cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

yene eyta

-W🙏 -E🤗 -L💘 -C💓 -O😉 -M🙋 -E😘 to 👇👇👇 LOVELY WORDS(TEXTS)💬 POEMS MUSIC🎼 APHORISMS LETTERS💌 PHOTOS(PICTURES) FICTIONS 👍👇👇👇👇 @Philo😇¿

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
201
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✍👌 ከማበዴ በፊት አገር ጭንጫ ሆነች ትውልድ የሙጃ አረም እምነት ተበላሽ ጠፋ የእውነት ቀለም ህዝብ ተማረረ እንደ ደረቅ ጌሾ ተስፍ ከሸለለ... የትእቢት ሀውልት በራሳችን ቀዬ በግፍ ተተከለ የፍትህ ጉልላት እንዳሮጌ ጎጆ ኗሪው ላይ ወደቀ ለዘላለም ያልነው የሀቅ እንቶ ፈንቶ ዛሬ ላይ አለቀ ለጥላ ያልነው ዛፍ ለንዳድ አጋልጦን ማለዳ ደርቀ አንሱ ብረት አንሱ የባርነት ቀንበር አፈር እናስልሰው የወሰዳትን ቀን ቀኑን አጨልመን እስክናስመልሰው እያሉ ሲያወሩ በወኔ ሲናጡ እኔ ያንቺ ገልቱ ባካቹ እሱን ተዉት ካለችበት ቦታ የነብሴን ሀቅ አንጡ አምጡልኝ አለሜን የቀልቤን ሽራፊ የኔን ፖለቲካ የኔን ቀዳዳ ልብ በፍቅር ክር ሰፊ ብረት ወዲያ ጣሉ አቀብሉኝ ቀለም የውስጤን ሰቆቃ... የፍቅሬን ስንክሳር ከመከተብ ሚበልጥ ሌላ ትግል የለም እያልኩ እጮሀለው... አገር ታክል ነገር ... ባንዲት የመንደር ሴት በድፍረት ለውጠ የህዝቡን አደራ ለሰላሳ ዲናር ዶሮ ሳይጮው ሸጠ ይሉኛል ጀግኖቹ... እንኳንስ አደራ ሊሸከም ጫንቃዬ እኔንም ባደራ የማስቀምጥበት አጥቻለውኝ ልብ ቸግሮኛል ቅዬ... ከማበዴ በፉት... ከአገሬ አብልጬ እንድወድሽ ልነግር ይኸው እጽፋለው አንባቢ ይሰልቸኝ ካሻበት ያቋርጠው ካሻበት ይመለስ እኔ ግን ፅፋለው ጥልቅ የፍቅር ባህር የወለሉ አሽዋ እስኪነካኝ ድረስ ደግሞ ቅጥ የጠፍው ዝብርቅርቅ አቅጣጫ ከዝብርቅርቅ ነብሴ ከቱባው መዝዤ በፍቅር ቁማር ውስጥ አንድ እኔኑ አስይዤ ከማበዴ በፊት... ልብሴን ቀዳድጄ ወዲያ ከመጣሌ ከመሮጤ በፊት ያዙት ከመባሌ ላንቺ ያልኩትን ገላ ላንቺ የጋረድኩትን አገር ባይኑ እስኪያፍሰው ሰውን ያህል ናፍቆት እንዴት ይችላል ስው እልሻለው