ar
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

تُعد قناة ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 954 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 154 في فئة الطب والمرتبة 1 678 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 954 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 26 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -547، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -20، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 24.05‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 7.27‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 805 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 453 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 9.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 27 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الطب.

19 954
المشتركون
-2024 ساعات
-1217 أيام
-54730 أيام
أرشيف المشاركات
በወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል በአንድ እናት የወሊድ ወቅት የተከሰተ ድርጊትን በተመለከተ ትናንት ምሽት መረጃ አቅርቤ ነበር! ይህን ተከትሎ የሆስፒታሉ ኃላፊዎች በቀኑ ስራ ላይ የነበሩት ሰራተኞች ጋር
በወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል በአንድ እናት የወሊድ ወቅት የተከሰተ ድርጊትን በተመለከተ ትናንት ምሽት መረጃ አቅርቤ ነበር! ይህን ተከትሎ የሆስፒታሉ ኃላፊዎች በቀኑ ስራ ላይ የነበሩት ሰራተኞች ጋር እየደወሉ "ለዚህ ዋጋ ትከፍላላችሁ" እያሉ እንደነበረ ዛሬ ሰምቻለሁ፣ "ሚድያ ላይ አወጣችሁ" ተብለው ማስፈራርያ የደረሳቸው በርካቶች ናቸው። እንደሰማሁት ምናልባትም አንዳንዶችን ከስራ ሊያባርሩ ወይም የሆነ ነገር ለጥፈዉ ሊያሳስሩ ይችላሉ። እኔ ይህን መረጃ ስፅፈው እርግጠኝነቱን በደንብ አጣርቼ፣ ከዛ ደግሞ መረጃው ቢወጣ የዚህች እናት አሳዛኝ ክስተት ሌሎች ላይ እንዳይደገም ትምህርት ይሆናል በሚል እሳቤ ነበር። ይህ በሆስፒታሉ ችግሮች እንዳሉ ማሳያ ነው። ሌላው ቀርቶ ትናንት (በቀን 3/5/2014) ሁለት የእናት ሞት ተመዝግቧል (ለዚህም ማስረጃ አለኝ)፣ ምክንያቱ ደግሞ ደም ባለመኖሩ እንዲሁም ኦክስጅን ባለመኖሩና ያለበት ቦታ ለመሄድ አቅም በማጣት ነበር። በተጨማሪም በሆስፒታሉ የባለሙያ የ5 ወር duty ክፍያ አልተፈፀመም። የማዋለድ አገልግሎት በነፃ በመላው ኢትዮጵያ እየተሰጠ ባለበት ወቅት በዚህ ሆስፒታል እናቶች እንዲህ ሲሆኑ ማየት እና መስማት ይከብዳል። ከዛ ደግሞ አለ የተባለ ችግር ሲነሳ አጣርቶ መልስ ከመስጠት እና ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ የጤና ባለሙያዎችን ማስፈራራት ያልተገባ ድርጊት ነው። @EliasMeseret

ይህ የሆነዉ በወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል ነዉ! በሆስፒታሉ ለመውለድ የሄደች ስሟን የሸፈንኩት እናት መድኃኒት መግዛት ባለመቻሏ ፅንሱ ማህጸን ዉስጥ እንዳለ አልፏል። ጉዳዩ እንዲህ ነው: እናትየው ም
ይህ የሆነዉ በወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል ነዉ! በሆስፒታሉ ለመውለድ የሄደች ስሟን የሸፈንኩት እናት መድኃኒት መግዛት ባለመቻሏ ፅንሱ ማህጸን ዉስጥ እንዳለ አልፏል። ጉዳዩ እንዲህ ነው: እናትየው ምጥ ላይ እያለች ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ስለተፈጠረ ጠበላ ሆስፒታል ወደ ኦቶና ይልካታል። ኦቶና ስትደርስ ለኦፕራስዮን የሚያስፈልጉ (እንደ ጓንት፣ የቁስል መስፊያ ያሉ) ስለሌለ እንድትገዛ ይታዘዛል። ከዚህ በፊት ባለሙያዉ ከሌላ የተረፈዉን እያጠራቀመ ለእንደዚህ ዓይነት ጊዜ ይጠቀም ነበር፣ ነገር ግን እንዲህ የሚያደርጉት ላይ እርምጃ መውሰድ ስለተጀመረ ባለሙያዉ አቁሟል። እናትየው እና ቤተሰቧ ይህን መግዛት ስላልቻሉ ዉጤቱም ይህ ሆኗል። ሲጀመር ለእናቶች ነጻ ህክምና እንሰጣለን በሚል ተቋም ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ? ሌላው ቀርቶ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ለወራት ያለ እንቅልፍ የሰሩበትን duty ክፍያ እያገኙ እንዳልሆነ የደረሰኝ መረጃ ያሳያል፣ ከደሞዛቸውም ሳይፈቅዱ ይቆረጥባቸዋል። ሆስፒታሉ ወላይታ ዉስጥ የኦፕራስዎን ወሊድ አገልግሎት የሚሰጥበት ብቸኛዉ ተቋም ነዉ፣ እንደውም በቅርቡ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሆኗል። የዚህች እናት አሳዛኝ ክስተት ሌሎች ላይ እንዳይደገም እንዲሁም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጉዳዮች ከነበሩ ማጣራት ቢደረግ ቢያንስ የወደፊቱን ማስተካከል ይቻል ይሆናል። መልስ ቢሰጥበት መልካም ነው። @EliasMeseret

