cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ “ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።” — 2ኛ ቆሮ 11፥28

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
15 013
المشتركون
+11724 ساعات
+2407 أيام
+1 55930 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
‹‹በዚያን ጊዜ ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፮) በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት በዓለ ጰራቅሊጦስ በዋለ ማግስት ጀምሮ የሚጾመው ጾም ጾመ ሐዋርያት ተብሎ ይጠራል። የዚህ ጾም የመግቢያው ቀን በየዓመቱ የሚለያይ ሲሆን “ቢፈጥን ከግንቦት ፲፮ አይቀድምም፤ ቢዘገይ ደግሞ ከሰኔ ፳ አያልፍም” ብለው ሊቃውንት አባቶቻችን ያስተምራሉ። ይህ ጾም የሚፈታበት ቀን ግን እንደ መግቢያው የማይቀያየር ሲሆን ሁልጊዜ ሐምሌ አምስት በቅዱሳን ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓል ቀን ጾሙ ይጠናቀቃል። በዚህ ጾም የሐዋርያት ክብራቸው፣ ቅድስናቸው እንዲሁም አገልግሎታቸው ይታሰባል፡፡ ሁሉን ትተው ጌታን መከተላቸው፣ ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውና ስለ ቅዱስ ስሙ በጽናትና በጥብዐት መከራ መቀበላቸው ይታወሳል፡፡ ስለ ተሰጣቸው የወንጌል አደራ እስከ ሞት ድረስ መታመናቸው ይሰበካል። ቅዱሳን ሐዋርያት ይህን ጾም ሁለት ነገሮችን መሠረት በማድረግ ጾመውታል። የመጀመሪያው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወላቸውን ጾምን የአገልግሎት መጀመሪያ የማድረግ አርአያነት ነው። ይኸውም ክብር ይግባውና አምላካችን ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ አብ በሰማይ ተናግሮ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ ክብሩ፣ አምላክነቱ የባሕርይ ልጅነቱ የተገለጠ ሲሆን ከተጠመቀ በኋላ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሄድ ፵ ቀን እና ፵ ሌሊት ጾሟል። (ማቴ.፫ እና ፬) ቅዱሳን ሐዋርያትም ይህን ጌታችን ያደረገውን ተግባር አርአያ በማድረግ በበዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ፣ ኃይልን ተቀብለው የጸጋ ልጅነታቸው ሲገለጥ ለአገልግሎት ከኢየሩሳሌም ከመውጣታቸው በፊት ጾምን የአገልግሎታቸው መጀመሪያ በማድረግ ጾመዋል። ይህም አርአያነት ቀጥሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እና በርናባስ ለስብከት አገልግሎት በተለዩ/በተመረጡ ጊዜም ጾመዋል። (ሐዋ.፲፫፥፪-፫) ስለዚህ ጾምን የአገልግሎት መጀመሪያ ማድረግ የመጀመሪያው መሠረት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀራጭ በነበረው በማቴዎስ ቤት ተቀምጦ ሳለ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ‹‹እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ለጠየቁት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ነው። ይኽውም ‹‹ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ይጾማሉ›› ብሎ የመለሰው መልስ በሐዋርያት በተግባር መፈጸሙን እንድረዳ ነው። ይህም ቃል ይፈጸም ዘንድ ሚዜዎች የተባሉ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙሽራው ክርስቶስ ከእነርሱ በተለየ/ባረገ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ጾመውታል።(ማቴ.፱፥፲፴-፲፮) ዛሬ ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች ከቅዱሳን ሐዋርያት በረከት እንሳተፍ ዘንድ ይህን ቅዱስ ጾም እንጾማለን። እነርሱ ጾመው በጀመሩት አገልግሎት ዓለምን በስብከተ ወንጌል ጨው ሆነው እንዳጣፈጡ በክህነት የሚያገልግሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክላቸው፣ ይቀበልላቸው፣ ያሳካላቸው ዘንድ በትጋት ሆነው ይጾሙታል። ይህ ሲባል ግን ምንም እንኳን ይህን ትልቅ በረከት የሚያሰጥ ጾም ‹‹የቄስ ጾም›› እያሉ ራሳቸውን የሚያስቱ ቢኖሩም ቤተ ክርስቲያናችን ግን በቀኖና ወስና የዐዋጅ ጾም ብላዋለችና ሁላችንም ክርስቲያኖች ከሰባት ዓመት ጀምሮ ልንጾመው ይገባል። (ፍት.ነገ.፲፭፣ገጽ.፭፻፷፮) በዚህ ጾም ቅዱሳን ሐዋርያት ራሳቸውን ለአገልግሎት እንዳዘጋጁ፣ እንደጸለዩ እና አገልግሎታቸውንም እንደፈጸሙ እኛም በቀጣይ ልንጀምረው ያሰብነው በልቦናችን ያለው መልካም አሳብ ይፈጸም ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመንን እንጾመዋለን። የእነርሱን አገልግሎት የባረከ አምላክ የእኛንም አገልግሎታችንን፣ ሥራችንን፣ ትምህርታችንን፣ ትዳራችንን በአጠቃላይ ሕይወታችንን እንዲባርክልን እየተማጸንን እንጾመዋለን። የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤት፣ በረከት፣ ድል የምትነሣ፣ ጥርጥር ነቅዕ የሌለባት ሃይማኖታቸው ከሁላችን ጋር ትሁን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር! Mahebere kidusan
1 04323Loading...
02
በዚህ ስብከት ልባቸው ተነካ፤ ጴጥሮስንና ሌሎእንም ‹‹ምን እናድርግ›› አሏቸው፡፡ ጴጥሮስም ‹‹ንስሐ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይሰረይላችሁ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ›› አላቸው፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፭-፴፰) ቋንቋ የሚያናግረውን፣ በጥበብና በዕውቀት የሚሞላውን፣ በሀብቱ ስቦ በረድኤት አቅርቦ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ የኃጢአት ስርየትም የሚገኝበትን በክርስቶስ አምኖ በመጠመቅ የሚገኘውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንዲቀበሉ መከራቸው፡፡ ቃሉንም የሰሙ፣ ሰምተውም ያመኑ ብዙ ነፍሳት ተጠመቁ፤ ቁጥራቸውም ሦስት ሺህ ያህል ነበሩ፡፡ እናም በዓለ ጰራቅሊጦስ እያልን ከዕርገት በዐሥረኛው ቀን፣ ከትንሣኤው በሃምሳኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ በዓል መሠረቱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሰማያት የወረደበት፣ ለጌታ ቤተ ሰቦች የተገለጠበትና በእያንዳንዳቸው ላይ ያደረበት፣ በዚህም ሕይወት የሚሰጠውን አምላካዊ ዕውቀት ያገኙበት፣ ዓለምን ተዘዋውረው ያስተምሩበትና ተአምራት መንክራት ያድርጉ ዘንድ ሕዝቡንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚጠሩበትን የዓለም ቋንቋ የገለጠበት፣ በዚህም የመንፈስ ቅዱስን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት ልባቸው የተነካ ብዙዎች በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የተጠመቁበትና ወደ በረቱ የተሰበሰቡበት ድንቅ የተአምራትና የምሥጢር ቀን በመሆኑ እንድናከብረው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡ መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት ‹‹በበዓለ ሃምሳ ሥራ አትሥሩ፤ ነገረ ክርስቶስን ባመኑ ምእመናን ላይ የወረደ መንፈስ ቅዱስ ተገልጦበታልና›› ይላል፡፡ (ፍት.ነገ.አን.፲፱፥፯፻፵) እናም እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ታላቅ የበረከት በዓል፣ ይህንን የተቀደሰ ቀን ስናከብረው እንዴት ይሆን? በወይን ጠጅ ሰክረን ወይስ ኃጢአታችን ይሰረይልን ዘንድ ንስሓ ገብተን ወይስ በሌላ ሁኔታ? ጰራቅሊጦስ ነፍስና ሥጋን የሚያጸና፣ ለንጹሐን የክብር አክሊልና ሞገስ ነው፤ ይህን የእውነት መንፈስ በእኛ ላይ ያድር ዘንድ፣ ስብራታችን እንዲጠገን፣ ጎደሏችን እንዲሞላ፣ ድንቁርናችንን እንዲያስወግድ፣ ከኀዘናችን እንዲያጽናናን፣ እንለምነዋለን ወይስ በምግበ ሥጋ ተጠምደን ጨለማውን የማያርቀውን ዕውቀት የማይገልጸውን፣ ኀዘንና ትካዜ የሚጨምረውን የበዓል አከባበር እናከብራለን? ራሳችንን እንድናይ፣ ንስሐን የሚቀበል፣ ኃጢአትንም ይቅር የሚል፣ የሚያነጻ መንፈስ (ጰራቅሊጦስ) በእውነት ይርዳን! ተቀድቶ የማያልቅ የዕውቀት መጠጥ ነው፤ ምሥጢር ገላጭ በመሁኑ ምሥጢሩን እንዲገልጽልን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ያድር ዘንድ አእምሮውን፣ ማስተዋሉን እንዲሰጠን መልካም ፈቃዱ ይሁን፤ አሜን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
4 67659Loading...
03
"ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል" (ዮሐ.፲፬፥፲፮) እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ! የቤዛነት ሥራውን ከፈጸመ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲያርግ ለሐዋርያት የሰጣቸው ተስፋ አጽናኝና የእውነት መንፈስ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን አብ እንደሚልክላቸው፣ እርሱም አጽናኝ የሆነ ጰራቅሊጦስ እንደሆነ ለዘለዓለሙም ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ነግሯቸው ነበር፡፡ ጌታችን እንደተናገረውም በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ባረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሣ ደግሞ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ‹‹ወአነ እስእሎ ለአብ ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ ካልአ ዘይሄሉ ምስሌክሙ ለዓለም፤ እኔም አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል›› እንዲል፡፡ (ዮሐ.፲፬፥፲፮) ይህንንም መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስ እያልን እናከብረዋለን፤ ከጌታ ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፡፡ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ወይም ለመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ሌላኛው ስሙ እንደሆነ ከርእሳችን እንረዳለን፡፡‹‹ጰራቅሊጦስ መንፈሰ አብ ወወልድ ስቡሕ፤ ጰራቅሊጦስ የተመሰገነ የአብና የወልድ መንፈስ ነው›› በማለት አምላክነቱን በአንድነት በሦስትነት ጸንቶ የሚኖር እውነተኛ አምላክ፣ ከአብ የሠረጸ የእውነት መንፈስ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ (ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ) ጰራቅሊጦስ ማለት ‹‹መንፈስ ቅዱስ፣ አጽናኝ፣ አስታራቂ፣ አሳምሮ የሚያናግር ማለት ነው›› ይላል፡፡ (ሕያው ልሳን) አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ‹‹ጰራቅሊጦስ›› ማለት ‹‹ናዛዚ፣ መጽንዒ፣ መስተፍስሒ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በዓለ ሃምሳ፣ የትንሣኤ ሃምሳኛ፣ የዕርገት ዐሥረኛ፣ እሑድ ቀን የሚውል ወዘተ…›› እያሉ ይተረጉሙታል፡፡ (ገጽ ፱፻፯) በጥቅሉ ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ያዘኑትን የሚያጽናና፣ የራቁትን የሚያቀርብ፣ የተሰወረውን የሚገልጥ፣ የረቀቀውን የሚያጎላ፣ የተከፉትን የሚያስደስት፣ ለመምህራን አንደበት የሆነ መጽንዒ፣ የሚያጸና፣ መንጽሒ የሚያነጻ ኃጢአትን ይቅር የሚል የሚደመስስ የእውነት መንፈስ፣ የእውነት አምላክ ነው፡፡ ጌታችን እርሱን እስኪልክላቸው ኃይልን ብርታትን እስኪላበሱ አላዋቂዎችን አዋቂ የሚያደርግ ከሣቴ ምሥጢር፣ ፈሪዎችን ደፋር (ጥቡዓን) የሚያድርጋቸው፣ በአሕዛብ በዓላውያን ፊት ያለ ኀፍረት፣ ያለ ፍርሃት እንዲመሰክሩ፣ በእሳቱ፣ በስለቱ እንዳይሸማቀቁ የሚያደርጋቸውን የእውነት መንፈስ እንደሚልክላቸውና እርሱም ለዘለዓለሙ አብሯቸው እንደሚኖር ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ እንዲህም ብሏቸዋልና፤ ‹‹ዘኢይክል ዓለም ነሢኦቶ፤ ዓለም እኔን ለሕማም ለሞት አሳልፎ እንዲሰጠኝ ለሕማም ለሞት አሳልፎ ሊሰጠው የማይቻለው፤ እስመ ኢይሬእዮ ወኢየአምሮ፤ አያየውም፤ አያውቀውምና፤ ወአንትሙሰ ተአምርዎ፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ አድሮባችሁ ይኖራልና በውስጣችሁም ይኖራልና፡፡›› አድሮባቸው የሚኖረውን፣ ሕማመ ሥጋ፣ ድካመ ሥጋን የሚያርቅላቸውን፣ የምሥራቹን ለዓለም ሁሉ የሚያደርሱበትን ኃይል ጸወን የሚሆናቸውን እውነተኛ የሆነ የራሱንና የአባቱን መንፈስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን፣ ባረገ በዐሥረኛው ቀን በዕለተ እሑድ ጰራቅሊጦስ የተባለውን የእውነት መንፈስ ላከላቸው፡፡ እርሱ የእውነት መንፈስ ነው አለ፤ የሐሰት መንፈስ አለና ሲለይ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በ፻፳ው ቤተ ሰብ ላይ እንደወረደ፡- ‹‹እንዘ ሀለዉ ኩሎሙ ኅቡረ አሀተኔ መጽአ ግብተ እምሰማይ ድምፅ ከመ ድምፀ ነፋሰ ዓውሎ፤በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጉዶ ተሰማ …›› (የሐዋ.