ውዴ እንደውም እራሴን ሳየው በጥሞና ላብድ ነው አልኩ እንጂ ካወኩሽ ጀምሮ መች ጤና አለኝና አንዴ ሲያስናፍቀኝ እንዴ ሲያስመርረኝ በባዶ እያሳቀ ደግሞ ሲያስደምመኝ በደረቀ ለሊትክ መንደርሽን ሲያዞረኝ አንድ ቀን ሳይደላኝ ይኸው ከእብደት አፋፉ ላይ ጠርዙ ላይ ቆሜአለው ድሮ ያበድኩ እኔ "ላብድ ነው" እላለው ቢሆንም... ለይቶልኝ ልብሴን ከመጣሌ በፊት ጎዳና ወጥቼ ድንጋይ ሳልወረውር መስታወት ሳልሰብር ሀዘን በውስጤ አለ እንባ የሚይስጨርስ ቅስም የሚሰብር የልቤን ስብራት ባደራ በል አገር ለንፋስ ከምተው ወደ እብደት ዘመቻ ይዤው እዘምታለው ከማበዴ በፊት... ምን አለበት ፍቅሬ ..መወፈፍ አፋፍ ላይ በቆምኩበት አሁን ብትሰናበቺኝ ብትይኝ ደህና ሁን ወደ እብደት አለሜ ደስ ብሎኝ ብገባ እንደ ፈሪ ማቶ ከምወፍፍ በእንባ እብዶች ምን ይሉኛል እይተነፋረኩ ስቀላቀላቸው በፈሪ ወፈፌ ሲደፈር ቀያቸው ዘራፍ እያልኩ ባብድ እንቢ እያልኩ ብወፍፍ በጤነኞቹ ፊት እየፎከርኩ ባልፍ እልም ጭልጥ ነው ውሀ አይላመጥም ላረባ ጤንነት ፍቅር ለሞተበት ቀኝ እጄን አልሰጥም ከማበዴ በፊት... ምን አለበት አሁን እብደትን አትፍራልው ባንተ አልተጀመረም ማንም በእናቱ ሆድ ልብስ ጥሎ መሮጥ በፅንሱ አልተማረም ብለሽ ብትመክሪኝ እቅፍቅፍ ብለን ለፅበት ጠረንሽ በደሜ ውስጥ ቢናኝ በጤናና ጤና ለመጨረሻ ቀን ላንዴ ብንገናኝ ከዛሬ በኋላ አንቺም እንዴሌላው እብድ ብለሽ መሮጥ መሸሽሽ አይቀርም የሚጠራ ይጥራው ይሄ ወፈፌነት ካልጠራሽ አንቺንም ጠረንሽ ሲርበኝ በየ ሱቁ እየዞሩኩ እሷን እሷን የሚል ሽቶ አለ ስላቸው አበደ ይሉኛል ምን አስቸኮላቸው እኔ እኮ ስወ.........ድሽ ደሞ እንደጫካ ማር ስምሽ ሲጣፍጠኝ እንደውም.... ከማበዴ በፊት ቆይ ስምሽን ልጥራው እግዚሆ መሀረነ በቃ ስምሽ ጠፋኝ እብደት ጀመረነ (ቻው ጤነኝነቴ ገደል ግባ ማሰብ፣ መንገዱም የኔ ነው ሜዳውም የሴጣን፣) የላይኛው ስንኝ ቤት አልመታም አሉ፣ ቤትን ከማፍረስ ነው የእብደት ጅማሬ የመወፈፍ ውሉ። ካበድኩኝ በኋላ... አንዴ አድምጪኝማ አንዴ ስሚኝ ውዴ ከጭቃ ጠፍጥፈሽ ፍቅርን እፍ ያልሺብኝ አንቺ ነበርሽ እንዴ ልስገድላት እግዜር ወግድ ከመንገዴ @berkrekta @lovelyhistory • ∞
إظهار الكل...
