ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ 2018 በፎቶ

‎በኢሬቻ በዓል በሆረ ፊንፊኔ የአባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ምርቃት፡ ‎ ‎ፈጣሪ ሆይ በእቅፍህ ስር ጠብቀን ‎ፈጣሪ ሆይ በትከሻህ ተሸከመን ‎ይህ በዓል የስኬት ይሁን ‎ገዳችን የሰላም ገዳ ይሁን ‎ይህ ጉባዬ የሰላም ይሁንልን ‎ኢሬቻ የሰላም ኢሬቻ የእውነት ነው ‎አንድነት የሰላም አንድነት ነው ‎ሰምምነቱ የሰላም ስምምነት ነው ‎ኢሬቻ የሰላም ይሁን ‎ፀደይ እጩ ነው እጩውን አሳካላት ‎ኢሬቻ ሰላም ነው፤ በሰላም አውለህ በሰላም አስገባን ‎ከመልካም ጋር አውለን ‎ከሰላም ቤት የመጣነው በሰላም ቀዬ አስገባን ‎ሰው ሰላም ይሁን ‎ከብቶች ሰላም ይሁኑ ‎አገራችንን ሰላም አድርግልን ‎ከክፉ ጦርነት ሰውረን ‎የተጣላን አስታርቅልን ‌‎ቀዬአችን አማን ይሁን ‎ከክፉ ጠብቀን ‎ደግ ደጉን አምጣልን ‎ኢትዮጵያን ሰላም አድርጋት ‎አካባቢውን ሰላም አድርግ ‎ከሰላምና እውነት ጋር አውለን ‎ዓመቱን የሰላም ይሁን ‎ዘመኑ የእድገት ይሁን ‎

አባገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች ከቄሮዎች፤ ቀሬዎች፤ ፎሌዎች እና ከበዓሉ ታዳሚዎች ጋር በመሆን የተለያዩ ባህላዊ ዝማሬዎችንና ጭፈራዎችን በማሰማት ወደ መልካ ወይንም ወደ ሆረ ፊንፊኔ መልካ (ወንዝ) በመሄድ መልካዉን (ወንዙን) በመመረቅ በእጥብ ሳር ኢሬፈና ወይንም ምስጋና የማቅረብ ሥነ ሥርዓት አስጀምረዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ለረጅም ዓመታት በየአመቱ በሆረ ፊንፊኔ መልካ (ወንዝ) በመገናኘት የኢሬፈና ወይንም ለፈጣሪ ምስጋና የማቅረብ ሥነ ሥርዓት ሲካናዉን ቆይቷል፡፡

በሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ የኢሬፈና ስንስርዓት በመከናወን ላይ ነው:: Irreecha Hora Finfinneetti Sagantaan Irreeffannaa Gaggeeffamaa Jira.

የ2018 ዓ.ም የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የ2018 ዓ.ም የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል

አሁን በዚህ ሰዓት በአዲስ አዲስ አበባ ሰማይ ስር የ2018 የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የድሮን ትርዒት በመከናወን ላይ ነው:: ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!

አብሮነት፣ ፍቅር እና አንድነት በኢሬቻ ዋዜማ ምሽት በሕብረ ቀለማት ያሸበረቀው የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ዋዜማ ድባብ በአዲስ አበባ

በመድመቅ ላይ ያለው የሆረ-ፊንፊኔ የኢሬቻ ዋዜማ አሁናዊ የምሽት ገፅታ በምስል:-

ኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እጅግ ዉብ ሆኖ የተሰራዉ የኢሬቻ ፓርክ!

በነገው እለት ቅዳሜ መስከረም 24 በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከማእከል ጀምሮ እስከወረዳ ያለው የፅዳት መዋቅር መዲናዋን ፅዱና ውብ የማድረጉ ስራ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ለበአሉ አከባበር ከአገርውስጥና ከውጭ አገራት ለሚታደሙ እንግዶችና ቱሪስቶች መዲናችን ይበልጥ በፅዳቷና ውበቷ ጎልቷ እንድትታይ ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በትጋት እያገለገላችሁ ያላችሁ ከማእከል-ክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያላችሁ የፅዳት አመራሮችና ባለሙያዎች ለዚሁ ተግባራችሁ ምስጋና ይገባችሁዋል ሲሉ አድናቆታቸውን ገልፀዋል። ኢንጅነር ወንድሙ በዚሁ መልእክታቸው ላይ መላው የፅዳት መዋቅራችን አመራሮችና ባለሙያዎች ከኢሬቻ በአል አከባበር አስቀድሞ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ሲካሄድ በቆየ ተከታታይ ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ በልዩ ትጋትና ተነሳሺነት ያከናወናችሁት አስደናቂ የከተማ ፅዳትና የውበት ስራዎች መዲናችን ይህ ወሳኝ ህዝባዊና ባህላዊ በዓል በልዩ ሞገስ፣ ድምቀትና ውበት እንድታከብር አስችሏታል ብለዋል። አክለውም መላው መዋቅራችን በዓሉ ካለፉት አመታት በበለጠ ጽዳትና ውበት እንዲከበር ያደረጋችሁት ዝግጁነትና ቅንጅታዊ ጥረት ለህዝባችን የላቀ አገልግሎትን ለማረጋገጥ የገባችሁትን ቃል ለመፈፀም ያላችሁን ቁርጠኝነትና ሃላፊነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ይህ አብነታዊ ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ሲሉም አመልክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ በአሁኑ ስአት በመዲናችን በሁሉም የመግቢያ በሮች እና በሁሉም የከተማችን መንገዶች እየተካሄደ ያለው ከተማዋን የማፅዳትና የማስዋብ ተግባር እስከ ዛሬ እኩለ ሌሊት የሚቀጥል መሆኑን ገልፀው በነገው እለትም በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ የሚመነጩ ተረፈ ምርቶችን የመሰብሰብና የማስወገድ ስራ እስከ በአሉ ማግስት ድረስ በልዩ ትኩረትና ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድም አስገንዝበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanage

አሁን በሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ላይ የሚታደሙ እንግዶች በአዲስ አበባ እየተደረገ ያለዉ አቀባበል - በምስል

በአዲስ አበባ ከተማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል በመዲናችን ሲከበር ማንኛውም አይነት አደጋዎች እንዳያጋጥም አሰፈላጊዉ የቅድመ ጥንቃቄ እና የዝግጅት ስራ መጠናቀቁን እየገለፀ ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ ድንገተኛ አደጋዎች የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነፃ የስልክ መስመር 939 ወይንም የማእከልና በ11ዱም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ፈጥነው ያሳዉቁ! 👉የማዕከልና የቅርንጫፍ ጣቢያዎች የአደጋ ጥሪ መቀበያ ስልክ ቁጥሮች 👉 ነፃ መስመር 939 ወይም 0111555300 👉ቅርንጫፍ 0111-56-02-49 ቂርቆስ ቅርንጫፍ 0114663420/21 👉አራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 0111555300 0111567004 ወይም 0111560249 👉አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ 0112-76-91-45 👉ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ 0114-42-55-63 👉 አቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ 0114-34-00-96 👉ቦሌ ቅርንጫፍ 0116-63-03-73 👉ኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ 0113-69-60-85 👉ጉለሌ ቅርንጫፍ 0112-73-06-53 👉ለሚኩራ ቅርንጫፍ 0116-68-08-46 👉ልደታ ቅርንጫፍ 0115-58-95-33 👉የካ ቅርንጫፍ 0116680236 0116684793 116668173 ይደውሉ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager