cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ከመጽሐፍት መንደር💠

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨 🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥 ለማንኛውም አስተያየት @manbabemuluyadergal_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 678
المشتركون
+624 ساعات
+337 أيام
+7430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🔪🔪🔪ግድያው🔪🔪🔪 ክፍል 9 ብዙም የደም ምርመራው ውጤት ከቤተሰቡ ውስጥ የአንዳቸው ደም ውስጥ ቅድም ያልኳችሁን አደንዛዥ እፅ አገኘን ስለዚህ ግምታችን ከሞላ ጎደል ተረጋገጠ ማለት ነው። እንደነገርኳችሁ የተወጋባቸው ቦታዎች ሲታዩ ጥልቅ ስለነበሩ በሴቶች እጅ ይሆናል ብለን አልገመትንም ነበረ እንደገመትነውም አደንዛዥ እፁ የተገኘው ከወንዶቹ አንዳቸው ደም ውስጥ ነው።" ጉሮሮው የደረቀበት ስለመሰለው ውሀ ሊጠጣ ንግግሩን ገታ ሲያደርግ ሁሉም ልብ አንጠልጣይ ድራማ እንደሚያዩ ተመስጠው እየሰሙት ነበረ። "ከዛ ደሙ ውስጥ ያገኘንበትን ሰው ወስደን መረመርነው። ያው እንዳልኳችሁ የተጠቀምነው መንገድ ህጋዊ አይደለም ግን እውነታው ላይ እንድንደርስ ጠቅሞናል። ያው የተጠቀምነውን ተጠቅመን..." ሲል አያሌውና ብስራት ተያዩ "የተጠቀምነውን ተጠቅመን አናዘነዋል... ያው የግድያው ምክንያት ብዙም አዲስ ነገር የለውም እኛ እንደ ቀልድ ልጆቻችንን ከሌሎች ልጆች ጋር ስናወዳድር የሚፈጥርባቸውን ጉዳት አለማወቅ ብቻ ነው። እዚህም የሆነው ይህ ነው ግን የሚገርመው ይሄ ልጅ ያደገው ከሟች ጋር ሲፎካከር በመሆኑ ሳያውቀው በውስጡ ትልቅ ቅናት ተፈጥሯል ሌላውን ተዉት ከማክዳ ጋር ባለው ነገር ሳይቀር ነበረ በቅናት የሚቃጠለው እናም ለራሱ ራሱ ሳያውቀው sub-consciously ባደረበት ቅናት የተነሳ ሊገድለው ችሏል" አለ እና ጨረሰ። "እና... አቤል ነበረ ማለት ነው?!" አለ ብስራት አፉን በእጁ ሸፍኖ ሁሉም አጉረመረሙ። "አይ፤ ብሩክ ነው" የገደለው። አለ ሚኪ ተፈፀመ ✍nani
إظهار الكل...
👍 1
🔪🔪🔪ግድያው 🔪🔪🔪 ሊያልቅ አንድ ክፍል ቀረው... ክፍል  8 "ግድያው ከተፈፀመ በኋላ የተረሳ ነገር መኖሩን ለማረጋገጥ በተደጋጋሚ የፖሊስ ቡድን እየላክን ስናጣራ ነበረ እኛ ምንም የተለየ ያገኘነው ነገር አልነበረም። ከዛ ግን በሶስተኛው ቀን አደገኛ አደንዛዥ እፅ በችኮላ ተጥሎ ተገኘ። የእፁ መገኘት ከግድያው ጋር ሊያያዝ ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስለነበረን... ከሌሎች ማስረጃዎች ያገኘነው ደግሞ ከዛ ቤተሰብ ውጭ እንዳልሆነ የሚያመላክት ስለነበረ ማድረግ የምችለው ሁሉንም መመርመር ነበረ ምክንያቱም የተገኘው እፅ LSD ይባላል በጣም ከባድ እፅ ነው እናም ይሄንን እፅ ለየት ሚያደርገው ተጠቃሚው flash back effect ያጋጥመዋል ይህም ማለት ትላንትና የወሰደው ሰው በማግስቱ የእፁ ተፅዕኖ ይኖርበትና የተለያዩ ድርጊቶችን ሊፈፅም ይችላል። የሚገርማችሁ ነገር ይሄንን ሁሉ የሚያደርገው ሰው ምንም አለማስታወሱ ነው። ስለዚህ ወንጀለኛው ወንጀሉን ስለመፈፀሙ አያውቅም ማለት ነው። ስለዚህ የማምለጥ ወይም ራሱን የመሸሸግ ሙከራ አለማድረጉ ወንጀለኛውን ለመያዝ ቀላል አድርጎልናል።" "ታድያ ገዳዩ ማን ነው??" አለ የሆነ ድምፅ ከተሰበሰበው መሀል ✍nani
إظهار الكل...