መንጋጋ ቆልፍ፦ በባክቴሪያ የሚመጣና ነርቭን የሚያጠቃ በሽታ ነው። ይህ ባክቴሪያ አጣዳፊ በቀላሉ የሚዛመት ነርቭን በመጉዳት ፓራላይዝድ የሚያደርግ በማህበረሰቡ ዘንድ መጋጋ ቆልፍ የሚባል በህክምና ደግሞ ቴታነስ በሚባል ባክቴሪያ የሚመጣ በሽታ ነው። • ምክናየቱ ክሎስትሪደም ቴታኒ በሚባል ባክቴሪያ የሚመረት መርዛማ ኬሚካል አማካኝነት ነርቭን በመመረዝ ጡንቻን ማዘዝ እንዳይቻል ከፍተኛ ህመም መፍጠር ነው። • ይህ ባክቴሪያ ልዩ የሚያደርገው በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ መኖር የሚችል፣ ያለ ኦክስጅን ካርቦንዳይ ኦክሳይድን በመጠቀም የሚኖር፣ ጨለማንና ጥልቅ ቦታን የሚፈልግ መሆኑ ነው። በብረት ዝገት ውስጥ፣ አፈር ውስጥ፣ በከብቶች እበት ውስጥ እና በእንስሳት አንጀት ውስጥ ሊኖር ይችላል። የፈላ ውሀም ሆነ እሳት አይገለውም። • ብዙ ጊዜ በገጠሩ አካባቢ ከከተማ በተለየ መልኩ ሊኖር ይችላል። ካልታከመ 100% ገዳይ ነው። • ህፃናት ይበልጥ ይጠቃሉ። በተለይ ገጠር ላይ እትብት በሚቆርጡ ሰአት ሊጠቁ ይችላሉ። በቀላሉ አደጋም ስለሚደርስባቸው ምላጭና ሌሎች ስለታም ነገሮች ሊቆርጣቸው ስለሚችል ነው። ቴታነስ በአፈር ውስጥ፡ የከብቶች እበት በተለይ አንድ ቦታ ላይ የቆየ፡ የዛገ ብረት፡ የበሰበሰ እንጨትና አፈር ውስጥ ያለ ሹል ድንጋይ ላይ ይኖራል። በነዚህ ስንጎዳ የመያዝ እድሉ ይኖራል ማለት ነው። • የመረቀዘ የእትብት ቁስል፡ የደም አቅርቦት የተቋረጠበት ቁስል፡ በጩቤ የተወጋ ሰውነት፡ የሰውና የእንስሳት ንክሻ፡ ቃጠሎ፡ በሹል ነገር መወጋት፡ የማህፀን ውስጥ ኢንፌክሽን፡ ለረጅም ጊዜ የቆየ ቁስል፡ ለረጅም ጊዜ የቆየ ከጆሮ የሚወጣ ፈሳሽ መኖር ለቴታነስ ሊያጋልጥ ይችላል። • ባክቴሪያው በቁስል በኩል ወደ ሰውነት ከገባ በሗላ ሰውነት ውስጥ መርዛማ ኬሚካል ያመርታል። ይህ መርዛማ ኬሚካል በጡንቻና በነርቭ መሀል ላይ በተለይ ሞተር ኒውሮን በሚባለው የነርቭ ህዋስ ላይ ላይላቀቅ ይጣበቃል። ይህም ወደ አንጎል በመጎዝ ጭምር አጠቃላይ የጡንቻ አለመታዘዝና የጡንቻ መገተርን ይፈጥራል። መገለጫውም • ጡንቻ መድረቅ ወይም መገተር • የእንቅስቃሴ መታወክ • አንገትን በተለይ መንጋጭላን ማንቀሳቀስ አለመቻል • የልብ ምት መጨመር • ቀላል ደም ግፊት መጨመር • የደም ቱቦ መስፋት • መጠነኛ ትኩሳት • ከፍተኛ ላብ • እየሰፋ የሚሄድ ቁስል ብዙ ጊዜ ይህ በሽታ ጉዳቱ በደረሰ ከ5-21ቀን ምልክት ያሳያል። እስከ 3 ወር ተደብቆም ያለምልክት ሊቆይ ይችላል። • ጨቅላ ህፃን፡ ልጆች፡ ገበሪዎች፡ ማንኛውም ደረቅ ቁስል ያለበት እንድሁም ወታደሮች ከሌላል ሰው በበለጠ ሊጠቁ ይችላሉ። • የመጋጋ መቆለፍ፡ የመዋጥ ችግር፡ ውሀ መፍራት፡ የአየር ቱቦ መጥበብ፡ የሽንት መጠራቀም፡ እረፍት ማጣት፡ መገርጣት፡ ትንፋሽ ማጠር ተጨማሪ ምልክቶቹ ናቸው። የትንፋሽ መቆም፡ የአየር ቱቦ መዘጋት፡ የልብ ስራ ማቆም፡ መዋጥ አለመቻል፡ በሳንባ ውስጥ አየር መጠራቀም፡ ሽንት መሽናት አለመቻል፡ የሰገራ መድረቅ፡ የሳንባ ምች፡ የፈሳሽ ማጠርና ሌሎችም ችግሮች የበሽታው ውጤት ናቸው። ህክምናው • ታካሚው ግደታ ሆስፒታል መተኛት ይኖርበታል። ከዚያም ባክቴሪያው ያመረተው መረዛማ ኬሚካል እንድወገድና እንድታከም ይደረጋል። ከላይ የዘረዘርናቸው እያንዳንዱ ችግር ይታከማል። መንጋጋ ቆልፍን መከላከልና መቆጣጠር ይቻላል። በተለይ ክትባት መውሰድ ትልቁን ድርሻ ይይዛል። ቴታነስን ካልታከሙ ገዳይ ነው!

በደም ምርመራ ጊዜ ስለጤናችን የሚነግሩን አንዳንድ እውነታዎች ቀይ የደም ሴሎች የእነዚህ ህዋሳት ዋነኛ ተግባር ሄሞግሎቢን መሸከምና በእርሱም አማካኝነት ኦክስጅን ማመላለስ ነው፡፡ የጤነኛ ወንድ ቀይ የደም ሲል ብዛት ከ 4.6 እስከ 6.2 ሚሊዮን በኩቢክ ሚሊ ሜትር ሲሆን የጤነኛ ሴት ቀይ የደም ሲል ብዛት ከ 4.2 እስከ 5.4 ሚሊዮን በኩቢክ ሚሊ ሜትር ነው፡፡ ነጭ የደም ሴሎች የእነዚህ ሕዋሳት ዋነኛ ተግባር በሽታን መቋቋምና ተዋግቶ ማጥፋት ነው፡፡ የአንድ ጤነኛ ሰው ነጭ የደም ሴል ብዛት ከ4500 እስከ 11000 በኩቢክ ሚሊ ሜትር ነው፡፡ ሄማቶክሪት ደም በውስጡ ፕላዝማና (ውሃ) ልዩ ልዩ ሴሎችን የያዘ ነው፡፡ሄማቶክሪን የፕላዝማውንና የሴሎችን መጠን በመቶኛ ለማወቅ የሚረዳ መለኪያ ነው፡፡ ደም በብዛት ሲፈስ፣በከባድ ቃጠሎና ሌሎች ጥቂት በሽታዎች ይህ መለኪያ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ የወንድ ሄማቶክሪት ከ 40 እስከ 54 በመቶ የሴት ሄማቶክሪት ከ 38 እስከ 47 በመቶ ይሆናል፡፡ ኮሌስትሮል ( የደም ቅባት) በደማችን ውስጥ የሚገኘው የቅባት (ስብ) ክምችት በደም ምርመራ ሊታወቅ ይችላል፡፡ አንድ ጤነኛ ሰው ሊኖረው የሚገባ የኮሌስትሮል መጠን ከ 150 እስከ 250 ሚሊግራም በዴሲ ሊትር ነው፡፡ ስኳር አንድ ጤነኛ ሰው በደም ውስጥ ሊኖረው የሚገባው የስኳር መጠን ቁርስ ሳይበላ በሚደረገ የደም ምርመራ ከ 70 እስከ 110 ሚሊ ግራም በዴሲ ሊትር ነው፡፡ ዩሪክ አሲድ አንድ ጤነኛ ሰው በደሙ ውስጥ ሊኖረው የሚገባው የዩሪክ አሲድ መጠን ከ 4 እስከ 8.5 ሚሊ ግራም በዴሲ ሊትር ነው፡፡ ሄሞግሎቢን ይህ በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ ያለና ኦክስጅን ለማመላለስ የሚያገለግል ንጥረ ነገር (ፕሮቲን) ነው፡፡ የሄሞግሎቢን ማነስ አኒሚያ (ደም ማነስ) ያስከትላል፡፡ የጤነኛ ወንድ ሄሞግሎቢን ከ 13.5 እስከ 18 ግራም በዴሲ ሊትር ሲሆን የጤነኛ ሴት ሄሞግሎቢን ከ12.0 እስከ 16.0 ግራም በዴሲ ሊትር ነው፡፡

ትኩረት ልናደርግባቸው የሚገቡ የጉበት በሽታዋና ዋናዎቹ ምልክቶች 1) የሰውነት ክፍል ማበጥ፥ በሰውነት ውስጥ የፈሳሽ ክምችት እና ጥርቅም የከፍተኛ የሆነ የጉበት ጉዳት እንደተከሰተ ማሳያ ምልክት ነው። ይህም የአልበሚን መጠንን ከፍ በማድረግ በደም ውስጥ አላስፈላጊ እና ከመጠን በላይ የሆነ ፈሳሽ እንዲኖር ያደርጋል፤ ይህ ሂደት ደግሞ የችግሩ ተጠቂ የሆነውን ሰውነት በአላስፈላጊ ሁኔታ ያሳብጠዋል። 2) የቆዳ እና የአይን ቀለም መቀየር፥ በተለምዶ የወፍ በሽታ ተይዟል በሚል ምክንያት ባህላዊ ህክምና የሚደረግለት የቆዳ በተለይም ደግሞ የአይን ቀለም ወደ ቢጫነት መለወጥም ጉበት በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን ማሳያ ምልክት ነው። ይህ የሰውነት እና የአይን ወደ ቢጫነት መቀየር ደግሞ ደምን በሃሞት እንዲቀላቀል ያደርገዋል 3) የሆድ ህመም፥ በላይኛው እና በታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል የሚከሰት የሆድ ህመም የዚህ ችግር ተጠቂ ስለመሆንዎት ማሳያ ነው፤ በእነዚህ የሆድ ክፍሎች ላይ የውጋት እና ትር ትር የሚል ተደጋጋሚ ስሜት የዚህ በሽታ ምልክቶች ናቸው። 