cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Modlochu♥♥♥

መሳጭ ጥቅሶች የፎቶ ውድድር ቀልድ ና ቁምነገር ወግ ግርምት ጭውውት እና የፎቶ ዘድድር

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
156
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Join 👉 @tiktok_ethiopia1 size1.8m.b Share
إظهار الكل...
Join 👉 @tiktok_ethiopia1 size2.1mb Share
إظهار الكل...
እድሜ ለኮሮና ስንቱን አስተዋውቆ ያሳየናል ገና 'ርዕሱ ነው 😁 ______ ( ሚካኤል_እንዳለ ) አንቺ ሥራ ዋይ ነሽ ማታ ገቢ እኔም አላይሽ በቀኑ ፥ አታይኝም አንቺም ጠዋት እንደወጣን ፥ እንደ ግንቦት ጀንበር ማታ ነው 'ምንገባው ግጦሽ ተሰማርታ እንደዋለች ጊደር እሱንም ለማደር ! . . የት ውዬ እንደመጣው ፥ በምንም አታውቂ ያንቺን አትነግሪኝ ፥ የኔን አጠይቂ ? ቀኑን ሙሉ ስንዞር ውሃ እንደተጠማ እንደራበው ንሥር ለወግ ያህል ነበር የምንተያየው ስንገባ 'ባንድ በር እሱንም ለማድር ! . . አመታትን ቆጥረን አብረን ብንኖርም በአንድ ትሪ እንጂ አብረን አልበላንም ገላችን የሚያርፈው 'ባንድ አልጋ ቢሆንም ጎን ለጎን እንጂ ፥ አብረን አልተኛንም ትዳር ይሄ አይደለም እስኪ እወቂያቸው አብሮ መብላትና ባንድ ትሪ መብላት ልዩነት አላቸው አብሮ መተኛትም ባንድ አልጋ ከማደር ለየቅል እያቸው . . ያኔ ድሮ ድሮ ከሥር ከመሰረት ካብሮነት ጅማሮ ተቀንጭቦ ጊዜ ለማሳለፍ አብሮ አንድነት ከሌለ የሚያስተዋውቀን ፥ የጋርዮሽ ዓለም አብሮ መኖር ከንቱ ለመተኛትማ ይገናኛል ሁሉም . . ዛሬ ደዌ ሰፍቶ ሳታውቂው አግብተሽ ሳያውቅሽ አግብቶ እንደ እኔና እንዳንቺ ፥ ሁሉ ቀሳ ገብቶ ጊዜ ሲያበጥረው ሲሰለቻች ሁሉም ጠባያችን እርቃን ፥ አደባባይ ሲቆም እንደ በጋ ሰማይ ፥ ሲገለጥ እውነቱ በአንድ አብሮ ሲውል ፥ ሁሉ ሰው ከቤቱ እድሜ ለበሽታ ደፋሪው ሲበዛ ይተዋወቅ ጀመር ያገር 'ባል ከሚስቱ @ethio_art @ethio_art @mebacha @mebacha
إظهار الكل...
አቡነ ሚርየል ከግል ደሞዛቸው 15 ሺ ፍራክ ላይ አንድ ሺ በመቀነስ ሌላው አስራአራት ሺ በሙሉ ለምንዱባን እንደየፈርጁ የሚቸር ነበርና እህታቸው ማድሟዜልም ሆነ ሰራተኛቸው ማዳም ማርሏ ቤቱን ለመምራት በገንዘብ እጥረት ውስጥ ነበሩ። ማርሏ አንድ ቀን ተጨማሪ አበል እንዲጠይቁ ትገፋፋቸዋለች። አበል ጠየቁ። ባለስልጣኖችን ቢያስቆጣም ሲኖዶሱ ተጨማሪ የመጓጓዣና ደብዳቤዎች መላላኪያ አበል 3000 ሺ ፍራንክ ጨመረላቸው። ዜናውን ስትሰማ ማዳም ማርሏ በደስታ ፈነደቀች። የተለወጠ ግን አልነበረም። ከተመደበላቸው አበል አንዱም እልፍኛቸውን ለመጥቀም አትውልም ይልቁንም ሆስፒታሎችን፣ እናቶችን፣ ተጥለው የተገኙ ህፃናትና የሙት ልጆችን ለመርዳት አውለውት ነበር ይሄ ልብ ወለድ ነው— በልብ ወለድ ውስጥ የሃይማኖት አባቶች ባለጠግነታቸው የመንፈስ ነው። ------ በኤሌክትሪክ አጥር የሚጠበቅ፣ የደህንነት ካሜራዎች፣ ውሾች፣ ቦዲጋርዶች የሚጠብቁት ቤት። ምቹና ዘመናዊ መኪኖች የቆሙበት ጊቢ። በፋርስ ምንጣፎች፣ ወርቅ ቁሶች ያማረ እልፍኝ፣ በምቾት የሚያንደባልል አልጋ፣ ምናልባትም ያን ሁሉ ጥበቃን አልፎ የሚመጣ ጠላትን የሚከላከል ከ መፅሃፍ ስር ያደፈጠ ማካሮቭ። ከግቢው ስትወጣ ደግሞ ከግንቡ ስር