cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃዎች መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
75 623
المشتركون
-1524 ساعات
-867 أيام
-36430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ? ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራር አገኘሁት ብሎ ያጋራው መረጃ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል። የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ ይደረጋል። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 10😐 2
Photo unavailableShow in Telegram
TELEGRAMን ብቻ በመጠቀም በONLINE ብር መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ !?! ሙሉ ዝርዝር መረጃ ቻናል ላይ አስቀምጠናል, ቀለል አርጋቹ ገቢያችሁን ማሳደግ ትችላላችሁ። ➨ቻናል ለማግኘት👇👇👇
إظهار الكل...
🎲ቻናል ይ🀄️ላ🀄️ሉ🎲
💰JOIN CHANNEL💰
Photo unavailableShow in Telegram
የ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ተጠናቀቀ የከፍተኛ ትምህርት የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተጠናቅቋል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሐመድ፤ በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐ ግብሮች ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን ገልጸዋል። 57 የመንግስትና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ያስፈተኑ ሲሆን ፈተናውም በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል። ለፈተናው ከተመዘገቡት 169ሺህ 790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ 117ሺህ 192 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡ እንዲሁም 52ሺህ 598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዝደንቱ "ተሸንፊያለሁ" አሉ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተቃውሞ ያስነሳባቸውን "የግብር ማሻሻያ" እቅዳቸውን መሰረዛቸውን ለመላው የኬንያ ህዝብ አሳውቀዋል። ህዝብን ልመራ ነው የተመረጥኩት፣ ህዝብ ከተቃወመኝ ማዳመጥ አለብኝ። "ተሸንፌያለሁ። ሀሳቤን ሰርዢያለሁ" ብለዋል። በዚህ ምክንያት በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፓርላማው የፀደቀውን የግብር ማሻሻያ ሰርዘናል፣አልፈርምም ብለዋል። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 49
የአማራ ክልል ቀውስ እንዲፈታ በጦር አመራሮች የሚመራ ድርድር ዋጋ ሊሰጠው ይገባል- ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ መከላከያ ለግጭቱ ቅርበት ስላለሁ የአገር ውስጥ ግጭት እንዲቆም ፍላጎት አለው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በጦር አመራሮች የሚመራ የሰላም ሂደት ጥሩ አማራጭ እንደሆነ ገለጹ። ፖለቲከኛው በዛሬው ዕለት በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው እንደጻፉት "በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አመራር ጥሪውን አጠናክሮ ለመቀጠል ያሳለፈው ውሳኔ በቁም ነገር መታየት አለበት"። ጃዋር መሀመድ በዝርዝር የትኛዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች መልዕክትን በተመለከተ እንደጻፉ ባይጠቀስም፤ ፖለቲከኛ መከላከያ ሠራዊት "ለትጥቅ ግጭቶች ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት እውነተኛ ቁርጠኝነትን ያሳየ አንድ የመንግስት አካል ነው" በማለት ገልጸውታል። የሠራዊቱ አመራሮች በትግራይ ጦርነት ወቅት "ከትግራይ ጦር አዛዦች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ለመገናኘት ወደ ሲሸልስ የበረሩ" መሆናቸው በፖለቲከኛው ጽሁፍ እንደማሳያ ተወስዷል። ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር የተደረጉትን ሁለት ዙር ንግግሮች እንዲደረጉ ሁኔታውን የፈጠረውም በዋናነት የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች እንደሆኑ ጃዋር መሀመድ ጽፈዋል። እንደ ጃዋር መሀመድ ገለጻ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በክልሉ ያለውን ግጭት ለመቋቋም ኃላፊነት እንደተሰጠው አካል ስለ ሁኔታው ​​ተጨባጭ ግምገማ ያለው በመሆኑ "የአገር ውስጥ የትጥቅ ግጭቶችን ማቆም ይፈልጋል"። በተጨማሪም፣ ገዥው ቡድን በጦር ኃይሉ ላይ የበለጠ ጥገኛ እየሆነ በመምጣቱ፣ የአመራሮቹ አስተያየት "አሁን ከበፊቱ የበለጠ ክብደት አለው" ያሉት ፖለቲከኛው፤ የፋኖ አዛዦች እና የአማራ የማህበረሰብ አንቂዎች (አክቲቪስቶች) ይህንን በክልሉ ያለውን አስከፊ ግጭት ለማስቆም በጦር ኃይሎች የሚመራውን የሰላም እርምጃ እንዲቀበሉት በአጽንዖት ጠይቀዋል። Via አዲስማለዳ @Addis_News
إظهار الكل...