👍 1
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 11🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍ . . ይሄን የመሠለ ውበትማ ለትውልድ እንደ ቅርስ መተላለፍ አለበት ብዬ ስላሰብኩኝ አስተናጋጁን ፎቶ አንሳን ብዬው ተነሳን ። እኔ በሱፍ ነኝ ፤ እሷ ቬሎ ነገር ጣል ብታደርግ ኖሮ የሰርግ ፎቶ ነው የሚመስለው ። እጅ ለእጅ ተያይዘን አስተናጋጁ ወደ ሚወስደን ቦታ ደረስን ። በአበባ የተሽቆጠቆጠ መሬት ፣ እጅግ ውብ በሆኑ ምግብና ወይን የተሞላ ጠረጴዛ ፣ ለስለስ ብሎ ከተለቀቀ ሙዚቃ ጋር ተፋጠጥን ። የከንቲባው ልጅ ቅድም ተኮራርፈን ስትተኛ ከአስተናጋጁ ጋር በመተባበር ‍ ነበር እንዲህ ያስዋብነው ። ለቦታው ደግሞ ይበልጥ ውበት የሰጠው ፡ አጠገቡ ሀይቅ መኖሩ ነው ። አስተናጋጁ "መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ፡ የምትፈልጉት ነገር ካለ ይችን ደወል መጫን ብቻ ነው" ብሎን ጠረጴዛ ላይ ወዳለው ነገር ጠቁሞን ሄደ ። ጨረቃዋ ቁልቁል በቅናት እያየችን ደስ የሚል እራት በልተን ወይን እየጠጣን ነው ። "ጨረቃዋ አታምርም የኔ ጌታ ...?" አለችኝ ። ትኩር ብዬ አይኖቿን እያየሁ 'ካንቺ ባትበልጥም ቆንጅዬ ናት' አልኳት ። እንደተለመደው በፍቅር ትከሻዬን እየመታች "ሙት እሺ" ትለኛለች ። ለጨዋታው ድምቀት 'አንቺ እንዳታለቅሺ አስቤ እንጂ እኔኮ መሞት አላቃተኝም' ስላት ፡ ባንዴ ፊቷ ተቀያይሮ ብርሃን ይመስሉ የነበሩ አይኖቿ ወደ ደመናነት ተቀይረው በእንባ ተሞሉ ። 'አንቺ አመረርሽው እንዴ ፡ እኔኮ እየቀለድኩ ነው' ስላት ፡ "ካሁን በዋላ ግን ለቀልድም ይሁን አይሁን ፡ እሞታለሁ እንዳትለኝ እሺ ...?" አለችኝ እንባ እየተናነቃት ። አንጀቴን ስትበላኝ ቁጭ ብዬ ማየት ከበደኝ ። ከወንበሬ ላይ ተነሳሁና ተንበርክኬ 'እሺ በቃ አይለምደኝም' አልኳትና እንባዋን ጠራርጌ ከተቀመጠችበት እጇን ይዤ ተነሳን ። ወደ ጆሮዋ በአፌ ተጠግቼ በለሆሳስ 'ከኔጋር መደነስ አትፈልጊም...?' አልኳት ። "አሎድህም እሺ ...!" አለችኝና በፈገግታ ለዳንሱ እጇን ዘረጋችልኝ ። ያው የተከፈተው ሙዚቃ ለስለስ ያለ ስለሆነ የኛም ውዝዋዜ ጠንከር ያለ አይደለም ። ግራ እጄን እንደ እናቶቻችን መቀነት ወገቧ ላይ ጠምጥሜ ፣ የቀኝ እጄን ጣቶች የግራ እጇን ጣቶች ክፍተት ሞልቼበት ፣ እሷም ቀኝ እጇን ትከሻዬ ላይ አሳርፋ ፣ በእግሮቻችን አንዴ ወደፊት ፡ አንዴ ወደዋላ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ጎን እያልን በመሀል በመሀል ደግሞ እያወራን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። ከደሬቴ ላይ ተነስታ ቀና ብላ አይን አይኔን ታያለች ። እንዲህ ስታየኝ ደግሞ ልቤን ታቆመዋለች ፤ ምድር ላይ መኖሬን ታስረሳኛለች ። አይኖቿ ውስጥ እስከ ዳግም ምፅአት ድረስ የሚበቃ የብርሃን ሀይል ይታየኛል ። ወረድ ብዬ ከንፈሯን ሳይ ደግሞ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ትዝ ይለኛል ።    "ሳማት ሳማት አለኝና ፡    ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣    ሳሙኝ ፡ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ፡    ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር" ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል የሚያደርገኝ ። እነዚያ የህይወትን ነዳጅ የሚያመነጩ ከንፈሮቿን ስጎርስ እስከ እለተ ሞቴ ድረስ ምግብ ባልበላ እንኳ የሚያኖሩኝ ይመስሉኛል ። ስስማት አይኖቿን ጭፍን አርጋ ትቀልጥብኝ ነበር ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ "ውጪው ይበርዳል አይደል የኔ ጌታ ፡ ወደ ውስጥ እንግባ ...?" አለችኝ ። እንዳለችውም ውጪው ያን ያክል ባይበርድም ፡ ሃሳቧን ላለመቃወም ብዬ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ክፍላችን አመራን ። ወደ ክፍላችን የሚወስደን ደረጃ ጋ ስንደርስ "እንደ ቅድሙ ተሸክመኸኝ አትገባም የኔ ጌታ" አለችኝ ። ልክ ሙሽሮች የሰርጋቸው ለት ማታ እንግዳውን "በሉ እናንተ ብሉ ፣ ጠጡ ፣ ጨፍሩ ፡ እኛ ልንተኛ ነው" ብለው ወደ መኝታቸው እንደ ሚሄዱ ፤ እኔም ልጅቷን እንደ ሙሽራ ተሸክሜያት ፡ እሷ ደግሞ በተዘረጉላት እጆቼ ላይ ፍልስስ ብላ ወደላይ እያየችኝ አልጋው ጋር ደረስን ። ዛሬ ፈርቻለሁ ፤ የፈሩት ደግሞ ይደርሳል ተብሎ ተፅፏል ። ከጠጣነው ወይን ይልቅ ትንፋሿ አሰከረኝ ። ከተቀባነው ሽቶ ይበልጥ የገላዋ መዐዛ ማረከኝ ። ልብሶቻችንን ማወላለቅ ጀመርን ። ኮቴ ፣ ሸሚዜ ፣ የሷም ልብስ እንደዛው ። እኔ ከላይ ፤ እሷ ከታች ። በዚህ መሀል ነበር የአንገት መስቀሌ ከአንገቴ ላይ በመሀላችን ሲንጠለጠል በድንጋጤ የተነሳሁት ። እንደ ቅድሙ ዝም አላለችኝም ። "የሆንከው ነገር ካለ ለምን አትነግረኝም ፡ እእእ ...?" አለችኝ በልመና አይነት ድምፅ ። አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ልነግራት ተዘጋጀሁ ። 