የተኮለኮሉ ለማኞች፣ ራቁታቸውን የሚሯሯጡ ወላጅ አልቦች፣ እድሜና ችጋር ወድቆባቸው የጎበጡ አዛውንቶች። በገሃዱ አለም የሃይማኖት አባቶች ባለጠግነታቸው ቁሳዊ ነው። ፍልስፍናን ለምቾታቸው ማረፊያ ደንበኛ አድርገው ያነጣጥፏታል። • "ባለጠጎች ሰማያትን ከሚወርሱ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ ይቀላል" ይልሃል ድህነትን አለማምዶ ልብህን በስንፍና ያጭቀዋል። ያራገፍከውን ፀጋ እሱ ይሸከመዋል። ያኔ እንዳይገርምህ " እግዜር ሰጠ እግዜር ነሳ" ንም አብሮ ያለማምድሃል። ላብህን በዚህ መልኩ ያራገፍክ እለት መከረኛ ትሆንና ባሪያው ያደርግሃል። • ስለ ነገ አትጨነቅ ይልሃል— በሰውና በኤሌክትሪክ አጥር ከልሎ ወደ ነገ ራሱን ለማሻገር ይጥራል። ለነገ ክፋቱ ይበቃዋል በሚል አይዘናጋም ። • "ወፎቹን አታይምን? " እያለ ወደሰማይ እንድታንጋጥጥ ያደርግሃል— ያኔ ኪስህ ገብቶ ለራሱ ይወሰወዳል። (አይዞህ እራስህ ነህ ኪስህ የምትገባው። ወፍን እያየህ ኪስህ ውስጥ ዱዲ የማስቀመጥ ፍላጎት የለህም። እሱን አበልፅገኸው አንተ ትደኸያለህ— ሃጥያተኛ ነህ!) • "ና ለፈጣሪ ቤት እንስራለት" ይልሃል። ልብህን ሊያንፅ ሲገባው ድንጋይ በማሸከም ስጋህን ያንፀዋል። • ስለ ህግና አስራትም ይነግርሃል። ታምነዋለህ። እምነትህ ደግሞ ጣፍጦት የሚመገበው አመሉ ነው። በላብህ ከሰራኸው ላይ ከፈጣሪም ከቄሳርም ድርሻ እያፈራረቀ ይቀምሳል። • "ፈውስ ወዲህ ነው" ይልሃል። እንደ ሸቀጥና ቁስ "ፈውስን በሚዲያና በጋዜጣ አስተዋውቆ እንድትገዛው ያባብልሃል። "አልጋሃን ይዘህ ሂድ" መባል ናፍቆህ ፈውስ ልትገዛ ብር በከረጢት ይዘህለት ትሄዳለህ። ሰይጣንህን ለማባረር ሲያንሰኝ ነው በሚል ያሽሟጥጠሃል። አትዘን የግዢ ነገር በሙሉ ሁሌ ልክ ሆኖ አያውቅም። • "ማንም ሁለት ያለው አንዱን ያካፍል" ይልሃል። ልቡናህን ማነውለል ተክኗል። በዚያ የንብረትህ ህጋዊ ሳይሆን ዶግማዊ ተካፋይ መሆኑን በልቡናህ ያውጃል። ሚስትህን ሳይቀር ሊካፈልህ ይፈልጋል።( አትናደድ) ምክኒያቱም የምስጢር አባቴ ነው ብለህ ትናንት ሌላ ቅምጥ እንዳለህ ተናዘህለት ይሆናላ። ስለዚህ ካለህ ሁለት አንዱን ማካፈልህ የውዴታ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው( "አለዚያ" ይልሃል፣ ከአስርቱ ትዕዛዝ አንድ ሁለቱን ጠቅሶ የመዋሸትና የማመንዘርህን መረጃ ለራስህ መልሶ ይሸጥልሃል። • የሆነ ቀን ይሄን አለም ትሰናበተዋለህ። ልብህ ሳይፀዳ አካልህም እንደዛለ ትሄዳለህ። በመጨረሻው ሰአት እንኳ ከራስህ ጋር አይተውህም፣ ፈጣሪህን ሳይሆን እሱን ስታገለግለው እንደኖርክ እንዲገለጥልህ ብቻህን አይተውህም። ኑዛዜህን ሊረከብ ይመጣል። በሃዘን ቀናቶችም ከተውከው ቤት አይቀርም አፅናኝ አንደበቱን ተጠቅሞ ሌላ ባሪያ አይኖቹ ይቀላምዳሉ። ማነው ተረኛ… ሚስትህ፣ እህቷ? ምስኪኑ አጎትህ፣ ባለፀጋው የቢዝነስ ሸሪክህ፣ "በታላቅ የፈውሰወና ታምዕራት ኮንሰርት" ዕለት የተዋወቅከውና ወዳጅህ ሆኖ የዘለቀ አልቃሽ…? እንጃልህ! ከቪክተር ሂዩጎ መከረኞች በላይ አንተ መከረኛ ነህ። —————— "ይሄ ህዝብ በከንፈሩ ያመልከኛል ልቡ ግን ከኔ በጣም የራቀ ነው፣ የሰውም ስርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ፣ በከንቱ ያመልኩኛል " ማቴ 15:9 ሱራፌል አየለ @ethio_art @ethio_art @ethio_art
إظهار الكل...
ደመ -ነፍስ ....... ©ሲራክ የነገ ህልሙ ዛሬ ቀድማ በቅፅበታት ስትዘከር ሰውነቱ አይጥ ሁና በድመቶች ስትባረር የአዝማናት አይነ ውሃ በአዘኔታ እምባ ሲያቀር ክፉ ህልም ናት ይህቺ ነገር ብሂም ሆነው ለታወሩ በተዘጋች ሀገር ሲያንኳኩ ለኖሩ .......................////...................... ሲራክ @siraaq @ethio_art @ethio_art @ethio_art
إظهار الكل...
ለክቡር ዘበኛ ገንዘብ ቤት አንደኛ መምሪያ ሬድዮ ጣብያ አገልግሎት ጉዳዩ:- ስለ ሰራተኛ መቀጠር አቶ ጥላሁን ገሰሰ የተባሉ ግለሰብ ከ መጋቢት 25 ቀን 1949 ዓ.ም ጀምሮ በወር 40 ብር ደመወዝ ተቀጥረዋልና ከዚህ ቀን አንስቶ ስማቸው ከ አንደኛ መምሪያ ደመወዝ መክፈያ መዝገብ ላይ ተሞልቶ ሰቀርብልዎ በየወሩ ወጪ እየሆነ እንዲከፈላቸው ይሁን :: ግንቦት 13 ቀን 1949 ዓ.ም **************** ጥሬ ቆሎ ለክቡር ዘበኛ ገንዘብ ቤት አንደኛ መምሪያ ሬድዮ ጣብያ አገልግሎት ጉዳዩ:-የደመውዝ ቅጣትን ይመለከታል አቶ ጥላሁን ገሰሰ የተባለው የክፍሉ ሰራተኛ ጥሬ ቆሎ አምጥቶ የሙዚቃ ስራ በሚሰራበት ቀን እየጎረመደና እያስጎረመደ ለሠራተኞችም እያደለ ሥራ በማስፈታት ከአንድ ወር ደመወዙ ላይ 3 ብር እንዲቆረጥበት ይሁን። ሐምሌ 9 ቀን 1949 ዓ.ም ***** ታሪክን የኃሌት ********* 💜ውብ አሁን💜 ┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄ @Keneyalew_teweld @Keneyalew_teweld ┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄
إظهار الكل...
የጠቢቧ ሴት ድንጋይ —— ጠቢቧ ሴት በተራሮች መካከል ስትጓዝ ወንዙ ላይ አንድ የከበረ ድንጋይ አገኘች። በቀጣዩ ቀን ደግሞ አንድ የተራበ ሌላ ተጓዥ አገኘች፡፡ ጠቢቧ ሴትም የያዘችውን ስንቅ ከፍታ እንዲመገብ አደረገችው፡፡ የተራበው መንገደኛም ምግቡ ይብቃኝ ብሎ ከመሄድ ይልቅ ያገኘችውን የከበረ ድንጋይ ተመለከተውና የከበረውን ድንጋይ እንድትሰጠው ጠየቃት፡፡ የከበረውን ድንጋይም ያለምንም ማቅማማት ሰጠችው፡፡ ተጓዡም ዕድል ፋንታውን እያሰበ እያመሰገነ ጉዞውን ቀጠለ። የከበረው ድንጋይ ሙሉ ሕይወቱን ያለምንም ሥራ በተድላ እና በደስታ ማሳለፍ እንዲችል እንደሚያደርገው ያውቅ ነበር፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ድንጋዩን ለመመለስ ወደ ጠቢቧ ሴት ተመልሶ መጣ፡፡ "እያሰብኩበት ነበር" አለ "ድንጋዩ ምን ያህል የከበረ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ከዚህ የበለጠ የከበረ ነገር ትሰጭኛለሽ ብዬ ተስፋ ስላደረኩ ለመመለስ ወስኛለሁ፡፡ እጅግ የከበሩ ነገሮችን ለመስጠት የሚያስችልሽን የበለጠ የከበረ ነገር እንድትሰጭኝ እሻለሁ፡፡ ይህን ክቡር ድንጋይ እንድትሰጭኝ ያደረገሽን የከበረ ነገር ስጭኝ፡፡" *** በምድር ላይ የጥበብ ሁሉ ጥበብ ራስን መግዛት ነው፡፡ ራሳችንን መግዛት የሚያስችለንን የከበረውን ጥበብ ከከበሩ ቁሶች በላይ አንሻ፡፡ ደስታ የሚገኘው በከበሩ ቁሶች ሳይሆን በከበረ ማንነት እንጂ። የከበረ ማንነት ደግሞ ራስን መግዛት ነው፡፡ @ethio_art @ethio_art
إظهار الكل...
