cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

|ATTORNEY & CONSULTANT at LAW||BUSINESS & CORPORATE LAWYER(LL.M|Blogger| @lawyerhenoktaye 📞 0953758395 Youtube https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg Tiktok https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
11 180
المشتركون
-424 ساعات
+77 أيام
+3330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
Legal Aid Provider

Bachelor's Degree in Law or in a related field of study with relevant work experience Duties & Responsibilities: - Work closely together with lawyers and legal representatives in the research and preparation of cases brought to courts - Assist in the paper work of cases and management of the administrative side of court affairs

👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
8
ግዛት የዳኝነት ስልጣን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🔥 • አንድ ጉዳይ ለማየት የሚታይበትን ቦታ በተመለከት አንድ ፍርድ ቤት ያለው አካባቢያዊ ወይም የቦታ ስልጣን የግዛት የዳኝነት ስልጣን በዋነኛነት መሰረት የሚያደርገው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተፈጠረበትን ቦታ፤ ለተከራካሪ ወገኖች የሚኖረውን አመቺነት እና መሰል ሁኔታዎችን ሲሆን የስረ ነገር ስልጣን መሰረት የሚያደርገው ግን ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ይዘት፣ የተከራካሪ ወገኖችን መብትና ጥቅም ክብደት እና መጠን፤ የጉዳዩን የውስብስበነት ደረጃ እና መሰል ነጥቦችን በመሆኑ በጉዳዮች አመራር ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለስረ ነገር የዳኝነት ስልጣን ነው፡፡ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 9 እና 10 ድንጋጌዎች ተገናዝበው ሲታዩም ሕጉ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ከግዛት ስልጣን ይልቅ ለስረ ነገር ስልጣን መሆኑን መገንዘብ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ሰ/መ/ቁ. 109383 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 9፣ 10 ጉዳት ካሣ በመርህ ደረጃ በሰዎች ወይም በሚንቀሳቀስ ሀብት ላይ በደረሰ ጉዳት ካሣ ለማግኘት የሚቀርብ ክስ ጉዳቱ በደረሰበት ሥፍራ የሥረ-ነገረ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሔ/ቁ. 27 ንኡስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል፡፡ ይህም የሆነው የደረሰው የጉዳት እና ከጉዳቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ጉዳቱ በደረሰበት አካባቢ በቀላሉ ማስረጃ ለማግኘትና ማስረጃም ለማቅረብ የሚቻል በመሆኑ ነው፡፡ ሆኖም የፍትሐብሓር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 27 ንኡስ አንቀጽ 1 ከላይ የተገለጸውን የሕጉን ዓላማ በአግባቡ ማሣካት የማይከለክል በሆነ ጊዜ በሰው ወይም በሚንቀሣቀስ ንብረት ላይ ለደረሰ ጉዳት ካሣ ለማግኘት የሚቀርብ ክስ ተከሳሽ በሚኖርበት ቦታ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚቻል ይደነግጋል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 48018 ቅጽ 10፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 27(1) ውርስ በግዛት ክልል ስለሚወሰን የዳኝነት ሥልጣን በተመለከተ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንደኛ መጽሐፍ በምእራፍ 3 ስር ካሉት ድንጋጌዎች ውስጥ በቁጥር 23 የተመለከተው ድንጋጌ በውርስ ምክንያት የሚቀርብ ክስ የሚታይበትን ቦታ የሚወስን ነው፡፡ ክሱ መቅረብ ያለበት ወይም የሚቀርበው የውርሱ ክፍያ በተጀመረበት ቦታ ለሚገኘው ፍ/ቤት እንደሆነም ያመለክታል፡፡ ሕጉ ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ የውርስ ሃብት የሆኑ ንብርቶች በተለያዩ ቦታዎች የመኖራቸውን ጉዳይ ግምት ውስጥ የሚገባ አይደለም። Join 👇💥 https://t.me/ethiolawtips
إظهار الكل...
5👍 2
Share የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል.pdf
إظهار الكل...
👍 6
Share 4_5936206060808311349.pdf
إظهار الكل...
👍 4
የማይንቃሳቀስ ንብረት ገዥ ስመ ንብረቱ በሻጭ የተመዘገበና ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን ከሚመለከተዉ አስተዳደር አካል በማረጋገጥ የተዋዋለ እንደሆነ አንድ ጠንቃቃ ሰዉ ማድረግ የሚጠበቅበት ጥንቃቄ እንዳደረገ ግምት ተወስዶ ሕጉ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1553 እስከ 1646፤2878 እና 3052 ድንጋጌዎች የማይንቀሰቃስ ንብረት ምዝገባ አስፈላጊነትም የንብረት መብት ጥበቃ ለማረጋገጥ፣ የግብይት ዋስትና እና የ3ኛ ወገኖችን መብት ለማስከበር እንደሆነ የሚያሥገነዝቡ ናቸዉ፡፡ ስለዚህም የማይንቃሳቀስ ንብረት ላይ በዉል መብት ለማቋቋም የፈለገ ሰዉ እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ይህንኑ ስርዓት ተከትሎ ማለትም ስመ ንብረቱ በሻጭ ስም የተመዘገበና ንብረቱ ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት፡፡በዚህ ረገድ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረጉ ከተረጋገጠ ዉሉ የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም፡፡ (የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2881 ይመለከታል፡፡) ሰበር መ/ቁ 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015ዓ.ም https://t.me/ethiolawtips
إظهار الكل...
Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው። ለጥያቄ እና አስተያየት @lawyerhenoktaye 📞 0953758395 ☎️LL.B)LL.M) 🔔 👇ሌሎች አማራጮችን ለማግኘት 🛑