'እየውልሽ ህይወት ፡ የፍቅር ታሪኬን አንድ ቀን እነግርሻለሁ ብዬሽ ነበር ። እና እሱን ዛሬ ብነግርሽ ነው የሚሻለው ብዬ ታሪኩን ጀመርኩላት ። #2007 ዓ.ም ክረምት ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ከዱከም / ደብረ ዘይት ከተማ ዘመድ ጥየቃ ወደ ሙገር ትመጣለች ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየዋት በካምፓችን ውስጥ በሚገኘው ሆቴል ቁጭ ብላ መፅሐፍ ስታነብ ነበር ። ብዙ የሰፈራችን ልጆችም በስፍራው ላይ ነበሩ ። አዲስ ሴት በሰፈራችን ከታየች ደግሞ አብዛኛው ወንድ ይጋደልባታል ። እዛ የነበሩት ወንዶች ተራ በተራ ወደሷ እየሄዱ አፍረው ተመለሱ ። ልጅቷ መስሚያዋ ጥጥ ነበር ። እኔ ደግሞ በዚያን ጊዜ ሴት ልጅን እንኳን ቀርቤ ላናግራት ይቅርና አይኔን ብቻ ካዩኝ በፍርሃት እምባዬ ይመጣል ። ያቺን ቀን ያቺን ልጅ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኜ በማየት ብቻ ቀኑ አለፈ ። ከዛን ቀን በዋላ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ ነበርኩና ፕሮግራም አዘጋጅተን ነበር ። እና ያቺን ልጅ ድጋሜ እዛ አየዋት ። ያን ምሽት ተዋውቀን ከቤተ ክርስቲያን አብረን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ መንገድ ላይ ዝናብ መጣብን ። ፀጉሯ ቱክስ ስለነበር እንዳይበላሽባት እንሩጥ አልኳት ። እሷ ግን "ዝናብ በጣም ስለምወድ እንደውም ቀስ ብለን እንሂድ" አለችኝ ። ሁሉም ሰው ከዝናቡ ሸሽቶ ወደቤት ገብቷል ። እኔና እሷ ብቻ በእግዚአብሔር ፀበል እየተጠመቅን በኩራት ዝናብ ውስጥ እየሄድን ፡ እሷ ስለምትወድ ብቻ ብርዱን እየጠጣሁ እስከ ዘመዷ ቤት አደረስኳት ። ብዙም አልተግባባንም ፤ ልጅቷ ብዙም አታወራም ነበር ። ግን በጣም ሳቂታ እንደ ነበረች አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል ። ብዙም ሳላውቃት መሄጃዋ እንደ ደረሰ ነገረችኝ ። የተገናኘነው ከሶስት ቀን አያልፍም ፤ እሱንም ለትንሽ ደቂቃ ፡ ያውም ብዙም ሳናወራ ። ስልክ ቁጥሬን የ #2008 የእንቁጣጣሽ ፖስት ካርድ ላይ ፅፌ ሰጥቻት ተሰነባበትን ። ከዛን ቀን በዋላ ያቺን ልጅ ሳላያት አንዱ ክረምት አልቆ ሌላኛው ተተካ ። ከሁለት ዓመት በዋላ #2009 ዓ.ም ክረምት ላይ ድጋሜ ወደ ሙገር መጣች ። ስለሷ ከስሟና ከመጣችበት ዘመድ ቤት ውጪ ምንም ነገር አላውቅም ነበር ። እሷ ደግሞ ከመጣች በዋላ ስሜ ጠፍቶባት ታሪኩ በሚል ስም እኔን ፍለጋ ጀመረች ።...
إظهار الكل...
👍 6
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 10🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍ . . . የሆነ ነገር ወዳልሆነ ነገር ሊመራክ ከሆነ ፡ ማድረግ ያለብህ ከሆነ ነገር መራቅ ነው ። አልጋ ልብሱን አልብሻት ወደ አልጋዬ ተመልሼ ተኛሁ ። ጠዋት ነግቶ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፡ #03 ሰዓት አልፎ ነበር ። እዛው ካለንበት ሆቴል ቆንጆ ቁርስ በልተን ፡ ያለብንን የ #1 ለሊት የቤት ኪራይ ከፍለን ወደ ቡቲክ አመራን ። ውቢቷ ቢሾፍቱ ላይ ፈክተን የምናበራበትን ልብስ ገዝተን #05:30 ላይ ጉዞአችንን ወደዛው አደረግን ። ለሸገር ቅርብ ስለሆነች ብዙም ደቂቃ አልፈጀብንም ። ኩሪፍቱ ሪዞርት ከበር ላይ በክብር ተቀበሉን ። የምንቆይበት ክፍል ይዘን ፈታ ለማለት ትጥቃችንን አሟልተን ወደ መዋኛ ገንዳ አመራን ። ዋና እንደማትችል ጠጋ ብላ በጆሮዬ ነገረችኝ ። እኔም ልክ እሷ እንደነገረችኝ ፈራ ተባ እያልኩ በጆሮዋ እንደማልችል ነገርኳት ። በድንጋጤ አየችኝና "እና ምን ልናደርግ ነው የመጣነው ...? ፡ እኔ ደግሞ ምትችል መስሎኝ አንተን ተስፋ ማድረጌ" አለችኝ አኩርፋ ። ከዛን ሳኩባትና 'ስቀልድ ነው ባክሽ ፡ ዶልፊን እራሱ ጉልበቴ ስር ቁጭ ብሎ ነው የተማረው' አልኳት ። (ዶልፊን ግን ቁጭ ማለት ይችላል እንዴ ...😝) ። "ሂድ ፡ ጉረኛ" አለችኝና ትከሻዬን በፍቅር መታችኝ ። እኔ ለክባድ ብዬ ተከርብቼ ውሃው ውስጥ ገባሁ ። እሷ ግን ውሃ ነክታ አታውቅም መሠለኝ በስንት ልመና በዳዴ ገባች ። ለመዋኘት ገብቼ አሰልጣኝ ሆኜ አረፍኩ ። ያን ያክል እንኳን አላስቸገረችኝም ። ነገሮችን በቀላሉ የመያዝ ልዩ ችሎታ አላት ። ዋና የለመድኩት እንዲህ ባማረ ገንዳ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንዝ ውስጥ ነበር ። እየዋኘሁ ፣ እያለማመድኳት ፣ እያረፍን ፣ በድጋሜ ያሁኑን step እየደገምን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። አይን አይኔን እያየች "አስቸገርኩህ አይደል ...? ፡ በቃ የመጨረሻ አንድ ዙር አለማምደኝና ይብቃን" አለችኝ ። ሁለቱ እጆቼን ውሃው ውስጥ እንደ ምንጣፍ ዘረጋሁላት ። በሆዷና ታፋዋ እጆቼ ላይ ተኝታ በእጆቿ ደግሞ ውሃውን ወደ ዋላዋ እየገፋች ወደ ፊት ትመነጠቃለች ። እኔም ከጎኗ ሆኜ እከተላታለሁ ። እንደዛ እያደረገን የገንዳው ጫፍ ላይ ደረስን ። ከእጆቼ ላይ ወርዳ እዛው ውሃው ውስጥ በኔ ፊትለፊት ቆመችና አይን ለአይን ተጋጨን ። ውበቷ እንዴት እንደ ሚያስደነግጥ ideaw የላቹም ። አላወቁም እንጂ ሴቶቻችን የሚያምሩት በሜካፕ ሳይሆን በተፈጥሮአቸው ነው ። በዋናው ውሃ ታጥባ ኩልል ብላ ቆማ ስታየኝ ፈዘዝኩኝ ። በጣም ተቀራርበናል ። እንደውም ንፋስ በመሃላችን ለማለፍ ፈልጎ ሲታገለን ይሰማኛል ። አይኖቼ ከንፈሯ ላይ ደርቀው ቀሩ ። እሷም እንደኔው በአይኖቿ ከንፈሬ አካባቢ እየሾፈችኝ ነው ። ወደ ከንፈሬ በጣም ቀረበች ። ከንፈሯ እንኳን እሁድ ተገኝቶ ፡ እሮብንና አርብን እራሱ ያስገድፋሉ ። የሁለታችንም ስሜት እናታችን ላይ ሲወጣ ተጎራረስን ። ከንፈሯ ከከንፈሬ ፣ ትንፋሿ ከትንፋሼ ተዳመረ ። የኔን ትንፋሽ ወስዳ የሷን ለገሰችኝ ። ትንፋሿ ይሞቃል ፤ ከንፈሯ ይጣፍጣል ። ለብዙ ሴኮንዶች ከንፈር ለከንፈር ተገጣጥመን ፡ የአለምን አየር ንቀን ውስጣችን ያለውን ተለጋግሰን ዋና ገንዳው ውስጥ ከቆየን በዋላ ከንፈራችን ተላቀቀ ፡ አይናችንም ተከፈተ ። ትንሽ እንደ መተፋፈር ሆነን ከውሃው ውስጥ ወጣን ። በርዷት ነው መሠለኝ መንሰፍሰፍ ጀመረች ። አሳዘነችኝና ፎጣ አልብሻት ተሸከምኳትና ወደ ክፍላችን ጉዞ ጀመርኩኝ ። እሷን መሸከም ለኔ ብርቄም ድንቄም አይደለም ። ሶፋ ላይ በተኛችና በሰከረች ቁጥር እስከ መኝታ ክፍሏ የማድረስ የሁለት ቀን ስራ ልምድ አለኝ ። የዛሬው ግን ለየት ይላል ። አልሰከረችም ፣ አልተኛችም ፣ እራሷን አልሳተችም ፣ አይኖቿ አልተከደኑም ፣ ወዘተ ። ክፍላችንን እንደምንም በአንድ እጄ ከፍቼ ገባንና መልሼ በእግሬ ዘግቼው አልጋው ላይ ቀስ ብዬ አስተኛዋት ። አይኗን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ወደላይ በስስት ታየኛለች ። እኔም ወደታች እንደዛው ። አንዲት ቃል ሳናወጣ በአይኖቻችን ብቻ እናወራለን ። ከዛን እጆቿን አንገቴ ላይ ጠምጥማ ወደራሷ ጎተተችኝና ድጋሜ ከንፈሮቻችን ህብረት ፈጠሩ ። ፎጣውን ከላዩዋ ላይ ወርውራ አልጋው ላይ ጣለችኝ ። ሁለታችንም ከዋና ገንዳው እንደ ወጣን ፡ እኔ ከላይ ራቁቴን ፡ ከስር ደግሞ በዋናው ቁምጣ ፤ እሷ ደግሞ ከላይ ጡት ማስያዣና ከስር በዋናው ፓንት ነው ያለነው ። ቅድም ከውሃው ስንወጣ በርዷት እንደዛ እንዳል ተንዘፈዘፈች ፡ አሁን ላይ ግን ገላዋ በሙሉ እንደ እሳት እየፈጀኝ ይገኛል ። አንገቷ ስር ገብቼ ስስማት ፡ አይኖቿን ጨፍና ፣ ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፣ መልሳ ደግሞ በሀይል ትተነፍሳለች ። (አንገቷ ስር ከገባህ ፡ አይኗን ስትጨፍን እንዴት አየህ ...😝) ። ዛሬም እንደ በፊቱ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም' አልኩ ለራሴ ። ምን እያደረግን ነው ...? ፡ እዚህ ድረስ ለምን መጣን ...? ፡ ፈታ ማለት ምን ማለት ነው ...? ፡ አልኩኝ ለራሴ ። ከሀሳቤ ነቃሁ ፡ ከአንገቷ ምሽግ ወጣሁ ፡ ከአልጋዋ ላይ ተነሳሁ ፡ ወደ ራሴ አልጋ ሄድኩ ፡ ወደ ራሴም ተመለስኩ ። እሷም ግራ በመጋባትና በመናደድ አይነት ስሜት ከተኛችበት ቀና ብላ ታየኛለች ። የሆነ ነገር ልትለኝ ስትል በራችን ተንኳኳ ። እኔ እከፍታለሁ አልኳትና ከላይ ሸሚዝ ለብሼ ከፈትኩኝ ። አስተናጋጅ ነበር እና "የምትፈልጉት ነገር ካለ ማዘዝ ይቻላል" አለኝ በክብር እጅ እየነሳኝ ። እኔም 'ትንሽ ርቦናልና ምግብ ብናገኝ ደስ ይለናል' አልኩት ። እሱም "ከፈለጋችሁ እዚህ ፡ ፍቃዳችሁ ከሆነም ደስ የሚል ቦታ እወስዳችሁና እዛ ትበላላችሁ" አለኝ ። 'አይ ፡ ላሁኑ እዚህ እንበላለን ፤ ባይሆን ደስ የሚለውን ቦታ ማታ ትወስደናለህ' አልኩትና ሄደ ። #08 ሰዓት አልፏል ። አኩርፋኝ ቢሆንም አስተናጋጁ ያመጣልንን ምግብ እንደ ተለመደው ለራሷ ሳትበላ መጀመሪያ አጎረሰችኝ ። እኔም አጎረስኳትና ትንሽ በልተን ተውነው ። ከበላን በዋላም ሁለታችንም በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን ሳናወራ ጀምበር እየታዘበችን ወደ ቤቷ ገባች ። ላወራት ብዬ ስነሳ በራችን ድጋሜ ተንኳኳ ። ስከፍት የቅድሙ አስተናጋጅ ነበርና ቅድም ወዳለኝ ቦታ ሊወስደን እንደ መጣ ነገረኝ ። #10 ደቂቃ ስጠን ብዬው ፡ ተመልሼ ፈራ ተባ እያልኩ ልጅቷን ቀሰቀስኳት ። 'ተነሽና ልብስሽን ቀይሪ ፡ ወደ ሆነ ቦታ እንሄዳለን' አልኳት ። አልተቃወመችኝም ፡ ልትቀይር ወደ ውስጥ ገባች ። ከሸገር የገዛነውን ልብስ አውጥቼ ለበስኩትና እሷ እስክትጨርስ መጠበቅ ጀመርኩኝ ። በዛ ውበቷ ላይ ቅድም የገዛነውን ልብስ እሷ ላይ ስስለው ፡ በቃ ጨረቃ እራሷ በአካል መጥታ የምታገኘኝ መሠለኝ ። ልጅቷ ከገባችበት ቀይራ ወጣች ።      "ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ደምቀሽ ስትወጪ ፣       ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ጨረቃ አፈረች"። ❥
إظهار الكل...
