cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣ አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣ ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው። @MentalCounsel ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል! ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ! 🏠Welcome to your Home! 🏘 Personal Contact: @epha_aschalew Insta: instagra.com/epha_aschalew

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
42 260
المشتركون
-3124 ساعات
-1967 أيام
-75430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ወቀሳውን አቁም! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ በህይወትህ ውስጥ እየተከናወነ ላለው ከባድም ሆነ ቀላል ነገር ተጠያቂው አንተ ነህ። ልትቀይረውና ልታሻሽለው የምትችለውም አንተ ነህ። ማንም መጥቶ ላንተ ሃላፊነት አይወስድልህም፤ ከተኛህበት አይቀሰቅስህም። በዚሪያህ የሚመላለሱ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ፤ ታገኛቸዋለህ፣ ረጅም ጊዜ አብረሃቸው ታሳልፋለህ፣ የሚሄዱበት ትሔዳለህ፣ የሚያደርጉትን ታደርጋለህ። "ለምን" ብለህ እራስህን ብትጠይቅ ግን አጥጋቢ መልስ ላታገኝ ትችላለህ። ብቸኝነትህ ለምን የሚለውን ጥያቄ ደጋግሞ ስለሚያስነሳብህ በፍፁም ብቻህን መሆን አትፈልግም። ለእራስህ ጊዜ መስጠት ትዝ አይልህም፤ ከጓደኞችህ ጋር መዝናናት፣ መቃለድ፣ ማፌዝ፣ ሌሎች ላይ ጣት መቀሰር፣ ሌሎችን መውቀስ ተቀዳሚ ስራህ ይሆናል። አዎ! ጀግናዬ..! ወቀሳውን አቁም፤ እራስህን፣ ገቢህን፣ ማንነትህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ ወገንህን፣ ሀገርህን መቀየር ከፈለክ በእርግጥም ወቀሳውን አቁም፣ ጣት መቀሰሩን፣ ማሳበቡን አቁም። እይታህ ሁሉ ወደውጭ ከሆነ እራስህን ታጣዋለህ፤ ምን እንደሚያስፈልግህ፣ የት እንዳለህ፣ ለምን ወደ እዚች ምድር እንደመጣህ ይጠፋሃል። ወቀሳ በሌሎች ላይ እንድትፈርድ ያደርግሃል፤ ፍርጃ ደግሞ ያንተን ህይወት በፍፁም ሊያስተካክለው አይችልም። ለአመታት ብዙ ነገረ ከሌላ አካል እየጠበክ ቆይተሃል፤ ዛሬ ነገ የተሻለ እድል ይፈጠርልኛል ብለህ ተመኝተሃል። አሁን ግን ይበቃሃል፤ ጥበቃውንም ሆነ ወቀሳውን አቁም። ጣትህን ወደእራስህ መልስ፤ ወደእራስህ ተመልከት፤ ችግሮችህ ላይ አተኩር፣ ክፍተቶችህን እወቅ፤ ድክመቶችህን ለይተህ አውጣ። አዎ! እስከ ዛሬ ብዙ ወቅሰሃል፤ ብዙ ተችተሃል፤ ብዙ የእንደዛ እንደዚ ቢሆን አስተያየት ሰተሃል ነገር ግን ችግሮችህ በእጥፍ ከመጨመራቸው በላይ ለእራስህ ያገኘሀው ነገር የለም። መንግስት ደሞዝ ካልጨመረ ያንተ ህይወት በዚው እንዲቀጥል ትፈልጋለህን? አሰሪህ የደረጃ እድገት ካልሰጠህ በቀር እራስህን የምታሳድግበት መንገድ የለህምን? ያለህበት አካባቢ ካልተመቸህ፣ ጓደኞችህ ካንተ ጋር ካልተጣጣሙ መቀየር አትችልምን? አዎ! አንተ በእራስህ መቀየር የምትችላቸው ነገሮች እያሉ ለወቀሳ ሩቅ መንገድ አትሒድ፣ እራስህን አታድክም፣ ጉልበትህን አታዝል። ወቀሳህ የበዛ ምሬትን ቢወልድ እንጂ ምንም አያመጣልህም፤ ሮሮና ለቅሶህ ለጊዜው ብሶት ያስታግስ ይሆናል እንጂ በፍፁም የግል ችግርህን አይቀርፍም። ሩቁ ላለው መንግስት አስተያየት ከምትደረድር አብሮህ ላለው ለእራስህ አስተማሪ መልዕክቶችን አስተላልፍ፤ ለውድቀትህ ሌላውን ከምትወቅስ ከወደክበት ለመነሳት ታገል፤ ለገጠመህ ፈተና ቤተሰቦችህን ተጠያቂ ከምታደርግ እራስህ በቻልከው መጠን ፈተናህን ተጋፈጠው። ውጪውን ከማየትህ በፊት ውስጥህን ተመልከት፤ ለእራስህ የሰጠሀውን ግምት አስተካክል። ስለደረሰብህ በደል ሳይሆን አንተ ምን ማድረግ እንደምትችል ደጋግመህ አስብ፤ መፍትሔ አግኝ፣ ኑሮህን ቀይር፣ እራስህን አሳድግ፤ ከባቢህንም አበልፅግ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
إظهار الكل...
