cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ክብርን ለሚገባው ክብርን ስጡ" ሮሜ 13፡7 ተብሎ እንደተጻፈ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳንን ታከብራለች።የዚህ ቻናል አላማም ስለ ድንግል ማርያም፣ፃድቃን፣መላእክት፣እና ሰማዕታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
692
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
+130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ኮከበ ክብር ጽዱል ፀሐዬ አግዓዚ ብሩህ አቡነ ጊዮርጊስ ጥዑመስመ ወሠናየ ግዕዝ መጋቤ ሃይማኖት ወመሠረተ ቤተ ክርስቲያን፤ አባታችን ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሚያበራ የክብር ኮከብ፣የኢትዮጵያ ብሩህ ፀሐይ፣ ስሙ የሚጣፍጥ፣ ምግባሩ የቀናነው።›› (ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) የቅዱሳን ታሪክ የትውልድን አእምሮ የሚያንጽ እንዲሁም የእነርሱን ፈለግ እንድንከተል የሚያደረግ ነው፡፡ የቀደመውን ትውልድ በማውሳት፣ አሁን ያለውንና ወደፊት የሚመጣውን ትውልድ ደግሞ ከተያዘበት የኃጢአት አረንቋ ለማውጣትና ካለበት የሥጋ ሕማም ለመፈወስ እንዲሁም ሃይማኖትንና ጥበበ እግዚአብሔር ገንዘብ አድርጎ መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርስ የደከሙት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ከቅዱሳኑ አባት አንዱ ናቸው። አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት ጥንተ ስሙ ብሔረ አምሃራ ነገሥታት መናገሻ ከነበረው ከአማራ ሳይንት አካበ በአሁኑ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና አውራጃ በከለላ ወረዳ በወለቃ እናበበቶ ወንዝ መካከል በምትገኘዋ ልዩ ስሟ ሸግላ/ሰግላ/ደብረ ማኅው በ፲፫፻፶፯ ዓ.ም በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ አባታቸው ሕዝበ ጽዮን እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፤ ቤተሰቦቻቸው ከካህናት ወገን እና ከነገሥታት ወገን ናቸው። እንደነ ኤልሳቤጥ እና እንደ ዘካርያስ በሕግ የጸኑ ደጋግ አባቶች ቢሆኑም ልጅ ስለ አልነበራቸው፤ ዘወትር ወደ ቤተ እግዚአብሔር በመመለስ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል አድኅኖ ፊት እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ይጸልዩ ነበር። ሁሉን ማድረግ የሚቻለው እግዚአብሔር ጸሎታቸዉን ካደረሱ በኋላ ‹‹አስመ አልቦ ነገር ዘይሳኖ ለእግዚአብሔር፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና›› ይህን ቅዱስ በቅዱስ ዑራኤል አብሣሪነት ተወልዷል፤ ቅዱሱ ጥቅምት ሦስት ቀን ፲፫፻፶፯ ዓም ተፀንሰው ሐምሌ ፯ ቀን ዕለተ ማክሰኞ ቅድስ አባታችን ተወለዱ። (ድርሳነ ዑራኤል) አብርሃም ሥላሴን ባስተናገደበት ዕለት አባ ጊዮርጊስ ዕድሚያቸው ለትምህርት እስኪ በቃ ድረስ እናታቸው ጋር እግዚአብሔርን እንዲፈራና ትሕትናን ገንዘብ እንዲያደርግ እናቱ አስተማረችው። ከዚህ በመቀጠል አባታቸው በቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ ካህናት ወስደው ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት በማስተመር አሳደጓቸው። ምንም እንኳን አባታቸው ወደ ተምህርት ቤት ቢወስዷቸውም ትምህርት ቶሎ ሊገባቸውም አልቻለም ነበር፤ ይህ የእርሳቸው ትምህርት አለመግባት የቅዱስ ያሬድን ታሪክ ያስመስላል፤ ቢሆንም ሁል ጌዜ የእመቤታችን ስዕል ፊት እየሆኑ ማኅፀናት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን እመቤታችን ተገልፃ ‹‹አይዞህ አታልቅስ፤ ትምህርት ተከልክሎብህ ሳይሆን የምትጠቀምበት ጊዜው እስኪ ደርስ ነው፤ አሁን ጊዜዉ ደርሷል›› አለችው፤ ‹‹እስከ ፯ ቀን በዚሁ እንዳለህ ጠብቀኝ›› ብለውም ተሠወረች። እርሳቸውም ተስፋውን ተቀብለው በሱባዔ እንዳሉ እንደተለመደው በስዕለ ማርያም ሥር ተደፍተው ሲያለቅሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመልአክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤልን አስከትላ ጽዋ እሳት (ጽዋ ልቦና እንዳጠጠው ዕዝራ ሱቱኤልን) የሕይወት ጽዋ አጠጣችው። አባ ጊዮርጊስ የሕይወት ጽዋ ከተጎነጩ በኋላ የሰማይና የምድር ምሥጢር ተገለጸላቸው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የደረሱት መጽሐፍት ከሃምሳ በላይ ይሆናሉ፡፡ በስም የሚታወቁት ግን ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት፣ ኖኅተ ብርሃን ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ ታትሟል፣ ውዳሴ መስቀል፣ ቅዳሴ፣ ውዳሴ ሐዋርያት፣ አርጋኖነ ውዳሴ፣ ፍካሬ ሃይማኖት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ ውዳሴ ስብሐት፣ እንዚራ ስብሐት፣ ሕይወተ ማርያም፣ ተአምኖ ቅዱሳን፣ መጽሐፈ ብርሃን እንዲሁም ጸሎት ዘቤት ናቸው፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አባት ናቸው፡፡ በዜማ ትምህርት በጣም ጠልቀው ያውቁ፣ የቅዱስ ያሬድን ዜማ በተለይም ድጓውን በዘመናት ከፋፍለው እና በየበዓላቱ አደራጅተው፣ ቅርጽ በማያስያዝ ለቅዱሳኑ ሁሉ በየባህሎታቸው የሚዜመውን አዘጋጅተው ለደቀ መዛሙራቶቻቸው በማስተማር እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድጓውን በደብር ነጎድጓድ ሐይቅ ለሰባት ፯ ‹በርእስ አድባራት ተድባበ ማርያም› አስተምረዋል፡፡ በዜማው በኩል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ከያሬድ በኋላ የተነሡ ዳግማዊ ያሬድ ሲባሉ በዘመኑ የነበሩትን መናፍቃንን በመከራከርና አስተምረው በመርታታቸው ‹ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ› የሚል ስምም ተሰጥታቸዋል፡፡ አባ ጊዮርጊስ ስለ ሰማይ፣ ስለ መብረቅና ስለ ዝናም አፈጣጠርና ባሕርያት በሚገባ አስተምረዋል፡፡ ሆኖም ግን ድርሰቶቻቸውን የውጭ አንብባቢዎች ሲጠቀሙበት የሀገራችን ሰዎች ግን የታላቁን ቅዱስ ታሪክ እንኳን በቅጡ የማያውቅ ነው፡፡ እርሳቸው ግን የቤተ ክርስቲያን መብራት ናቸው፡፡ ምክንያቱም ዛሬ በቅዳሴው፣ በማኅሌቱ፣ በሰዓታቱ፣ በምሥጢሩና የምስጋና ድርሰቶች አሁንም ቤተ ክርስቲያን እየተጠቀመችባቸው ትገኛለች፡፡ ይህ ሕሙም ትውልድ መድኃኒት ያስፈልገዋለና መድኃኒቱን ለማግኘት ሌት ከቀን በመጾም፣ በመጸለይና መትጋት እንዳለበት በአጽንዖት አስተምረዋል፡፡አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአጼ ይስሐቅ ዘመነ መንግሥትም ‹‹ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ተጠያቂ ሊቅ›› ተደርገው ተሹመው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የትሕት፣ የርኅራኄና የምሥጢር ባለቤት አባት ናቸው፡፡ የርኅራኄ አባት ያልንበት ምክንያት እንዲህ ነው፤ በአንድ ወቅት ሳያመነኩሱ ገና ንጉሥ ዳዊት ልጃቸውን እንዲያገቡና በእርሳቸው ቦታ እንዲተከቱ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቀረቡላቸው፡፡ እርሳቸውም የንጉሡን መልክእት በመስማትና ያሞክሮ ልብስ በመልበስ የመጣባቸውን ፈተና አልፈውታል፡፡ በዚህ ምክንያት ንጉሥ ዳዊት ስላልሰሟቸው ብዙ መከራና ሥቃይ አድርሰውባቸዋል፡፡ ግን እኚህ ንጉሥ መስቀሉን ሊያመጡ ሲሄዱ ጎዳና ላይ በቅሎ ረግጣቸው ሞቱ። አባ ጊዮርጊስም የንጉሡን ሞት በሰሙ ጊዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ ‹‹ምነው ያ ሲያንገላታህ፣ ብዙ መከራ ሲያደርስብህና በጨለማ ቤት ሲወረውርህ ደስ ሊል ይገባል እንጂ እንዴት ታለቅሳለህ?›› ብሎ ሰዎች ሲጠይቋቸው ‹‹እንደዚያም ቢሆን ንጉሡ እመቤታችንን ይወዱ ስለነበረ ነው ያዘንኩት›› ብለው መልሰውላቸዋል፡፡ በመጽሐፍ ‹‹የእግዚብሔር መንገድ ቅን ነው። ጻድቃን ይሄዱበታል፡፡ ሕግ ተላላፊዎች ግን ይወድቁበታል፤›› ተብሏል፡፡ (ሆሴ.፲፬፥፱) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተወለዱ በ፷ ዓመታቸው ኢትዮጵያ አበቅቴ አልቦ በሆነበት ጊዜ ጥንተ ዮን በወንጌላዊው ማቴዎች ዘመን ረቡዕ ቀን ይስሐቅ በነገሥ በዐሥራ አንድ ዓመት በ፲፬፻፰ ሐምሌ ፯ ቀን ዐርፈዋል፡፡ የጻድቁ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን፤ አሜን፡፡