4) የሽንት ቀለም መቀየር፥ ይህ ሁኔታ ከተከሰት ጉበት በኩላሊት በኩል የሚያደርገውን የማጣራት እና ፅዳጅን የማስወገድ ሂደት አደጋ ላይ ነው ማለት ነው፤ የሽንት ቀለም ጠቆር ያለ ቢጫ አይነት ቀለም ሲኖረው። 5) የሰውነት መቆጣት፥ ሌላው የጉበት በሽታ ተጠቂ ስለመሆንዎት ማሳያ መንገድ ደግሞ የቆዳ ላይ መቆጣት ነው፤ የፈሳሽ በሰውነት ውስጥ በበቂ ሁኔታ አለመኖር ቆዳን በማስቆጣት የማሳከክ እና የማደብደብ ምልክት ያሳያል።ከዚህ ባለፈም ቆዳን ወደ ቢጫነት የመቀየርና በእግር የውስጠኛው ክፍልና የእጅ መዳፍን ማቅላትም ሌላው ምልክቱ ነው። 6) ተደጋጋሚ የሆነ የማቅለሽለሽ ስሜት፥ ጉበት ላይ የሚደርስ ጉዳት ጨጓራ ብዛት ያለው አሲድ እንዲረጭ በማድረግ ለጨጓራ ህመም ይዳርጋል፤ በዚህ ሂደት ውስጥም ተደጋጋሚ የማቅለሽለሽና የማስመለስ ችግር ይከሰታል። 7) የምግብ ፍላጎት ማጣትና መቀነስ፥ የምግብ ፍላጎት ማጣትና መቀነስ ዋናውና አንደኛው ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ ጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ማሳያ ሲሆን ልዩ የሆነ የህክምና ክትትልም ያስፈልገዋል። ከዚህ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ፈጣን የሰውነት ክብደት መቀነስ ደግሞ ለዚህ ማረጋገጫው ነው። ለዚህ ችግር የሚታዘዙ ንጥረ ምግቦች ታማሚውን ለማገገም ሊረዱት ይችላሉ። 8) በሰውነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የፈሳሽ ክምችት፥ ከባድ የጉበት ላይ ጉዳት ለበርካታ ጊዜያት በሰውነት ውስጥ፤ በተለይም በእግር፣ በጉልበት፣ በታችኛው የመጫሚያ ክፍል እና በሆድ አካባቢ ለበርካታ እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ የፈሳሽ ክምችትን ያስከትላል።

በተለይ በሴቷ በኩል? • ጤናማ የአኖኖር ዘይቤን መከተል • ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴን መተው • አነቃቂ መጠጦችን መቀነስ • አልኮልን መተው ወይም መቀነስ • አለማጤስ • የተመጣጠነ ምግብ • አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ • ክብደትን ማመጣጠን • የተለያዩ በሽታዎች ካሉ መታከም • ስኳር ህመም ካለ መታከም • የታይሮድ መጠን አነስተኛ ወይም ከፍተኛ መሆነ ለማስተካከል መሞከር • እራስን ከአባላዘር በሽታ መጠበቅ። ካለ ፈጥኖ መታከም • ሳይዘገዩ ለማርገዝ መሞከር • የጤና ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ስለመካንነትና ህክምናው ማወቅ ይፈልጋሉ? እንግዳውስ ይሄው ብለናል። ግን ግን ሸር ማድረጉን አደራ! (መካንነት ወይም መፀነስ አለመቻል) • ይህ ችግር Infertility ከፍ ሲልም sterility እየተባለ ይጠራል። Infertility በተለያየ ምክናየት መፀነስ ማርገዝ አለመቻል ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። Sterility ግን ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖርም ሲሆን ይህ አይነት ችግርም የመፈጠር እድሉ በጣም አነሳ ነው። ውድ ስለጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀት ቤተሰቦችና ተከታታዮች ዛሬ ካላይ የጠቀስኩትን ርዕስ ጠቅለል አድርጌ መካንነት በሚል እርስ ዙሪያ ይጠቅማል ያሉኩትን አጠር ያለ፡ ግልፅና አስተማሪ የሆነ መረጃ እንሆ ብያለሁ። ይህን መረጃ ከወደዱት ቢያጋሩት የብዙዎችን ጭንቀት እንደሚቀርፍ አልጠራጠርም። • አንድት እናት እድሚዋ ከ35 አመት በላይ ከሆናትና ለአድ አመት ያህል የመውለድ ሙከራ አድርጋ ካልተሳካ መከነች (ማርገዝ አትችልም) እንላለን። መፀነስ እንኳ ብትችል እድገት መጀመርና መቀጠል ካልቻለም እንድሁ የማርገዝ ችግር እንዳለባት ይቆጠራል። • እንደሚታወቀው እርግዝና ሂደት ነው። ደረጃ በደረጃ የሚከወን። ሴቷ ካሏት ሁለት ኦቫሪ (እንቁላል መፈጠሪያና ማደጊያ ክፍል) በየወሩ እንቁላል ትለቃለች። ይህ የሚሆነው የወር አበባ ማየት በጀመረች በ14ኛው ቀን ነው። በመቀጠል የምትለቀቀው እንቁላል ፊምብሪያ (የማህፀን ጣት) በሚባል የማህፀን ከፍል በመነጠቅ fallopian tube (የማህፀን ክንፍ) በሚባለው የማህፀን ክፍል ላይ ማለፍ ይጠበቅባታል። እዚሁ ክፍል ላይም የወንድ የዘር ፍሬ ደርሶ ውህደት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። በመቀጠል እቡጡ(zygote) ወደ ማህፀን ዋና ክፍል ወይም ሆድ ክፍሉ Endometrium (የማህፀን የውስጠኛ ክፍል) ላይ መቀመጥና እድገት መጀመር ይጠበቅባቸዋል። • እንግድህ መካንነት(ማርገዝ አለመቻል) የሚፈጠረው ከላይ ከዘረዘርናቸው ሄደቶች ወይም ክንውኖች አንዱ ወይም ሁለት ሶስቱ ሳይካሄድ ሲቀር ነው። በአጭሩ ችግሩ ከእንቁላሏ ጤንነት ወይም ከዘር ፍሬ ጤንነት አለያም ከጉዞአቸው መደናቀፍ ወይም ከቦታው አለመመቸት ጋር የተያያዘ ነው። • የመካንነት ምክናየት ከሴቷ ወይም ከወንዱ ችግር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሁለቱም። 1/3ኛ የሴቷ፡ 1/3ኛ የወንዱ፡ ቀሪው 1/3ኛ የሁለቱም ወይም የማይታወቅ ምክናየት ነው። በወንዶች በኩል የሚመጣው ችግር ከምን ጋር ሊያያዝ ይችላል? • Varicocele የሚባል ችግር ቀዳሚ ነው። ይህ ችግር ቀጫጭን የደም ቱቦዎች ተፈጥረው(viens) ከዘር ፍሬ የሚነሱ ስለሆኑ ያብጡና ትላልቅ ይሆናሉ። ይህም የዘር ፍሬ ለከፍተኛ ሙቀት ያጋልጠውና ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል። • የዘር ፍሬ ቅርፅ መበላሸት፡ በቁጥርና መጠን ማነስ • እንቅስቃሴው ዘገምተኛ ወይም ደካማ መሆን • የተለያዩ አካላዊ ጉዳት ወይም አደጋ ማጋጠም • አልኮል ጠጭ መሆን • የተለያዩ መድሀኒቶችን ተጠቃሚ መሆን • መርዛማ ለሆኑ ነገሮች መጋለጥ • ማጤስ • የኩላሊት ችግር • የሆርሞን መዛባት • የካንሰር ህክምና • እርጅና በሴቶች በኩል የሚመጣ ችግር ከምን ጋር ሊያያዝ ይችላል? • ብዙ ጊዜ በሴቶች በኩል የሚፈጠረው ችግር በኦቩሌሽን ወቅት የሚፈጠር ነው። እንቁላልን መልቀቅና አለመልቀቅ ጋር ይያያዛል።