cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Rapture daily devotion 🪶

(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 12) ---------- 39፤ ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር። 40፤ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። Admins Bruke: @life_time_winner Tsion: @Zionhop Amanuel: @SirEmmanuell

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
957
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-57 أيام
-2130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
እጅግ ድንቅ እና ለመንፈሳዊ እድገታችን የሚጠቅም channel ልጠቁማቹ !!!!!
إظهار الكل...
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን ለማግኘት
አጫጭር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በየቀኑ ለማግኘት
በ Live የእግዚአብሔርን ቃል ለመማር
መንፈሳዊ ውይይት ለማድረግ
☑️ Post has been saved. your post number is: 71730 to send it via inline mode use: @Qualitymovebot 71730
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄 " ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" (ትንቢተ ኢሳይያስ 9:6) እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይህ በዓል የጌታችንና የመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል ዓለማት የተፈጠሩበት ምድር የተመሰረተችበት ሰማያት ፀንተው የቆሙበት ቃል ፀጋን እና እውነትን ተሞልቶ በመካከላችን ያደረበት ከሰማይ ሰማያት ዝቅ ብሎ የወረደበት፣ ፍጥረትን ከወደቀበት ርኩሰትና ከታሰረበት የክፉ ሰንሰለት ሊቤዥ የወደደበት፣ ክብሩን ሁሉ ትቶ ስለእኛ በደል መስዋዕት ሊሆን ለመስቀል ሞት እንኳ ሊታዘዝ ፈቅዶ ጌታችን እና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁሙ አምላክ ፍፁም ሰው የሆነበትን ድንቅ ቀን የምናስብበት በዓል ነው። ስለዚህ በዚህ ቀን ሁላቹም ከምሽቱ 2:30 ላይ በሚኖረን የlive🛑 ፕሮግራማችን ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን ➛ መቅረት በፍፁም አይፈቀድም Join our group for live experience ⏩https://t.me/TheRaptureGen7 RAPTURE GENERATION
إظهار الكل...
❤ 2
#catch_the_fire 🔥 #SUNDAY__service 2:30pm #The_Rapture_Generation ☁️ ሻሎም 👋 እንዴት ቆያቹ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ በሚኖረን የlive🛑 ፕሮግራማችን ላይ እንድትገኙ እያሳሰብን፣ በእለቱ፣ #የእግዚአብር_ቃል_ጊዜ #የትንቢት_ጊዜ ስለሚኖረን ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ እንድትመጡ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ተባረኩ Join our group for live ⏩ https://t.me/TheRaptureGen7 ➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛ የወሩን Daily devotion በሙሉ ለማግኘት የRAPTUR GENERATION ዌብሳይት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ይችላሉ። website link ➛ https://raptue_generation_2023.renderforestsites.com THE RAPTURE GENERATION
إظهار الكل...
RAPTURE Generation

" ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።" (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4:17) The year of Divine visitation Admins @life_time_winner @zionhop Channel⏩

https://t.me/RaptureDailydevo_7

إظهار الكل...
RAPTURE Generation

" ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።" (1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4:17) website link ➛

