cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

✞ ዲያቆን ዘማሪ ናትናኤል ዘደብረ ምህረት ሚዲያ // ᴅᴇᴀᴄᴏɴ zemari ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ ᴢᴇ ᴅᴇʙʀᴇ ᴍɪʜɪʀᴇᴛ ᴍᴇᴅɪᴀ ✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ 👉ሥርዓተ ዋይዜማ ወማኅሌት 👉መዝሙር ዘሰንበት፣ ምስባክ ዘዘወትር ወዘሰንበት 👉ዝማሬያት 👉ስንክሳር ዘቅዱሳን፤ ከነ ቅዱሳን ሥዕላት 👉መንፈሳዊ ትምህርት 👉ሥርዓተ ቅዳሴ 🎯ለማግኘት ቻናላችንን ይጐብኙ። ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ። መወያያ 👉 @deaconnatnael_group ለአስተያየት👉 @Deaconnatnael01_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
351
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#ዜና_ቤተክርስቲያን 🙏💒🙏💒🙏💒 በምሑር አክሊል ወረዳ የመቆርቆር  ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተመረቀ። ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጉራጌ ሀገረ ስብከት ምሑር አክሊል ወረዳ የሚገኘው የመቆርቆር ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ህንፃ መቅደሱ ተጠናቆ ተመረቀ። ቤተ ክርስቲያኑ ከ156 ዓመታት በፊት የነበረና በአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሎ እስካሁን ድረስ ሳይሰራ የቆየ ጥንታዊ የሆነ ቦታ እንደሆነ የአካባቢው ምዕመናን የተናገሩ ሲሆን በአንድ ግለሰብ አማካኝነትና በምዕመናን ድጋፍ አሁን የተመረቀው ህንፃ ቤተመቅደስ መሰራቱን አያይዘው ገልፀዋል። በዕለቱ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እና የአቡነ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ፣ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ፣ ከተለያየ ቦታ ስፍራው ላይ በመጡ እና የአካባቢው ምዕመናን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል። #Ethiopia #ለጽድቅ_እንስራ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆቼ ናቸው በመረጡት የማህበራዊ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ🙏  ለበለጠ መረጃ  📞 +251931635019 ይደውሉ!!! ➽ የፌስቡክ ገጼ      👇👇👇👇 https://www.facebook.com/deaconnatnaelmedia ➽የቴሌግራም ገጼ      👇👇👇👇 https://t.me/deaconnatnaelmedia ➽ የኢንስታግራም ገጼ       👇👇👇👇👇 https://www.instagram.com/deaconnatnaelmedia ➽ የዩቲዩብ ቻናሌ      👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@deaconnatnaelmedia ➽ የቲክ ቶክ ገጼ      👇👇👇👇 https://vm.tiktok.com/zemarideaconnati ➽የትዊተር ገጼ     👇👇👇👇 https://twitter.com/dn_natnael ➽ ሁሉንም የማህበራዊ ሚዲያዎቼን ለማግኘት      👇👇👇👇👇👇👇👇 https://solo.to/deaconnatnaelmedia መረጃው ለብዙዎች እንዲዳረስ #ላይክ #ሼር በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታዎ ይወጡ🙏
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

#ዜና_ምርቃት 🙏👏❤👏 ዘማሪ ዲያቆን Dani Birega ይህን ድግስ አዘጋጅቻለሁ ኑ ተቋደሱልኝ እያለ ነው! ወንድም እንኳን እግዚአብሔር እረዳህ🙏
إظهار الكل...