ኦቩሌሽን ፔሪድ ማለት የወር አበባ ማየት ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ሲቆጠር 14ኛዋ ቀን ነች። ይች ቀን እንቁላል የምትለቀቅባትና ለፅንስ ዝግጁ የምትሆንባት ቀን ነች። ስለዚህ በዚህ ቀን እንቁላል ካልተለቀቀ ፅንስ አይፈጠርም። የዚህ ምልክቱ ደግሞ የወር አበባ መዛባት አንዳንድ ጊዜም ፈፅሞ አለመኖር ነው። • እንቁላል ካለችበት ቦታ (ከኦቫሪ) እንዳትወጣ የሚያደርጋት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዋናዋናዎቹ ግን ትናንሽ እጢ መሳይ ነገሮች በኦቫሪ ውስጥ መፈጠራቸውና ኦቫሪ ከ40 አመት ቀድሞ ስራውን ሲያቆም ነው። • ሌላው ብዙ የተለመደ ባይሆንም የማህፀን ቀኝና ግራ ክፍሉ (ክንፍ) በተለያየ መንገድ በመዘጋቱ እንቁላሏ ከዘር ፍሬ ጋር እንዳትገናኝ በማድረጉ ሊሆን ይችላል። ይህ ችግር የዳሌ አጥንት ዙሪያ ኢንፌክሽን፡ ኢንዶሜትሪዎሲስና ከማህፀን ውጭ በተፈጠረ ፅንስ ሊከሰት ይችላል። • በተጨማሪም ማንኛውም በማህፀንና በኦቫሪ ውስጥ የሚፈጠር ችግርና የሚያድግ እጢ ምክናየት ይሆናል። ሴቶች እርግዝናቸውን እንድያጡ ወይም መካን ሆነው እንድቆዩ የሚያደርጉ ሌሎች አጋላጭ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው። • እድሜ • ጭንቀትና ውጥረት • ያልተመጣጠነ ምግብ • የሩጫ ልምምዶች • ከመጠን በላይ መወፈር • ከመጠን በታች መቅጠን • ማጤስ • ከመጠን ያለፈ መጠጥ • የአባላዘር በሽታ • የተለያዩ የጤና ችግሮን ለምሳሌ እጢ፡ የኦቫሪ ስራ ማቆም፡ የሆርሞን ችግርና ሌሎችም። • እርጅና/ እድሜ መጨመር ይህም በቂ እንቁላል አለማምረት፡ አነሳ እንቁላል መልቀቅ፡ ጤናማ እንቁላል አለመኖርና ሌሎችም ናቸው። ®በነገራችን ላይ አንድት ሴት እድሜዋ 30ን ካለፈ በየአመቱ የማርገዝ እድሏ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ስለዚህ ሴቶች እድሜአችሁን ሳትገድሉ እንድትወልዱ ይመከራል። እድሜ አሳልፎ የመጣ ርግዝና ሌላም ሌላ ችግር አለውና። ይህ ማለት ግን ማንኛዋም በእድሜ የገፋች ሴት ለመውለድ ትቸገራለች እያልን አይደለም። የመካንነት ህክምና ምንድን ነው? • ነፃ ሆኖ ጊዜ መስጠት ይጠበቃል። ውጤታማ ህክምናም አለው። 1. የመጀመሪያው ለእርግዝና ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ እንድችሉ ማድረግ ነው። ይህም ችግሩ ከምን እንደሆነ ለማወቅ ያግዛል። ለምሳሌ የማይዛባ የወር አበባ ኡደት ላላት ሴት የሚከተለውን ምሳሌ እንይ። ለምሳሌ ወይዘሮ ከበቡሽ የወር አበባዋ በ18/09/12 መምጣት ቢጀምር ዛሬ ማለት ነው። ደግሞም በየ28 ቀኑ የሚመጣ ወጥ ከሆነ፡ 02/10/12 ቀን ኦቩሌሽን ፔሬድዋ ነው። ከበቡሽ ማርገዝ ከፈለገች በሚከተሉትን ቀናት የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም ይኖርባታል። 29/09/12, 30/09/12, 01/10/12, 02/10/12, 03/10/12, 04/10/12 እና 05/10/12 ዓ.ም. ከበቡሽ ምንም አይነት ችግር ከሌለባት የትዳር አጋሯም ጤናማ ከሆነ እነዚህን ቀናት ሳትፀንስባቸው ልታልፍ አትችልም። በተለይ 02/10/12 ዓ.ምን። 3እጅ መካንነትም ከዚህ አለመመጣጠን ጋር የተያያዘ ነው። 2. የተለያዩ መድሀኒቶችን በመጠቀም መካንነትን ማከም ይቻላል። ለምሳሌ Clomphene እና Serophene ውጤታማ ናቸው። መካን ነን ከሚሉ ግማሽ ያህሎቹ ሴቶች በClomphene መድሀኒት ውጤት ያመጣሉ። (እንድያረግዙ ያደርጋቸዋል)። ይህን መድሀኒት የተጠቀመች ሴት መትያ ልጆችን የመውለድ እድሏን ይጨምራል። 3. የተዘጋ የማህፀን ክፍልን በቀዶ ጥገና በመክፈት እንቁላሏና የዘር ፍሬ በቀላሉ እንድገናኙ በማድረግ ይታከማል። 4. የዘር ፍሬ እንቅስቃሴ ደካማ ከሆነ ከወንዱ ወስዶ ሴቷ ውስጥ በመሳሪያ በመጨመር የዘር ፍሬዎቹ በራሳቸው እንድገናኝ በማድረግ ይታከማል። 80% ውጤታማ ነው። 5. ከላይ ያለው ካልተሳካ በኦቩሌሽን ወቅት ስፐር ሴሉን በመውሰድ ከእንቁላሏ አጠገብ በማስቀመጥ ይታከማል። እጅግ ውጤታማ ነው። 6. ከላይ ባሉት እንደ አጋጣሚ ባይሳካ በውጮቹ ዘንድ እንቁላልንና የዘር ፍሬን ውጭ ላይ በማሽን ውስጥ በማገናኝት ውህደቱን በመፍጠር የመጨረሻው ህክምናም ይሞከራል። መካንነትን እንደት መከላከል ይቻላል?

➥ በህፃናት ላይ የህክምና እርዳታ ማግኘት የሚፈልጉ ዘላቂ ምልክቶች የሚባሉት፦ 📌📌 አዲስ የተወለዱ ሕፃናት እስከ 12 ሳምንታት ድረስ 100.4F (38 C) ትኩሳት 📌📌 በማንኛውም እድሜ ላይ ያለ ልጅ ከሁለት ቀን በላይ የሚቆይ ትኩሳት 📌📌 ራስ ምታት, 📌📌 የጉሮሮ ህመም ወይም ሳል የመሳሰሉ ከባድ ምልክቶች 📌📌 የመተንፈስ ችግር 📌📌 የጆሮ ህመም 📌📌 በጣም ግራ መጋባት 📌📌 ያልተለመደ እንቅልፍ እና 📌📌 የምግብ ፍላጎት ማጣት እነዚህ ምልክቶች ለቀናቶች ከቀጠሉ የህክምና እርዳታን ይፈልጋሉ። ✍️ የጉንፋን መንስኤዎች ➥ ብዙ አይነት ቫይረሶች ጉንፋን ሊያስከትሉ ቢችሉም በጣም የተለመዱት መንስኤዎች rhinoviruses ናቸው። ቀዝቃዛ ቫይረስ በአፍዎ፣ በአይንዎ ወይም በአፍንጫዎ በኩል ወደ ሰውነትዎ ይገባል። የታመመ ሰው ሲያስል፣ ሲያስነጥስ ወይም ሲያወራ ቫይረሱ በአየር ውስጥ ባሉ ጠብታዎች ሊተላለፍ ይችላል። እንዲሁም ጉንፋን ካለበት ሰው ጋር በእጅ ለእጅ በመገናኘት ወይም የተበከሉ ነገሮችን ለምሳሌ የምግብ ዕቃዎችን፣ ፎጣዎችን፣ መጫወቻዎችን ወይም ስልኮችን በመጋራት ይተላለፋል። ከእንደዚህ አይነት ግንኙነት በኋላ አይኖችዎን, አፍንጫዎን ወይም አፍዎን ከነካዎ, ጉንፋን ሊይዝዎት ይችላል። ➥ ለጉንፋን የመጋለጥ እድሎችን የሚጨምሩ አንዳንድ ሁኔታዎች አሉ እነዚህም፦ 1, ዕድሜ - ጨቅላ ህጻናት እና ትንንሽ ልጆች ለጉንፋን በጣም የተጋለጡ ናቸው, በተለይም በህጻናት እንክብካቤ መስጫ ቦታዎች ውስጥ ጊዜ ካሳለፉ። 2, የተዳከመ የበሽታ መቋቋም ስርዓት - ሥር የሰደደ በሽታ ወይም ሌላ የተዳከመ የበሽታ መቋቋም ስርዓት አደጋን ይጨምራል። 3, የዓመቱ/የጊዜ ሁኔታ - ልጆችም ሆኑ ጎልማሶች በበልግ እና በክረምት ለጉንፋን የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፣ ነገር ግን በማንኛውም ጊዜ ጉንፋን ሊያዙ ይችላሉ። 