ሥራ ፪፥፪) ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስትና ሰባ ሁለቱ አርድእት መቶ ሃያው ቤተ ሰብ በኅብረት በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም፤ እናንተ ግን ከሰማይ ኃይል እስክትለብሱ ማለትም ሰማያዊ ሀብትን፣ ሰማያዊ ዕውቀትን፣ ሰማያዊ ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ›› ብሏቸው ነበርና በኅብረት ይኖሩና፣ በኅብረት ይጸልዩ፣ የተስፋውንም ቃል ይጠብቁ ነበርና ድንገት በተሰበሰቡበት እንደ ዓውሎ ነፋስ ያለ ታላቅ ድምፅ አሰምቶ የተቀመጡበትን ቤት ሞላው፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፪) ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት መስሎም ታያቸው፤ በሁላቸውም ላይ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፡፡ በዚህም ኃይል የሚሆናቸውን፣ ሀብት የሚሆናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡ ሁሉም በየራስ በየራሳቸው ሰባ ሁለት ቋንቋ መናገር ጀመሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያትና በሌሎቹ ላይ እንደ ነፋሰ ዓውሎ ሆኖ ነው የወረደው፡፡ ምክንያቱም ነፋስ ረቂቅ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ረቂቂ ነውና፤ ነፋስ ኃያል ነው፤ ፍሬውን ከገለባው ይለያል፤ መንፈስ ቅዱስም ጻድቃንን ከኃጥአን ይለያልና፡፡ ነፋስ በምልዓት ሳለ አይታይም፤ አይታወቅም፤ ነገር ግን የሚታወቀው ባሕር ሲያናውጥ፣ ዛፍ ሰያወዛወዝ፣ ቅጠሉን ሲያረግፈው፣ አቧራውን ሲያስነሣው በሥራው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም በምልአት ሳለ አይታወቅም፤ ነገር ግን ቋንቋ ሲያናግር፣ ምሥጢር ሲያስተረጉም ይታያልና፡፡ ነፋስ መዓዛ ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስም መዓዛ ጸጋን ያመጣልና በነፋስ ተመስሎ ወርዷል፡፡ ሰባ ሁለት ቋንቋ ሲናገሩም ከልዩ ልዩ ቦታ የተሰበሰቡና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ በዚያ (በኢየሩሳሌም) ነበሩና አደነቁ፤አንዳንዶቹ እንዲያውም ግራ ተጋብተው ‹‹እነዚህ ሰዎች ሁላቸውም የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንደምን እንሰማቸዋለን›› እያሉ ያደንቁ ነበር፤ አንዳንዶቹ ግን ይስቁባቸው ነበር፡፡ምክንያቱም ከከተማ የመጡ እኩያን አይሁድ ሰቃልያነ አምላክ ናቸውና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ላለማድነቅ በሐዋርያት ላይ ሳቁባቸው፤ ‹‹እሊህ ያልፈላ ጉሽ ጠጅ ጠጥተው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› ብለው ተሳለቁ፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፭-፲፫) እንደ እውነቱ ከሆነ ያልፈላ ጉሽ የወይን ጠጅ የጠጣ፣ ጠጥቶም የሰከረ ሰው፣ እንኳን የማያውቀውን ቋንቋ ሊናገር ቀርቶ የሚያውቀውንም በተናገረው አይናገረም፤ ስካር አንደበትን ያስራል፤ ትንፋሽን ያሳጥራል እንጂ አዲስ ቋንቋ፣ ሁላቸውም የሚሰሙት የሀገራቸውን ቋንቋ ሊናገሩ አይችሉም ነበር፡፡ አይሁድ ግን ክፉዎች ነበሩና እውነቱን መቀበል አይሹም፡፡ የዘመናችን መናፍቃንም ወንጌል ተከድኖባቸው፣ እውነቱ ተሸፍኖባቸው፣ በዕውቀት የተራቀቁትን፣ መንፈስ ቅዱስ ተመልተው ምሥጢር የሚያመሠጥሩትን፣ ክብሩን የሚገልጡትን በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ መምህራንን፣ ሊቃውንትን እንደሚያቃልሉትና እንደሚያሾፉ ዓይነት ማለት ነው፡፡ ግን ጊዜው የስካር አይደለም፤ ምክንያቱ ገና ንጋት (ነግህ) ነውና፤ ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረው ቢፈጸም ነው እንጂ፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ መንፈሴን አሳድርበታለሁ›› ያለው ጌታ አስቀድሞ በነቢዩ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነርሱ ላይ ስለ መውረዱ አዲስ ዕውቀትን እንደገለጠላቸው ነገራቸው፤ ገሠጻቸው፤ ስለ ጌታችን ወደዚህ ዓለም መምጣት፣ አይሁድ ግን በክፋት እንደሰቀሉት፣ እርሱ ግን በሥጋ ሞቶ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ስለ መነሣቱና ስለማረጉ ለዚህም ምስክሮቹ መሆናቸውን ጭምር ሰበከ፡፡
4 31370Loading...
04
https://youtu.be/xBBQ2M98_9Q?si=C2UPL2c41f9QozQ3
3 59315Loading...
05
#ሳታቋርጡ_ጸልዩ "ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተጠምዶ መዋል አይችልም" አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይሆን ሀሳብ ነው ፤ እጅ ሳይሆን እደ ልቦናን ማንሣት  ነው፤   አፍአዊ ሳይሆን ውስጣዊ አኳኋን ነው ።ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፤ ደረትህንም ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከሆነ ጸሎትህ ሥልጡን ነው ።     #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
4 50476Loading...
06
ቅዱስ ሚካኤል - መልአከ ምክሩ *** በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ስለሚያደርገው የምክር ጉባኤ ተጽፏል። ይህ መለኮታዊ ምክር ( the devine council) እግዚአብሔር ስለሚያደርገው እና ስለፍርዱ ከተመረጡ ቅዱሳን ጋር የሚያደርገው ነው። ይህን የሚያደርገውም ከቅዱሳንም መርጦ ላከበራቸው ያለውን ክብር ያሳይ ዘንድ ከሥልጣኑ በጸጋ እያሳተፋቸው እንጂ ከእግዚአብሔር ፍርድ እና ምክር የሚጎድል ኖሮ እነርሱ ሊሞሉለት አይደለም። የመጀመሪያው ይህን የተመረጡ ቅዱሳን ምክር የሚያሳይ ጥቅስ መዝ. 81/82 ነው፦ “እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።" ሌላኛው ደግሞ "እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል? በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው፤" የሚለው ነው። (መዝ. 89፥6-7) *** ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ምክሩ የሚባል የመላእክት አለቃ ሆኖ የዚህ መለኮታዊ ምክር አካል ስለሆነ ነው። 'ተሾመ' የሚለው ቃል ይህን መመረጥ ይገልጣል። ከሌሎች መላእክት በተለየ በዙፋን ላይ ተቀምጦ መሳሉም ለዚሁ ነው። ድንግል ማርያምም የዚህ ማኅበር አካል ነች። ቀድሞ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ሰሎሞን ለእናቱ ያለውን ክብር ይገልጥ በጎኑ ዙፋን አስቀምጦ ያማክራት ነበር። (1ኛ ነገ. 2፥19) ዳዊትም "ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ ተናግሮላታል። (መዝ. 44/45፥9) ሐዋርያትም እንዲሁ ናቸው፤ ጌታ በ12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ላይ ሲፈርዱ በዙፋን እንደሚቀመጡ መናገሩ የመለኮታዊው ምክር አካላት እንዳደረጋቸው ያሳያልና። (ማቴ. 19፥28) ይህንም ነቢዩ ዳንኤል ቀድሞ ተናግሮታል፦ “ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።” (ዳን. 7፥9) ነቢዩ 'ዙፋኖች' ያለው እግዚአብሔር ብዙ ዙፋኖች ኑረውት ሳይሆን የተመረጡ ቅዱሳን የሚሳተፉበትን ከእግዚአብሔር ፍርድ ሲወጣ ቀድመው የሚያውቁ እና በባለሟልነት የሚማልዱ የቅዱሳን ጉባኤ ክብራቸውን ለማመልከት ነው። *** በዚህ ሁሉ ታላቁ መልአክ ሚካኤል አለ! ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል! ከእግዚአብሔር የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ለጎስቋሎች ባሮችህ ለምንልን። አሜን።
6 64566Loading...
07
Media files
7 204159Loading...
08
Media files
6 912138Loading...
09
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።” (ያዕ. 4፥8) *** የመልካም ነገር ጅማሮ ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ወይስ ከሰው? የዚህ ጥያቄ መልስ ግልጽ ነው፦ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ከእግዚአብሔር ነው። ታዲያ ያዕቆብ በመልእክቱ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፤" ብሎ ሲናገር መቅረብ ከሰው የሚጀምር ይመስል የእኛን ኃላፊነት ቀድሞ መናገሩ ለምንድር ነው? ብለን እንጠይቃለን። መልሱ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔርማ ሁሉን ፈጽሞ ትቀበለው ዘንድ እየጠበቀን ነው። ከሰው በኩል ግን መቀበል ይገባል። እንዴት ነው የምንቀበለው? በእምነት፣ በንስሐ፣ ከኃጢአት ጋር ተጋድሎ በማድረግ እና በክርስቶስ ትእዛዛት ለመኖር በመጣር ነው። እነዚህ ነገሮች የጸጋ ሁሉ ምንጭ ወደሆነው እግዚአብሔር ለመቅረብ ጽኑ ፈቃዳችን በውስጥም በውጭም የምንገልጽባቸው ናቸው። እግዚአብሔር በእንዲህ ያለ ተግባር ውስጥ ሲያየን በእኛ ጥረት ሊገኝ የማይችለውን ዘላለማዊ ድኅነት ያጎናጽፈናል፤ የጸጋ አማልክት እስክንባል ደርሰን የእርሱ ጸጋ የሞላብን ያደርገናል። በእርሱ ዘንድ በባሕርዩ ያለ ቅድስናን ወደ እርሱ ቀርበን እናገኘው ዘንድ ይሰጠናል። ይህን ሁሉ የምናገኘው ከእኛ ብቃት ሳይሆን ከእሱ ጸጋ ነው፤ ነገር ግን በየጊዜው በምናደርገው የእምነት መታዘዝ እና ተጋድሎ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እና እርሱን ለመምሰል ያለነን በተግባር የተፈተነ ጽኑ ፈቃድ እንገልጣለን። *** “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ... እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።” *** (ያዕ. 4፥8-12) Bereket Azmeraw
8 43179Loading...