👍 7
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 9🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍ . . ስትሸና ያው እኔን ማፈሯ አይቀርም ብዬ እንድትከለል ፡ ጫካ እንደሌለ እያወኩ ለወጉ በአይኔ መፈለግ ጀመርኩኝ ። የድሬ ሸገር መንገድ ዳር ላይ መደበቅያ ጫካ ከመፈልግ ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኝነትን ማስቆም ይቀላል ። ለነገሩ ሽንት ለመሽናት ጫካው አስፈላጊ አይመስለኝም ። ብዙ ጊዜ መንገድ ስንሄድ ሽንት ሲመጣብን ለዛፎቹ አስበን ይመስል ወደ ጫካ እንሮጣለን ። ከሰው ለመደበቅ ነው እኮ ...🙆 ። በነ ጦጢት እየተሾፈን እንደሆነ ማን በነገረን ። anyways ጫካ ስላጣን በመኪናው ተከልላ ሸንታለች ። እኔኮ ግርም የሚለኝ ሰው ሲሸና ጠብቆ ሽንቴ የሚመጣው ጉድ ነው ።  ውሃ ስለማልጠጣ ሽንት አዘውትሮ የመሽናት ልምድ የለኝም ። (መሽናቴ ካልቀረ ምን አስጠጣኝ ...😜) ። #08:00 ሰዓት አልፏል ። አዲስ አበባ ለመግባት በግምት #2 ሰዓት ይቀረናል ። ሸገር ለ #1 ቀን ማደር ስለፈለግን እንጂ ቀጥታ ቢሾፍቱ መሄድ አላቃተንም ። ከስንት ድካም በዋላ ልክ #09:42 ደቂቃ ላይ በአቂቃ ቃሊቲ በኩል አዲስ አበባ ገባን ። መንገዶች ሁሉ በመኪናና ሰዎች ተሸፍኗል ። እንደምንም ክፍት መንገድ ባየን ቁጥር እየሾለክን ቦሌ ካንዱ ሆቴል ጎራ ብለን #1 ክፍል ያዝን ። በጣም ደክሞን ስለነበር ሁለታችንም ሻዎር ገባን (አንድላይ አይደለም ፡ ብቻ ለብቻ ነው ደግሞ...😜) ። እንግዲህ ዛሬን ሸገር ላይ ፍልስስ ልንል ነው ። አዲስ አበባ እንደ ድሬ አይደለችም ። የሰው ብዛት ፣ የመኪናው ጋጋታ ፣ የህንፃዎቹ ብዛትና ውበት ፣ የከተማው ስፋት ፣ ባጠቃላይ ሸገር እንደ ድሬ ቶሎ ምትለመድ አይነት አይደለችም ። እዛው ከያዝነው ሆቴል እራት በልተን ፡ ወይን እየጠጣን ስሟን ለመምሰል ሌት ተቀን ደፋ ቀና የምትለዋን ከተማ ከላይኛው ፎቅ ቁልቁል ወደታች እያየናት ነው ። ሆቴሉ ግሩም ነው ፤ ከላይ በሁሉም አቅጣጫ ከተማዋን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ። ምሽት ላይ ከላይ ስትታይ ስሟን ትመሰላለች ። የከንቲባው ልጅ "ወይ አዲስ አበባ" እያለች ትገረማለች ። ከዛን ወደኔ ዙራ "ስማኝማ ፡ ፈታ ልንል ነው አይደል ይሄን ሁሉ ርቀት አቋርጠን የመጣነው ...?" አለችኝ ። አዎ ስላት "እንደዛ ከሆነ ፡ በናትህ ፡ ስወድህ ፡ night club ውሰደኝ" አለችኝ ። "ጀማሪ እረኛ ፡ ከብት አያስተኛ" ይለዋል የሀገሬ ሰው ። ልጅቷ እቤት ሆና በፊልም ያየችውን ነገር ባካል ማየትና ማድረግ ትፈልጋለች ። ደግነቱ ከያዝነው ሆቴል አጠገብ club ይታየኛል ። እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደዛው አመራን ። entrance / መግቢያ ከፍለን ፡ ተፈትሸን ገባን ። ጎበዝ ፡ ወጣቱ እዚህ አ እንዴ ያለው ። ለካ ኢትዮጵያ ወደ ዋላ የቀረችው ወዳ አይደለም ። መደማመጥ የለም ፡ ጭፈራ ብቻ ነው ። የእስፒከሩ ጩኸት ፣ የሰው ጫጫታና ዳንስ ቦታውን ሶሪያ አስመስሎታል ። "እንቅስቃሴዎች ሁሉ dance ናቸው" የሚለውን ዘፈን teddy yo እዚህ ቤት ቁጭ ብሎ የፃፈ ይመስላል ። እኔ እንኳን club ስገባ የመጀመሪያዬ ስለሆነ ስራቴን ይዤ ቁጭ ብያለሁ ። ባይሆን መጠጧን አንድ ሁለት እያልኩኝ ፡ ትርዒቱን እያየሁ ልምድ እየቀሰምኩ ነው ። ልጅት ደግሞ በስሜት አሸሸ ገዳሜውን ለመቀላቀል #1mm ነው የቀራት። "ሂድልኝ ሀዘን ጭንቀቴ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ ፣    ጥፋልኝ ሀዘን ህመሜ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ" ። ብቻችሁን መምጣት ክልክል ነው የተባለ ይመስል ፡ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የመጡት (ልክ እንደኛው ...