#መንፈሳዊ_ጥቆማ 👇👂💒👂👇 #ጌታችን_ከትንሣኤው_በኋላ_ለምን_በላ? (ሉቃ 24፡36-46) 1. ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ 2. ሥጋውንም ነፍሱንም ተዋሕዶ እንደተነሣ ለማጠየቅ 3. ቀጠሮ ስለነበረው ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በኅብረት ሳሉ 3 ጊዜ እንደተገለጠላቸው የታወቀ ነው ፤ በኅብረታቸው ውስጥ የተገለጠው 3 ጊዜ ይሁን እንጂ በ40ው ቀናት ውስጥ ለእያንዳዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት ሆነውም ሳይገለጥላቸው የዋለበት ያደረበት ጊዜ እንደሌለ መተርጉማነ ሐዲስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ በተገለጠላቸው ጊዜም አስገራሚና አስደናቂ ያልተለመዱ ነገሮችን በማሳየት ነበር፡፡ በተዘጋ ደጅ መግባቱ አስደንግጧቸዋል፤ እሱ መሆኑን በአካለ ሥጋ እየተመለከቱ ቢሆንም ምናልባት ምትሐት ቢሆንስ? መንፈስ እሱን መስሎ አስመስሎ ተገልጦልን ቢሆንስ? የሚል ከባድ ጥያቄ በኅሊናቸው ይወጣ ይወርድ ነበር፡፡ ረስተዉት ነው እንጂ በባህር ላይ ሲራመድ አይተዉት ነበር፤ ባህሩን ሲገሥጸው ማዕበሉን ጸጥ ሲያደርገው ነፋሱን ሲያዘው ተመልክተው ነበር ዘንግተዉት እንጂ የአራት ቀን ሬሳ ሲቀሰቅስ የዕለት ሬሳ ከእንቅልፍ እንደማንቃት ሲያስነሣ በዓይናቸው አይተው ነበር ግን ሌሎችን ከሞት ያስነሣውን አምላክ የእሱን ከሞት መነሣት ለማመን ተቸገሩ! በዚህ ምክንያት "በምትሐትነት" ጠረጠሩት! ጌታም  በተዘጋው ደጅ ብቻ ሳይሆን በተዘጋው ልባቸውም ውስጥ ገብቶ ሀሳባቸውን እየመረመረው ነበርና  "ለምንት የዐርግ ኅሊና እኩይ ውስተ ልብክሙ፤ ክፉ ሀሳብ በልባችሁ ለምን ይመላለሳል?" እኔ ራሴ እንደሆንኩ እጆቼንና እግሮቼን እዩ ...መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ግን ዳስሳችሁ አረጋግጡ አላቸው፡፡ ይህንም ብሏቸው ግን አላመኑም ነበር ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው "ወእንዘ ዓዲ ኢአምኑ እምድንጋፄ.." ከድንጋጤም ከደስታም የተነሣ ገና አለማመናቸውን ተመልክቶ ♥በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን?♥ በማለት ጠየቃቸው አነሱም የተጠበሰ ዓሣና የማር ወለላ ሰጡት፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ፡፡ ለልማዱ ጌታችን ሲመገብ 6ቱ ይቆማሉ ስድስቱ ይቀመጡ ነበር በዚህ ጊዜ ግን ሁሉም ቆመው ዓይን ዓይኑን እያዩት በፊታቸው በላ፡፡ በፊታቸው የበላበት ምክንያት፦ 1. ምትሐት እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ፦ ✝ጌታችን ፍጹም ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ብዙ ነገሮች አሉ ፤ መራብ መጠማት መብላት መጠጣት፤መተኛት መነሣት፤ ራሱን ከምእመናን ጋር መቁጠር፤ መፍራት መጸለይ ...