10
አንድ ወንድም ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ሄደና “እድን ዘንድ የሚረዳኝን ምክር ምከረኝ አለው፡፡ መታርዮስም “ወደ መቃብር ቦታ ሒድና ሙታንን ስደባቸው አለው፡፡ ያ ወንድምም ወደዚያ ሄዶ ሰድቧቸውና ድንጋይ ወርውሮባቸው ተመለሰና ይህንኑ ማድረጉን ነገረው፡፡ መቃርዮስም “ምን አለህ?” ሲለው እርሱም “ምንም ነገር አላሉኝ" አለው። አረጋዊውም “ነገ ተመልሰህ ሒድና አመስግናቸው” አለው፡፡ ያ ወንድምም ተመልሶ ሔደና “እናንተ እናንተ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰዎች ናችሁ" እያለ ሲያመሰግናቸው ውሎ ተመለሰ፡፡ አረጋዊውም “ምንም አልመለሱልህም?" አለው፡፡ እርሱም “የለም” አለ፡፡ መቃርዮስም “ሙታንን እንደ ሰደብካቸውና ምንም እንዳልመለሱልህ፣ እንደ ገናም እንዳመሰገንካቸውና ምንም ነገር እንዳልተናገሩህ አይተሃል፡፡ አንተም ልትድን ከፈለግህ እንዲሁ ማድረግና የሞትህ መሆን አለብህ። ልክ እንደ ሙታን የሰዎችን ነቀፌታቸውንም ሆነ ምስጋናቸውን ከቁም ነገር አትቁጠረው፣ ቦታም አትስጠው፣ እንዲህ ብታደርግ ትድናለህ” አለው፡፡ ++++++++~~~~~++++++ በአንጾኪያ የነበረ አንድ ደግ መነኩስ እንዲህ አለ፦ “እጸልይ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም የምመገበው ስላልነበረኝ እንደ ራበኝ አዝኜ ተኛሁ:: ክርስቶስ ሌሊት ታየኝና «ጎልጎታ ወዳለ ቄስ ሂድና አንዲት ዲናር ትሰጠኝ ዘንድ ክርስቶስ ወዳንተ ልኮኛል፣ እርሱ መጥቶ ይከፍልሃል በለው» አለኝ:: በነቃሁ ጊዜ ወደ ቄሱ ሄድሁና ነገርሁት:: እርሱም «ክርስቶስ የሚመጣና ገንዘቤን የሚሰጠኝ መቼ ነው?» አለኝ፡፡ እኔም እርሱ ያለኝን ነግሬሃለሁ፣ ከዚህ በኋላ የወደድከውን አድርግ አልሁት፡፡ እርሱም «ጻፍልኝ» ኣለኝ፡፡ እኔም እኔ የአንጾኪያው ዮሐንስ ከኢየሩሳሌሙ ቀሲስ እስጢፋኖስ አንድ ዲናር ወስጃለሁ፤ ክርስቶስ መጥቶ ዲናሩን እንደሚከፍለው ይኸው በእጄ ጽፌአለሁ ብዬ ጻፍሁለት፡ እርሱም ሰጠኝ። በዚያው ሌሊት ክርስቶስ ታየውና «ዲናርህን ውሰድና ያ መነኰስ የጻፈውን ጽሑፍ መልስልኝ» አለው᎓᎓ እርሱም «ክርስቶስ መጥቶ ይመልስልሃል ብሎኝ አልነበረምን?» አለው፡፡ እርሱም «ዲናርህን ውሰድና የዚያን መነኰስ ጽሑፍ መልስልኝ የምልህ እኔ ራሴ ክርስቶስ ነኝ» አለው:: ያም ቄስ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ወደዚያ መነኰስም ወደ እርሱ በፍቅር ይመጣ ዘንድ ላከበት፡፡ መነኲሴው ግን ያቺን ዲናር አምጣ ሊለኝ ነው ብሎ ፈራ፡፡ ኣብረው ሲበሉም «ከገንዘቤ የፈለግከውን ሁሉ ውሰድ» አለው፡፡ መነኲሴው ግን ከታዘዘልኝ በቀር ሌላ አልፈልግም” አለው፡፡ ቄሱም በሀልሙ የሆነውን ነገር ነገረውና “አሥር መክሊት ወርቅ ውሰድና ጻፍልኝ” አለው። እርሱ ግን “ከአንድ ዲናር በቀር ሌላ እወስድ ዘንድ አምላኬ አላዘዘኝም፡፡ ነገር ግን በፍጹም ልብህ ካመንህ ብዙ ነዳያንን ታገኛለህ፤ እነርሱም እንዲህ ይጽፉልሃል” አለው:: ++++++++++++~~~~+++++++++ ነፍስህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ስትሰለች ፣ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብና መስማት ደስ የማይላት ሲሆንና ሲያስጠላት፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ተግሳፅን ስታቃልል ካየሀት በክፉ ደዌ ላይ እንደወደቅህ ተገንዘብ፤ ሰዎች የሞትን ፍሬ የሚቀጥፉበት መጀመሪያው ይህ ነውና። #ከበረሐውያን_አንደበት #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
8 61296Loading...
11
https://youtu.be/yJiuD68IMtY?si=cFpiJFLMYfnP1x3j
7 29826Loading...
12
በምሥጋና ዐረገ፤ ቤተ ክርስቲያኑንም ከፍ ከፍ አደረጋት። *** እየታያቸው ከፍ ከፍ አለ፤ የባሕርይ ክብሩን የምታመለክት ደመና ተቀበለችው። በእርሱ ዕርገትም አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን በእርሱ ሆና ከፍ ያለች እና በሰማያዊ ሥፍራ የተቀመጠች ሆነች። የዚህ ዓለም ኃያላን የሚያናንቋት ሐረገ ወይን የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯ በምድር ቢሆን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ናቸው። ይህ ምን ይደንቅ! አንዳንድ አገልጋዮቿ በሥርዓተ አምልኮዋ በዘፈቀደ እና በቸልተኝነት የምንመላለስባት ቤተ ክርስቲያን በመንቀጥቀጥ የሚያገለግሉ ሰማያውያን መላእክት ጋር ኅብረት ያላት ናት። በላይ በበጉ ዙፋን የምትቀድስ ናት! ለዚህ ጸጋዋ አንክሮ ይገባል! ይህ ሁሉ የሆነው ግን ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባቱ ያቀርበን ዘንድ በእኛ ሥጋ ከፍ ከፍ ብሎ በአብ ቀኝ በመቀመጡ የተሰጠን ጸጋ ነው። *** "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።" *** (ሉቃ. 24፥50-53)
10 04283Loading...
13
Media files
7 88470Loading...
14
Every hour expect your death and the coming of Christ, and say: "Now I will survive to work over my soul; in the evening I can die." When the evening comes, think, "will I not die in this very night? or death will suddenly come, my breath will suddenly stop, and as a flower falls I will fade. As the grass dries up, I shall die and then will be without a trace. God alone knows where I will then be, for He will judge each according to his deeds, saying 'I assign him to go there.'" Think then every day, and so not be concerned about anything, only about your own sins, and in this way your soul will enter into humility and lamentation and you will consider yourself as a frightful sinner and will ceaselessly gush forth founts of tears. but in necessities, in clothing, vessels, and things, observe simplicity, poverty, modesty, not because there is nothing to buy these things with, but because by this the soul is humbled and is not removed from God, and then everywhere it will be easy to find them. - St. Paisios
7 65641Loading...
15
https://vm.tiktok.com/ZMr85XaT8/
8 2355Loading...
16
https://youtu.be/XnYoB-_Cy54?si=E9kFEJJWxrVEc99K
7 8695Loading...
17
https://youtu.be/4YOiKQWiXJs?si=w6rZFoVq0blaOR-8
1 8432Loading...
18
A humble person takes everything calmly. I will emphasize it at once, calmly does not mean indifferently. Humility is not indifference. An indifferent person is not God's person. He is like the one who was given a talent and buried it (see Mt. 25:14-30). A humble person takes bad circumstances peacefully, and good situations do not make him euphoric, fanciful, or emotionally exultant. #archpriestSergiyBaranov
9 70429Loading...
19
ክህነት በሀዲስ ኪዳን * የተለየ ክህነት * አዲስ ክርስቲያን ካህን መሆን ይችላል? * ሽማግሌ ወይስ ካህን ? ++++++++++~~~~~+++++++++ ኃጢአትን ይቅር የማለትን ሥልጣን ለራሱ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባ ሥልጣን ስለሆነ ይህን ለሌላ ለማንም አንሰጥም በማለት፣ እግዚአብሔርን ታላቅ በሆነ አክብሮት እናከብረዋለን ይላሉ። ሆኖም ግን እርሱ በግልጽ የተናገረውን ትእዛዙን እንደሚሽሩትና ለካህናት የሰጠውን ሥልጣን አንቀበልም እንደሚሉት እንደ እነርሱ አድርጎ የሚያቃልለው ሌላ ማንም የለም። ራሱ ጌታችን “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” ያላቸው ከሆነ፣ እግዚአብሔርን የሚያከብረው የእርሱን ትእዛዝ ተቀብሎ የሚታዘዘው ነው? ወይስ ትእዛዙን አልቀበልም የሚለው? .. " (ቅዱስ አምብሮስ በእንተ ንስሐ፣ መጽሐፍ 1፡6-7) #መድሎተ_ጽድቅ #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
8 950100Loading...
20
"ኦርቶዶክስ መሆን በራሱ ኋላ ቀርነት እንደሆነ ተደርጎ ነው የተሰበከው" #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
8 47336Loading...
21
ከውዝግብ ባሻገር... ያዳነንን እናውቃለን! *** 1. የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ወልድ ከአብ ጋር ዘላለማዊ ህልውና ያለው የባሕርይ አምላክ ነው። የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ነው። በሁሉ ፍጹም የሆነ የአባቱ የባሕርዩ ነጸብራቅ ነው። ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንዲት መለኮታዊ ሥልጣን እና ኃይል ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ ነው፤ ከሆነው ያለ እርሱም የሆነ ምንም ምን የለም። ፈጣሪ አምላክ ነው። (ዮሐ. 1፥1-14፣ ዕብ. 1፣ 1ኛ ቆሮ. 8፥6) 2. ይህ ዘላለማዊ ህልውና ያለው እና ፍጥረት ሁሉ በእርሱ የተፈጠረበት የአብ አካላዊ ቃል በዘመኑ ፍጻሜ እኛን ለማዳን ራሱን ዝቅ አድርጎ ሰው ሆነ። ሰው ሲሆን ግን አምላክነቱን እና መለኮታዊ ክብሩን አጥቶ አይደለም፤ አምላክነት የሚቀማ እና የሚለወጥ ነገር አይደለምና። ይልቁንስ አምላክነቱን ሳይለቅ ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ ሰው ሆነ። ሰው በመሆኑም የትሕትና ነገሮች ተነገሩለት። በባሕርዩ ፍጡር የሆነ ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ስለሆነ አማናዊ ሰውነቱን ለማጠየቅ የባሕርይ አባቱን 'አምላኬ' አለው። ተራበ፤ ተጠማ፤ በላ፤ ጠጣ፤ መከራ ተቀበለ፤ ጸለየ፤ ተኛ፤ ወዘተ...። በዚህ በለበሰው ሥጋው ምክንያት ከኃጢአት በቀር ለሥጋ የሚገቡ ነገሮች ሁሉ ስለ እርሱ ተብለዋል። ይህን ያደረገውም ለእኛ ቤዛ እና መድኃኒት ይሆን ዘንድ በፈቃዱ እንጂ ግዴታ ወድቆበት አይደለም። በዚህም ፍቅሩን እንረዳለን እንጂ እንደ አይሁድ ውለታቢሶች ሆነን አምላካዊ ክብሩን ዝቅ አድርገን አናይም።(ዮሐ. 1፥1-14፣ ፊል. 2፥6-11፣ ዕብ. 4፥15) 3. ክርስቶስ ሰው ሆኖ እኛን ከማዳኑ የተነሣ ከዘላለማዊ አምላክነቱ እና ክብሩ ዝቅ ያለ አይደለም። ይልቁንም እርሱን (ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር) የምናመልክበት እና ለዘላለም የምናመሰግንበት እጅግ ከፍ ያለ ምክንያት ሰጠን እንጂ። ቀድሞ ስለፈጠረን እና ስለሚመግበን እናመሰግነው እና እናመልከው ነበር። አሁን ግን የእኛን ባሕርይ ለብሶ እና እስከሞት የሚደርስ መከራ ተቀብሎ በማዳኑ የማንከፍለውን ውለታ ውሎልናል፤ አምልኳችንን በማዳን ደስታ እና ምሥጋና ሞልቶታል። 4. እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው መሠረታዊ እና የመዳን ወንጌል ምሰሶዎች ናቸው። ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት (በአይሁድ ነገረ ሃይማኖታዊ ብያኔ - in the paradigm of Judaism) የተገለጸው በዚህ መልኩ ነው። ከዚያ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ከግሪክ የእውቀት ባሕል ጋር መስተጋብር ስታደርግ አስተምሮዋን በግሪክ ፍልስፍናዊ ብያኔ (Hellenistic paradigm) መግለጽ ነበረባት። ይህም ውስብስብ ነገሮችን ፈጠረ፤ ምሥጢረ ሥላሴን እና ነገረ ክርስቶስን በተወሳሰበ መንገድ መግለጽን አመጣ። ቤተ ክርስቲያን ለአሕዛብም ስለሆነች በግሪክ ፍልስፍና ተጽሕኖ ሥር የነበረውን ዓለም ለማምጣት ወደዚህ ተዋሥኦ መግባቷ ትክክል እና የግድ መሆን የነበረበት ነገር ነበር። ግን ከላይ ያልናቸውን መሠረታዊ ነገረ ክርስቶሳዊ ጉዳዮች ተምሮ እስካመነ ድረስ ሁሉም ክርስቲያን ይህን ውስብስብ ተዋሥኦ የመመርመር እና የመረዳት ግዴታ የለበትም። (ይህ ቢሆንስ ክርስትና 'ተራው' ምእመን የማይረዳው የelite ሃይማኖት በሆነ ነበር)። ከሁሉም ክርስቲያን የሚጠበቀው መሠረተ እምነትን አውቆ በዚያ በተአምኖ መኖር ነው። መምህራን ሊይዙት እና ቤተ ክርስቲያንን ከስህተት ይጠብቁበት ዘንድ የሚማሩት ረቂቅ እና ሐተታዊ (speculative) ትምህርት አለ። ሁሉም ሄዶ ሄዶ የሚያርፈው ግን መሠረታዊው ትምህርት ላይ ነው። ሂደቱ simplicity ----> complexity -----> simplicity ነው። ውስብስብ ጉዳዮችን ወደ ምእመናን አውርዶ በማኅበራዊ ሚዲያ መወዛገብ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል። Bereket Azmeraw
10 07981Loading...
22
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤ 2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤
7 90016Loading...
23
3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤ 6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡ 10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
7 53225Loading...