إظهار الكل...
Today, July 12th, we celebrated and commemorated the two great Apostles Peter and Paul. Their martyrdom in Rome is a very well-attested historical event, happening probably between the years 64 and 68 A.D. under the Roman emperor Nero. The two great saints Peter and Paul, were martyred. Peter was from Bethsaida, and he was a fisherman. The Lord chose him on the second day of His baptism after He chose Andrew his brother. He had fervent faith and strong zeal. When the Lord asked His disciples: "Who do men say that I am?" So they answered, "Some say John the Baptist, some Elijah, and others Jeremiah or one of the prophets." ... Simon Peter answered and said, "You are the Christ, the Son of the living God." (Mat. 16:13-20) After he received the grace of the Holy Spirit, he went around in the world preaching of the crucified Christ, and he converted many to the faith. God wrought great and innumerable signs and wonders by his hands. He wrote two catholic Epistles to the believers. When he came to the city of Rome, he found there St. Paul the Apostle. Through their preaching, most of the people of Rome believed, so Nero seized Peter and commanded to crucify him. Peter asked them to crucify him head downwards, and he delivered up his soul into the hand of the Lord. As of St. Paul the Apostle, he was born in Tarsus two years before the advent of the Savior. He was a Jew, of the tribe of Benjamin, a Pharisee, the son of a Pharisee. He was well learned in the Law of the Torah, and he was zealous for it. He persecuted the Christians. When they stoned St. Stephen, Paul was guarding the clothes of those who were stoning him. He took from Caiaphas, the high priest, letters to the synagogues of Damascus, to bind the Christians and bring them to Jerusalem. As he journeyed, he came near Damascus, and suddenly a light shone around him from heaven. Then he fell to the ground, and heard a voice saying to him, "Saul, Saul, why are you persecuting Me?" And he said, "Who are You, Lord?" And the Lord said, "I am Jesus, whom you are persecuting. It