4, ማጨስ - የሚያጨሱ ከሆነ በጉንፋን የመያዝ ዕድላችሁ ከፍ ያለ ነው። 5, የውሎ ሁኔታ - እንደ ትምህርት ቤት ባሉ አካባቢ ከሆናችሁ ለጉንፋን ለሚዳርጉ ቫይረሶች መጋለጣችሁ አይቀርም። ➥ አንዳንድ የህመም ችግሮች ከጉንፋንዎ ጋር ሊከሰቱ ይችላሉ እነዚህም፦ 🔷 አጣዳፊ የጆሮ ኢንፌክሽን (otitis media) - ይህ የሚከሰተው ባክቴሪያ ወይም ቫይረሶች ከጆሮ ማዳመጫው በስተጀርባ ባለው ክፍተት ውስጥ ሲገቡ ነው። የተለመዱት ምልክቶች የጆሮ ህመም ወይም ጉንፋን ተከትሎ ትኩሳት መመለስን ያካትታሉ። 🔷 አስም - ምንም እንኳን አስም ባይኖርቦዎትም እንኳን ጉንፋን የትንፋሽ እጥረት ሊያመጣ ይችላል። አስም ካለብዎ ጉንፋን ሊያባብሰው ይችላል። 🔷 አጣዳፊ የ sinusitis - በአዋቂዎችም ሆነ በልጆች ላይ፣ የማይፈታ ጉንፋን ወደ እብጠት እና ህመም (መቆጣት) እና የ sinuses ኢንፌክሽን ያስከትላል። 🔷 ሌሎች ኢንፌክሽኖች - ጉንፋን ወደ ሌሎች ኢንፌክሽኖች ሊያመራ ይችላል ፣ እነዚህም የጉሮሮ መቁሰል ፣ የሳንባ ምች እና ክሮፕ ወይም ብሮንካይተስ ይከሰታሉ። እነዚህ ኢንፌክሽኖች በዶክተር መታከም አለባቸው። ✍️ መከላከያ መንገዶች ➥ ለጉንፋን ምንም አይነት ክትባት የለም፣ ነገር ግን የጉንፋን ቫይረሶች ስርጭትን ለመግታት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይችላሉ። 📌📌 እጅዎን ይታጠቡ- ቢያንስ ለ 20 ሰከንድ እጅዎን በደንብ እና ብዙ ጊዜ በሳሙና እና በውሃ ይታጠቡ። ሳሙና እና ውሃ ከሌሉ ቢያንስ 60% አልኮልን የያዘ አልኮል ላይ የተመሰረተ የእጅ ማጽጃ ይጠቀሙ። ለልጆቻችሁ የእጅ መታጠብን አስፈላጊነት አስተምሯቸው። ባልታጠበ እጅ አይንን፣ አፍንጫዎን ወይም አፍዎን ከመንካት ይቆጠቡ። 📌📌 ነገሮችዎን ያጽዱ - ከፍተኛ ንክኪ ያላቸውን እንደ የበር እጀታዎች፣ የመብራት መቀየሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የኩሽና እና የመታጠቢያ ቤት ጠረጴዛዎችን በየቀኑ ያጽዱ። በተለይም ከቤተሰብዎ ውስጥ አንድ ሰው ጉንፋን ሲይዝ ይህ በጣም አስፈላጊ ነው። 📌📌 የልጆችን መጫወቻዎች በየጊዜው ይጠቡ. 📌📌 ሲያስሉ ይሸፈኑ 📌📌 ያገለገሉ እቃዎችን ወዲያውኑ ይጣሉ ፣ ከዚያ እጅዎን በደንብ ይታጠቡ። 📌📌 በማስነጠስ ወይም በክርንዎ መታጠፊያ ላይ ማሳል እና ከዚያ እጅዎን ይታጠቡ። 📌📌 የመመገቢያ ዕቃዎችን ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር አይጋሩ። እርስዎ ወይም ሌላ ሰው ሲታመሙ የራስዎን ብርጭቆ ወይም የሚጣሉ ኩባያዎችን ይጠቀሙ። ጉንፋን ካለባቸው ሰዎች ይራቁ። ጉንፋን ካለበት ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነትን ያስወግዱ። 📌📌 አይኖችዎን፣ አፍንጫዎን እና አፍዎን ከመንካት ይቆጠቡ። 📌📌 በደንብ መመገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና በቂ እንቅልፍ መተኛት ለአጠቃላይ ጤናዎ ጠቃሚ ነው።

✍️ " ጉንፋን መንስኤ እና መፍትሄ" 🔷 "ሼር በማድረግ ሌሎችንም አስተምሩ" ➥ የተለመደው ጉንፋን በአፍንጫዎ እና በጉሮሮዎ (የላይኛው የመተንፈሻ አካላት) ላይ የሚከሰት የቫይረስ ኢንፌክሽን ነው። ብዙውን ጊዜ ምንም ጉዳት የለውም። ብዙ አይነት ቫይረሶች ጉንፋን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ጤናማ አዋቂዎች በየአመቱ ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ በጉንፋን ሊጠቁ ይችላሉ። ጨቅላ ህጻናት እና ትንንሽ ልጆች ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ በጉንፋን ሊጠቁ ይችላል። ብዙ ሰዎች በአንድ ሳምንት ወይም በ10 ቀናት ውስጥ ከጉንፋን ይድናሉ። በሚያጨሱ ሰዎች ላይ ምልክቶቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ። በአጠቃላይ ለጉንፋን የህክምና እርዳታ አያስፈልግዎትም። ሆኖም ምልክቶቹ ካልተሻሻሉ ወይም እየባሱ ከሄዱ መታከም ያስፈልጋል። መቼም ሰሞኑን እርስዎ ወይም በቅርበት የሚያውቋቸው በርካታ ሰዎች 'በኃይለኛ ጉንፋን' ተይዘው ትኩስ ነገር ሲወስዱ ተመልከተዋል። ሌሎችም ከወረርሽኙ ራሳቸውን ለመታደግ መፍትሔ ያሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው። ይህ ጉንፋን መሰል ሕመም በርካቶችን ይዞ አንዳንዶችን በከባድ ህመም አሰቃይቶ ቢያልፍም፣ ሌሎችን ክፉኛ አጎሳቁሎ አልጋ ላይ አውሏቸው የጎዳቸው ስዎችም አሉ። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እያሻቀበ ይገኛል። ለነገሩ ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ እየተስተዋለ ይገኛል። ልዩነቱ የተለያዩ አገራት በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ ለማደጉ ምክንያት የሚያደርጉት ኦሚክሮን የተሰኘውን አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያን ነው። ➥ የሰሞኑ ጉንፋን የሚያስከትለው ሕመም 📌📌 ከፍተኛ ትኩሳት 📌📌ጠንካራ ሳል 📌📌 ብርድ ብርድ ማለት 📌📌 የመገጣጠሚያ ህመም 📌📌 የጀርባ ህመም 📌📌 የጡንቻ ህመም 📌📌 ምግብ ፍላጎት መቀነስ 📌📌 ኃይለኛ ራስ ምታት የሚከሰቱ ምልክቶች ናቸው። ➥ ጥንቃቄ የጎደለው የሰዎች መሰባሰብና ንክኪ መበራከትና የእንቅስቃሴ መጨመር 'ለሰሞነኛው ህመም' ከሰዎች ወደ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት እንዲዛመት አድርጓል። ይህ በሽታ ኮሮናቫይረስ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም በሽታው የተለየ ባህሪ አለው ለማለት ጥናት ይፈልጋል። ሆኖም ያሁኑ ገንፋን ለየት ያለ ነገር" ጠንከር ያለ ሳል፣ ጠንከር ያለ ተኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የወገብ ህመም፣ ቁርጥማት የማሽተት እና የማጣጣም ስሜትን ማሳጣት የሚስተዋሉት ምልክቶች ናቸው። ኮቪድም ከኮቪድ ውጪም ያሉ ቫይረሶች እንደዚህ አይነት ምልክቶች ያስከትላሉ። ነገር ግን ከሌላው ጊዜ የሚለው ይሄ ቫይረስ ብዙ ስዎችን መያዙ እና ጠንከር ያሉ ምልክቶች ማሳየቱ ነው። ምን አልባት እንዚህ ምልክቶች ሁሉም ሰው ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ላያደርጉት ይችላሉ። ብዙ ስዎች በቤት ውስጥ ያገግማሉ። ➥ ለመከላከል ዘወትር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ንክኪዎችን ይቀንሱ/ጥንቃቄ ያድርጉ፣በርካታ ሰዎች ከሚገኙባቸው ቦታዎች ይራቁ፣ሲያስነጥሱ እና ሲያስሉ አፍና አፍንጫን በአግባቡ መሸፈን እና የኮቪድ መከላከያን መከተብ ያስፈልጋል። ➥ እድሜያቸው ከሦስት ወር በታች የሆኑ ህጸናት እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን አዋቂ ሰዎች ይህ ሰሞነኛ በሽታ ክፉኛ ሊጎዳቸው ይችላል፣ ለምሳሌ ሰኳር፣ የደም ግፊት የመሳሰሉ ተጨማሪ ህመም ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ወደ ከፋ ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ። በተለይ "ከሦሰት ወር በታች ያሉ ህጻናት ደግሞ የአየር ቧንቧቸው እና አፍንጫቸው በጣም ጠባብ ስለሆነ በቀላሉ የመታፈን፣ ለመተንፈስ የመቸገር፣ የመጨናነቅ እና እስከ ሆስፒታል ደረጃ ሊያደርሳቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ከጉንፋን መሰል ሕመሞች ግማሹ ኮሮናቫይረስ ሊሆኑ ይችላሉ። ➥ "በተለይ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ሌሎች ህጻናት ወደ ጨቅላዎቹ በሽታውን ወይም ቫይረሱን ይዘው እንዳይመጡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።በሌላ በኩል ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው እና በሽታ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ስዎችም በበሽታው ከፍ ላለ የመተንፈስ ችግር ሊዳርግም ይችላል። በመሆኑም የትንፋሽ ማጠር ወይም ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፣ ከፍተኛ ትኩሳት እና መድከም ካለ ምን አልባት በሽታው የከፋ ደረጃ መድረሱን ያሳያል። 🔷 ለልጆችና ለህፃናት የቤት ውስጥ ሕክምና 📌📌 ጨው ባለው ለብ ያለ ውሃ አፍንጫቸውን ማጽዳት 📌📌 ትኩሳት የሚቀንስ መድኃኒት መስጠት 📌📌 ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት 📌📌 ንጽህናቸውን መጠበቅ 📌📌 ተጨማሪ ፈሳሽ እንዲወስዱ ማድረግ ➥ ይህንን ህመም ለመከላከል በሚል በሐኪም ካልታዘዘ በስተቀር ፀረ ባክቴሪያዎችን ወይም አንቲባዮቲክስን መወሰድ በፍጹም ተገቢ አደለም። ለምሳሌ አሞክሳሲሊን፣ አዚትሮማይሲን፣ ኦግመንቲን የሚባሉ አንቲባዮቲክሶች አለመጠቀም ነው ሚመከረው። ምክንያቱም እነዚህ ባክቴሪያ እንጂ ቫይረስ የሚያጠፉ መድኃኒቶች ስላልሆኑ ሐኪም እስካላዘዘልን ድረስ መጠቀም የለብንም። ከዚህ ባሻገር በበሽታው የተያዙ ጨቅላ ህጻናት በቤት ውስጥ ለማከም 'ለብ ያለ' ውሃ በጨው አድርጎ ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ በጠብታ መልክ በአፍንጫው መስጠት እንዲሁም የአፍንጫ ንጽህናቸውን በአግባቡ መጠበቅ ይገባል። ታዲጊዎች ደግሞ በቂ እረፍት መውሰድን ጨምሮ እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ማር፣ ዝንጀብል ያላቸውን ምግቦች መመገብ የበሽታ መከልከል አቅምን በማሳደግ በሽታውን ለመቋቋም ያግዛል። ለአዋቂዎችም ይሁን ለህጻናት ከሰውነታቸው የሚያስወጡትን ፈሳሽ ለመተካት ትኩስ ነገሮችን መጠጣት፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ወሳኝ ነው። 🔷 ለታዳጊዎችና ለአዋቂዎች የቤት ውስጥ ሕክምና 📌📌 ትኩስ መጠጦችን ደጋግሞ መውሰድ 📌📌 ነጭ ሽንኩርት፣ ማር እና ዝንጅብል መውስድ 📌📌 እረፍት ማድረግ እና 📌📌 የትኩሳት እና የራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ ➥ ሰውነታችን ለእንዲህ አይነት በሽታ የሚጋለጠው ወይም ከተጋለጠ በኋላ የከፋ ሕመምና ጉዳት የሚደርስበት የበሽታ መከላከል አቅም ሳይዳብር ወይም ሲዳከም ነው። ስለዚህ የሰውነት በሽታ የመከላክል አቅምን ለማሳደግ ደግሞ አዘውትሮ አትክልት እና ፍራፍሬን መመገብ ሁነኛ መፍትሄ እንደሆነና ይህም ወቅት ለሚያመጣቸው በሽታዎች በቀላሉ 'እጅ' ላለመስጠት ያግዛል። በሰሞነኛው በሽታ የተያዙ ደግሞ የአትክልት ሾርባዎችን፣ እንደ ተልባ፣ ሰሊጥ፣ ለውዝ፣ ኑግን የመሳሰሉ የቅባት እህሎችን ከትኩስ መጠጦች ጋር መውሰድ ከበሽታው በፍጥነት ለማገገም ይረዳል። ✍️ የጉንፋን ምልክቶች ➥ የጉንፋን ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ለጉንፋን መንስኤ ቫይረስ ከተጋለጡ ከአንድ እስከ ሶስት ቀናት በኋላ ይታያሉ። እነዚህም፦ 📌📌 ንፍጥ 📌📌 በጉንፋን የተዘጋ ጉሮሮ እና አፍንጫ 📌📌 ሳል 📌📌 መጨናነቅ 📌📌 ትንሽ የሰውነት ህመም ወይም ቀላል ራስ ምታት 📌📌 ማስነጠስ 📌📌 ዝቅተኛ-ደረጃ ትኩሳት እና 📌📌 ከአፍንጫዎ የሚወጣው ፈሳሽ በጠራ ሁኔታ ሊጀምር እና ጥቅጥቅ ያለ እና ቢጫ ወይም አረንጓዴ ሊሆን ይችላል። ይህ ማለት ብዙውን ጊዜ የባክቴሪያ በሽታ አለብዎት ማለት አይደለም። ➥ በአጠቃላይ, ለጉንፋን የሕክምና እርዳታ አያስፈልግዎትም። ይሁን እንጂ ህመሙ ከፍተኛ ከህነ እና እየተባባሰ የሚመጣ ምልክቶች ካለው ማለትም፦ 📌📌 ከሶስት ቀናት በላይ የሚቆይ ከ101.3F (38.5C) በላይ የሆነ ትኩሳት 📌📌 የትንፋሽ እጥረት 📌📌 ማስለቀስ 📌📌 ከባድ የጉሮሮ መቁሰል እና 📌📌 ራስ ምታት ፦ እነዚህ ምልክቶች ካልጠፉ የህክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል።

#ጥንቃቄ የጤና ባለሙያዎች ህብረተሰቡ ለኮቪድ -19 የሳል ማስታገሻ በሚል ከሚወሰዱ መድኃኒቶች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል። ከኮቪድ - 19 መስፋፋትን ተከትሎ በየፋርማሲዎች የሳል ማስታገሻ መድኃኒ
+1