24
Prayer is the energy of life. As long as water runs and murmurs, it is alive. As soon as it stops, it begins to turn into a bog. The same thing happens inside of us. As long as prayer moves in us, our soul is alive. When it stops for a while, our soul begins to perish. Cherish prayer. Do not say it just because it was given to you as a rule you need to fulfill. Take it as the energy of your life. If there is prayer, then there is life! #archpriestSergiyBaranov
6 26143Loading...
25
Media files
8 67092Loading...
26
https://youtu.be/8pYrv_s2wRQ?si=vJ01y4ykxbp3gBBm
6 85814Loading...
27
እነዚህን የመምህር ያረጋል መጻሕፍቶችን በግዮን  መጻሕፍት  መደብር በልዩ ቅናሽ  ታገኙታላችሁ። ፦ስልክ 0913083816 /0931144330 አድራሻ ምኒልክ አደባባይ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በምዕራብ በር ማይክሮ ሊንክ እንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
6 81728Loading...
28
በዕቅበተ እምነት ጥንቃቄ የሚሹ ተግባራት (ከብርሃኑ አድማስ ጽሑፍ በምኅጻር የተወሰደ) -- 1.የዕቅበተ አምነትን ሁለት ዋና ጠባያት መረዳት፡- (1) ሃይማኖት/እምነት ከአምላክ የተገለጠ እውነት መሆኑን ተረድቶ ለማጽናት መታገልና (2) በእምነት የደከሙትን/የሳቱትን ሰዎች ራሳን እንደ ደጉ ሳምራዊ አድርጎ በርኅራኄ ቁስላቸውን አክሞ ለማዳን መፋጠን ሁለቱ የቅበተ እምነት መሠረታውያን ጠባዕያት ናቸው፡፡ -- 2.በዕቅበተ እምነት ውስጥ የማይታለፉ ጉዳዮች፡- (1)ዐቂበ እምነት፡- የሃይማኖትን ምንነት በቤተ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ላይ ተመሥርቶ መግለጥና ያንን የሚቃወም ስሑት ትምህርት በየዘመናቱ ሲመጣ ትምህርቱ የአባቶች አለመሆኑን ማሳየት፡፡ (2)እውነት ላይ ማተኮር፡- ዐቃቤ እምነት ትኩረቱ እውነት እንጂ አሸናፊነት አይደለም፣ ትኩረቱ ወደተሳሳተው አስተምህሮ እንጂ ወደተሳሳተው ግለሰብ አይደለም- ልክ መድኃኒት በሽታን እንጂ በሽተኛን ለማጥቃት እንደማይሰጠው፡፡ (3)አሳማኝነት፡- ጭብጥ አቀራረጹና አቀራረቡ ሐሳብን ሊያስተላልፍና የተለያየ ዕውቀትና ግንዛቤ ላላላቸው ሰዎች ተደራሽና ሰዎች ሐሳቡን ሊጋሩት በሚችል መመልኩ መቅረብ አለበት፡፡ (4)ክርክርን በተገቢው መንገድ ማቅረብ፡- የዕቅበተ እምነት ሥራ ዐላማው አማኞች ከመጠራጠር መጠበቅና የሔዱትን መመለስ እንደመሆኑ መጠን አቀራረቡ የሚያቀርቡትን ጭብጥ መረዳት (understanding)ንና ተደራስያን ሊረዱ በሚችሉበት ቋንቋ የማቅረብ አቅም፣ ያልተድበሰበሰ ውሳኔን (judgment)ና የሚሟገታቸውን ሐሳቦች ስሑትነት የሚያሳይና የሚያቀርበውን ሐሳብ ከትችት ያራቀ አጠይቆት(reasoning)ን ማማከል ይገባዋል፡፡ -- 3.የዕቅበተ እምነት ጸያፎች፡- (1)ሐሰተኛ ትርጉም መስጠት (Proselytism)፡- ማለትም የምንሞግተውን ሐሳብ ተሞጋቹ በሚለው ሳይሆን እኛ በሰጠነው ትርጉም ሰይሞ ምላሽ ለማዘጋጀት መሞከር፡፡ ለምሳሌ፡- ኦርቶዶክሳውያን እመቤታችንን እናከብራታለን እንጂ አናመልካትም፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ማክነራችንን ማምለክ ብለው ተርጉመው የዕቅበተ እምነት ሥራ ሠራን ይላሉ፡፡ በእኛም ቤት ካቶሊካውያን እመቤታችንን ኃይል አርያማዊት ይላሉ የሚል ልማድ ያገነነው ስሑት አበባል አለ፡፡ ሐሰተኛ ትርጉም መስጠጥ ይባላል፡፡ (2)ሥነ ልቡናዊ ርግጠኝነት (Psychological Certainity)፡- የሰማዕያን/አንባብያንን ድክመት ተጠቅሞ የማያውቁትን ሐሳብ ወይም ቋንቋ ከዐውድ ውጪ በመውሰድ ለማሳመን መሞከር ነው፡፡ ምሳሌ፡- ኦርቶዶክሳውያን ለሥዕል የምንሰጠውን ክብር ዘፀ.20፡4 ላይ ያለውን ‹‹የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ›› የሚል ጥቅስ ተጠቅሞ ቅዱሳት ሥዕላትን ጣኦት አድርጎና የጥቅሱ መተርጎሚያ አድርጎ መጠቀም፡፡ ያላነበቡትን እንዳነበቡ፣ የማያውቁትን ግእዝ ወይም እንግሊዝኛ ወይም ደግሞ ሌላ ቋቋ የሚያውቁ መስሎ ለማሳመን መሞከርም በሰማዒው/አንባቢው ላይ የሥነ ልቡና ርግጠኝነትን ፈጥሮ ለመቀሰጥ ሙከራ የሚደረግበት የዕቅበተ እምነት ጸያፍ ነው፡፡ (3)መንሸራተት (Deviation)፡- ከጭብጥ መሸሽ ወይም ጭብጥን ለራስ በሚመች መልኩ ቀርጾ መዳከር፡፡ (4)ከአመክንዮ በተቃርኖ መቆም (Logical fallacy)፡- ምንም እንኳ ነገረ ሃይማኖት ከአመክንዮ ባሻገር ቢሆንም አንድን የፍሬ ነገር መለኪያ ለተለያየ መደምደሚያ መጠቀም፡፡ ምሳሌ፡- ተሐድሶዎች የደቂቀ እስጢፋስ ገድላት ላይ መፍቀርያነ ገድል መስለው ሲያበቁ በሌሎች ቅዱሳን ላይ ሲሆን የምናውቀውንና እዚህ የማንናገረውን ጸያፍ አንደበት እንደሚጠቀሙት፡፡ (5)ሁሉን ጠልነት (Negativism)፡- የሚቃወሙት ሰው/ቡድን የተናገረውን ሁሉ በጅምላ ማነወር፡፡ አውንታዊ ምሳሌ ብንጠቅስ፡- መልአከ ብርሃን አድማሱ ምላሽ የጻፉላቸው ሰዎች ትክክለኛ ነገር ሲጽፉ እንዳላዩ አያልፉም፤ እዚህ ላይ ትክክል ነህ ይላሉ፡፡ (6)አድሏዊነት (Inclination/Bias)፡- በአንድ ስሕተት የሚያውቁትን ሰው እንደሚሳሳት አስቦ ሥራዎቹን ማየት ወይም በስሕተት የወደቁ ሰዎችን በአካባቢ ወይም በተማሩበት ት/ቤት ፈርጆ ‹‹ወትሮስ ከዚያ የወጡ!›› እያሉ መፈረጅ ጸያፍ ነው፡፡ -- ምንጭ፡- አድማሱ ጀንበሬ፡ ሕይወቱ ወሐተታ መጻሕፍቱ፣ 2011፣ ገጽ 12-39 (በምኅፃር ተጨምቆ የቀረበ፡፡)
7 387111Loading...
29
“እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” (ዮሐ. 6፥63) *** የክርስትና አስተምህሮ አመክንዮአዊ ቀመር እና የቃላት ብያኔ ብቻ አይደለም። ጌታችን እንደነገረን ከዚያ የሚያልፍ መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው። በመሆኑም አንድ ንባብ በቅዱሳት መጻሕፍት ቢገኝም 'መንፈሱን' ካልተረዳን እንስታለን። ያ አገላለጽ የተነገረው ምንን ለማጠየቅ ነው? ምን ብለን ብንረዳው ደግሞ ስህተት ይሆናል? ብሎ ትውፊታዊ መረዳትን ይጠይቃል። አንዳንዶቹ አገላለጾች ደግሞ እጅግ ትልቅ ቅጥነተ ህሊና ይጠይቃሉ። ከእነዚህ አንዱ 'ፈጣሪ ወፍጡር' የሚለው ትምህርት ነው። ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮች እንኳ ክርስቶስን 'በሥጋው ፍጡር' ማለት በትክክለኛ ዓውዱ ከተነገረ ስህተት ባይሆንም ምእመናን እንዳይደናገሩ በነገረ ሃይማኖት ሐተታዎች ውስጥ በብዛት አንጠቀመውም ይላሉ። (Catholic Encyclopedia) ይህ ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ውስጥም ያለ ነው። እኔ እስከማውቀው በአምልኮ መጽሐፎቻችን ውስጥ አይነገርም። እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኘው በአንዳንድ ሊቃውንት ድርሳናት ውስጥ ነው። ይህ የሚያመለክተው አገላለጹ በቅጥነተ ህሊና ከነሙሉ ዓውዱ ካልተረዱት ምእመናን 'በሥጋው ፍጡር ስለሆነ በሥጋው አናመልከውም' ብለው እንዳይሰናከሉ ነው። 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ሲባል፦ 1. የለበሰው ሥጋ ዘላለማዊ ህልውና ያልነበረው የእኛ የተፈጠረ እውነተኛ ሥጋ ነው ለማለት ነው። 2. የሰው ልጆች ሐዲስ ተፈጥሮ (መታደስ) ከእርሱ የተጀመረበት ዳግማይ አዳም፣ በኲረ ፍጥረታት መሆኑን ለመናገር ነው። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ያልነሳውን አላዳነምና። 3. ሌሎችም። *** ነገር ግን ከነዚህ እሳቤዎች መጠንቀቅ ደግሞ ይገባል፦ 1. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው አምልኮ አይገባውም ማለት አይደለም። የክርስቶስን ሥጋ ከመለኮቱ ለይተን በመለኮቱ ብቻ እናምልክ ካልን የማይከፈለውን አንዱን ክርስቶስን እየከፈልነው ነው፤ ስለ መዳናችን ሰው የሆነውን ክርስቶስን ስለእኛ ሰው በመሆኑ ዝቅ እያደረግነው ነው። ስለ ሕዝቡ ሲል ከአባቱ ዙፋን ወርዶ ሕዝቡ የሚለብሱትን መናኛ ልብስ ለብሶ የሚታደገውን የንጉሥ ልጅ ውለታ ባለመረዳት 'በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሥ አናይህም' ብሎ እንደመሳለቅ ነው። 2. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ማኅየዊ (ሕይወትን የሚሰጥ) አይደለም ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ቅዱስ ቄርሎስ እንዳለው ሥጋውን እና ደሙን መቀበል ከንቱ በሆነ! 3. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ለአብ ይገዛል ማለት አይደለም። አብ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስምን ሰጠው የተባለ በሥጋው ነው። ታዲያ ይህ ከፍታ ከመገዛት የማያወጣ ከሆነ ከቅዱሳን የጸጋ ክብር በምን በለጠ? ቅዱስ አትናቴዎስ እንዳለው ከፍጡራን ግብርናት እስካልወጣ ድረስ ምን ቢከብር ለእርሱ የሚገባ ክብር አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ የተነገሩ የትሕትና ንግግሮች ከማዳን ግብሩ እና አርአያነቱ (economy of salvation) አንጻር የምንረዳቸው ናቸው። ካልሆነ ግን በክርስቶስ ዘንድ ሰው ከመሆኑ የተነሣ ዘላለማዊ ተዋርዶ ገብቷል ያስብላል። በሥላሴ አካላት ዘንድ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈስ ዘላለማዊ ክብርና ምሥጋና አለ። ነገር ግን ሰው ከመሆኑ የተነሣ በወልድ ዘንድ የፍጡር አምልኮ ግዴታ አልወደቀበትም። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ይህን አብም አይፈልግም፤ ወልድም አይሰጥም። Bereket Azmeraw
8 18399Loading...
30
Media files
9 56821Loading...
31
Media files
10 19853Loading...
32
ጥያቄ ብቻ ነው። በዚህ የምትቀየሙ ሁሉ፣ ሳላውቅ የበደልኳቸሁ ካላችሁም ይቅር በሉኝ፣ እንድትድን ለምን ትጠይቃለህ ግን አትበሉኝ። እንድድን በወልደ እግዚአብሔር ሞት ተጠርቻለሁና። Dn. Birhanu Admas
11 23650Loading...