ብልኋ  እንቁራሪት ----------- (ሚካኤል_እንዳለ) አንዲት እንቁራሪት በኩሬ ውስጥ ያለች የሚቃጠል መንደር ፥ ከሩቁ እያየች ትፀልይ ጀመረ ፥ እንደዚህ እያለች . . እባክህ ጌታዬ ይህን እሳት አጥፋው ባለበት እንዲቆም ግዛቱን አታስፋው ብላ ለፈጣሪ ፥ አዝና ስትናገር ለካስ ካጠገቧ እባብ ቆሞ ነበር እሱም በመገረም ፥ በጸሎቷ ነገር የሽሙጥ እያየ እንዲህ ይላት ጀመር . . እንደው ምን ትገርሚ እንደምን ትደንቂ እሳቱ እንዲጠፋ ፥ ጌታን 'ምጠይቂ እሱ 'ሚደድ እዛ እሩቅ ነው ካንቺ ዘንድ በምን ደርሶብሽ ነው ያንቺን ቤት የሚያነድ ? ደሞም ከውሃ ውስጥ ቁጭ ብለሽ ያለሽው የማይደርስብሽን ፥ እሳት የምትፈሪው እያለ በሹፈት ፥ ከልቡ ሳቀባት ወደታች በንቀት አዘቅዝቆ እያያት . . ይ'ን ጊዜ እቁራሪት እየተገረመች በእባብ ጅልነት በጣም እያዘነች እንዲት ትለው ጀመር ቀና ብላ እያየች አዎ ትክክል ነህ ፥ እሳቱ እሩቅ ነው እኔም ያለሁበት ዙሪያውን ውሀ ነው ነገር ግን አስተውል እጅግ አትሳት ቃጠሎውን ቶሎ ወዲያው ካላቆሙት ከ'ኔ ዘንድ መ'ተው ነው ውሀ የሚቀዱት . . እናም ያላወከው እውነታው ይሄ ነው ምንም'ኳ እዚህ ብቀመጥ ከውሃው እዛ እሩቅ ቢሆን መንደሩ 'ሚነደደው ካልጠፋ በጊዜ ፥ አምላክ ካላቆመው የ' ኔም ቤት ነውና ተዝቆ የሚያልቀው . . ስለዚህ ወዳጄ አያጥቃህ ጅልነት ቃጠሎው ባይደርስም እኔ ካልሁበት እዛ ነዶ ነዶ ፥ እጅግ ከባሰበት ባልዲ ተሸክመው ሲመጡ ለመቅዳት ይከቱኛል ወስደው ፥ ከሚነደው እሳት . . ይህን አውቄ ነው ከሩቁ መፍራቴ አጥፋው በሚል ፀሎት ምድር መደፋቴ የአቅሜን ያህል እነሱን መርዳቴ ብላ ስትናገር ፥ እባብን ገረመው ማየት ያልቻለውን ገልጣ ስታሳየው . . እናም እሩቅ ያለ ከ' እኛ የማይደርስ የሌላ ነው ያልነው ፥ እሳቱ ሲለኮስ ስለማይቀር እዚ ፥ መምጣቱ ቀስ በቀስ ትልቅ እገዛ ነው የሰው ችግር አይቶ ፥ ለኔ ብሎ ማልቀስ --- (ሚካኤል እንዳለ) ሰኔ 1 , 2012 ዓ.ም አ.አ አስኮ መነሻ ሃሳብ - ዳኒኤል ክብረት @ethio_art @ethio_art @Mebacha @Mebacha
إظهار الكل...
🤣🤣🤣አይ እማማ😂😂😂 @emperorzkm
إظهار الكل...