🙈) ። የፈራሁት አልቀረም ፡ የከንቲባው ልጅ እጄን ይዛ አስነስታኝ ትርዒቱ መሃል ቁጭ (ይቅርታ ቁም ለማለት ነው ...🙆) ። እንቅስቃሴ ጀምረናል ፡ ለነገሩ dance ላይ ብዙም የስራ ልምድ ስለሌለኝ እየጨፈርኩ ሳይሆን እየተወላገድኩ ነው ብል ይቀለኛል ። በመሀል በመሀል አንድ ሁለቱን ፡ ሶስት አራት እያልነው ነው ። ፊልም ላይ አረቄ /Jin ባንድ ትንፋሽ እንደዛ ሲጨልጡት በውሃ የሚያታልሉን ይመስለኝ ነበር ። ዛሬ ግን በአይኔ በብረቱ አይቼ አምኛለሁ (አይን ብረት ነው እንዴ ...🙄) ። ኧረ ሴቶቻችን ተበላሽተዋል ጎበዝ ። ከወንዶቹ ይልቅ እነሱ ባሱኮ ። የሌሎቹ ሲገርመኝ የኔዋ ጉድ ብሳ ተገኘች ። እየጠጣን ፣ እየጨፈርን ፣ እያረፍን ፣ በድጋሚ የአሁኑን step እየደገምን በስተመጨረሻ ልጅቷ ውሃ ሆና እላዬ ላይ ተዘረገፈች ። እንዴት ተሸክሜያት ከክለቡ እስከ ያዝንበት ሆቴል እንዳደረስኳት ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው (እኔም ግን አውቃለሁ ...😜) ። በስንት ድካም የያዝነው ክፍል ደረስንና አልጋው ላይ ዘረገፍኳት ። ንሰሐ ገብቼ ሀጥያቴን የተናዘዝኩ ያክል ነው ቅልል ያለኝ ። የለበሰችው አጭር ቀሚስ ገላዋን ሙሉ በሙሉ የመሸፈን አቅም አልነበረውም ። በቀላል maths ከወገብ በታች አካሏ #80% ይታያል ። አልተን ገዳገድኩም እንጂ መጠጡ አናቴ ላይ ወጥቷል ። እሷ ግን የት እንዳለች እራሱ የምታውቅ አይመስለኝም ። የያዝነው #1 ክፍል ቢሆንም #2 አልጋ አለው ። እኔ አልጋዬ ላይ ሆኜ በእውን እያየዃት ፤ እሷ ደግሞ በስካር አለም ተወስዳ ተኝታለች ። የሰው ልጅ ከእንስሳ የሚለየው እራሱን መግዛት በመቻሉ ነው ። እንስሳት እራሳቸውን መግዛት ስለማይችሉ ያገኙትን በልተው ፣ ካገኙት ጋር ወስበው ፣ ሂድ ወደ ተባሉበት ሄደው ይኖራሉ እንጂ እንደ ሰው በእቅድና አላማ አይንቀሳቀሱም ። የሰው አፈጣጠር ግን ይለያል ። ህሊና ከሚባል ዳኛ ጋር ስለተፈጠረ በጎ ሲያደርግ በርታ ፣ መጥፎውን ነገር ሊሰራ ሲል ደግሞ እረፍ ፣ ከሰራም በዋላ ደግሞ በድለሀል ይቅር በል የሚል ከሳሽ አይምሮው ውስጥ ተቀምጧል ። የሰው ልጅ በሁለት መንገድ ይበድላል ። አውቆና ሳያውቅ ። ሳያውቁ ያደረጉት ይሁን ፤ ነገር ግን እያወቁ ማጥፋት የጥፋት ሁሉ ጥፋት ነው ። ብዙ ጊዜ ስካርን ተገን በማድረግ ብዙ ስተት ይፈፀማል ። በዚች ሰዓት እኔ እራሴን አልሳትኩም ። ስለዚህ እራሴን መግዛት እችላለሁ ማለት ነው ። መጥፎ ነገርን አለማድረግ እየተቻለ ማድረግ ሰይጣንነት ነው ። ይቺ ልጅ እዚህ ድረስ አብራኝ የመጣችው ስላመነችኝ ነው ። በዚህ ዘመን ደግሞ የሰውን እምነት ማግኘት የማይገኝ ትልቁ ፀጋ ነው ። ወደሷ ጠጋ ብዬ ጫማዋን አወለኩላት ። ወደ ከንፈሯ ተጠጋሁና ጆሮዬን አፏ ላይ ደቀንኩት ። ትንፋሿ ሰውነቴን ውርር ስያደርገኝ በህይወት እንዳለች አረጋገጥኩኝ ። አይኖቼ ከእግር እስከ እራስ ፀጉሯ ድረስ scan አረጓት ። ይሄ ነገር ወንድነቴን እየተፈታተነው ነው መሰለኝ ። ⚘_❥
إظهار الكل...