#ጥንቃቄ የጤና ባለሙያዎች ህብረተሰቡ ለኮቪድ -19 የሳል ማስታገሻ በሚል ከሚወሰዱ መድኃኒቶች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል። ከኮቪድ - 19 መስፋፋትን ተከትሎ በየፋርማሲዎች የሳል ማስታገሻ መድኃኒቶች ፍላጎት መጨመሩን ባለሙያዎች እየገለፁ ይገኛሉ። የአለርት ሆስፒታል የፋርማሲ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አሸብር ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ ከኮቪድና ጉንፋን ወረርሽኞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካቶች ያለሐኪም ምክር ከየፋርማሲው የሳል ማስታገሻ መድኃኒቶችን እየወሰዱ ነው ብለዋል። ይህ ልምድ ለተጓዳኝ በሽታዎች መባባስ የሚዳርግ በመሆኑ መጠንቀቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በተለይ በከተሞች ላይ የጉንፋን በሽታ ይዞኛል የሚሉ በርካታ ሰዎች “ፍሉ ስቶፕ” የተሰኘውን ማስታገሻ መድኃኒት በመግዛት ያለሐኪም ምክር እየወሰዱ ይገኛሉ ያሉት አቶ ዮናስ፤ ተመሳሳይ መድኃኒቶችን ያለባለሙያ ምክር መውሰድ በተለይ የደምግፊት፣ ስኳር፣ አስምና ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ላለባቸው ሰዎች አደገኛ ነው ብለዋል። ተመሳሳይ መድኃኒቶች በመንግሥት ሆስፒታሎች በሚገኙ ፋርማሲዎች ውስጥ ያለሐኪም ትዕዛዝ እንደማይሸጡ የጠቆሙት አቶ ዮናስ፣ በግል ፋርማሲዎች ግን መድኃኒቱን ለጠየቀ ሁሉ የመሸጥ ልምድ እንዳለ አስረድተዋል። ሰዎችም የጉንፋን ምልክት ስላሳዩ ብቻ ያለሐኪም ምክር ማስታገሻዎችን መውሰዳቸው ለከፋ የጤና ችግር እንደሚያጋልጥ በማወቅ በቅድሚያ መመርመር ይኖርባቸዋል ብለዋል። ያለበለዚያ ግን ለውስብስብ የጤና ችግር የመዳረግ እድላቸው ይሰፋል ሲሉ አሳስበዋል። ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-01-03 ምንጭ፦ ኢፕድ

ቡግንጅ(Boils) ቡግንጅ የምንለው በባክቴሪያ(Staphylococcus aures) የሚመጣ የቆዳ በሽታ ሲሆን ቆዳችን በባክቴሪያው ሲጠቃ በእባጩ ውስጥ መግል እና የሞቱ የቆዳ ክፍሎች ይይዛል፡፡ ✅የቡ
ቡግንጅ(Boils) ቡግንጅ የምንለው በባክቴሪያ(Staphylococcus aures) የሚመጣ የቆዳ በሽታ ሲሆን ቆዳችን በባክቴሪያው ሲጠቃ በእባጩ ውስጥ መግል እና የሞቱ የቆዳ ክፍሎች ይይዛል፡፡ ✅የቡግንጅ በሽታ ምልክቶች 📌 እያደገ የሚሄድ እባጭ 📌 ከፍተኛ የሆነ ህመም 📌 ትኩሳት 📌 አካባቢው ላይ ያለ ቆዳ መቅላት እና መጠንከር 📌 ማሳከክ 📌 በዙሪያው ተጨማሪ እባጮች መኖር ✅የቡግንጅ በሽታ መንስኤዎች 📌 በሽታ የመከላከል ሥርዓት ላይ ችግር መኖር(immunity deficiency) 📌 የስኳር በሽታ 📌 ደካማ የአመጋገብ ሥርዓት 📌 ንጽህናን በአግባቡ አለመጠበቅ 📌 ቆዳ ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ 📌 በበሽታው ከተያዘ ሠው ጋር ንክኪ መኖር ✅የቡግንጅ በሽታ በቤት ውስጥ እንዴት ማከም ይቻላል 📌 የግል ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ 📌 በቡግንጅ ላይ ትኩስ ፎጣ መያዝ 📌 እርድን አፍልቶ በቀን አንድ ብርጭቆ መጠጣት 📌 የጉሎ ዘይት መቀባት 📌 ቀይ ሽንኩርት በክብ ቆርጦ ቦታው ላይ ማስቀመጥ 📌 የተቀቀለ እንቁላል ነጩን ክፍል ቁስሉ ላይ መሸፈን 📌 ወተት መጠጣት

ምላሳችን ስለጤናችን ምን ይነግረናል? ምላሳችን እንደ አንድ የሰውነታችን ክፍል ስለ ጤናችን በርካታ ጉዳዮችን ይናገራል። የምላሳችን ቀለም በመመልከት ብቻ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣችንን መረዳት እንችላለን። ይሁን እንጂ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የምላስ ቀለም ለውጦች ሲያጋጥሙን ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋማት በማምራት ሀኪሞችን ማማከር ተገቢ ነው። 1. ቀላ ያለ ምላስ – ምላሳችን ይህን አይነት ቀለም ሲኖረው ሰውነታችን እንደ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ እና አይረን ያሉ ንጥረ ነገሮች እጥረት እንዳጋጠመው የሚያሳይ ነው። – አንዳንድ የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎች ደግሞ ይህ ሁኔታ በአንድ በተወሰነ የሰውነታችን ክፍል ሙቀት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ይላሉ። – የጥርስ ሳሙና፣ መድሃኒት አልያም አሲዳማ ምግቦች በአፍ ውስጥ ከሚፈጥሩት ውህደት ጋር ተያይዞም ሊከሰት ይችላል። 2. ሀምራዊ ምላስ – ለጉሮሮ ቁስል (ብሮንካይትስ) መጋለጥን የሚያሳይ ነው። – ሰውነታችን በቂ ኦክስጂን አለማግኘቱንም ያመላክታል። – ዝቅተኛ የደም ዝውውር እና ከፍተኛ የኮሊስትሮል መጠንንም ይጠቁማል። – በጣም የቀዘቀዙ ምግቦችን እንዲሁም ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል መውሰድ ደግሞ ለችግሩ ሊያጋልጥ ይችላል። 3. ሻካራ እና ቢጫ ምላስ – አነስተኛ የሆሞግሎቢን መጠንን ያሳያል። – ድካም እና መዛል፣ ከሳንባ እና ትልቅ አንጀት ጋር የተያያዙ ችግሮችንም ያመለክታል። – ዝንጅብል፣ ቀረፋ እና ነጭ ሽንኩርት መጠቀም ከዚህ ችግር ለመውጣት ይረዳል። – የሄሞግሎቢን መጠንን ከፍ ለማድረግ እንደ ስፒናች፣ ቀይ ስር፣ አፕል፣ ቀይ ስጋ፣ ዘቢብ፣ ማንጎ፣ ለውዝ እና የመሳሰሉ የምግብ አይነቶችን መመገብ ይመከራል። 4. ጥቁር ምላስ – ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰው ልጆች ምላስ ወደ ጥቁርነት እና ጸጉር የበዛበት መሆን ይሸጋገራል። – ጥቁርና ጸጉር የሚያወጣ ምላስ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ነው የሚነገረው። – በምላስ ላይ የሚወጣው ጸጉር በአፍ ውስጥ ለባክቴሪያዎች መራባትና ለቆሻሻዎች መጠራቀሚያነት በማገልገል በርካታ የጤና ችግሮችን ያስከትላል። 