ሁሉ ለአጽድቆተ ትስብእቱ (ሰው የመሆኑ ትክክለኛነት) ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሐዋርያት ምትሐት እንዳልሆነ ያምኑ ዘንድ ቀድሞ ሲበላ እንዳዩት ሁሉ ዛሬም እያዩት በፊታቸው መመገቡ ምትሐት ላለመሆኑ ማረጋገጫ ነበር፡፡ 2. ሥጋውንና ነፍሱን ተዋሕዶት እንደተነሣ ለማጠየቅ፦ ✝ ብዙ መናፍቃን ከጥንት ጀምሮ ይሰናከሉ ከነበረበት ትልቅ ጉዳይ አንዱ የጌታችንን ትንሣኤያዊ ማንንነት የተመለከተ ነው ፤ መለኮቱና ሥጋው በመስቀል በሞት የተለያዩ የሚመስላቸው ፤ ያም ባይሆን ሥጋን በመቃብር ትቶት የተነሣ የሚመስላቸው ፤ ወይም በሌላ የተለየ አዲስ ሥጋ የተነሣ የመሰላቸው ብዙዎች አሉ፡፡ ጌታችን እዩት እጄን እዩት እግሬን እዩት ጎኔን ብሎ የቀኖትና የጦር ምልክቱን ያሳያቸው ያንኑ የተገረፈውን የተሰቀለውን ሥጋ ተዋሕዶት የማይፈርስ የማይበሰብስ አድርጎ እንዳስነሣው ለማጠየቅ ነው፤ ቶማስም በተወጋው ጎኑ ቀዳዳ እጁን እንዲያስገባ የፈቀደለት ከሌላ የክህደት ቀዳዳ ለመታደግ ነው ፡፡ መብላት መጠጣት የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ምልክት ነው፤ ጌታም ይህንን ተዋሕዶ ለማረጋገጥ እንጂ ርቦት ወይም ከትንሣኤ ወዲያ መራብ መጠማት መብላትና መጠጣት ያለ ሆኖ አይደለም፡፡ The Orthodox Study Bible ላይ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ኅዳግ (Foot note) ላይ እናገኛለን " Christ eats not because He in His resurrected body needs food, but to prove to the disciples that He is truly risen in the flesh" ክርስቶስ የተመገበው በተነሣበት አካል ምግብ የሚያስፈልገው ሆኖ ሳይሆን በእውነት በሥጋ መነሣቱን ለደቀመዛሙርቱ ለማረጋገጥ ነው እንጂ" ይላል፡፡ ትርጓሜ ወንጌልም "ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ" ካለ በኋላ "ትንሣኤውን እንዲረዱ እንዲያምኑ" በፊታቸው በላ በማለት ግልጽ አድርጎታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም "አኮ ፈቂዶ ለመብልዕ አላ በልዐ ወሰትየ ከመ ይእመኑ ከመ ውእቱ ተንሥአ እምውታን፤ ምግብ የሚያስፈልገው ሆኖ እይደለም፤ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን ያምኑ ዘንድ በላ ጠጣ እንጂ" ብሏል፤ ሃይ.አበ 66፡8፡፡ 3. ቀጠሮ ስለነበራቸው፦ ዕለተ ሐሙስ ማታ ላይ "ኢይሰቲ እምዝንቱ አጺረ ፍሬ ወይን እስከ አመ እሰትዮ ምስሌክሙ ሐዲሰ በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት፤ በአባቴ ሥልጣን ታድሼ እስከምነሣ ድረስ ከዚህ የወይን ጭማቂ አልጠጣም" ብሏቸው ነበር ፡፡ ይህ አነጋገር ብዙ ምሥጢራት ያሉት ቢሆንም በዋናነት የሚያመለክተው ግን ትንሣኤን ነው፦ "በአባቴ ሥልጣን.." የሚለው የማይራብ የማይጠማ የማይደክም አይሁድ ለመከራ የማይፈልጉት፤ ከእንግዲህ ወዲህ የመስቀል ሞት የሌለበት ሆኖ መነሣቱን የሚያመለክት ሲሆን የወይኑን ጭማቂ ጽዋ አለመጠጣቱ ግን እሱ የሚጠጣው የመስቀል ጽዋ ስለነበረው ነው ...