is hard for you to kick against the goads." Then He ordered him to go to Ananias in Damascus, who baptized him, and he received his sight at once. He was filled by the grace of the Comforter, and he proclaimed boldly the Faith. He went around in the world preaching of the crucified Christ. He suffered much beatings, imprisonment, and was bound with fetters, some of which are mentioned in the book of the Acts of the Apostles and in his Epistles. He went to Rome and proclaimed the Faith there and many believed by his hands. He wrote for them the Epistle to the Romans which was the first of his fourteen Epistles. Finally, Nero seized him, tortured him severely and ordered his head cut off. While St. Paul was passing along with the executioner, he met a damsel who was a kinswoman of the Emperor Nero, and who had believed through him. She walked along with St. Paul, weeping, to where they carried out the sentence. He comforted her and asked her for her veil. He wrapped his head with the veil, and asked her to return back. The executioner cut off his head and left it wrapped in the veil of the young girl, and that was in the year 67 A.D. The young girl met the executioner on his way back to the Emperor, and asked him about Paul and he replied, "He is lying where I left him and his head is wrapped in your veil." She told him, "You are lying, for he and Peter had just passed by me, they were arrayed in the apparel of kings, and had crowns decorated with jewels on their heads, and they gave me my veil, and here it is." She showed it to the executioner, and to those who were with him. They marvelled, and believed on the Lord Christ. God wrought by the hands of Peter and Paul many great signs and wonders, that they even carried the sick out into the streets ... that as Peter came by ... his shadow might fall on them ... and they were all healed. (Acts 5:15) The handkerchiefs or aprons were brought from Paul's body to the sick, and the diseases left them and the evil spirits went out of them.
إظهار الكل...
(Acts 19:12) The Apostles Peter and Paul are truly “rivers of wisdom and upholders of the Cross!” They exemplified the later teaching of Saint Ignatius of Antioch of the mystery of Christ that conveys “life in death,” for they died as martyrs but are eternally alive in Christ. We can now read their epistles and their lives as “living books which teach us the way to better things” as Saint Gregory Palamas said of them. We seek their prayers as we strive to be worthy of the title of “Christian.” May their prayers be with us, and Glory be to God forever. Amen.