👍 9🥰 2
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 8🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ .አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከደራሲያን አለም የቴሌግራም ቻናል ✍ . . እጄን ይዛኝ ፡ ወደ ቤት እየወሰደችኝ "እንዴት በዚህ ሰዓት መጣህ ...? ፡ ትምህርት የለም ወይንስ #03:00 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ናፈኩህ ...?" አለችኝ እንደ መሽኮርመም ነገር ሆና ። ስለ ጊቢው ሁኔታ ጓደኛዬ የነገረኝን እንዳለ ነገርኳት ። እሷም እንደኔው በረብሻው ደስተኛ ባትሆንም ትምህርት እስከ ቀጣይ እሮብ ባለመኖሩ በውስጧ እልል እያለች እንደሆነ ያስታውቅባታል ። ለምን እንዲህ አናደርግም "ዛሬ አርብም አይደል ፡ እስከ እሮብ ድረስ #5 ቀን አለን ። እና ይሄን ሁሉ ቀን #1 ቤት ውስጥ ከምንጎለት ፡ ለምን ከዚህ ርቀን የሆነ ቦታ ሄደን ፈታ ብለን አንመለስም ...?" አለችኝ ። አሰብኩበት ፡ ጉዳቱ አልታየኝም ፤ ተስማማሁላት ። በውሳኔው ሁለታችንም ደስተኞች ነን ። "ከበቂ በላይ ገንዘብና መኪና አለን ፡ ግን የት ነው የምንሄደው ...?" የሚል ሀሳብ አነሳች ።        "ብቻ አንቺ ኑሪልኝ ኑሪልኝ          ኑሪልኝ እንጂ ፣          የትም ይመቸኛል የትም          የትም ይመቸኛል የትም" ። አይነት መልስ ሰጠዋት ። "ለመዝናናት ደብረ ዘይት እና ሀዋሳ አሪፍ እንደሆኑ በቲቪ አይቻለሁና ከሁለቱ አንዱ ቢሆን ደስ ይለኛል" አለችኝ ። እኔም 'ሀዋሳ ሄጄ አላውቅም ፤ ቡሾፍቱ ግን #3 ጊዜ ስለሄድኩኝ እዛ ሳይሻል አይቀርም' ስላት በደስታ ተስማማች ። ነገ በጠዋት ጉዞ ወደ ውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ። ከባንክ ቤት ለጉዞው ብለን #10 ሺህ ብር አወጣች ። ATM ስላላት ተጨማሪም ካስፈለገን ፡ ባስፈለገን ሰዓት እናወጣለን ብላኛለች ። ምናልባት መንገድ ላይ ረሀብ ከለቀቀብን ብለን ለነገ ምግብ ተባብረን አዘጋጅተናል ። ነጋና ጉዞ በጠዋት ጀመርን ። ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ መካከል የ #512km ርቀት እንዳለ ታፔላ ላይ ተለጥፎ አምብቤያለሁ ፤ ሰዎች ስያወሩም ሰምቻለሁ ። Google ላይ search ሳደርግ ግን #452 km ነው የሚለው ። በዚህም በዚያም በመኪና (ኢትዮ ፣ ዘመን ፣ ገዳ ፣ ሰላም ፣ ወዘተ bus'ኦች) ከድሬ ሸገር ለመድረስ ከ #8 ሰዓት እስከ #9 ሰዓት ይፈጃል ። በባቡር እራሱ ሄደን ነበርና ከሸገር ጠዋት #02:00 ሰዓት ተነስቶ ቀን #10:00 ሰዓት ነው ድሬ የሚደርሰው ። እሱም መብራት ካልጠፋ ነው ፤ ከጠፋ ማታ #03:00 ሰዓትም ሊገባ ይችላል ። ከድሬ ደግሞ ቀን #07:00 ሰዓት ይነሳና ምሽት #03:00 ሰዓት ለቡ ፡ አዲስ አበባ ይገባል ። በፕሌን ደግሞ የ #45 ደቂቃ መንገድ ነው ። እኛ #01:00 ሰዓት ነበር በ Rava #4 መኪና ከድሬ የተነሳው ። ፈጣሪ ካለ እስከ #10:00 ሰዓት ፊንፊኔ እንገባለን ። anyways የከንቲባው ልጅ መኪናዋን አየር ላይ እያከነፈችው ነው ። ቢቻለኝና ስልጣኑ ቢኖረኝ የአምስት ዓመት ስራ ልምድ እፅፍላት ነበር ። በአነዳዷ ስገረም አየችኝ መሠለኝ "አይዞህ እሺ ፡ ከቢሾፍቱ ስንመለስ አለማምድሀለው" አለችኝ ። የድሬ ሸገር asphalt ብዙም ውጣ ውረድ የለውም ። በግራም በቀኝም አልፎ አልፎ ከሚታይ ትናንሽ ሰፈር ውጪ በረሀ ነው ማለት ይቻላል ። አብዛኛው መሬት ሰውም ፣ እንስሳም ፣ እፅዋትም የለውም ። አፈር ብቻ ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ ፡ "እስቲ ሶስቴ ደብረ ዘይት የሄድክባቸውን ጊዜያት አስታውሰኝ ...?" አለችኝ ። 'ለመጀመሪያ ጊዜ ደብረ ዘይት ከተማ የሄድኩት #6ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። በወቅቱ scout የሚባል የወጣቶች ህብረት ነበር ። scout ማለት ወጣቶች ከትምህርት ሰዓታቸው ውጪ መጥፎ ቦታዎች እንዳይውሉ ፣ የሀገር ፍቅር እንዲኖራቸው ፣ ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ፣ በትምህርታቸውም እንዲጠነክሩ የሚያደርግ ምርጥ ማህበር ነው ። ወጣቶች ላይ ትኩረት ያድርግ እንጂ ህፃናትና ጎልማሶችም የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ ። እና ያኔ ነበር ቢሾፍቱን ከጓደኞቼ ጋር ሀ ብዬ የረገጥኩኝ (ሀ እንኳን ያልኩ አይመስለኝም ...😜) ። እዛ የሚገኙትን አየር ሀይል ተቋምና ባቦጋያ ሀይቅን ጎብኝተን ገባን ። በዓመቱም ድጋሜ በ scout ሄደንና ሆራ አርሰዴንና የወጣቶች ማዕከልን አይተን ፡ ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን ተመለስን ። ለመጀመሪያ ጊዜ በጀልባ ሀይቅ ላይም የተንሳፈፍኩትም ያኔ ነበር ። እንዴት ደስ እንደሚል አጠይቂኝ ። በዛን ጊዜ ሙገር scout በእግረኛ ሰልፍ እንደ ኢትዮጵያ ታዋቂ ነበር ። ብዙ ፕሮግራም ላይ ተሳትፈናል ፣ ብዙ ቦታዎችን ሄደናል ። እንደውም ከአባሎቻችን መካከል አንዱ እድል አግኝቶ አሁን USA ነው ያለው ። አሁን ላይ ግን አባላቱ በትምህርት ምከንያት በየ ዩኒቨርስቲው ስለተበታተኑ ማህበሩ ፈርሷል' አልኳት ትንሽ እንደማዘን ሆኜ ። "እሺ ለሶስተኛ ጊዜስ እንዴት ሄድክ ...?" አለችኝ ። 