጋዊ፣ ለአስተዳደራዊና ለስታትስቲካዊ ዓላማዎች እንዲውሉ ለማድረግ ለ364,894 ነዋሪዎች የልደት ምዝገባ እና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት ተችሏል፣
👉ለ38,239 ተገልጋዮች የጋብቻ ምዝገባ እና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት ተችሏል፣
👉በበጀት ዓመቱ ለ8,949 ተገልጋዮች የፍቺ ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት ተችሏል።
+8
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማከናወን ጀምሯል::
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያን የከተሞች ልማት ሥራ የጥራት ደረጃ ከፍ ያደረገ ፤ የአዲስ አበባን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌትነትን ያመላከተ ነው !!"
የኮሪደር ልማቱ በከተማዉ የሚያጋጥሙ የጎርፍ አደጋዎችን ለመከላከል አስተዋጾ እያደረገ እንደሆነ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ በጎርፍ አደጋ ምክንያት በሰዉና በንብረት ላይ እየደረሱ ያሉ አደጋዎችን ለመከላከል እንዲቻል እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም መድረክ ዛሬ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች ላይ ኮሚሽን መ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያከናወናቸዉን ተግባራት የተመለከተ የዉይይት መነሻ ሪፖርት በም/ኮሚሽነርና በአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ይክፈለዉ ወ/መስቀል ቀርቧል።
በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አሰኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በመሩት በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ተቋማትና የክፍለ-ከተማ ስራ አስኪያጆች በጥናት በተለዩ ቦታዎች ላይ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ያከናወኗቸዉን ተግባራት በዝርዝር አብራርተዋል።
በዚህም ተቋማቱ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች ላይ ችግሩን ለማቅለል አዳዲስ የቱቦ ቀበራ ፣ የድጋፍ ግንብ ስራዎች ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን ማጽዳት ፣ ተቆፍረዉ ክፍት የተተዉና ዉሀ ያቆሩ ጉድጓዶችን የመድፈን እንዲሁም ነዋሪዎችን ከቦታዉ የማስነሳትና ወደተሻለ ቦታ የማዛወር ስራዎች መከናወናቸዉን አስረድተዉ የኮሪደር ልማቱ እየተካሄደ ባለባቸዉ ቦታዎች ላይ የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቀነስ አስተዋፅኦ ማድረጉንም ጨምረዉ ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በኮሚሽኑ ለአደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች ላይ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም ያልተጠናቀቁ ቀሪ ስራዎች ተጠናቅቀዉ በሰዉና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ ለመከላከል ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ እንደሆነም ተናግረዋል።
ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል በየተቋማቱ የተከናወኑት ተግባራት የተሻሉ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር የቀሩት ስራዎች ላይ የየተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር በልዩ ትኩረት ስራዉ ላይ መሳተፍ እንደሚገባቸዉ አሳስበዉ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቱ እስካሁን ሲያደርግ የነበረዉን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታዉቀዋል።
በዉይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፣ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ የክፍለ-ከተማ ስራ አስኪያጆችና የኮሚሽን መ/ቤቱ ስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከ240 በላይ ዘመናዊ ካሜራዎች ገጠማ የተደረገበት የ119ኙም ወረዳ ጽ/ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ እና የደህንነት ካሜራ ቁጥጥር ስርዓት ሙከራ ተጀመረ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እያጠናቀቀ ያለው የDhCI SD WAN እና LAN የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት አካል የሆነው የወረዳ ጽ/ቤቶቹን በካሜራ ቁጥጥር እና ዕይታ ስራ እንዲሆን የማድረግ ስራ በዋና መስሪያ ቤት ሙከራ እየተደረገ እንደሚገኝ ኤጀንሲው በዛሬው እለት ሐምሌ 8 ቀን 2016 አ.ም አስታውቋል።
ኤጀንሲው ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው በዋና መስርያ ቤት አስቀድመው የተተከሉ 58 የደህንነት መቆጣጠርያ ጨምሮን በድምሩ 321 ካሜራዎች በዋና መስርያ ቤቱ ሁለት አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች፣ በ11ዱም ክ/ከተማ እና በ119 ወረዳ ጽ/ቤቶቹ የገጠማ ፕሮጀክት ስራ ከከተማው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቀን ገልፆ ስፋታቸው 55 ኢንች የሆነ 15 ስክሪኖች ለቁጥጥር ዝግጁ በማድረግ የደህንነት እና የአገልግሎት ቅኝት ሙከራ መጀመሩን አመልክቷል።
ይህ የካሜራ ቁጥጥር ስርዓት ክፍል ቀድሞ ከዋና መስርያ ቤት የህንፃ ምርቃት ጋር ወደ ስራ ከገባው የቅኝት እና የቁጥጥር ስርዓት በዓይነት እና ይዘቱ ሰፊ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ለበለጠ መረጃ ወይም ጥቆማ በነፃ መስመር 7533 ይደውሉ።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+5
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ህብረት ሽርክና ፅዳት ማህበራት ሳሊተ ምህርት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ተገኝተው እየተሰራ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራ በማገዝ ላይ ....