إظهار الكل...
💒 ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ 💒 𝗠𝗮𝗿𝘁𝘆𝗿𝗱𝗼𝗺 𝗼𝗳 𝗦𝗮𝗶𝗻𝘁𝘀 𝗣𝗘𝗧𝗘𝗥 𝗮𝗻𝗱 𝗣𝗔𝗨𝗟 𝕋𝕙𝕖 𝕘𝕣𝕖𝕒𝕥𝕖𝕤𝕥 𝕒𝕟𝕕 𝕞𝕠𝕤𝕥 𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥𝕖𝕠𝕦𝕤 𝕡𝕚𝕝𝕝𝕒𝕣𝕤 𝕠𝕗 𝕥𝕙𝕖 ℂ𝕙𝕦𝕣𝕔𝕙 ተዘኪረከ ክርስቶስ ዘሐዋርያት ኲሎሙ ህየንተ ክቡር ደምከ እለ ከዓዉ ደሞሙ አክሊለ ስምዕ ሀበኒ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ ወደምስስ ለአጽራርየ እመጽሐፈ ህይወት ዝክሮሙ ከመ ለይሁዳ ረሲዕ ተደምሰሰ ስሙ። አመ ሐምሱ ለሐምሌ ኮነ በዓለ ዕረፍቶሙ ለጴጥሮስ ወለጳውሎስ ሐዋርያት ብርሃናተ ዓለም ጸሎቶሙ ወሀብተ ረድኤቶሙ የሀሉ ምስለ ኵልነ ሰማዕያን ወአንባብያን አሜን። 𝙏𝙝𝙚 𝙈𝙖𝙧𝙩𝙮𝙧𝙙𝙤𝙢 𝙤𝙛 𝙎𝙩𝙨. 𝙋𝙚𝙩𝙚𝙧 𝙖𝙣𝙙 𝙋𝙖𝙪𝙡, 𝙩𝙝𝙚 𝘼𝙥𝙤𝙨𝙩𝙡𝙚𝙨 ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘአልባስጥሮስ አፈው ወለሥዕርትክሙ ጸሊም ዘድላሌሁ ፍትው ምቱረ ክሣድ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ቅንው ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስል መዓዛሁ ቅድው ደመ ስምክሙ ሐዋርያ ዘኅብሩ ከዋው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው ኬፋ የተባለውን ጴጥሮስና ሳዖል ይባል የነበረውን ጳውሎስ ፦ "አፍቅሮተክሙ አኃውየ ውስተ ራኅበ ልብየ ተጽሕፋ፤ ወኪያክሙ እሬሲ እምታሕተ እግዚአብሔር ተስፋ፤ አጋእዝትየ ጳውሎስ ወኬፋ።" ብሏል። ✔ ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19 ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣንና ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሊሄድ በመሞከሩ (ማቴ. 6፥45)፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ (ማቴ. 16፥16) ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቆጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ መሆኑን መፅሐፍ ቅዱስ በዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/ ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበረና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ አካይያ ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት ከዚህ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር አሁንም እሳት ከሰማይ ወርዳ ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን? አለ አንተ ብትፈራ እንጂ ነዋ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚህች ሐምሌ 5 ቀን ይታሰባል፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቶ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡ ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘአልባስጥሮስ አፈው ወለሥዕርትክሙ ጸሊም ዘድላሌሁ ፍትው ምቱረ ክሣድ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ቅንው ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስል መዓዛሁ ቅድው ደመ ስምክሙ ሐዋርያ ዘኅብሩ ከዋው። ✔ ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ (የተመረጠ ዕቃ) ማለት ነው፡፡ ሐዋ.9፥15 አንድም ብርሃን ማለት ነው፡፡ አንድም መድቅሕ ማለት ነው፡፡ ደንጊያ በመዶሻ ተጠርቦ ለሕንፃ ሥራ እንዲውል አሕዛብም በእርሱ ትምህርት ታንፀው ለገቢረ ጽድቅ ይበቃሉና የመጀመሪያ ስሙ ሳውል ነው፤ ሳውልም ማለት ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ነው፡፡ ፊል. 3፥5 አባቱ ዮስአል ይባላል፡፡ የተወለደው ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ነው፡፡ ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እኅቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ ሐዋ. 22፥3 ለሕገ ኦሪት ቀናዒ ከመሆኑ የተነሣ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ እያለ ሐዋርያትን ይቃወም ምእመናንን ያሳድድ ነበር፡፡ በወንጌል ያመነው ጌታ በዐረገ በ8ኛ ዓመት ነው፡፡ ምዕመናንን ለማሳደድ ከሊቀ ካህናት የሹመት ደብዳቤ ተቀብሎ ወደ ደማስቆ ሲሄድ መብረቅ ጣለበት፤ ደንግጦ ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ አንተ ማነህ? አለ ምእመናንን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበት አላውል የምትልብኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፣ ሰይፍ ቢረግጡት የረገጠው ሰው እንጂ ሰይፉ ይጎዳልን? ፣ አንተስ እኔን ብትክድ ምእመናንን ብታሳድድ አንተ እንጂ እኔ እጎዳለሁን? አለው፡፡ አሁን ምን ላድርግ አለው ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባ የምታደርገውን ይነግሩሃል አለው፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩም ድምጹን ይሰማሉ መልኩን ግን አላዩም፤ ከወደቀበት ተነሥቶ ዓይኑ ጠፍቷልና ሰዎች እየመሩት ቤተ ይሁዳ አደረሱት እኅል ውኃ ሳይቀምስ 3 ቀን ውሎ አድሯል፡፡ ከ72 ቱ አርድዕት አንዱ ሐናንያ በደማስቆ ይኖር ነበር። ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎስን አሳምነህ አጥምቀው አለው፡፡ ምርጥ ዕቃ አድርጌዋለሁና ሂድ ይቀበልሃል አለው፡፡ ሄዶ ወንድሜ ሳውል በመንገድ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ ያድርብህ ዘንድ ወዳንተ ልኮኛል ብሎ ቢዳስሰው ዓይኑን ሸፍኖት የነበረው እንደ ቅርፊት ተቀርፎ ወድቆለታል፡፡ ሐዋ. 9፥1-19 በ69 ዓ.ም ሮም ገብቶ ሲያስተምር ንጉሡ ኔሮን ቄሣር አሥሮት ነበርና አካይያ ዘምቶ ጠላት ድል ነሥቶ ሲመለስ ጥሩት አለ፤ መስቀሉን በእጁ ይዞ ቀረበ፤ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡት አለ፤ እንደ በግ እየነዱ ሲወስዱት የንጉሡ ልጅ አገኘቻቸው፤ አምና ነበርና መጎናጸፊያሽን ስጪኝ አላት ሰጠችው በዚያ ሸፋፍነው ሰይፈውታል፡፡ ደሙም ሰማየ ሰማያት ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል፡፡ ‹‹ደምከ ጴጥሮስ ወልደዮና በጽዋዐ መስቀል ተቀድሐ፤ ወደመ ጳውሎስ ሰማያተ ጸርሐ›› እንዳለ ደራሲ እሱን ገድለው ሲመለሱ የንጉሥ ልጅ አገኘቻቸው ጳውሎስስ? አለቻቸው፡፡ በልብስሽ ሸፋፍነን በሰይፍ ገደልነው አሏት፡፡ ልብሴን መልሶልኝ ከጴጥሮስ ጋር አሁን በዚህ ሲያልፍ እያየሁት ገደልነው ትሉኛላችሁን አለቻቸው ልብሷን አይተው አምነዋል፡፡ ተቆርጦ የወደቀ ራሱንም ከአንገቱ ቢያጋጥሙት እንደ ቀድሞው ሆኖላቸው ቀብረውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚች ሐምሌ 5 ይታሰባል፡፡ ደምረነ ምስለ ኩሎሙ ቅዱሳን ምስለ እለ ገብሩ ፈቃድከ እለ እምዓለም አስመሩከ እለ ዐቀቡ በንጽህ ሥርዓተ ቤትከ ወእለ ሰበኩ በሠናይ ዜናከ በረከተ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይሀሉ ምስለ ኩልነ ክርስቶሳውያን ! The Martyrdom of Sts. Peter and Paul, the Apostles
إظهار الكل...