https://raptue_generation_2023.renderforest

Admins @life_time_winner @zionhop Channel⏊

https://t.me/RaptureDailydevo_7

Photo unavailableShow in Telegram
የፀሎት ሰው ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 23፤ በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። 24፤ እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። ---------- (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 16) እግዚአብሔር ሊሰጠን ያላሰበውን ነገር እንድንጸልይ ፈጽሞ አይጠይቀንም። መልስ ለመስጠት ስላሰበ እንድንጸልይ ይነግረናል። ብዙ ሰዎች ይህንን ስለማያውቁ ጸሎታቸው የማይሰራ እየመሰላቸው ይበሳጫሉ እንዲሁም ተስፋ ይቆርጣሉ። ሰዎች መፀለይ የማይችሉት ፀሎታቸው መልስ የሚያገኝ ስለማይመስላቸው ነው። አምላክ ለፀሎታችሁ መልስ በመስጠት እንደሚደሰት ብታውቁ ኖሮ በሁሉም የህይወታቹ አቅጣጫ ሰላም ፣ እረፍት፣ የፀሎት ህይወት ይበዛላቹ ነበር። ደስታችን ፍፁም እንደሚሆን ከላይ ባለው ጥቅስ ላይ ተናግሯል። ፀሎት በህይወታችን ላይ ለውጦችን የምናደርግበት ድል የምናገኝበት መንገድ ነው። የቀደሙት ነቢያት ፀልዩ፣ የቀደሙት ሐዋርያት ፀልዩ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ፀልዮ እንድንጸልይ አስተምሮናል። በዚህ ዘመን ወደ መጨረሻ እየተቃረብን በምንሄድበት፣ የበለጠ ለመፀለይ ጥረት ማድረግ አለብን። ይህ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር የሚንገናኝበት መንገድ ነው፣ ስለዚህ ካልፀለይክ፣ በቀላሉ ከእሱ ጋር ምንም ግንኙነት የለህም። እኛ የፀሎት ሰዎች ነን፣ ጸሎት ደግሞ የሕይወታችን መለኪያ ነው! ትንቢታዊ መግለጫ እኔ የፀሎት ሰው በመሆኔ የድል አድራጊ ሕይወት እኖራለሁ ፣ ከአምላኬ ጋር በየእለቱ እገናኛለሁ፣ በመፀለይ በስኬት የተሞላ ሕይወት እኖራለሁ። አሜን!
إظهار الكل...
🔥 4❤ 2🎉 2😁 1🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
ድል መንሻ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ " ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።" (መዝሙረ ዳዊት 8:2) ብዙ ሰዎች በተለያየ መከራ እና ችግር ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ለማጉረምረም ከማንም ይልቅ ቅርብ ናቸው። በህይወትህ ላይ የሚመጣው መከራ ይሁን ችግር በማጉረምረምህ ወይም ዝም በማለት ልትወጣው እንደማትችል ማወቅ አለብህ። አሁን ካለህበት ይሁን ወደፍት ከሚመጣብህ ከየትኛውም አይነት ከማይመቹ ሁኔታዎች ለመውጣት እግዚአብሔር ካዘጋጀልህ መንገዶች አንዱ ድል መንሻክ ምስጋና ነው። አንተ ክርስቲያን ከሆንክበት ጊዜ አንስቶ ለጠላት ኢላማ ሆነሃል። ምክንያቱም አንተም ኢየሱስን በማመንህ የሰይጣን ተቃዋሚ ሆነሃል። ሁለት ተቃራኒ መንግስታት ሊስማሙ በፍፁም አይችሉም አንተ የተቃወምከው መንገስት ደግሞ አንተን መቃወሙ የማይቀር ነው ስለዚህ በህይወትህ ለሚመጡ ለየትኛውም ጦርነቶች ድል መንሻህ ምስጋና ነው። በምስጋና ውስጥ ድል፣ባለጠግነት ፣ሰላም፣እረፍት፣ ማሸነፍ አለበት። እግዚአብሔር እንኳን ጣላቶቹንና ቂመኞቹን ለማጥፋት ከሚጠቡት ልጆች ምስጋናን ነው ያዘጋጀው። ስለዚህ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ በሚያጋጥሙህ መከራዎች እና ጦርነቶች ድል መንሻህ ምስጋና ስለሆነ ከማመስገን መቆጠብ የለብህም። ትንቢታዊ አዋጅ እኔ በህይወቴ ሁሉ አመሰግናለሁ። ጠላትን በምስጋናዬ ድል ነሰዋለው። የናዝሬቱ እየሱስ ድልን ሰቶኛል። ድል:፣ማሸነፍ፣ ባለጠግነት በህይወቴ ዘመኔ ሁሉ ይከተሉኛል። እኔ የአሸናፊ ልጅ ነኝ።
إظهار الكل...
👍 4🥰 2🔥 1👏 1🎉 1🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
📆ሰኞ_17 እውነተኛ ወዳጅ   " ብዙ ወዳጆች ያሉት ሰው ይጠፋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ። (መጽሐፈ ምሳሌ 18:24) ታማኝ ጓደኞችህ እና የምትወዳቸው ሰዎች በጣም በሚያስፈልጉበት ጊዜ አንተን ሊያሳዝኑህ ይችላሉ።  እርግጠኛ ነኝ ብዙዎች ይህ እንዳጋጠማቸው በተለያዩ መልኩ ቢሆንም አጣጥመውታል። ነገር ግን ወቅቱ ምንም ይሁን ምን ሊተማመኑበት የሚችሉት አንድ ወዳጅ ብቻ ነው። አይወድቅም ፣ አያሳፍርም ፣ እንድሁም ለእርሱ ሲመችው ብቻ አይታይም ወይም አይገለጥም። እርሱ ሁል ጊዜ ከአንተ ጋር አለ፣ እርሱም  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በህይወትህ አንተ እርሱን እውነተኛ ወዳጅ ለማድረግ ራስህን የሰጠህበት እና ከእርሱ ጋር ግንኙነተት የጀመርክበት ያች ቀን በእውነት የማይጥለውን እውነተኛ ወዳጅ ፤ ወደ ከፍታ የሚያደርሰውን ይዘሃል ማለት ነው! ሃሌ ሉያ! ይህን አዲስ ሳምንት ስትጀምር ከእውነተኛ ወዳጅህ ጋር ህብረት በማድረግ ጀምር። እርሱ ይመራሃል፣ ጥበቡ በአንተ ህይወት ላይ ይፈሳል። መፅሐፍ ቅዱስ ስናገር ከወንድም ይልቅ አብልጦ ይጠጋል ወይም ይጣበቃል ይላል፣ ይጣበቃል ‘ የሚለው አገላለጽ እንደ ሙጫ መጣበቅ ማለት ነው። እርሱ የትም አይሄድም እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ለመሆን ቃል የገባ እና የገባውን ቃል የማያፈርስ ውድ ወዳጅ አለህ።   ትንቢታዊ አዋጅ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ክብር፣ ሃሌ ሉያ፣ አምላኬ በእኔ ውስጥ ነው፣ የእኔ እውነተኛ ወዳጅ፣ ሙሉ በሙሉ  የምተማመንበት ብቸኛው ወዳጅ! የእኔ ዓለም ለዘላለም ተለውጧል. ዛሬ በኢየሱስ ስም አሜን! ተጨማሪ ጥናት ዮሐንስ 14፡8-9
إظهار الكل...
🥰 4👍 2🔥 2🤩 2❤ 1
Photo unavailableShow in Telegram
እሁድ 16 RAPTURE GENERATION DAILY ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ___የሚፍለቀለቅ ደስታ_ " የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።" .............................. መዝሙረ ዳዊት 16:11 የእግዚአብሔር መገኘት በመንፈሳችሁ እንዲሁም በሕይወታችሁ ውስጥ ሊገለጽ የማይችል ደስታ እንደሚያመጣ በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ ይህ ደስታ ማንም ሊያጠፋው የማይችለው የደስታ ዓይነት ነው። በዚህ ባልተረጋጋ ዓለም ውስጥ እየኖርን እንኳ ደስታችን የማይጠፋ ነው። ይህ ደስታ ወደ መንፈሳችሁ ሲገባ ሰላምን፣ ሳቅን፣ እረፍትን እንዲሁም