33
ቅዱስ ሲኖዶስ ሠራኤ ሕግ ወፈጻሜ ሕግ የሆነውን ጌታቸውን የተከተሉ፣ ሙጽአ ሕግ የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በሕገ እግዚአብሔር በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈጽሙ አባቶች ስብስብ እንደሆነ አምናለሁ፣ አውቃለሁም። ለዚህም ነው በዘወትር ጸሎታችን ያለውን እንደ ሁሉም ክርስቲያኖች ሁሉ ዕለት ዕለት “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” ብለው ያስተማሩኝን የማምነው፣ የምመሰክረው፣ የምጸልየውም። ቤተ ክርስቲያን ከጉባኤያት ፣ ከምክር ቤቶች፣ ከስብሰባዎች ሁሉ በላይ የሆነችውም በተፈጥሮዋም፣ በአሠራሯም፣ በሒደቷም ከሁሉም በላይ በሆነው በጌታዋ በቤዛዋ በመድኃኒቷ እንዲህ ጸንታ የምትኖር ስለሆነች እና መሆንም ስላለባት እንደሆነ አውቃለሁ፣ አምናለሁም። አንዳንድ ሰዎች ዘመን ሰጠን፣ ጉልበት አገኘን ብለው ይህን አስትተው እንደ ጎሣ ምክር ቤት፣ እንደ ፌዴሪሽን ምክር ቤት፣ እንደ ወንድማማቾች እድር፣ እንደ ተወላጆች ማኅበር፣ እንደ መሳሰሉት ቅርጽ እና መልክ ይዛ እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ መሆኗ ቀርቶ እንተ ታሕተ ኩሉ መንግሥታት፣ ፓርቲያት ፣ ብሔር ወጎሣ ወመማክርት እንድትሆን የሚፈልጉትን ሁሉ ነፍሴ አጥብቃ ትጸየፋለች፣ በሚቻለኝም ሁሉ እንደ አባቶቼ ይህን እቃወመዋለሁ። እንዲህ እንዲሆን የሚመኝ የሚሠራ ካለም ክርስቶስን ረዳቴ እና ጌታየ አድርጌ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሞንን እንደረገመው እረግመዋለሁ፣ ከኅብረቱ እንደለየውም ቢያንስ ራሴን ከእንዲህ ያለው እለያለሁ። የእኔ ጥያቄ ለሲኖዶስ፦ እኔ ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የመብት ጥያቄ የለኝም። ቅዱስ ሲኖዶስ የታዛዦች የአገልጋዮች ጉባኤ እንጂ የባላ ሥልጣናት ምክር ቤት አይደለምና። እኔ ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የአካባቢ፣ የጎሳ፣ የቋንቋ፣ ... የመሳሰሉት የውክልና ጥያቄም የለኝም። የሰማያውያን የመላእክት ወንድሞች የሆኑ ይህን ዐለም የካዱ አባቶች ጉባኤ ነውና። ቅዱስ ሲኖዶስን የምጠይቀው የእገሌ ይሾም የእገሌ አይሾም ጥያቄም የለኝም። ጥያቂዬ የሕግ እና የሥርዓት እንጂ የመብት እና የፖለቲካ አይደለምና። ቅዱስ ሲኖዶስ አማኞች እንደ ፓርቲ ያቋቋሙት በፈለጉ ጊዜ ሕጉን ቀይረው ዘመን የወለደውን ንጉሥ የወደደውን አስመስለው የሚሠሩት ተራ ተቋም እንዳልሆነ ስማር ኖሪያለሁ፣ በዐለም ባሉት ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉም እንዲህ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ አያለሁምና ምንም ዐይነት የመብት ጥያቄ የለኝም። የመብት ጥያቄ ያለው ክርስቲያን ሆኖ ሊኖር የሚችልም የለምና። የእኔ ጥያቄ መዳኑ በቤተ ክርስቲያን ሊፈጸምለት እንደሚሻ አንድ ኃጢአተኛ እና ደካማ ሲኖዶሴ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኔም ቤተ ክርስቲያን ሆና ማየት ብቻ ነው። ቤተ ክርስቲያንን መገለጫዋን ቅዱስ ሲኖዶስን በሌላው እንዳደረጉት ኢትዮጵያን ይምሰል በሚል ሽፋን ምክር ቤት ይምስል፣ የጎሳ ውክልና ምጥጥን ስሌት ይጠቀም የሚሉትን የምቃወመው ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን የልጅነት ድምፄን፣ ክርስቲያናዊ ግዴታዬን ለመወጣት ብቻ ነው። መብት በሚል አደገኛ የፖለቲካ ቃል በር አስከፍቶ ሲኖዶስን የጎሳ ምክር ቤት፣ ቤተ ክርስቲያንም የድኅነት ቤት የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ሐመረ ኖኅ መሆኗን አስጥሎ ጥቅመ ሰናዖር፣ ሐይመተ ፈርዖን ሆና እንድትቆጠር እና ራሷ ከሆነው ከጌታ ከክርስቶስ ከብልቶቿ ከንጹሐን ምእመናን ለመለየት የሚደረገውን ጥረት የምቃወመው ሊቀርብ የሚገባው ጥያቄ የሕግ እና የሥርዓት እንጂ የመብት እና የፖለቲካ አይደለም ብዬ ስለማምን ነው። ባለፈው ጊዜ በሻሸመኔ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የታሠሩ የተገርፉ እና አሁንም የሚታሠሩ፣ ቤተ ክርስቲያናቸው እስካሁን የተዘጋባቸው፣ በአዲስ አበባ እንኳ ከሥራቸው ተፈናቅለው በደስታ የተቀበሉት ጥያቄያቸው የድኅነት የሕግ የሥርዓት ይከበር ጥያቄ ስለሆነ እንጂ የመብትማ ቢሆን እንዲህ አይሆንም ነበር። እነዚህ ሁሉ ጥያቄያቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን ከወንበዴዎች፣ በጎቹንም ከተኩላ ጠብቃችሁ አድኑን የሚል ትሑት እና የመጨረሻ አነሥተኛ ጥያቄ ነው። የእኔም ጥያቄ ድኅነት ፈለገው የመጡ ምእመናን የጌታን ደም በቁርባን ሰጥተው በማዳን ፈንታ የምእመናን ደም ላፈሰሱ፣ በልተው ላልጠገቡ ለተራቡ ተኩላዎች ሰጥታችሁ አታስበሉን፣ ይልቁንም ድኅነታቸውን ሽተው ለሚያድኑን እረኞች አብቁን የሚል ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ ሲኖዶሱ ሲኖዶስ አይደለም ያሰኝና ብዙዎችን ሊያስወጣ፣ ምእመናን ሊከፋፍል፣ ... ሌላም ሌላም ችግር ሊያስከትል ስለሚችል የእነዚያ ሰዎች የድኅነት ጥያቄ የእኔም ልባዊ ጥያቄ ነው። አባቶቼ የምታመልኩት የምታገለግሉት፣ እኔም ኃጢአተኛው እና ደካማው የማመልከው ላገለግለውም የምመኘው ሕያው እግዚአብሔር በሚያውቀው ጥያቄዬ አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትም ሆነ ማንኛውም ነገር በሕግ እና በሥርዓት ፣ ቀኖናውን መሠረት ባደረገ ለማንም በማያዘነብል፣ ለምእመናን ድኅነት እና ለቤተ ክርስቲያን እድገት እንጂ ለፓርቲዎችና እና ለፖለቲከኞች መሣሪያ ባልሆነ ግልጽ እና ሁሉም ሊያውቀው በሚችል በሲኖዶስ በጸደቀ የምርጫ መመሪያ እና ባለማድላት በተመሰከረላቸው አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሲፈጸም ሕግ ሥርዓት ሲተገበር የማየት የልጅነት ጥያቄ ብቻ ነው። በእኛ ዘመን ለምን ሕግ ይወጣል? ቀኖናስ ለምን ይጠበቃል የሚል ድምጽ ለሚሰሙት እንዴት ይረብሻል በእውነት። ይህ ድምፅ ይሰማል የሚል እምነት ባይኖረኝም መረበሹን አለመናገር ግን ድምፃቸውን እንደ አማራጭ ማስቆጠር መስሎ ስለተሰማኝ ከፊል የተስማማሁ ስለመሰለኝ ነው ያነሣሁት እንጂ ይደረጋል ብዬ አላስብም። ጥያቄዬ ቅዱስ ሲኖዶስ በዓላማው በክብሩ ጸንቶ እንዲኖር ቅዱስ ጳውሎስ የሚያውኳችሁ ይቆረጡ እንዳለው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመጣል እና ቤተ ክርስቲያንን ለማወክ ያሰፈሰፉ ሁሉ በሕግ ተቆርጠው እንዲወድቁ ብቻ ነው። ጥያቄዬ ቤተ ክርስቲያንን ተሳታፊዎች የሚዘውሯት ተራ ምድራዊ ተቋም ሳትሆን ሰማያዊ መልኳን ይዛ እንድትጸና ሕግ ሥርዓቷ ይከበር የሚል ብቻ ነው። ጥያቄዬ አሳሳቾች በሚፈጽሙት ችግር ምእመናን እንዳይረበሹ ለድኅነታቸውም መሰናክል እንዳይበዛ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይከበር የሚል የልጅነት ጥያቄ ብቻ ነው። ይህን መጥየቅ ካልቻልኩማ ምኑን ልጇ ሆንኩት፣ ስማረው የኖሩክትስ ምን ይጠቅመኛል። ለድኅነት ካልሆነስ ምን ይረዳኛል። ቤተ ክርስቲያኔ ቤተ ክርስቲያን ካልሆነችስ ምን ይጠቅመኛል። ፓርቲማ መች ቸገረኝ፣ ሕግ ጥሰት እና ድፈረትማ በዓለም ሁሉ ሞልቶ የለ። ከዚህ ሁሉ የጥፋት ባሕር ቀዝፋ የምታሽግር መርከቤን ሽንቁረው ውኃውን አስገብትው አብረን እናስጥምህ ሲሉኝ ዝም ካልኩኝማ ምኑን ሰው ሆንኩ? የተርሴስ ተጓዦች የተጨነቁትን ያህል ካልተጨነቅሁ ምን እጠቅማለሁ? እነሱ እንዳደረጉት ለመርከቢቱ የከበደውን ነገር ባላውቀው እንኳ ሸክም ካልቀነስኩ ምን ረባሁ? የተኛውን ካልቀሰቀስኩ ወደ አምላክህ ጩህ ካላልኩ ከእነዚያ ተጓዦች የማንስ እጅግ ምስኪን አልሆንምን? ስለዚህ የእኔ ጥያቄ የድኅነት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም። የመብት ጠያቂዎችንም መስማት አልፈልግም። እርሱ ለፖለቲካ ፣ ለድርጅት፣ ለዚህ ዓለም ሰው ሰራሽ ተቋም እንጂ እግዚአብሔር ለመሠረታት፣ ፍጽምት እና አለነውር እንድትሆን ላደረጋት ቤተ ክርስቲያን የመብት ጥያቄ የለኝም፣ ሊኖረኝም አይችልም። የእኔ ጥያቄ እንተ ላዕኩሉን እንተ ታሕተ ኩሉ ሊያደርጉ የመጡትን በሕግ በሥርዓት ቆርጣችሁ፣ መርከባችን ከሚያናውጥ ማዕበል ቀዝፋችሁ አድኑን የሚል የድኅነት የሕግ የሥርዓት
11 15971Loading...