https://linktr.ee/lawyerhenok?

Youtube 🔥

https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg

👍 12👌 1
በይርጋ የሚታገዱ የወንጀል ክስ ማቅረቢያ ጊዜዋች 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 የይርጋ ዘመን መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛ የወንጀሉን ድርጊት ከፈፀመበት ቀን አንስቶ ሲሆን የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው። ሕጉ ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን በሚል ከላይ በየቅጣቶቹ የተቀመጡ የይርጋ ጊዚያት በእጥፍ ጊዜ ካለፈ የወንጀል ክስ ማቅረብ እንደሚቻል ደንግጓል። ለምሳሌ :መደበኛ የይርጋ ዘመኑ አስር አመት ለሆነ ወንጀል ፍፁም ይርጋው ሃያ ዓመት ይሆናል።ነገር ግን የወንጀል ሕጉ ክስ የማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ቢደነገግም የኢ.ፊ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት በበኩሉ በይርጋ የማይታገዱ ወንጀሎችን አስቀምጧል።በዚህም መሠረት ኢትዮጽያ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በሌሎች የአገሪቱ ሕጎች የሰው ልጅ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ተብለው የተለዩትን 💥 የሰው ዘር ማጥፋት 💥 ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መውሰድ 💥በአስገዳጅ ሰውን መሰወር 💥 አስገድደው የድብደባ ወንጀሎችን በፈፀሙ ሰዋች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም። የወንጀል ክስ አቅራቢነት መደበኛ ክስ የማቅረቢያ ጊዜን በተመለከተ ሕጉ በየወንጀሎች የቅጣት ጊዜ በመከፋፈል የይርጋ ዘመን አስቀምጧል።በዚህም መሠረት 👉⚖️ከ5 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ለሚያሰቀጣ ወንጀል በ15 ዓመት ውስጥ ክስ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 👉⚖️ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በ10 ዓመት ውስጥ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 👉⚖️ከ10 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በ20 ዓመት ውስጥ ክስ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 👉⚖️የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እክራት ለሚያስቀጣ ወንጀል በ25 ዓመት ውስጥ ክስ ካልተመሠረተ ጉዳዩ በይርጋ ይታገዳል። 💥ከዚህም ሌላ ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል አስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት አመት እንዲሁም እስከ አንድ አመት በቀላል እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሶስት አመት የይርጋ ጊዜ ተቀምጧል። ምንጭ የኢፊድሪ የወንጀል ሕቅ አንቀፅ 216-219 💥🇪🇹ለበለጠ የሕግ መረጃ በቴሌግራም ያግኙ 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/ethiolawtips ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ #AddisAbaba #Hawassa #Dilla #legalservice #Lawyer #ethiopialaw #ethiopia #law
إظهار الكل...
👍 20 1
የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection) ሲባል ምን ማለት ነው? ______ ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የፌስቡክ ገጻችን ተከታታዮች ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ፍርድ ቤቱ በነ እገሌ የክስ ሂደት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው? ለዛሬ በዚሁ አርዕሰት ላይ እናንተን ያስተምራል ያልነውን ጥንቅር ወደናንተ ልናደርስ ወደድን ተከታተሉን፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡ይህም ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት እንዲሁም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲገልፅ ያስፈልጋል፡፡እነዚህም ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ መያዝ አለበት፡፡ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡ በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ • ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ • በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ • ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡ ይርጋ ማለት አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ክስ ለማቅረብ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለት ነው፡፡በወንጀል ህግ አንቀጽ 219 ስር እንደተደነገገው የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማከበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውሰጥ ሳይገቡ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመበት አንስቶ ነው፡፡ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ወንጀሉ በተፈፀመ በአስር አመት ውስጥ ክስ መቅረብ አለበት፡፡አስር አመት ካለፈ ግን ክስ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው፡፡ • ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው መሆኑን፣ • ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣ • በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ፣ • ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም ፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ ስለሚሆን አይቀጣም፡፡ ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም ጠበቃ ካለው በጠበቃው አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.130/3)፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ጉዳዩ ባጭሩ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ከተቀጣ በኃላ ተበዳይ በመሞታቸው ዐቃቤ ህግ ድጋሚ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ሲያቀርብ ተከሳሽ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳያነሳ ቀርቶ በኃላ በተመሳሳይ ወንጀል ድጋሜ ያለመከሰስ መብት principle of double jeopardy ይነካል ማለቱ ተገቢ አይደለም ብሎ የተከራከረበት ጉደይ ነው፡፡ ሰበር በውሳኔ ዝርዘሩ ላይ እንዳስቀመጠው “ አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው አስፍሯል፡፡ ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡ ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱን እንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ ይችላሉ፡፡ Source:- Federal Justice and Legal Research and Training Institute official
إظهار الكل...
ገንዘቡ ገቢ ተደርጎ ለተነሺዎች ካልተከፈለ የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር መሬት አያስለቅቅም፡፡ 6. #የአገልግልት መስመሮች ስለሚነሱበት ሥርዓት የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳደር በሚለቀቀው መሬት በላይ ወይም በታች የአገልግልት መስመር መኖር አለመኖሩን የአገልግልት መሥመር ባለቤት ለሆኑ ተቋማት ምላሽ እንዱሰጡበት በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ አለበት፡፡ ጥያቄ የቀረበለት ተቋም ንብረት ካለው ለሚነሳው ንብረት ካሣ እውቅና ባለው ገለልተኛ ገማች በማስተመን ከነዝርዝር ማስረጃው ጥያቄው በደረሰው በ30 (ሰላሳ) ቀን ውስጥ በጽሑፍ ለጠያቂው አካል ይልካል፡፡ የከተማው ወይም የወረዳው አስተዳዳር ግምቱ በደረሰው በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ለባለንብረቱ የንብረቱን ግምት ካሣ ይከፈላል፡፡ የአገልግልት መስመሩ ባለቤት ክፍያው በተፈጸመለት በ60 (ስልሳ) ቀናት ውስጥ ካሣ የተከፈለበትን የአገልግልት መስመር አጠናቆ ማንሳትና መሬቱን መልቀቅ አለበት፡፡ የአገልግልት መስመሩ ባለቤት ክፍያው በተፈፀመ በ120 (አንድ መቶ ሀያ) ቀናት ውስጥ ውስብስብነት ያላቸውን የመሰረተ ልማት መስመሮች አጠናቆ ማንሳትና መሬቱን መልቀቅ አለበት፡፡ በዚህ በላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ልማቱ ካልተነሳ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት በማስነሳት ይዞታው የሚወሰድ ሲሆን በወቅቱ ተገቢውን ስራ ያልተወጣ የመሰረተ ልማት ተቋም ለሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
إظهار الكل...
👍 18