ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
በአዲስ አበባ ከተማ ለነዋሪዎች ቀልጣፋ፣ ተደራሽና የዘመነ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር የህብረተሰቡን ተሳትፎን ማጎልበት ወሳኝ እንደሆነ ተመለከተ። "ፅዳት ለራስ ነውና ፅዱና ማራኪ እየሆነች የመጣችውን ከተማችንን በዘላቂነት ፅዳቷን መጠበቅ የሁላችንም ሃላፊነት ነው" ድምፃዊ ኤልያስ ተባባል "በመዲናችን በሁሉም መስክ አየመጣ ያለው ለውጥና እየተቀየረ ያለው የከተማችን ገጽታ በሁላችንም ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል' ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ለዝርዝሩ የፕራይም ሚዲያ ዘገባን በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

#የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የታለመላቸውን አላማ እንዲያሳኩ እና ለትውልድ እንዲተላለፉ ባለድርሻ አካላት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባቸዋል - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ AMN-Addis Media Network ዝርዝር ዘገባ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+1

" ወደ አዲስ አበባ የሚመጣ ሰው የተመዘገበ መሆን አለበት። በአንድ ቦታ ወንጀል ሰርቶ የመጣ ሰው አዲስ አበባን መደበቂያ ማድረግ የለበትም " - ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለኅብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለማስገንዘብ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ መድረክ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ለተሳታፊዎች በተለይ ከሲቪል ምዝገባ እና ከቆሻሻ አስተዳደር ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መድረኩን ተከታትሎ ነበር። ዋና ሥራ አስኪያጁ ምን አሉ ? " ከዚህ ቀደም አንድ ሰው አንድ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ባለመቻላችን በሁለት በሦስት ማንነት መታወቂያ ማውጣት፤ የታክስ ማጭበርበር እንዲሁም በተጭበረበረ ማንነት የንብረት ቅሚያ ይከናወን ነበር " ብለዋል። አሁን ላይ " አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ስም መታወቂያ ያወጣ ሰው ዳግም በዛ ስም መታወቂያ የማያወጣበትን ሥርዓት ፈጥረናል " ሲሉ በሲቪል ምዝገባ ረገድ የተሰራውን ሥራ አስረድተዋል። አብዛኛው ሰው የፋይዳ መታወቂያ የሚመዘገበው በአስገዳጅ መልኩ ነው የሚሉት ኢንጂነር ወንድሙ " ይሄ መሆን አልነበረበትም " ሲሉ የማኅበረሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል። " ለምንድነው ፋይዳ የማትመዘገበው ? ሲባል ' ምን ያደርግልኛል ' የሚል ሰው በጣም ብዙ ነው ፤ ነገ ከፋይናንስ፣ ከታክስ፣ ከቤት ኪራይ፣ ከመንጃ ፈቃድ፣ ከንብረት ባለይዞታነት ጋር ይያያዛል " ሲሉ ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ የስበት ማዕከል መሆኗን በመጥቀስ ህጋዊ ያልሆኑ ፍልሰቶች መኖራቸው በከተማው መሰረተ ልማት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን አጭር ማብራሪያ ጠይቋቸዋል። ምን መለሱ ? " አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን ሰው ማወቅ አለብን ፤ በአግባቡ የተመዘገበ መሆን አለበት። መንግስት አገልግሎት የሚያቀርበው ለ5 ሚሊዮን ነው ለ8 ሚሊዮን የሚለው መታወቅ አለበት። ሰው ይምጣ ሲመጣ ግን የተመዘገበ ሰው መሆን አለበት። በአንድ ቦታ ወንጀል ሰርቶ የመጣ ሰው አዲስ አበባን መደበቂያ ማድረግ የለበትም ከተማ አስተዳደሩ ያወቀው ነዋሪ መሆን አለበት። ያንን ማድረግ የሚያስችል ሥራ እየሰራን ነው ያለነው " ብለዋል። በውይይት መድረኩ ከዚሁ ከሲቪል ምዝገባ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጉዳይ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ያለው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጉዳይ ነው። ለሚቀጥለው ዓመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ የፋይዳ መታወቂያ በመስፈርትነት በማስቀመጥ ለዚህም በአንድ ወር ውስጥ 450 ሺ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ ስራ ቢጀመርም መመዝገብ የተቻለው 130 ሺ የሚሆኑትን መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል። " ወላጆች የተሟላ መረጃ አይልኩልንም " ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ አንዳንዶቹ ለራሳቸውም የፋይዳ መታወቂያ የሌላቸው መሆኑን በመጥቀስ የግንዛቤ እጥረት ለሥራው ፈተና መሆኑን አንስተዋል። በተመሳሳይ ከሞት እና ጋብቻ ሰርተፊኬት ጋር ተያይዞ የማስመዝገብ ባህሉ ደካማ መሆኑን በማንሳት በተለይ ከሞት ምዝገባ ጋር ተያይዞ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት እዛው ሰርተፊኬት የሚያገኙበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው ብለዋል። አዲስ አበባ ከተማ ወደ 5 ሚሊዮን ነዋሪዎች አሏት ተብሎ እንደሚታሰብ በዚሁ መድረክ የተገለጸ ሲሆን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ድረገጽ ላይ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ የተመዘገቡ 2.7 ሚሊዮን እንዲሁም የዲጂታል መታወቂያ የወሰዱት 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑት ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba @tikvahethiopia

ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቱን በማዘመን የከተማዋን ነዋሪዎች እርካታ ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዝርዝር ዘገባ ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+3

photo content
+9

በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ የሚከናወነው ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል። መጋቢት 27/2017 ዓ.ም ******* የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወነው ብሎክን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ ታይዋን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል። በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበርያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ከተማችንን ውብና ማራኪ ለማድረግ ብሎኮችን፣ አደባባዮችን፣ የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ ድልድዮችን፣ ተርሚናሎችን እንዲሁም የመንገድ መሳለጫዎችን ከህገ ወጥ ቆሻሻ አወጋገድ መጠበቅና ከቆሻሻ ማፅዳት ይገባል ብለዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው የአካባቢ በየሳምንቱ በሚደረጉ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች ብቻ የከተማዋን ፅዳት በዘላቂነት ማስጠበቅ እንደማይቻል ገልፀው ይልቁንስ የፅዳት ስራን የዕለት ተዕለት ተግባር መሆን እንዳለበት አብራርተዋል። አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ መዲናችን አዲስ አበባ በተጨባጭ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ ነች ብለው ከተማችንን ከቆሻሻ ለማፅዳት ብሎክን ማዕከል ያደረገ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጽዳት ንቅናቄ የከተማውን የጸጥታ መዋቅር እና ማህበረሰቡን በማነቃነቅ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል:: የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበኩላቸው ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ፍሬ እያፈራ መሆኑን ጠቅሰው አጠቃላይ የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ለፅዳት እየሰጡት ያለውን ትኩረት አጠናክረው በማስቀጠል ውብና ማራኪ አካባቢን መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል:: በፅዳት ንቅናቄው ላይም የከተማ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አካላት ፣ የደንብ ማስከበር አባላት ፣ የፅዳት አምባሳደሮች : የተለያዩ አደረጃጀቶች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+8

photo content
+9

በመዲናችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ በአደጋ መከላከል፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በጽዳት ረገድ የህዝብ ተሳትፎን ለማጎልበት በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ከፍተኛ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማጎልበት የሚያስችል የውይይት መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው። በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ በም/ ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ባለፉት አመታት እንደ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ረገድ የተከናወኑ ስራዎች፣በተለይም በአደጋ ቅድመ መከላከል፣ በዲጂታል ማንነት (Identity) ፣ ስራዎች በኤሌክትሪክና መሰል የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች እና በከተማ ጽዳት የአለምዓቀፍ ተሞክሮና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በሰነድ አስደግፈው አቅርበዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ባቀረቡት ሰነድ ላይ በአሁኑ ወቅት በመዲናችን በጽዳት ረገድ የከተማችንን ገፅታ የቀየሩ እና በአለምዓቀፍ ደረጃ እውቅና ያሰገኙ እምርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን አውስተው በሲቪል ምዝገባ አገልግሎት ረገድም ለሌሎች ተቋማት እንደ ሞዴል መሆን የቻለ አብነታዊ ስራዎች መከናወኑን አመልክተዋል። እነዚህን በመዲናችን እየተካሄዱ ያሉ አብነታዊ እና አበረታች ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ዘላቂነት ኖሯቸው የትውልድ ባህል እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣የሚዲያ አመራሮች፣ የእምነት አባቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የተለያዩ አደረጃጀቶች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠርና ተሳትፏቸውን በማሳደግ ረገድ ኃላፊነታቸዉን መወጣት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል:: ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+3

photo content
+9

በከተማዉ እየተሰጡ ያሉ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በከተማዉ እየተሰጡ ያሉ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና ካላቸዉ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣የሀይማኖት አባቶች ፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም የዉይይት መድረክ አካሂዷል። በዉይይት መድረኩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድም ሴታ እንደተናገሩት የከተማዉ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የሚሰጡትን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፣ የጽዳት አስተዳደር ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን እየመራና እያስተባበረ መሆኑን ጠቅሰዉ በእነዚህ አገልግሎቶች ፅዱ ፣ ከአደጋ ስጋት የተጠበቀች፣ቀልጣፋ አገልግሎት የተረጋገጠባት አዲስ አባን እዉን ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን አብራርተዋል። ኢንጂነር ወንድሙ አያይዘውም እነዚህን አገልግሎቶች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠልና በተሟላ ሁኔታ ለመፈጸም በሚደረገዉ ጥረት ሁሉ በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ በህብረተሰቡ ያላቸዉን ተቀባይነት በመጠቀም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅና በማስገንዘብ ረገድ ከጽ/ቤቱ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር አህመድ አብዱራህማን እንደተናገሩት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ መምጣታቸዉን አዉሰተዉ በተለይም ቋሚ ኮሚቴው በየወቅቱ በሚያካሂደው ክትትልና ድጋፍ የታዩ ጠንካራና ውጤታማ ስራዎች በህዝብ ተሳትፎ ተጠናክረው የሚገባቸው በመሆኑ ይህን መሰል መድረክ የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ይመሰክራሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ምሽት ይጠብቁን