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአገልግሎቱ አሰጣጥ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ማንኛውንም ቅሬታ እና አቤቱታ የሚከተሉትን ሂደቶች በመከተል እንዲያቀርቡ ይጠይቃል።
+4
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስምምነት
ለሆስፒታሎች ትልቅ አቅም ይፈጥራል የተባለው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና የጤና ተቋማት ስምምነት
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስምምነት
ለሆስፒታሎች ትልቅ አቅም ይፈጥራል የተባለው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና የጤና ተቋማት ስምምነት
ለብልፅግና ጉዞ መሰረት እየጣለ የሚገኘው ኤኤምኤን
ኤኤምኤን የከተማዋ ነዋሪ ድምጽ ሆኖ በማገልገል ያመጣው ለውጥ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት - የኤኤምኤን ቦርድ
የመዲናችን የአደጋ መከላከል ዝግጁነትን ለማዘመን እየተካሄደ ባለው ዘርፈ ብዙ ተግባር የድንገተኛ አደጋዎች ህክምና (የፓራ ሜዲክ) የስልጠና ማእከልን በብቁ የሰው ሀይል ለማጠናከር ከጤና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት ውጤታማ የሚያደርግ ነው ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ሂክማ ከይረዲን ገለጹ።
ክብርት ሂክማ ከይረዲን ይህን የገለጹት ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2016 አ.ም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የፓራ ሜዲክ የስልጠና ዘርፍ ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ መግባቢያ የስምምነት ሰነድ በከተማው ጤና ቢሮ ስር ካሉ 7 ሆስፒታሎችና 1 የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በተፈራረሙበት ወቅት ነው።
ክብርት ሂክማ በዚሁ ወቅት የፓራሜዲክ የስልጠና ማእከል ቀደም ሲል በግብአት እና በሰው ሃይል ያለበትን ችግር ባደረጉት የስራ ጉብኝት ማረጋገጣቸውን አውስተው በተቋማቱ መካከል በጋራ እና በትብብር ለመስራት የተካሄደው የስምምነት ሰነድ ሀላፊነትን የጋራ በማድረግ ችግሮችን ለመፍታት እና የህክምና ማእከሉ በሀሉም መስክ ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ የጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ በበኩላቸው እንደተናገሩት የስልጠና ማእከሉ የሁላችንም እንደ መሆኑ ተቋሙ ቢደገፍ የተሻለ ሰብአዊ አገልግሎት እንደሚሰጥ በማመን ስምምነቱ ከጤና ተቋማት ጋር መፈፀሙ በጤናው ዘርፍ እንደ መልካም እድል የሚታይ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
በዛሬው እለት በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የየተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የጋራ መግባቢያ ስነድ የፊርማ ስነስርአቱ የተካሄደው በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የፓራሜዲክ ስልጠና ማእከል በኩል ኮ/ር አለማየሁ ጦፉ ሲሆኑ በጤና ተቋማት በኩል ደግሞ የዳግማዊ ምኒልክ ጤና ሳይንስ ሌጅ፣ የጋንዲ፣ዘውዲቱ፣ ምኒልክ፣ራስደስታ፣የካቲት 12 ሆስፒታል ፣ ጥሩነሽ ቤይጂንግና አበበች ጎበና ሆስፒታሎች ሀላፊዎችና ተወካዮች ናቸው።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