5. ነጭ ምላስ – በምላስ ጸጉሮች ባክቴሪያዎች መሰግሰጋቸውን ያመለክታል። – የሞቱ ህዋሳት እና ቆሻሻዎች በምላሳችን ጸጉሮች መመሸጋቸውንም ያመለክታል። – ሲጋራ ማጨስ፣ የውሃ ጥም፣ የአፍ መድረቅ እና መሰል ምክንያቶች ለችግሩ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። 6. ቀይ ምላስ – በአብዛኛው በህጻናት ጤና ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ያሳያል። – የእንጆሪ ቀለም ያለው ምላስ ደግሞ ህጻናት ለትኩሳት እና የደም ስሮችን ለሚያጠቃ በሽታ መጋለጣቸውን ያመለክታል። – ይህ አይነት ቀለም ያለው ምላስ በወጣቶች ላይ ብዙ ጊዜ አይታይም። – ምላሳችን በጣም ለስላሳና ቀይ ከሆነ የቫይታሚን ቢ በተለይም የኒያሲን እጥረት እንዳጋጠመን ያሳያል። 7. ግራጫ ምላስ ይህ ደግሞ ሜላኖማ ለተባለ የቆዳ ካንሰር በሽታ መጋለጥን ያሳያል። 8. ቀይ ነጠብጣቦች የበዙበት ምላስ – በምላስ ላይ የሚታዩ ቀይ ነጠብጣቦች የበርካታ ችግሮች ምልክት መሆናቸው ይነገራል። – ከቫይታሚን ሲ የሚገኙ ባዮፍላቮዶይሶችን በበቂ ሁኔታ አለማግኘትን ያመለክታል። – ትኩስ መጠጦችን ማዘውተር ለችግሩ በምክንያትነት ይጠቀሳል። – የአስም እና የተለያዩ አለርጂዎች ምልክትም ነው። 9. ደረቅ ምላስ – ሰውነታችን በርካታ ንፍጥ እያመረተ መሆኑን ያሳያል። – ችግሩን ለመፍታት ከስኳር ምርቶችና ከወተት ተዋጽኦዎች መራቅ ያስፈልጋል። – ጭንቀት ምራቅ አመንጪ እጢዎች እንዲያብጡ በማድረግ ምላስ እንዲደርቅ የማድረግ አቅም አለው። – አንድ ብርጭቆ የሎሚ ውሃ መጠጣት የምላስ ድርቀትን ለማስወገድ ይረዳል። 10. ያበጠ ምላስ – ለአለርጂ ወይም ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያመለክታል። – የቫይታሚን ቢ 12 እጥረትንም ያሳያል።

የደም ግፊት መድሃኒት ማቋረጥ እና መዘዙ ******* የደም ግፊት መድሃኒት ጀምሮ ማቋረጥ አብዛኛውን ጊዜ የደም ግፊት ታማሚዎች መድሃኒት ከጤና ባለሙያ ከታዘዘላቸው በኋላ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ መድሃኒት ያቋርጣሉ :: ይህ ደሞ ለከፋ የጤና እክል ሲጋለጡ እንመለከታለን:: 🔹የደም ግፊት መድሃኒት ጀምሮ ማቋረጥ እንዴት ይከሰታል? ▪️ከግንዛቤ እጥረት፦ለበሽታው በቂ የሆነ ግንዛቤ ካለመኖር የተነሳ መድሃኒትን ይቋረጣል፣ ▪️በመድሃኒቱ የጎንዮሽ ችግር ፣ ▪️ወደ ተለያዩ የእምነት ተቋማት በመሄድ፣ ▪️አሁን ተሽሎኛል ብሎ ማሰብ፣ ▪️ተገቢውን የህክምና ክትትል ባለማድረግ፣ ▪️በተለያዩ ምክንያቶች የመድሃኒት አቅርቦት አለማግኘት፣ 🔹መድሃኒት ከተጀመረ በኋላ ማቋረጥ ይቻላል? አንድ ጊዜ መድሃኒት ሃኪም ካዘዘ በኋላ ሃኪሙ እራሱ ይቁም ካላለ በስጠቀር ማቋረጥ ፈፅሞ የተከለከለ ነው 🔸መድሃኒት በድንገት ባቋርጥ ምን ችግር ይመጣል? ያለሃኪም ትዕዛዝ መዳኒት የሚያቋርጡ ታካሚዎች እስከ ሞት የሚዳርግ ችግር ውስጥ ይገባሉ፤ ከነዚህም መካከል ▪️ደም በጭንቅላት ውስጥ የመፍሰስ አደጋ ▪️የልብ ድካም ▪️የኩላሊት ደም ቧንቧ መጥበብ ▪️የአይን ላይ ደም ስሮች መወፈር እና ለ ድንገተኛ ዓይነስውርነት መጋለጥ ▶️ድንገተኛ ሞት 🔹የደም ግፊትን በሽታን ያለ መድሃኒት መቆጣጠር ይቻላል? የደም ግፊት በሽታ ከምንቆጣጠርበት ዘዴዎች ውስጥ አንዱ መድሃኒትን ሳይጠቀሙ በህይወት ስልት(life style)ወይም የአኗኗር ዘይቤያችንን በመቀየር ነው:: 🔹የደም ግፊትን ያለመድሃኒት መቆጣጠር ያለበት ማነው? በሃኪም ትዕዛዝ መሰረት ግፊቱ የመዳኒት መውሰድ ደረጃ ላይ ያልደረሰ ሰው ብቻ 🔹ምን አይነት የአኗኗር ዘይቤ ልከተል? ▪️ውፍረት መቀነስ ▪️የአመጋገብ ስርዓትን መቀየር (አትክልት እና ፍራፍሬዎችን መመገብ ቅባት የበዛበት ምግብ ማስወገድ) ▪️ጨው ያልበዛበት ምግብ መመገብ ▪️አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ▪️አልኮልን አዘውትሮ አለመጠቀም እና ለቀን ከተፈቀደው መጠን አለማለፍ ▪️ሲጋራ አለማጨስ:- ይህ ግፊትን ባይቀንስም ነገር ግን ከበሽታው ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የልብ ህመም ይቀንሳል። 🔥ስለዚህ የደም ግፊትን መድሃኒት ማቋረጥ ለተለያዩ የጤና እክሎች ስለሚዳርግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ለብዙዎች እንዲደርስ እባክዎ #ሼር ያድርጉ።

#መደንዘዝ .........! 💊ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ጠቃሚ የጤና መረጃችን ከጭን እስከ እግር ጣት ጫፍ ድረስ ስለሚፈጠር #የመደዘዝ፡ #የመጠዝጠዝ፡ #የማቃጠልና #የስሜት መጥፋትን አስመልክቶ ነው። • ይህ ችግር በዋናነት ሁለት ምክናየቶች አሉት። 1. ወደ እግር የሚሰራጨው የደም መጠን መቀነስና 2. እግርን የሚቆጣጠረውና ወደ እግር የተዘረጋው የነርቭ ክፍል ጉዳት ሲደርስበት ነው። #ከነዚህ ዋና ዋና ምክናየቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ተጨማሪ ምክናየቶችም አሉ። • የደም መርጋት • ቅዝቃዜ • የአጥንት መሳሳት • የድስክ መሸራተት • ብዙ አልኮል መጠጣት • የቫይታሚን ቢ 12 ማነስ • ኢንፌክሽን • የተለያየ አካላዊ ጉዳት በእግርና ጀርባ ላይ ሲደርስ • የሚሰራጭ የካንሰር አይነት • የተለያዩ በሽታዎች እንደ ደምግፊት፡ ስኳር፡ ሪህ፡ የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን፡ የኩላሊት ችግር፡ የጉበት ችግር፡ ስትሮክ፡ ሌሎችም • ለብዙ ሰአት መቀመጥና እግርን አነባብሮ መቀመጥ #ውድ የኛ ቤተሰቦች የመደዘዝና የመጠዝጠዝ ስሜቱ ጊዜአዊ ከሆነ በቀላሉ የሚለቅና የሚስተካከል ችግር ሲሆን ለረጅም ጊዜ የቆየና እየባሰ የሚሄድ የመደዘዝና የመጠዝጠዝ ስሜት ካለና እየቆየም ሰገራንና ሽንትን መቆጣጠር መቸገር፡ እግርን መቆጣጠርና ማንቀሳቀስ አለመቻል፡ የንግግር መቆራረጥና ግራ መጋባት ጋር ከሆነ ግን አስቸኳይ የጤና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል። #የእግር መደንዘዝ ከጀርባ ችግር በተለይ ከታችኛው የወገብ ክፍል ጋር ሊያያዝ ይችላል። • ስለዚህ መደንዘዝ፡ መጨነቅ፡ የማቃጠል ስሜት፡ ቶሎ ቶሎ መሽናት፡ ማሳከክ፡ መጠዝጠዝ፡ የጡንቻ መሸማቀቅና ሽፍታ የእግር የመደንዘዝ ስሜት ጋር የሚያያዝ ነው። በቅንት ሼር