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ (ሐምሌ 5) ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው። #ቅዱስ_ጴጥሮስ ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19 ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሲሄድ በመሞከሩ ማቴ. 6፥45፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ ማቴ. 16፥16 ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቶጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ ዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/ ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበረና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ አካይያ ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት ከዚህ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር አሁንም እሳት ከሰማይ ወርዳ ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን? አለ አንተ ብትፈራ እንጂ ነዋ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚህች ሐምሌ 5 ቀን ይታሰባል፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቶ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡ #ቅዱስ_ጳውሎስ ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ (የተመረጠ ዕቃ) ማለት ነው፡፡ ሐዋ.9፥15 አንድም ብርሃን ማለት ነው፡፡ አንድም መድቅሕ ማለት ነው፡፡ ደንጊያ በመዶሻ ተጠርቦ ለሕንፃ ሥራ እንዲውል አሕዛብም በእርሱ ትምህርት ታንፀው ለገቢረ ጽድቅ ይበቃሉና የመጀመሪያ ስሙ ሳውል ነው፤ ሳውልም ማለት ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ማለት ነው፡፡ ፊል. 3፥5 አባቱ ዮስአል ይባላል፡፡ የተወለደው ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ነው፡፡ ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ ሐዋ. 22፥3 ለሕገ ኦሪት ቀናዒ ከመሆኑ የተነሣ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ እያለ ሐዋርያትን ይቃወም ምእመናንን ያሳድድ ነበር፡፡ በወንጌል ያመነው ጌታ በዐረገ በ8ኛ ዓመት ነው፡፡ ምዕመናንን ለማሳደድ ከሊቀ ካህናት የሹመት ደብዳቤ ተቀብሎ ወደ ደማስቆ ሲሄድ መብረቅ ጣለበት፤ ደንግጦ ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ አንተ ማነህ አለ ምእመናንን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበት አላውል የምትልብኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፣ ሰይፍ ቢረግጡት የረገጠው ሰው እንጂ ሰይፉ ይጎዳልን፣ አንተስ እኔን ብትክድ ምእመናንን ብታሳድድ አንተ እንጂ እኔ እጎዳለሁን አለው፡፡ አሁን ምን ላድርግ አለው ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባ የምታደርገውን ይነግሩሃል አለው፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩም ድምጹን ይሰማሉ መልኩን ግን አላዩም፤ ከወደቀበት ተነሥቶ ዓይኑ ጠፍቷልና ሰዎች እየመሩት ቤተ ይሁዳ አደረሱት እኅል ውኃ ሳይቀምስ 3 ቀን ውሎ አድሯል፡፡ ሐናንያ በደማስቆ ይኖር ነበርና ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎስን አጠመቀው፡፡ ሐዋ. 9፥1-19 በ69 ዓ.ም ሮም ገብቶ ሲያስተምር ንጉሡ ኔሮን ቄሣር አሥሮት ነበርና አካይያ ዘምቶ ጠላት ድል ነሥቶ ሲመለስ ጥሩት አለ፤ መስቀሉን በእጁ ይዞ ቀረበ፤ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡት አለ፤ እንደ በግ እየነዱ ሲወስዱት የንጉሡ ልጅ አገኘቻቸው፤ አምና ነበርና መጎናጸፊያሽን ስጪኝ አላት ሰጠችው በዚያ ሸፋፍነው ሰይፈውታል፡፡ ደሙም ሰማየ ሰማያት ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል፡፡ እሱን ገድለው ሲመለሱ የንጉሥ ልጅ አገኘቻቸው ጳውሎስስ? አለቻቸው፡፡ በልብስሽ ሸፋፍነን በሰይፍ ገደልነው አሏት፡፡ ልብሴን መልሶልኝ ከጴጥሮስ ጋር አሁን በዚህ ሲያልፍ እያየሁት ገደልነው ትሉኛላችሁን አለቻቸው ልብሷን አይተው አምነዋል፡፡ ተቆርጦ የወደቀ ራሱንም ከአንገቱ ቢያጋጥሙት እንደ ቀድሞው ሆኖላቸው ቀብረውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚች ሐምሌ 5 ይታሰባል፡፡ የቅዱሳን አባቶች ጸሎታቸው በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደር፡፡ (ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ)
إظهار الكل...
ከዳዊት መዝሙር ቀጥሎ ብዙ ምዕራፎች ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?Anonymous voting
  • ሀ// ዘፍጥረት
  • ለ// ኤርሚያስ
  • ሐ// ሐጌ
  • መ// ኢሳይያስ
0 votes
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.