'ለ #3ኛ ጊዜ እንኳን ደብረ ዘይት የሄድኩበት ምክንያት ለየት ይላል ። ታሪኩም ረዘም ስለሚል እንዳላሰለችሽ ሌላ ጊዜ ልንገርሽ' አልኳትና በረዥሙ ተንፍሼ አየር ወሰድኩኝ ። "የምለቅህ እንዳይመስልህ ፡ ምሳ ከበላን በዋላ ትተነፍሽያታለሽ" አለችኝ እየሳቀች ። "ስማኝማ ፡ ፊትለፊታችን ምንድነው ይሄ ሁሉ መኪናና ሰው...?" አለችኝ ትንሽ እንደ መደንገጥ ነገር ሆና ። 'አይዞሽ አትፍሪ ፡ አሁን አዋሽ  ደርሰናል ። በዚህ መንገድ የሚያልፍ ማንኛውም መኪናና እቃ ሳይፈተሽ ንቅንቅ አይልም ። እንደ ኢትዮጵያ ብዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች የሚያዙት እዚህ ነው ። ምክንያቱ ደግሞ ህገ ወጥ መሣሪያዎች ፣ ጫማ ፣ ልብስ ፣ electronics ፣ ወዘተ ቁሳቁሶች በውጫሌ በኩል ወደ ድሬዳዋ ስለሚገቡ ነው' አልኳትና መኪናችንን check አርገው ምንም የተለየ ነገር ስላልያዝን ሳያቆዩን ለቀቁን ። አዋሽ የሚሰሩ ፈታሾች ግን የሚሰሩት እንደ ሙዳቸው ነው ። ደስ ሲላቸው ያለሽን controband እቃ እንዳለ ፣ ሲያሻቸው ግማሹን ይወስዱብሻል ። መፈተሽ ሲሰለቻቸው ደግሞ ምንም ነገር ሳያዩ ያሳልፋሉ ። ይሄን ደግሞ ብዙ ጊዜ በዚህ ስናልፍ ታዚቤያለሁ ። የድሬ ሸገር መንገድ ርዝመት ከሙቀቱ ጋር ተዳምሮ በጣም አሰልቺና አድካሚ ነው ። ብዙ ሰዓት ሄደናል ። መተሃራ ለምሳ ወርደን ማታ የሰራነውን take away በልተን ፣ ትንሽ አረፍ ብለን ጉዞ ቀጠልን ። ከመኪናው ቴፕ ላይ የምትከፍታቸው ሙዚቃዎች ያበዱ ናቸው ። ለነገሩ ልጅቷም እብድ ነገር ናት ። እንደኔው የአስቱካ ወዳጅ ናት ። "ጨጨሆ ፡ ጨጨሆ" እያለች ከአስቴር አወቀ በላይ እየጮኸች ሳያት እብደቷ ተጋብቶብኝ እኔም ሙድ ውስጥ ገባሁ ።እንዲህማ ከቀጠልን መኪናዋ አክሮባት መስራቷ ነው ። አሁን ተገለበጠች ፡ አሁን ተፈጠፈጠች እያልኩ ከምሰጋ ብዬ ለትንሽ ደቂቃ መኪናውን አቁመን እብደታችንን እንድንጨርስ ነገርኳት ። አቆመችና "ስማኝማ ፡ ሽንቴ መጣኮ" አለችኝ....
إظهار الكل...
👍 2
ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ ፍፁም አንዳልጓጓ ህመም በርትቶብኝ ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሞቴን ሲጠባበቅ ህመሜን ሳዳምጥ ስሜቶቼን ሳረቅ . . .          መኖር ማለት ስቃይ          መኖር ምለት ህመም          መኖር ማለት ጭንቀት          መኖር ማለት ድካም.... ወደ ተስፋ መንደር እልፍ ጊዜ ባመራ የ እድሌን ልሻማ ከ እኩዮቼ ጋራ ብፈልግ... ብጠብቅ ድርሻ የለኝ ሁኖ ጠብታ እንኳን ሳይቀር ከ እኔነቴ ተኖ ፀሐይ የለኝ ሁና ሕይዎቴ ዳምኖ . . .        ትላንት በመኖሬ ተስፋ እንኳን ሳይኖረኝ        ምንም ያህል ባዝን የሚያልፍ ባይመስለኝ        ቀን እየቆጠረ ቀን እየጨመረ        የደመናው ጥቁረት መጠኑ ቀንሶ        የስቃይ ዉርጅብኝ ከነበረው አንሶ        ከ ሕይወቴ ጠፋ ቀስ በቀስ ጨርሶ... . . . የ ፀሐይ ዉበቷ የፀሐይ ድምቀቷ የዉበት ፍካቷ ዛሬ ላይ ብሸፈን ደመናው ሲገፈፍ ወደጎን ሲበተን.... . . .        ህመም ብርድ ሁኖ ያገረጣው ትናንት        ተንፏቆ እየዳሀ ዛሬን በመጠጋት        አንድ ቀን ልጨምር ብዬ በመኖሬ        ተስፋ ፀሐይ ሁኖ ከች አለልኝ ዛሬ!!                        📆ሚያዚያ 25 - 2016                 ✍ዘይድ ሁሴን
إظهار الكل...
👍 5
ስ ን ለ ያ ይ እንደ እንባዬ ቁልቁል አልሰደድኳትም ፥ በሳቄ ረቂዮት ሸኘዋት፤ ፊቴ ላይ ያለውን ቅኔ ቁንጽል እስከምትፈትል ቢያንስ ስለኔ እያሰበች ነው።
إظهار الكل...
በሳቋ ላይ የሚታየኝ ልጅነቷ አ ፍ ላ ዕ ፀ ግ ሴ ት ነ ቷ የማይነካት ያልበሰለች ጥሬ ገፅን ባሳሳቋ ልቤ ውልቅ እርር ድብን! አለቀሰች አንድ ቀን. . . ሰው ቅጽበት መሰለች ኢምንት ብርሀን ተነካት በቀደም. . . አደገች አፈራች ማወቅ ይሉት ሰብልን፤ " እ ሰ ይ እ ል ል" መባ ነገር አልኩ መስማት እንዲሰማት እንባዋን ዘከርኩ ለተከፋት ቅጽበት ዘላለም ተጋራኝ በትንሿ ማ ዘ ን ማወቋ መዘነኝ
إظهار الكل...
መርሳትን ማስታወስ የረሳሁት በዳይ፡ ህመሜ ሲያገግም ይቅር በለኝ ቢለኝ- ይቅርታ አላደርግም ይቅር በለኝ ማለት በደሉን አስታውሶ፡ ይበድላል ዳግም። ይታወሳል እንጅ በበዳይ ይቅርታ በደል አይረሳም ሞኝ ያስብላል እንጅ ፃድቅ አያሰኝም፤ የነከሰን መሳም እንደኔ ላለ ሰው በበዳይ ይቅርታ፡ አይሽርም ህመሙ <<ይቅር በለኝ>> ማለት በደሌን አስታውሰው ማለት ነው ትርጉሙ። ✍️(በላይ በቀለ/ወያ)
إظهار الكل...