34
ከሲኖዶስ የምጠብቀው እና የምጠይቀው አቤቱ ጌታዬ እና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሳላውቅ በድፍረት አውቄ በትዕቢት ከመናገር እንድትጠብቀኝ እለምንሃለሁ። ጌታዬ መድኃኒቴ ኢይሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ በደምህ ከመሠርትሃት በኪዳንህም ካቆምካት፣ አካልህ ከሆነች፣ ብልት አድርጋ ከምትሰበስበን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት ከሚያወጣ ድፍረት፣ ምን አገባኝም ከሚል ፍርኅት እንድትጠብቀኝ እኔ ከሁሉ የማንሰው ኃጢአተኛ ልጅህ እለምንሃለሁ። ጌታዬ ሆይ ከእንግዲህስ ወዳጆቼ እንጂ ባሪያዎቼ አልላችሁም ብለህ ባከበርሃቸው፣ ምሥጢራትህንም ሁሉ በገለጽህላቸው ፍጹማን ወዳጆችህ፣ አንተ ታማኝ መልካም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ብለህ በምታከብራቸው ትጉኃን አገልጋዮችህ፣ ለባሕርይህ ለማይስማማ ሞት ራስህን አሳልፈህ በሰጠህላቸው ንጹሐን ምእመናን በጎችህ ብለህ እንኳን የአባቶቼን የየትኛውንም ሰው ኅሊና ሊጎዳ ከሚችል ክፉ ሐሳብም ሆነ ንግግር ትጠበቀኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። ጌታ ሆይ ከግብዝነት፣ ከአድርባይነት እና ከሚታወቅም ከማይታወቅም ጥፋት እንድትጠብቀን በጎውን እና እውነተኛውን ነገር ብቻም ለመናገር ከአንተ ውጭ እንኳን እኛ የበቁትም ቢሆኑ አይቻላቸውምና ስለቅዱሳንህ ሁሉ ይልቁንም የባሕርያችን መመኪያ የደኅንነታችን ዘውድ ስለምትሆን ንጽሕት እናትህ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ በመልካሙ መንገድ ብቻ ምራን፣ እኔንም ከዚህ መንገድ አታውጣኝ አሜን። ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ፤ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሜን። አንዳንድ ሰዎች ስለሲኖዶስ በጻፍናቸው ተነሥተው ጉዳዩን ለመጠምዘዝ ከተቻለም መለያየት እና ጸብ በመፍጠር የሚፈልጉትን ለማሳካት እንደሚጥሩ ስለተሰማኝ፣ በቅንነት ሆነው ጥያቄያችንም የመብት ጥያቄ የመሰላቸው እና እራሳቸውንም የሆነ አካባቢ ተወካይ አድርገው የመብት ጥያቄ ጠያቂ እና አስተባባሪ ሆነው ስላየሁ የእኔ እና እኔንም የሚመስሉ ወንድሞቼ ጥያቄ ምን ዓይነት ጥያቄ እንደሆነ ስለቅዱስ ሲኖዶስ ያለኝን እምነት በማስቀደም በመግለጽ ጥያቄዬን በድጋሜ አቀርባለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ ፦ ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት አስፋፊዎች የመላእክት ወንድሞች የሰማያዊ ዜጎች አንድነት እንጂ የከርስቲያኖች የየአካባቢው ተወካዮች የሚሰበስቡበት ምክር ቤት እንዳለሆነ በደንብ አዋቃለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ ከብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመጡ አባቶች ቢገኙበትም የየቋንቋቸው ወኪሎች ስብስብ እንዳልሆነም በደንብ አውቃለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ ከየአካባቢው ተወልደው አድገው በመጡ አባቶች የተመላ ቢሆንም የየተገኙበትና የየመጡበት አካባቢ ተወካዮች እና የወንበር ምድብ ቆጣሪዎች ስብስብ እንዳልሆነና ሊሆንም እንደማይችል፣ እንደማይገባውም በደንብ አውቃለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ በሰማይ ያለች የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ሆነው ያገለግሉ ዘንድ የሚላኩ የእግዚአብሔር አምባሳደሮች ስብስብ እና ለላካቸው ለእግዚአብሔር መንግሥት ፍላጎት ብቻ የሚሠሩ በተፈጥሮ ከሰው ወገን ቢሆኑም በክህነት ምክንያት ከመላእክት ወገን የሆኑ እና እንደ መላእክትም ለሁሉም እኩል ቅርብ የሆኑ ሊሆኑም የሚገባቸው አባቶች ስብስብ እንደሆነ አምናለሁ። ከዚህም የተነሣ ከመካከላቸው ከላከው ከእግዚአብሔር እና ከሾመችው ከአካሉ ከቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ወጥቶ የራሱን ፈቃድ የሚከተል፣ የምድራዊ መንግሥታትን ፈቃድ ለመፈጸም እና ለማስፈጸም የሚሠራ አካል ቢገኝ ከማኅበረ መላእክት ወገን ሳለ የራሱን ሌላ መንግሥት ማቋቋም ከፈለገ ከዲያብሎስ እና እርሱን እሺ በጄ ካሉት ከሠራዊቱ የሚመደብ እንደሆነ አምናለሁ፤ አውቃለሁም። በሐዋርያት መዓርግ ተሹሞና እና ተሰይሞ በጉባኤያቸውም ተገኝቶ እውጭ ላሉት ምሥጢር የሚሰጥ፣ ከእነርሱም ጋር የጥቅም ውል ያለው ቢኖር አልደነቅም። እንዲህ ያለው ከሐዋርያት ሲኖዶስ እያለ ከአይሁድ ጋር የጥቅም ውል የተዋዋለ እና ከጉባኤያቸውም የተሰናበተውን ይሁዳን እንደሚመስል እና በእርሱ ምክንያትም ሌሎች እንደማይተቹ በደንብ ተምሬያለሁና። ረቂቅ ባሕርይ በነበረው በሳጥናኤል ምትክ ከመሬት አፈር የተፈጥረው አዳም እንደተተካ፤ በይሁዳም ምትክ ማትያስ በሐዋርያት እጩነት ቀርቦ በዕጣ እንደገባ ከአባቶቼ ተምሬያለሁ፣ አዋቃለሁምና የሚወጣ ቢኖር አልደነግጥም አልረበሽምም። እንዲህ ባላው ሰው ምክን ያት ቤተ ክርስቲያን ስሟ እንደማይጎድፍ ክብሯ እንደማይቀንስ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ አስቀድሞ አለማስገባት እየተቻለው ለይሁዳ እድሉን በመስጠት አስተምሮናልና። ቅዱስ ሲኖዶስ ለእጃችሁ በትር አትያዙ የተባሉ ሐዋርያት ወራሽ እንጂ ሰይፍ፣ ጎራዴና እና ዱላ ይዘው ክርስቶስን ለመያዝ የመጡ፣ ዳዊት በመዝሙሩ አገቱኒ ከለባት ያላቸው ለምድራዊ ገዥዎች ፍላጎት የሚጮሁ የዚያ ዘመን አይሁድ ወራሽ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ አምናለሁም። ቅዱስ ሲኖዶስ በዐመጻው ምክንያት መልአከ እግዚአብሔር በሰይፍ እጁን የቀጣውን ታውፋንያን ንስሐውን ተቀብሎ በተአምራት እጁን መልሶ ዐመጸኛውንም ወደ ትሕትና እና መታዘዝ የሚመልሱ የቅዱስ ጴጥሮስ ልጆች ስብስብ እንጂ እንደ አውሳብዮስ እና ጓደኞቹ የመንግሥታትን ጉልበት ተጠቅሞ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍሉ ሰዎች ስብስብ እንዳለሆነ አውቃለሁ፣ እንዲህ ሆኖ እንዲኖርም እጠብቃለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት እንደ ጠቢቡ ሰሎሞን ረቂቅ ፍርድ ፈርዶ ሕዝቡን የእግዚአብሔርን መጋቢነት የሲኖዶስን መንፈስንቅዱሳዊነት ሊያሳይ እንደሚተጋ እንጂ እንደ ኢሳይያስ የንጉሥ ድምፅ ፈርቶ እኔ ምን አገባኝ ብሎ ቤተ ክርስቲያንን ለዖዝያን ፍላጎት አሳልፎ በመስጠት ለምጻም የሆኑ ሰዎች ስብስብ እንዳልሆነ ፣ እንደማይሆን፣ ሊሆንም እንደማይገባው አምናለሁ፤ እጠብቃለሁም። ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ተጭንቆና ተጠብቦ እንደ ጳውሎስ እስከ ዕልዋሪቆን እንደ በረተሎሜዎስም በላእተ ሰብእ ያሉበት ድረስ ሔዶ ለመስተማር የሚያስቡ አባቶች ስብስብ እንጂ እንደ አካባቢ የልማት ድርጅቶች በየአካባቢው ሕንፃ ለመሥራት ግንብ ለማቆም የሚሯሯጡ ዉሉደ ባቤል ደቂቀ ናምሩድ ስብስብ እንዳልሆነ አምናለሁ፣ ተስፋም አደርጋለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ እቄሣር ግቢ ቢገባ እዚያ ያሉትን ለውጦ እንደ ጳውሎስ ከቄሳር ቤት የሆኑት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል የሚሉ ጥቡዓን ስብስብ እንጂ እንደ ዴማስ በከተማ ውበት በቤተ መንግሥት ግርማ ተሰልቦ አላማውን ለውጦ የሚኖር ከተሜዎች ስብስብ እንዳለሆነ እረዳለሁ። ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ዲዮስቆሮስ ጥርሱ እስኪረግፍ ቢደበደብ እንደ አትናቴዎስ አምስት ጊዜ ቢሰደድ በትዕግሥት መከራውን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያንን የሚያሻግሩ ፣ ዐለም ትቷችኋል ቢባሉ ልክ እነደ አትናቴዎስ እኔም ዐለምን አልፈልገውም የሚሉ ልበ ሙሉዎች ስብስብ እንጂ በቤተ መንግሥት ማዕድ እና ሺንገላ ልባቸው የሚማልል አባቶች ስብስብ እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ እጠብቃለሁም። ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ሲሞን ገንዘባቸውን ይዘው እናንተ የያዛችሁትን መዓርግ ልያዝ፣ ጓደኞቼ ከደረሱበት ልድረስ ብለው በእኔ ጊዜ ነው ወይ መመሪያ የሚወጣው እያሉ ዘመድ አዝማድ ስጦታ አስይዘው በመላክ፣ ውለታ ቆጥረው በማስታወስ የሚወተውቱ ሲሞናዊያንን ገንዘብህ ይጥፋ፣ ሀሳብህም አይፈጸም እያለ እነርሱን ትቶ ማትያስን በይሁዳ ፈንታ በተካበት መንገድ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሚሆኑትን የሚሾም ወራሴ ጰጥሮስ ወሐዋርያት እንደሆነ አውቃለሁ አምናለሁም።
8 01269Loading...
35
On Marriage and Family Life St john chrysostom
8 36485Loading...
36
የቃልኪዳን ሀገር #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
10 41042Loading...
37
The Theology of Illness
8 63873Loading...
‹‹በዚያን ጊዜ ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፮) በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት በዓለ ጰራቅሊጦስ በዋለ ማግስት ጀምሮ የሚጾመው ጾም ጾመ ሐዋርያት ተብሎ ይጠራል። የዚህ ጾም የመግቢያው ቀን በየዓመቱ የሚለያይ ሲሆን “ቢፈጥን ከግንቦት ፲፮ አይቀድምም፤ ቢዘገይ ደግሞ ከሰኔ ፳ አያልፍም” ብለው ሊቃውንት አባቶቻችን ያስተምራሉ። ይህ ጾም የሚፈታበት ቀን ግን እንደ መግቢያው የማይቀያየር ሲሆን ሁልጊዜ ሐምሌ አምስት በቅዱሳን ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓል ቀን ጾሙ ይጠናቀቃል። በዚህ ጾም የሐዋርያት ክብራቸው፣ ቅድስናቸው እንዲሁም አገልግሎታቸው ይታሰባል፡፡ ሁሉን ትተው ጌታን መከተላቸው፣ ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውና ስለ ቅዱስ ስሙ በጽናትና በጥብዐት መከራ መቀበላቸው ይታወሳል፡፡ ስለ ተሰጣቸው የወንጌል አደራ እስከ ሞት ድረስ መታመናቸው ይሰበካል። ቅዱሳን ሐዋርያት ይህን ጾም ሁለት ነገሮችን መሠረት በማድረግ ጾመውታል። የመጀመሪያው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወላቸውን ጾምን የአገልግሎት መጀመሪያ የማድረግ አርአያነት ነው። ይኸውም ክብር ይግባውና አምላካችን ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ አብ በሰማይ ተናግሮ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ ክብሩ፣ አምላክነቱ የባሕርይ ልጅነቱ የተገለጠ ሲሆን ከተጠመቀ በኋላ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሄድ ፵ ቀን እና ፵ ሌሊት ጾሟል። (ማቴ.፫ እና ፬) ቅዱሳን ሐዋርያትም ይህን ጌታችን ያደረገውን ተግባር አርአያ በማድረግ በበዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ፣ ኃይልን ተቀብለው የጸጋ ልጅነታቸው ሲገለጥ ለአገልግሎት ከኢየሩሳሌም ከመውጣታቸው በፊት ጾምን የአገልግሎታቸው መጀመሪያ በማድረግ ጾመዋል። ይህም አርአያነት ቀጥሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እና በርናባስ ለስብከት አገልግሎት በተለዩ/በተመረጡ ጊዜም ጾመዋል። (ሐዋ.፲፫፥፪-፫) ስለዚህ ጾምን የአገልግሎት መጀመሪያ ማድረግ የመጀመሪያው መሠረት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀራጭ በነበረው በማቴዎስ ቤት ተቀምጦ ሳለ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ‹‹እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድን ነው?›› ብለው ለጠየቁት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ነው። ይኽውም ‹‹ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ይጾማሉ›› ብሎ የመለሰው መልስ በሐዋርያት በተግባር መፈጸሙን እንድረዳ ነው። ይህም ቃል ይፈጸም ዘንድ ሚዜዎች የተባሉ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙሽራው ክርስቶስ ከእነርሱ በተለየ/ባረገ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ጾመውታል።(ማቴ.፱፥፲፴-፲፮) ዛሬ ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች ከቅዱሳን ሐዋርያት በረከት እንሳተፍ ዘንድ ይህን ቅዱስ ጾም እንጾማለን። እነርሱ ጾመው በጀመሩት አገልግሎት ዓለምን በስብከተ ወንጌል ጨው ሆነው እንዳጣፈጡ በክህነት የሚያገልግሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክላቸው፣ ይቀበልላቸው፣ ያሳካላቸው ዘንድ በትጋት ሆነው ይጾሙታል። ይህ ሲባል ግን ምንም እንኳን ይህን ትልቅ በረከት የሚያሰጥ ጾም ‹‹የቄስ ጾም›› እያሉ ራሳቸውን የሚያስቱ ቢኖሩም ቤተ ክርስቲያናችን ግን በቀኖና ወስና የዐዋጅ ጾም ብላዋለችና ሁላችንም ክርስቲያኖች ከሰባት ዓመት ጀምሮ ልንጾመው ይገባል። (ፍት.ነገ.፲፭፣ገጽ.፭፻፷፮) በዚህ ጾም ቅዱሳን ሐዋርያት ራሳቸውን ለአገልግሎት እንዳዘጋጁ፣ እንደጸለዩ እና አገልግሎታቸውንም እንደፈጸሙ እኛም በቀጣይ ልንጀምረው ያሰብነው በልቦናችን ያለው መልካም አሳብ ይፈጸም ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመንን እንጾመዋለን። የእነርሱን አገልግሎት የባረከ አምላክ የእኛንም አገልግሎታችንን፣ ሥራችንን፣ ትምህርታችንን፣ ትዳራችንን በአጠቃላይ ሕይወታችንን እንዲባርክልን እየተማጸንን እንጾመዋለን። የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤት፣ በረከት፣ ድል የምትነሣ፣ ጥርጥር ነቅዕ የሌለባት ሃይማኖታቸው ከሁላችን ጋር ትሁን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር! Mahebere kidusan
إظهار الكل...