ይኸውም ሊታወቅ "ይህቺ ጽዋ ከእኔ ትለፍ" እያለ መላልሶ ይጸልይ እንደ ነበር ተገልጧል፤ ያን ጽዋ እሱ ካልጠጣልን እኛ የወይኑን/የደሙን ጽዋ መጠጣት አንችልምና፡፡ ያንን ሁሉ አጠናቆ በሐዋርያት ፊት የማር ወለላ ቀረበለት እሱንም በፊታቸው በመብላትና በመጠጣት የዕለተ ሐሙሱን ንግግሩን አስታወሳቸው፡፡ ይህንንም ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ ወንጌል "በበሊዖቱ አዖቀ ጽድቀ ትንሣኤሁ ወሰትዮቱኒ ያሌቡ እንበይነ ቃሉ ዘይቤ "ኢይሰቲ እምዝንቱ አጺረ ፍሬ ወይን"" በማለት ገልጦታል፡፡ ✝ማስታወሻ፦ የቀድሞው የፋሲካ በግ ሥጋው ተጠብሶ መራራ ቅጠል ይጨመርበት ነበር፤ አሁን ግን አዲሱ ፋሲካ ክርስቶስ ስለታረደ መራራ ቅጠል ሳይሆን እርሱ ባወቀ የማር ወለላ ቀረበለት! ✝ሌላው በጣም የምንገረምበት ጉዳይ ደግሞ "ወነሥአ ዘተርፈ ወወሀቦሙ፤ የተረፈውን አንሥቶ ሰጣቸው" የሚለው ነው፡፡ ☞ለምን ሁሉንም አልበላውም? ☞ለምን ቀምሶ አልተወውም? ☞ለምን አስተረፈ? ☞ካስተረፈስ ለምን የተረፈውን ለነሱ ሰጣቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች በመገረም መጠየቅ እንችላለን!!! የተጠበሰው ዓሣና የማር ወለላው፦ ➊የትንቢተ ነቢያት ምሳሌ ነው ➋የዘመን ምሳሌ ነው ➌የሥራ ምሳሌ ነው ➍የትምህርተ ወንጌል ምሳሌ ነው ➎የተአምራት ምሳሌ ነው ጌታ የበላውን በልቶ የተረፈውን ለሐዋርያት መስጠቱ፦ ✝፩. በእሱ የተፈጸመውንና ወደፊትም በእነርሱ የሚፈጸመውን ትንቢት ለትውልድ፡እንዲገልጡ የተረፈውን ሰጥቷቸዋል፡፡ ✝፪. ዘመነ ነቢያትንና የእርሱን ዘመን (33 ዓመት ከ 3 ወር) አሳልፎ የተረፈውን ዘመን ሰጥቷቸዋል (ዘመነ ሐዋርያት) ✝፫. እሱ ሠራዬ ኃጢአት ሊቀ ካህናት ከባቴ አበሳ እንደሆነው ሁሉ እነሱም እንዲያጠምቁ እንዲያቆርቡ እንዲያስሩ እንዲፈቱ ሥልጣነ ክህነትን ሰጥቷቸዋል ✝፬. እሱ 3 ዓመት ከ 3 ወር እንዳስተማረ እነሱንም "ሑሩ ወስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት" ብሏቸዋል
إظهار الكل...
👍 1
✝፭. እሱ ብዙ ተአምራትን እንዳደረገ እነሱንም ♥እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል♥ ብሏቸዋል፤ ዮሐ 14 ፡12፡፡ ከዚህ በኋላ የተረፈውን ምግብ እንደሰጣቸው ሁሉ ከ3 ዓመት ከ3 ወሩ የተረፈውን ትምህርት አስተማራቸው.... የነገርኳችሁ ሁሉ ቃሌ ይህ ነው ብሎ አእምሯቸውን እንደተዳመጠ ብራና ንጹሕና ቀለም ለመቀበል የተዘጋጀ አደረገላቸው፡፡ ....ሐዋርያትም ማስተዋል ጀመሩ...!!! እንድናስተውል ይርዳን!!! አሜን! @መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
إظهار الكل...