ድልን ያመጣል። ሰዎች አንተን እያዩ በደስታህ ይገረማሉ  ከውስጥህ ወደ ውጭ የሚፈልቀው የጌታ ደስታን ይመለከታሉ። በህይወትህ በተለያየ ሁኔታዎች ውስጥ  ሆነህ አንተን ሊያስቸግርህ ወይም ሊያሳዝንህ ለሚፈልግ ለእሱ አትገዛ ይልቁንም፣  የመንፈስ ደስታ በህይወትህ ውስጥ እንዳለ በማወቅ ዘመንህ በደስታ እንደሚሞላ በመረዳት በጌታ ደስታ ልትኖር ይገባል። የመንፈስ ደስታ ከአንተ ውስጥ በመውጣት ወደ ድል መንገድ የምመራህ እርሱ መሆኑን በመረዳት ነፍስህን ለዚህ ደስታ አስገዛው። ትንቢታዊ አዋጅ አፌ ዛሬ በሳቅ ተሞላ! በእኔ ውስጥ ያለው የጌታ ደስታ ኃይሌ ነውና እበረታለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ የማይነገር ደስታን በኢየሱስ ስም ማግኘቴን እቀጥላለሁ! ተጨማሪ ጥናት 1ኛ ጴጥሮስ 1:8
إظهار الكل...
👍 5❤ 4🔥 1👏 1
የመንፈሳዊ አይን መከፈት " የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ናት። ዓይንህ ጤናማ በሆነች ጊዜ ሰውነትህ ሁሉ ደግሞ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ታማሚ በሆነች ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ የጨለመ ይሆናል።" (የሉቃስ ወንጌል 11:34) መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከምድር አፈር አበጀው ይላል። ሰው ብሎ የጠራው አፍንጫውን ወይም እጁን ብቻ አይደለም ሁለንተናውን ነው ሰው ብሎ የጠራው ምክንያቱም የሰውን ልጅ ከብዙ ዓይነት የሰውነት ክፍሎች ነው ያበጀው። የሰውን ልጅ ካበጀው በኋላ ለአዳም  ኤደን ገነትን ይጠብቃትና ያበጃት á‹˜áŠ•á‹ľ ሀላፊነትን ሰጠው። ይጠብቃት ዘንድ የሚለውለውን ለመተካት የገባው የዕብራይስጥ ቃል ሾማር የሚል ነው ይህ ማለት መመልከት (watch) ማለት ነው። ለአዳም እግዚአብሔር ሀላፊነት የሰጠው ከመጠበቅና ከማበጀት ያለፈ ኤደን ገነትን እንዲመለከትም áŠá‰ áˆ­á˘ መፅሐፍ ቅዱስ  ስናገር ኤደን ገነት ለማየት ደስ የሚያሰኝ ነበር ይላል። እግዚአብሔር በኤደን ገነት ዛፎችን ሲያበቅል አራት አይነት ዛፎችን አብቅሎአል እነዚህም 1) የመብል ዛፍ ለስጋ ምግብ እንዲሆን 2)የህይወት ዛፍ ለህይወት መብል እንዲሆን ፣ 3)መልካም እና ክፉን የሚታሳውቅ ዛፍ ለዕውቀት እንዲሆን 4)ለማየት ለአይን ምግብ  የሚሆን ዛፍ እንዲበቅል አድርጎአል። መፅሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት ጀምሮ ስታነቡ አይን ወሳኝ እንደሆነ ይናገራል። እኛ ብዙ ጊዜ አይናችን ከውስጥ ወደ ውጭ የምናይበት መሳርያ ብቻ እንደሆነ እናስባለን ኢየሱስ ሲናገር ግን ከውጭ ወደ ውስጥ ብርሃን የሚገባበት በር እንደሆነ በማቴዎስ 6:22-23 ይናገራል። መፅሐፍ ቅዱስ እግሩ ሽባ የነበረውን ሰው ጴጥሮስ ወደ እኛ ተመልከት በማለት በማየት ውስጥ ጤንነትን እንደተካፈለው ይናገራል። ኤልሳዕ ቅባትን ከኤልያስ የተካፈለው በማየት ውስጥ ነው ምክንያቱም በማየት ብዙ ነገሮች ወደ አንተ ታስገባለህ። አይን ማለት ከውጭ ዓለም ወደ ውስጣቹ የሚታስገቡበት በር ነው አንደበታቹ ደግሞ ከውስጥ ወደ ውጭ የምታወጡበት ነው። ትንቢታዊ አዋጅ የእኔን አይኖች መንፈስ ቅዱስ በሀይል ይከፍተዋል። መንፈሳዊ code የምንረዳበትን አቅም መንፈስ ቅዱስ አውን ሰጠኝ በኢየሱስ ስም አሜን።
إظهار الكل...
❤ 5👍 1🔥 1🥰 1👏 1🤩 1