🙏 17🕊 12👍 4
በዚህ ስብከት ልባቸው ተነካ፤ ጴጥሮስንና ሌሎእንም ‹‹ምን እናድርግ›› አሏቸው፡፡ ጴጥሮስም ‹‹ንስሐ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይሰረይላችሁ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ›› አላቸው፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፭-፴፰) ቋንቋ የሚያናግረውን፣ በጥበብና በዕውቀት የሚሞላውን፣ በሀብቱ ስቦ በረድኤት አቅርቦ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ የኃጢአት ስርየትም የሚገኝበትን በክርስቶስ አምኖ በመጠመቅ የሚገኘውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንዲቀበሉ መከራቸው፡፡ ቃሉንም የሰሙ፣ ሰምተውም ያመኑ ብዙ ነፍሳት ተጠመቁ፤ ቁጥራቸውም ሦስት ሺህ ያህል ነበሩ፡፡ እናም በዓለ ጰራቅሊጦስ እያልን ከዕርገት በዐሥረኛው ቀን፣ ከትንሣኤው በሃምሳኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ በዓል መሠረቱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሰማያት የወረደበት፣ ለጌታ ቤተ ሰቦች የተገለጠበትና በእያንዳንዳቸው ላይ ያደረበት፣ በዚህም ሕይወት የሚሰጠውን አምላካዊ ዕውቀት ያገኙበት፣ ዓለምን ተዘዋውረው ያስተምሩበትና ተአምራት መንክራት ያድርጉ ዘንድ ሕዝቡንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚጠሩበትን የዓለም ቋንቋ የገለጠበት፣ በዚህም የመንፈስ ቅዱስን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት ልባቸው የተነካ ብዙዎች በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የተጠመቁበትና ወደ በረቱ የተሰበሰቡበት ድንቅ የተአምራትና የምሥጢር ቀን በመሆኑ እንድናከብረው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡ መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት ‹‹በበዓለ ሃምሳ ሥራ አትሥሩ፤ ነገረ ክርስቶስን ባመኑ ምእመናን ላይ የወረደ መንፈስ ቅዱስ ተገልጦበታልና›› ይላል፡፡ (ፍት.ነገ.አን.፲፱፥፯፻፵) እናም እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ታላቅ የበረከት በዓል፣ ይህንን የተቀደሰ ቀን ስናከብረው እንዴት ይሆን? በወይን ጠጅ ሰክረን ወይስ ኃጢአታችን ይሰረይልን ዘንድ ንስሓ ገብተን ወይስ በሌላ ሁኔታ? ጰራቅሊጦስ ነፍስና ሥጋን የሚያጸና፣ ለንጹሐን የክብር አክሊልና ሞገስ ነው፤ ይህን የእውነት መንፈስ በእኛ ላይ ያድር ዘንድ፣ ስብራታችን እንዲጠገን፣ ጎደሏችን እንዲሞላ፣ ድንቁርናችንን እንዲያስወግድ፣ ከኀዘናችን እንዲያጽናናን፣ እንለምነዋለን ወይስ በምግበ ሥጋ ተጠምደን ጨለማውን የማያርቀውን ዕውቀት የማይገልጸውን፣ ኀዘንና ትካዜ የሚጨምረውን የበዓል አከባበር እናከብራለን? ራሳችንን እንድናይ፣ ንስሐን የሚቀበል፣ ኃጢአትንም ይቅር የሚል፣ የሚያነጻ መንፈስ (ጰራቅሊጦስ) በእውነት ይርዳን! ተቀድቶ የማያልቅ የዕውቀት መጠጥ ነው፤ ምሥጢር ገላጭ በመሁኑ ምሥጢሩን እንዲገልጽልን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ያድር ዘንድ አእምሮውን፣ ማስተዋሉን እንዲሰጠን መልካም ፈቃዱ ይሁን፤ አሜን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
إظهار الكل...
🙏 45 25👍 8🕊 3
"ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል" (ዮሐ.፲፬፥፲፮) እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ! የቤዛነት ሥራውን ከፈጸመ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲያርግ ለሐዋርያት የሰጣቸው ተስፋ አጽናኝና የእውነት መንፈስ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን አብ እንደሚልክላቸው፣ እርሱም አጽናኝ የሆነ ጰራቅሊጦስ እንደሆነ ለዘለዓለሙም ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ነግሯቸው ነበር፡፡ ጌታችን እንደተናገረውም በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ባረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሣ ደግሞ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ‹‹ወአነ እስእሎ ለአብ ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ ካልአ ዘይሄሉ ምስሌክሙ ለዓለም፤ እኔም አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል›› እንዲል፡፡ (ዮሐ.፲፬፥፲፮) ይህንንም መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስ እያልን እናከብረዋለን፤ ከጌታ ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፡፡ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ወይም ለመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ሌላኛው ስሙ እንደሆነ ከርእሳችን እንረዳለን፡፡‹‹ጰራቅሊጦስ መንፈሰ አብ ወወልድ ስቡሕ፤ ጰራቅሊጦስ የተመሰገነ የአብና የወልድ መንፈስ ነው›› በማለት አምላክነቱን በአንድነት በሦስትነት ጸንቶ የሚኖር እውነተኛ አምላክ፣ ከአብ የሠረጸ የእውነት መንፈስ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ (ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ) ጰራቅሊጦስ ማለት ‹‹መንፈስ ቅዱስ፣ አጽናኝ፣ አስታራቂ፣ አሳምሮ የሚያናግር ማለት ነው›› ይላል፡፡ (ሕያው ልሳን) አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ‹‹ጰራቅሊጦስ›› ማለት ‹‹ናዛዚ፣ መጽንዒ፣ መስተፍስሒ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በዓለ ሃምሳ፣ የትንሣኤ ሃምሳኛ፣ የዕርገት ዐሥረኛ፣ እሑድ ቀን የሚውል ወዘተ…›› እያሉ ይተረጉሙታል፡፡ (ገጽ ፱፻፯) በጥቅሉ ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ያዘኑትን የሚያጽናና፣ የራቁትን የሚያቀርብ፣ የተሰወረውን የሚገልጥ፣ የረቀቀውን የሚያጎላ፣ የተከፉትን የሚያስደስት፣ ለመምህራን አንደበት የሆነ መጽንዒ፣ የሚያጸና፣ መንጽሒ የሚያነጻ ኃጢአትን ይቅር የሚል የሚደመስስ የእውነት መንፈስ፣ የእውነት አምላክ ነው፡፡ ጌታችን እርሱን እስኪልክላቸው ኃይልን ብርታትን እስኪላበሱ አላዋቂዎችን አዋቂ የሚያደርግ ከሣቴ ምሥጢር፣ ፈሪዎችን ደፋር (ጥቡዓን) የሚያድርጋቸው፣ በአሕዛብ በዓላውያን ፊት ያለ ኀፍረት፣ ያለ ፍርሃት እንዲመሰክሩ፣ በእሳቱ፣ በስለቱ እንዳይሸማቀቁ የሚያደርጋቸውን የእውነት መንፈስ እንደሚልክላቸውና እርሱም ለዘለዓለሙ አብሯቸው እንደሚኖር ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ እንዲህም ብሏቸዋልና፤ ‹‹ዘኢይክል ዓለም ነሢኦቶ፤ ዓለም እኔን ለሕማም ለሞት አሳልፎ እንዲሰጠኝ ለሕማም ለሞት አሳልፎ ሊሰጠው የማይቻለው፤ እስመ ኢይሬእዮ ወኢየአምሮ፤ አያየውም፤ አያውቀውምና፤ ወአንትሙሰ ተአምርዎ፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ አድሮባችሁ ይኖራልና በውስጣችሁም ይኖራልና፡፡›› አድሮባቸው የሚኖረውን፣ ሕማመ ሥጋ፣ ድካመ ሥጋን የሚያርቅላቸውን፣ የምሥራቹን ለዓለም ሁሉ የሚያደርሱበትን ኃይል ጸወን የሚሆናቸውን እውነተኛ የሆነ የራሱንና የአባቱን መንፈስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን፣ ባረገ በዐሥረኛው ቀን በዕለተ እሑድ ጰራቅሊጦስ የተባለውን የእውነት መንፈስ ላከላቸው፡፡ እርሱ የእውነት መንፈስ ነው አለ፤ የሐሰት መንፈስ አለና ሲለይ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በ፻፳ው ቤተ ሰብ ላይ እንደወረደ፡- ‹‹እንዘ ሀለዉ ኩሎሙ ኅቡረ አሀተኔ መጽአ ግብተ እምሰማይ ድምፅ ከመ ድምፀ ነፋሰ ዓውሎ፤በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጉዶ ተሰማ …›› (የሐዋ.ሥራ ፪፥፪) ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስትና ሰባ ሁለቱ አርድእት መቶ ሃያው ቤተ ሰብ በኅብረት በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም፤ እናንተ ግን ከሰማይ ኃይል እስክትለብሱ ማለትም ሰማያዊ ሀብትን፣ ሰማያዊ ዕውቀትን፣ ሰማያዊ ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ›› ብሏቸው ነበርና በኅብረት ይኖሩና፣ በኅብረት ይጸልዩ፣ የተስፋውንም ቃል ይጠብቁ ነበርና ድንገት በተሰበሰቡበት እንደ ዓውሎ ነፋስ ያለ ታላቅ ድምፅ አሰምቶ የተቀመጡበትን ቤት ሞላው፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፪) ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት መስሎም ታያቸው፤ በሁላቸውም ላይ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፡፡ በዚህም ኃይል የሚሆናቸውን፣ ሀብት የሚሆናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡ ሁሉም በየራስ በየራሳቸው ሰባ ሁለት ቋንቋ መናገር ጀመሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያትና በሌሎቹ ላይ እንደ ነፋሰ ዓውሎ ሆኖ ነው የወረደው፡፡ ምክንያቱም ነፋስ ረቂቅ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ረቂቂ ነውና፤ ነፋስ ኃያል ነው፤ ፍሬውን ከገለባው ይለያል፤ መንፈስ ቅዱስም ጻድቃንን ከኃጥአን ይለያልና፡፡ ነፋስ በምልዓት ሳለ አይታይም፤ አይታወቅም፤ ነገር ግን የሚታወቀው ባሕር ሲያናውጥ፣ ዛፍ ሰያወዛወዝ፣ ቅጠሉን ሲያረግፈው፣ አቧራውን ሲያስነሣው በሥራው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም በምልአት ሳለ አይታወቅም፤ ነገር ግን ቋንቋ ሲያናግር፣ ምሥጢር ሲያስተረጉም ይታያልና፡፡ ነፋስ መዓዛ ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስም መዓዛ ጸጋን ያመጣልና በነፋስ ተመስሎ ወርዷል፡፡ ሰባ ሁለት ቋንቋ ሲናገሩም ከልዩ ልዩ ቦታ የተሰበሰቡና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ በዚያ (በኢየሩሳሌም) ነበሩና አደነቁ፤አንዳንዶቹ እንዲያውም ግራ ተጋብተው ‹‹እነዚህ ሰዎች ሁላቸውም የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንደምን እንሰማቸዋለን›› እያሉ ያደንቁ ነበር፤ አንዳንዶቹ ግን ይስቁባቸው ነበር፡፡ምክንያቱም ከከተማ የመጡ እኩያን አይሁድ ሰቃልያነ አምላክ ናቸውና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ላለማድነቅ በሐዋርያት ላይ ሳቁባቸው፤ ‹‹እሊህ ያልፈላ ጉሽ ጠጅ ጠጥተው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› ብለው ተሳለቁ፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፭-፲፫) እንደ እውነቱ ከሆነ ያልፈላ ጉሽ የወይን ጠጅ የጠጣ፣ ጠጥቶም የሰከረ ሰው፣ እንኳን የማያውቀውን ቋንቋ ሊናገር ቀርቶ የሚያውቀውንም በተናገረው አይናገረም፤ ስካር አንደበትን ያስራል፤ ትንፋሽን ያሳጥራል እንጂ አዲስ ቋንቋ፣ ሁላቸውም የሚሰሙት የሀገራቸውን ቋንቋ ሊናገሩ አይችሉም ነበር፡፡ አይሁድ ግን ክፉዎች ነበሩና እውነቱን መቀበል አይሹም፡፡ የዘመናችን መናፍቃንም ወንጌል ተከድኖባቸው፣ እውነቱ ተሸፍኖባቸው፣ በዕውቀት የተራቀቁትን፣ መንፈስ ቅዱስ ተመልተው ምሥጢር የሚያመሠጥሩትን፣ ክብሩን የሚገልጡትን በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ መምህራንን፣ ሊቃውንትን እንደሚያቃልሉትና እንደሚያሾፉ ዓይነት ማለት ነው፡፡ ግን ጊዜው የስካር አይደለም፤ ምክንያቱ ገና ንጋት (ነግህ) ነውና፤ ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረው ቢፈጸም ነው እንጂ፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ መንፈሴን አሳድርበታለሁ›› ያለው ጌታ አስቀድሞ በነቢዩ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነርሱ ላይ ስለ መውረዱ አዲስ ዕውቀትን እንደገለጠላቸው ነገራቸው፤ ገሠጻቸው፤ ስለ ጌታችን ወደዚህ ዓለም መምጣት፣ አይሁድ ግን በክፋት እንደሰቀሉት፣ እርሱ ግን በሥጋ ሞቶ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ስለ መነሣቱና ስለማረጉ ለዚህም ምስክሮቹ መሆናቸውን ጭምር ሰበከ፡፡
إظهار الكل...