#ዜና_ቤተክርስቲያን 👇💒👇💒👇💒 የአቡነ ጴጥሮስን ጉዳይ........ 🎙🎙🎙🎙🎙👇👇 የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገር ያለመግባት ጉዳይ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ ዉዉይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም መጨረሻ ይሄንን ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ እነዚህ ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መንግስት እንዲያነጋግሩ ሰይሟል። 1 ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ 2 :-ብፁዕአቡነ አብርሃም ፣ 3 :-ብፁዕአቡነ ኤርምያስ ፣ 4 :-ብፁዕአቡነ ጎርጎርዮስ፣ 5 :-ብፁዕአቡነ ሳዊሮስ ፣ 6 :-ብፁዕአቡነ ሄኖክ ፣ እና 7 :-ብፁዕአቡነ ናትናኤል #ዘሚኔንሶታ በመሆን መንግስትን እንዲያናግሩ፣ችግሩ እንዲፈታና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ ዛሬ ወስኗል ፣
إظهار الكل...
#ዜና_ቤተክርስቲያን 🙏❤🙏❤🙏❤ ደጉ ሳምራዊ ክሊኒክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ! ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የጤና አገልግሎት ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ወገኖቻችን የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ተከታታይ የሕክምና የተልእኮ ጉዞዎችን (Medical Missions) እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት በጣም አስፈላጊ በሆኑ አካባቢዎች የሕክምና መስጫ ማዕከላትን መክፈት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ በመሆኑ የመጀመሪያውን ክሊኒክ በደብረሊባኖስ ገዳም ለማስጀመር ተችሏል። “ደጉ ሳምራዊ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም የአረጋውያን መርጃ መካከለኛ ክሊኒክ” በመባል የተሰየመው ይህ ክሊኒክ በገዳሙ አበው መነኮሳት ጸሎት እና ቡራኬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ክሊኒኩም በገዳሙ ውስጥ ለሚያገለግሉ መነኮሳት፣ ካህናት፣ የአብነት ትምህርት መምህራንና ተማሪዎች፣ ወደ ገዳሙ ለሚጓዙ ምእመናን እና ከ 60 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተቋቋመ የሕክምና ማዕከል ነው። ለዚህ መሳካት በገንዘብ፣ በግብአት፣ በእውቀት እና በጸሎት የረዳችሁንን በሙሉ በተጠቃሚዎቹ ስም ከልብ እናመሰግናለን። አላትዮን ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ሜዲኬር ስፔሻላይዝድ ክሊኒክ፣ ራዕይ ፋርማሲውቲካልስ፣ ያኔት ስፔሻላይዝድ ሜዲካል ሴንተር እና ጎፋር ስፔሻላይዝድ የዓይን ክሊኒክ ላደረጋችሁልን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ የላቀ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን ሲል ማኅበሩ በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል። #Ethiopia #ለጽድቅ_እንስራ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆቼ ናቸው በመረጡት የማህበራዊ ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ🙏  ለበለጠ መረጃ  📞 +251931635019 ይደውሉ!!! ➽ የፌስቡክ ገጼ      👇👇👇👇 https://www.facebook.com/deaconnatnaelmedia ➽የቴሌግራም ገጼ      👇👇👇👇 https://t.me/deaconnatnaelmedia ➽ የኢንስታግራም ገጼ       👇👇👇👇👇 https://www.instagram.com/deaconnatnaelmedia ➽ የዩቲዩብ ቻናሌ      👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@deaconnatnaelmedia ➽ የቲክ ቶክ ገጼ      👇👇👇👇 https://vm.tiktok.com/zemarideaconnati ➽የትዊተር ገጼ     👇👇👇👇 https://twitter.com/dn_natnael ➽ ሁሉንም የማህበራዊ ሚዲያዎቼን ለማግኘት      👇👇👇👇👇👇👇👇 https://solo.to/deaconnatnaelmedia መረጃው ለብዙዎች እንዲዳረስ #ላይክ #ሼር በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታዎ ይወጡ🙏
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 1