( በላይ በቀለ ወያ ) . . አንቺ ባለሽበት ፣ሚባለውን እንጃ እኔ ባለሁበት ፣ ወሬ እንደጠብ መንጃ የታጠቀ ሞልቷል ፣ ቢደላም ቢከፋም ጆሮ አይሰማው የለም የሚበላ እንጂ ፣ የሚባል አይጠፋም ! #ይባላል ! ።። ለምሳሌ ያህል ትጥቃችን ባያልፍም ከዱላ ከድንጋይ ፣ ግፋ ቢል ከክላሽ ወዮለት ለጠላት ፣ ኋላ እንዳይበላሽ ኒውክለር ሲመካ አደቧን ትያዝ ግብፅ ፣ ትረፍ አሜሪካ አላርፍም ካሉ ግን ፣ ወየው ለሁለቱም ባለም ፊት ፈስ በፈስ እንዳናደርጋቸው በእጃችን ነው ያለው ፣ ደብተራም መተቱም ይባላል ፣፣፣፣ ለምሳሌ ያህል ሰማንያ ሺህ ዳቦ ፣ ሊያውም በአንድ ቀን ሊጋገር ነው ሲሉን ፣ በምን መብራት ብለን ፣ አናውቅም ጠይቀን እንዲሁ በማመን ፣ ሆዳችን ይሞላል በመሪ አንደበት ደም ያፀናው ሰንደቅ ፣ ጨርቅ ነው ይባላል። ።።። እኔ ባለሁበት ፣ በመኖሬያዬ ሀገር ከፀሐይዋ በታች ፣ የማይባል ነገር አንዳች አይገኝም ፣ ሁሉ አፉን ያክላል የሚለው ያጣ ሰው የተባለን ነገር ፣ "አይባልም "ይላል ።። የሆነው ሆነና ፣ ባለሁበት ሀገር የማይባል ነገር አጋጥሞኝ አያውቅም ለምሳሌ ያህል አባይ በአምስ አመት ተገድቦ ያልቃል በኢትዮጵያ ምድር ፣ ፀሀይ አትጠልቅም አስራ አንድ ፐርሰንት ሀገሪቱ አድጋለች ፣ በኑሮ ብንደቅም ስልጣን የህዝብ ነው ፣ ግን ለህዝቡ አንለቅም ይባላል ። ለምሳሌ ያህል ባይቆጥራቸው እንጂ፣ ዘንግቶ ምናልባት ጠቢቡ ሶሎሞን ከጠቢቡ በላይ ፣ አይበልጥም በእቁባት #ይባላል ( በላይ በቀለ ወያ )
إظهار الكل...
የዉነት ያልነበሩህ ሰዎች ~ጊዜ እያነጠራቸዉ ~ማንነታቸዉ እየጎላባቸዉ ~ፍላጎታቸዉ እየተገፈፈባቸዉ ያላንተ ተፅእኖ ከህይወትህ ፈቀቅ እያሉ ማስተዋል የሆነ ስሜት አለዉ😊 #Vero
إظهار الكل...
Henok Abebe - Ande Sew 16k.m4a6.30 KB
በሰቀቀን ህይወት ከራሱ እየሸሸ ሰዉ እንዴት ይኖራል ሳይነጋ እየመሸ🤷🏻‍♀ ✍🏻Ana
إظهار الكل...
የሰዉ ሀገር ሆኖ ዋጋዉን አላዉቀዉ ለሰከንድ ሸለብታ እንቅልፍ ስንት ነዉ? …Ana
إظهار الكل...
Andra_Day_Rise_Up_Official_Music_Video_Inspiration_Vers1.m4a6.06 KB
ብታውቂ ስትስቂ! ጠፈርን እንደምታደምቂ፣ መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ፣ ብታውቂ! ÷÷÷÷÷ ስትስሚ! አጥንት እንደምታለመልሚ፣ ታማሚ ልብ እንደምታክሚ፣ ብታውቂ! ÷÷÷÷÷ ስታወሪ! ዱዳ እንደምታናግሪ፣ መነኩሴውን ከሱባዔ፣ ፈላስፋውን ከጉባዔ፣ እንደምትጠሪ፣ ብታውቂ! ÷÷÷÷÷ እንኳንስ በኔ ልትስቂ፣ ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ፣ አይሽ ነበር ስትማቅቂ!!! ✍🏻በእዉቀቱ ስዩም Share👍👍👍
إظهار الكل...
አግብተሻል አሉ የናጠጠ ሀብታም፣ ባለ ብዙ ዝና፣ ባለ ብዙ ካዝና፣ ብር ሚተነፍስ፣ ዶላር የሚሸና፣ አብረሽኝ ብትውዪ፣ አብሬሽ ባመሽም፣ እንዳዲሱ ባልሽ፣ አበል አልከፍልሽም! 😌😏🤗
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.