👍 27 15🕊 5🙏 2
إظهار الكل...
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ Yaregal Abegaz የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስብከት Sibket Ethiopia

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ Yaregal Abegaz ። የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ስብከት በክርስቲያን ሳንድ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ኖርዌይ ፳፻፲ ዓም New Sibket ስብከት ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያ Ethiopia Orthodox #sibket

👍 24 19
#ሳታቋርጡ_ጸልዩ "ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተጠምዶ መዋል አይችልም" አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይሆን ሀሳብ ነው ፤ እጅ ሳይሆን እደ ልቦናን ማንሣት  ነው፤   አፍአዊ ሳይሆን ውስጣዊ አኳኋን ነው ።ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፤ ደረትህንም ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከሆነ ጸሎትህ ሥልጡን ነው ።     #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
إظهار الكل...
👍 145 97🥰 13🙏 7🕊 6👏 3
ቅዱስ ሚካኤል - መልአከ ምክሩ *** በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ስለሚያደርገው የምክር ጉባኤ ተጽፏል። ይህ መለኮታዊ ምክር ( the devine council) እግዚአብሔር ስለሚያደርገው እና ስለፍርዱ ከተመረጡ ቅዱሳን ጋር የሚያደርገው ነው። ይህን የሚያደርገውም ከቅዱሳንም መርጦ ላከበራቸው ያለውን ክብር ያሳይ ዘንድ ከሥልጣኑ በጸጋ እያሳተፋቸው እንጂ ከእግዚአብሔር ፍርድ እና ምክር የሚጎድል ኖሮ እነርሱ ሊሞሉለት አይደለም። የመጀመሪያው ይህን የተመረጡ ቅዱሳን ምክር የሚያሳይ ጥቅስ መዝ. 81/82 ነው፦ “እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።" ሌላኛው ደግሞ "እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል? በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው፤" የሚለው ነው። (መዝ. 89፥6-7) *** ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ምክሩ የሚባል የመላእክት አለቃ ሆኖ የዚህ መለኮታዊ ምክር አካል ስለሆነ ነው። 'ተሾመ' የሚለው ቃል ይህን መመረጥ ይገልጣል። ከሌሎች መላእክት በተለየ በዙፋን ላይ ተቀምጦ መሳሉም ለዚሁ ነው። ድንግል ማርያምም የዚህ ማኅበር አካል ነች። ቀድሞ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ሰሎሞን ለእናቱ ያለውን ክብር ይገልጥ በጎኑ ዙፋን አስቀምጦ ያማክራት ነበር። (1ኛ ነገ. 2፥19) ዳዊትም "ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ ተናግሮላታል። (መዝ. 44/45፥9) ሐዋርያትም እንዲሁ ናቸው፤ ጌታ በ12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ላይ ሲፈርዱ በዙፋን እንደሚቀመጡ መናገሩ የመለኮታዊው ምክር አካላት እንዳደረጋቸው ያሳያልና። (ማቴ. 19፥28) ይህንም ነቢዩ ዳንኤል ቀድሞ ተናግሮታል፦ “ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።” (ዳን. 7፥9) ነቢዩ 'ዙፋኖች' ያለው እግዚአብሔር ብዙ ዙፋኖች ኑረውት ሳይሆን የተመረጡ ቅዱሳን የሚሳተፉበትን ከእግዚአብሔር ፍርድ ሲወጣ ቀድመው የሚያውቁ እና በባለሟልነት የሚማልዱ የቅዱሳን ጉባኤ ክብራቸውን ለማመልከት ነው። *** በዚህ ሁሉ ታላቁ መልአክ ሚካኤል አለ! ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል! ከእግዚአብሔር የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ለጎስቋሎች ባሮችህ ለምንልን። አሜን።
إظهار الكل...
147🙏 33👍 20🥰 12🕊 1
ሃይማኖተ አበው ምሉዕ by_pdf.pdf39.42 MB
75🥰 10👍 5🙏 4
መድሎተ አሚን (አድማሱ ጀንበሬ).pdf18.52 MB
76👍 10🙏 7🥰 4
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።” (ያዕ. 4፥8) *** የመልካም ነገር ጅማሮ ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ወይስ ከሰው? የዚህ ጥያቄ መልስ ግልጽ ነው፦ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ከእግዚአብሔር ነው። ታዲያ ያዕቆብ በመልእክቱ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፤" ብሎ ሲናገር መቅረብ ከሰው የሚጀምር ይመስል የእኛን ኃላፊነት ቀድሞ መናገሩ ለምንድር ነው? ብለን እንጠይቃለን። መልሱ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔርማ ሁሉን ፈጽሞ ትቀበለው ዘንድ እየጠበቀን ነው። ከሰው በኩል ግን መቀበል ይገባል። እንዴት ነው የምንቀበለው? በእምነት፣ በንስሐ፣ ከኃጢአት ጋር ተጋድሎ በማድረግ እና በክርስቶስ ትእዛዛት ለመኖር በመጣር ነው። እነዚህ ነገሮች የጸጋ ሁሉ ምንጭ ወደሆነው እግዚአብሔር ለመቅረብ ጽኑ ፈቃዳችን በውስጥም በውጭም የምንገልጽባቸው ናቸው። እግዚአብሔር በእንዲህ ያለ ተግባር ውስጥ ሲያየን በእኛ ጥረት ሊገኝ የማይችለውን ዘላለማዊ ድኅነት ያጎናጽፈናል፤ የጸጋ አማልክት እስክንባል ደርሰን የእርሱ ጸጋ የሞላብን ያደርገናል። በእርሱ ዘንድ በባሕርዩ ያለ ቅድስናን ወደ እርሱ ቀርበን እናገኘው ዘንድ ይሰጠናል። ይህን ሁሉ የምናገኘው ከእኛ ብቃት ሳይሆን ከእሱ ጸጋ ነው፤ ነገር ግን በየጊዜው በምናደርገው የእምነት መታዘዝ እና ተጋድሎ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እና እርሱን ለመምሰል ያለነን በተግባር የተፈተነ ጽኑ ፈቃድ እንገልጣለን። *** “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ... እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።” *** (ያዕ. 4፥8-12) Bereket Azmeraw
إظهار الكل...
99👍 40🙏 5🕊 4👏 2
አንድ ወንድም ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ሄደና “እድን ዘንድ የሚረዳኝን ምክር ምከረኝ አለው፡፡ መታርዮስም “ወደ መቃብር ቦታ ሒድና ሙታንን ስደባቸው አለው፡፡ ያ ወንድምም ወደዚያ ሄዶ ሰድቧቸውና ድንጋይ ወርውሮባቸው ተመለሰና ይህንኑ ማድረጉን ነገረው፡፡ መቃርዮስም “ምን አለህ?” ሲለው እርሱም “ምንም ነገር አላሉኝ" አለው። አረጋዊውም “ነገ ተመልሰህ ሒድና አመስግናቸው” አለው፡፡ ያ ወንድምም ተመልሶ ሔደና “እናንተ እናንተ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰዎች ናችሁ" እያለ ሲያመሰግናቸው ውሎ ተመለሰ፡፡ አረጋዊውም “ምንም አልመለሱልህም?" አለው፡፡ እርሱም “የለም” አለ፡፡ መቃርዮስም “ሙታንን እንደ ሰደብካቸውና ምንም እንዳልመለሱልህ፣ እንደ ገናም እንዳመሰገንካቸውና ምንም ነገር እንዳልተናገሩህ አይተሃል፡፡ አንተም ልትድን ከፈለግህ እንዲሁ ማድረግና የሞትህ መሆን አለብህ። ልክ እንደ ሙታን የሰዎችን ነቀፌታቸውንም ሆነ ምስጋናቸውን ከቁም ነገር አትቁጠረው፣ ቦታም አትስጠው፣ እንዲህ ብታደርግ ትድናለህ” አለው፡፡ ++++++++~~~~~++++++ በአንጾኪያ የነበረ አንድ ደግ መነኩስ እንዲህ አለ፦ “እጸልይ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም የምመገበው ስላልነበረኝ እንደ ራበኝ አዝኜ ተኛሁ:: ክርስቶስ ሌሊት ታየኝና «ጎልጎታ ወዳለ ቄስ ሂድና አንዲት ዲናር ትሰጠኝ ዘንድ ክርስቶስ ወዳንተ ልኮኛል፣ እርሱ መጥቶ ይከፍልሃል በለው» አለኝ:: በነቃሁ ጊዜ ወደ ቄሱ ሄድሁና ነገርሁት:: እርሱም «ክርስቶስ የሚመጣና ገንዘቤን የሚሰጠኝ መቼ ነው?» አለኝ፡፡ እኔም እርሱ ያለኝን ነግሬሃለሁ፣ ከዚህ በኋላ የወደድከውን አድርግ አልሁት፡፡ እርሱም «ጻፍልኝ» ኣለኝ፡፡ እኔም እኔ የአንጾኪያው ዮሐንስ ከኢየሩሳሌሙ ቀሲስ እስጢፋኖስ አንድ ዲናር ወስጃለሁ፤ ክርስቶስ መጥቶ ዲናሩን እንደሚከፍለው ይኸው በእጄ ጽፌአለሁ ብዬ ጻፍሁለት፡ እርሱም ሰጠኝ። በዚያው ሌሊት ክርስቶስ ታየውና «ዲናርህን ውሰድና ያ መነኰስ የጻፈውን ጽሑፍ መልስልኝ» አለው᎓᎓ እርሱም «ክርስቶስ መጥቶ ይመልስልሃል ብሎኝ አልነበረምን?» አለው፡፡ እርሱም «ዲናርህን ውሰድና የዚያን መነኰስ ጽሑፍ መልስልኝ የምልህ እኔ ራሴ ክርስቶስ ነኝ» አለው:: ያም ቄስ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ወደዚያ መነኰስም ወደ እርሱ በፍቅር ይመጣ ዘንድ ላከበት፡፡ መነኲሴው ግን ያቺን ዲናር አምጣ ሊለኝ ነው ብሎ ፈራ፡፡ ኣብረው ሲበሉም «ከገንዘቤ የፈለግከውን ሁሉ ውሰድ» አለው፡፡ መነኲሴው ግን ከታዘዘልኝ በቀር ሌላ አልፈልግም” አለው፡፡ ቄሱም በሀልሙ የሆነውን ነገር ነገረውና “አሥር መክሊት ወርቅ ውሰድና ጻፍልኝ” አለው። እርሱ ግን “ከአንድ ዲናር በቀር ሌላ እወስድ ዘንድ አምላኬ አላዘዘኝም፡፡ ነገር ግን በፍጹም ልብህ ካመንህ ብዙ ነዳያንን ታገኛለህ፤ እነርሱም እንዲህ ይጽፉልሃል” አለው:: ++++++++++++~~~~+++++++++ ነፍስህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ስትሰለች ፣ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብና መስማት ደስ የማይላት ሲሆንና ሲያስጠላት፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ተግሳፅን ስታቃልል ካየሀት በክፉ ደዌ ላይ እንደወደቅህ ተገንዘብ፤ ሰዎች የሞትን ፍሬ የሚቀጥፉበት መጀመሪያው ይህ ነውና። #ከበረሐውያን_አንደበት #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
إظهار الكل...
136👍 32🙏 5🥰 4👏 4🕊 2
تسجيل الدخول والحصول على الوصول إلى المعلومات التفصيلية

سوف نكشف لك عن هذه الكنوز بعد التصريح. نحن نعد، انها سريعة!