cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መዝሙረ ዳዊት

🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ ☞ @mezmurochh ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ☞ @Mezmuredawit_bot ላይ ያገኙናል

إظهار المزيد
Advertising posts
43 077المشتركون
+9724 hour
+3617 يوم
+98430 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

1️⃣ በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው? 2️⃣ በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም 3️⃣ የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ?       📚 የሕማማት ጸሎት 📚 በሕማማት የሚጸለየው በአብዛኛው ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት፤ የነቢያት ጸሎት ሲሆን የጌታን መከራ መስቀል የሚያነሱ መጻሕፍት ይጸለያሉ፡ ሕማማተ መስቀል፣ ድርሳነ ማሕየዊ የመሳሰሉ። መልክአ መልኮች፣ ድርሳናትና ገድላት የማይጸለዩት ዋናውን ጸሎት በጌታ ሕማማና መከራ መስቀል ለመስጠት ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ በቤተክርስቲያን የሚነበበው ንባብ (ግብረ ሕማም) ዋናው የጸሎት ክፍል በመሆኑ ያንንም መሳተፍ ትልቁ ጸሎት ነው።           🌿 ጥብጠባ 🌿 በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ  ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ  ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡  ይህም የጌታን ግርፋት ያሳያል።፡ሕዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ ይሆናል። አርብ ከ 11 ሰአት በኋላ ስግደት እንደሌለ ግብረ ሕማሙ "አልቦ ስግደት "ይላል። 📚 በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም 📚 በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡         📌 "ኪርያላይሶን" 📌 ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡             📌 "ናይናን" 📌 የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡              📌 "እብኖዲ"  📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው            📌 "ታኦስ" 📌 የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡             📌 "ማስያስ" 📌 የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው            📌 "ትስቡጣ" 📌 ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።   📌 "አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ" 📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡ 📌 "አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ" 📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ  ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው 📌 "አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ" 📌 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡ 👉 የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ? አንድ ክርስቲያን በፆም ጊዜ ከፀሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ 41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ 12 ጊዜ ---- #እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 12 ጊዜ ---- #በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ 12 ጊዜ ---- #ኪራላይሶን (አቤቱ ማረን) 5 ጊዜ ---- #ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ፣ ሮዳስ (አምስቱ የጌታ ችንካሮች) ✞ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ✞ ✞ አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ✞  ✞ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር ✞      ✞ በፍስሐ ወበሰላም:: ✞ የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት                    ✍     ✔ ❤ ከብርሃነ ትንሳኤው አምላክ በሰላም ያድርሰን ❤ ለመቀላቀል   👇       ┏━━° •❈• ° ━━┓     💚 @mezmurochh 💚     💛 @mezmurochh 💛     ❤ @mezmurochh ♥       ┗━━° •❈• ° ━━┛
إظهار الكل...
◦ የሰሙነ ህማማት ሰኞ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡     ◦ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ "ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ" ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ-እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡      ◦በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡     ◦በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ አንጽሆተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦          ◦ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፤ ቤተመቅደስ፣ቤተጸሎት፣ ቤተመሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ፦ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ፤ ገርፎም አስወጣቸው ፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡       ◦ በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና ፭ሺ ከ፭መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡ የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት                               ✍     ✔ ❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ለመቀላቀል   👇       ┏━━° •❈• ° ━━┓     💚 @mezmurochh 💚     💛 @mezmurochh 💛     ❤ @mezmurochh ♥       ┗━━° •❈• ° ━━┛
إظهار الكل...
⁉️ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል  ሊቀላቀሉት የሚገባ ቻናል ነው። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል) ቤተ ክርስቲያን ከሕግ በላይ ናት‼️ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነው ማለት ምን ማለት ነው⁉️ ሕግ መቼ ተመሠረተ⁉️ ለምንስ ተመሠረተ ⁉️      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel      @EOTC_-OPEN_channel
إظهار الكل...
❤️ተፈስሒ ኦድንግል❤️
📚ሕግ መቼ ተመሠረተ ⁉️
📢ድምፀ ተዋህዶ📢
📔ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት📔
🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት ✅JOIN✅ የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏
إظهار الكل...
❤️ተፈስሒ ኦድንግል❤️
✅JOIN✅
إظهار الكل...
🔐ክፈት🔐
🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት ✅JOIN✅ የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏
إظهار الكل...
❤️ተፈስሒ ኦድንግል❤️
✅JOIN✅
إظهار الكل...
🔐ክፈት🔐