👍 23
Photo unavailableShow in Telegram
ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሁሉም እስረኞች እንዲለቀቁ ተጠየቀ ለሁለት ቀናት የተካሄደው የሰላም ጉባዔ ባለአሥር ነጥቦች የአቋም መግለጫ በማውጣት ትናንት ተጠናቋል። በአቋም መግለጫው በክልሉ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲፈቱ ተጠየቋል፡፡ ታጥቀው በጫካ ለሚገኙ ኃይሎች ላላቸው ወገኖች ጥሪ የሚያቀርበው መግለጫው፣ በሰላማዊ መንገድና በድርድር ጥያቄዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ሲል ያብራራል፡፡ ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ለሚዲያዎች ዝግ በሆነ ሁኔታ ተከታታይ የሰላም ጉባዔዎች ሲካሄዱ ሰንብተዋል፡፡ ኮሚቴው ከፋኖ ኃይሎች ጋር የሚደረግ የሰላም ንግግርን የማመቻቸት ሥራ እንደሚሠራ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ሪፖርተር ከተለያዩ ምንጮች አደረኩት ባለው ማጣራት በአዲስ አበባውና በባህር ዳሩ ጉባዔ ላይ ስብሰባውን የመሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የጦር አመራሮች፣ ከፋኖ ኃይሎች ጋር በተደራጀ መንገድ ጥያቄ እስካቀረቡ ድረስ ለመነጋገር መንግሥት ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 29🕊 5
ፕሬዝዳንት ሩቶ ከፍተኛ አመጽ የታየበት ተቃውሞ ከገጠማቸው በኋላ የአገሪቱን ጦር አሰማሩ! የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማክሰኞ በመዲናዋ ናይሮቢ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ መሰል አመጽ እንዳይደገም ሁሉንም ሕግ አስከባሪ አሰማራለሁ አሉ።ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም. የኬንያ ፓርላማ ያጸደቀውን አዲስ የታክስ ሕግ ለመቃወም አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የአገሪቱን ፓርላማ ወረው በእሳት ያቃጠሉ ሲሆን፣ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገድለዋል። ፖሊስ በከፍተኛ ቁጥር የወጡ ወጣቶችን ለመበተን ጥይት ተኩሶ በርካታ ሰዎችን ማቁሰሉ ተገልጿል።ቀኑን ሙሉ ከዋለው ተቃውሞ በኋላ ማክሰኞ ምሽት የአገሪቱ ፀጥታ ኃይሎች በመዲናዋ በሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች እየተንቀሳቀሱ የሰልፉ መሪ እና አስተባባሪ ናቸው የተባሉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ስለማዋለቸው ተሰምቷል።ፕሬዝዳንት ሩቶ ማክሰኞ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ከቤተ-መንግሥታቸው በሰጡት መግለጫ “የተደራጁ ሕገ-ወጥ ቡድኖች በሕግ አክባሪ ኬንያውያን ተከልለው የአገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አደጋ ላይ ጥለዋል” ብለዋል። “ኬንያ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ በዴሞክራሲ ሥርዓቷ፣ በሕግ የበላይነት እና ሕገ-መንግሥታዊ ተቋማቷ ላይ ጥቃት ደርሷል” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የዚህ ዓይነቱ ክስተት “በብሔራዊ ደኅንነታችን ላይ ለሚደርሱ ከባድ አደጋዎች ምላሽ የምንሰጥበትን ሁኔታ የቀየረ ነው” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ሩቶ “የትኛውንም ዋጋ ቢያስከፍል” መሰል አመጽ ዳግም እንዳይፈጠር የተቻለንን ፀጥታ አስከባሪ አሰማርተናል ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ይበሉ እንጂ ኬንያውያኑ ነገ ሐሙስ ሰኔ 20/2016 ዓ.ም. ሌላ የተቃውሞ ሰልፍ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሐሳባቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።ማክሰኞ በአገሪቱ ፓርላማ የጸደቀው አዲሱ የቀረጥ ሕግ ኑሮ ያስወድድብናል ሲሉ የቆዩት ኬንያውያን ወጣቶች በኢንተርኔት አማካይነት ተሰባስበው ከአገሪቱ ፓርላማ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያስሙ ቆይተዋል።መንግሥት በበኩለ ታክስ በመጨመር ተጨማሪ ብድር ከሌሎች ምንጮች መውሰድ ሳያስፈልገው ለአስፈላጊ የመንግሥት ወጪዎች እና አገልግሎቶች ገቢ ለማግኘት ዓላማ አድርጎ መሆኑን ገልጿል። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 8😐 3
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት እንዳልሰጠ ገለፀ ድርጅቱ ዛሬ በኦንላይን ካደረገው ውይይት በመነሳት ባወጣው መግለጫ የአገሪቱን የመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት በማድረግ የደንበኞቹን ነፃነት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በፍርድ ቤት አማካኝነት ካልታዘዘ በስተቀር ማንኛውንም የደንበኞቹን መረጃ ለሌላ አካል አሳልፎ እንደማይሰጥ ጠቅሷል፡፡ ጨምሮም እስካሁን ድረስ እንዲህ አይነት የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አካል እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳልደረሰው አስረድቷል፡፡ @Addis_News
إظهار الكل...
👍 36
እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ዲዔታ ታዬ ደንደአ ጠበቆቻቸው ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደኾነ ዛሬ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተናግረዋል። ታዬ ፍርድ ቤቱ፣ በጠበቆቻቸው ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ማስፈራሪያ እንዲያስቆምላቸው ጠይቀዋል። ታዬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት፣ ከአምስቱ ጠበቆቻቸው አንዳቸውም እንዳልተገኙ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ችሎቱ በሥራ መደራረብ የተነሳ የተከሳሹን ጉዳይ ሳያይ እንደቀረ ገልጦ፣ ለሐምሌ 17 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ተብሏል። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 5
መንግሥት ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ግንባታ ከ2017 ረቂቅ በጀት 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድቤያለኹ ማለቱን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። መንግሥት አዳዲስ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች መገንባት ያስፈለገው፣ ባኹኑ ወቅት የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ለቢሮ ኪራይ የሚያወጡት ገንዘብ ከፍተኛ በመኾኑ፣ ኪራዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄዱና መስሪያ ቤቶች በተመቻቸ ኹኔታ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ታስቦ እንደኾነ ገንዘብ ሚንስቴር ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን ግንባታ የሚመራው፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ነው። መንግሥት በቀጣዩ በጀት ዓመት ለስንት የፌደራል መስሪያ ቤቶች ቢሮ መገንባት እንዳቀደ እና ባኹኑ ወቅት ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች የቢሮ ኪራይ ምን ያህል ገንዘብ እያወጣ እንደኾነ እንዳልገለጠ ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። ቋሚ ኮሚቴው፣ አዲስ ቢሮዎችን ወይም ሕንጻዎችን የመገንባት አዋጭነቱ በጥናት የተደገፈ ነው ወይ? በማለት ላቀረበው ጥያቄ፣ የገንዘብ ሚንስቴር ሃላፊዎች ጉዳዩ የአዋጭነት ጥናት አያስፈልገውም በማለት መልሰዋል ተብሏል። @Addis_News
إظهار الكل...
👍 3
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.