🥰 7👍 2👏 1
እራሳችሁን ተቀበሉ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/uiJht2ATOiY?si=wKrIB-ib6GufNWM4
إظهار الكل...
ይቅርታ አታድርጉ፤ ማንም ህመማችሁን አይረዳችሁም! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ታሪካችሁን ተቀበሉ!@mikre_aimro ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video ...

3👍 1
ነገ የለም! ፨፨////፨፨ ብዘዎቻችን ከነገ ጋር ያለን ፍቅር እጅጉን ይለያል፤ ነገ የሚባል ተጨባጭ ቀን ሳይኖር በውስጡ ተዓምራዊ ምቾት እንዳለው እናስባለን። በህይወት ዘመናችን እንደ ነገ የጠበቅነው፣ በጥበቃችን ልክም ያላገኘው ነገር የለም። ሁሉን ነገር ለማድረግ ነገን መጠበቅ፣ ምንም ለመጀመር ነገን መናፈቅ፣ ስንፍናን ለመሸፈን፣ ድካምን ለማስታገስ፣ ምቾትን ለመጠበቅ ነገ የተባለ ቀን ሁነኛ ምክንያት ሆኖልናል። ነገ የት ነው ቢባል ምላሽ የለም፤ ምንም የሚታቅ ነገር የለም። ለነገ ይታሰባል፤ ለወደፊት ይታቀዳል ነገ ግን አይኖርም፤ ወደፊት ውስጥ እቅዱ አይፈፀምም። የማይደርስ መስሎህ በነገ ስም ያራዘምከው ቀን ዛሬ ሆኖ ከፊትህ ይደቀናል፤ ዛሬ ነገ እያልክ ያሸጋገርከው ጉዳይ ነገን አያውቅምና በጊዜው አሁን መፈፀምን ይፈልጋል። ረጅም ጊዜ እንዳለህ እያሰብክ፣ ብዙ የምትኖረው እድሜ እንደቀረህ እያለምክ ለነገ የምትገፋቸው ጉዳዮችህ ዋጋ ማስከፈላቸው ግድ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! ነገ የለም! ልያዘው ብትል አትይዘውም፤ ልጨብጠው ብትል አትጨብጠውም፤ ትርጉም ያለው ትርፋማ ነገር ላድርግበት ብትል አታደርግበትም። የምትናፍቀው ነገ ዛሬ ነው፤ የምትመኘው ተጨባጩ ወደፊት አሁን ነው። ፍቅር ለመስጠት፣ ያለህን ለማካፈል፣ የምትችለውን ለማድረግ፣ ጥረትህን ለመጨመር ያለህ ጊዜ አጭርና አሁን ብቻ ነው። ሃሳቦችህ የእራሳቸው ደረጃ አላቸው፤ እቅድችህ የቀን ገደብ ይኖራቸዋል እውንነታቸው ግን በዛሬ ውስጥ ነው። ትልቁ ህልምህ የሚኖረው አንድ በማይታወቅ ቀን ሳይሆን ዛሬ በሚታይ፣ በሚጨበጥ፣ በሚዳሰስና በሚታወቅ ቀን ነው። በነገ ምክንያት ያመለጡህን አጋጣሚዎች፣ የረሳሃቸውን አስገራሚ ሃሳቦች፣ ያጣሃቸውን ሰዎች፣ የደከሙብህን መገለጫዎችህን አስታውስ። ስታቅድ ኖረህ ስታቅድ ማለፍ አትፈልግምና በትንሹም ቢሆን መራመድ ጀምር። አዎ! ያንተ የሆነው የትም አይሔድም፤ ነገር ግን አንተ ከገፋሀው ለማንም ሳይሆን ያልፋል። ዛሬና ነገ በእጅጉ ይለያያሉ። ልዩነታቸውም በየሃሳብ ህልውናና በተግባር ህልውና ነው። ነገን ከሃሳብ ውጪ የምትይዝበት መንገድ የለም፤ ከምናብ በተለየ የምትዳስስበት ሁኔታ የለም። ህልውናው፣ መኖሩ በሙሉ ሃሳባዊ ነው። ዛሬ ግን አሁን ነው፤ ሙሉ ነው፤ የሚታይ፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ፣ ከሃሳብ የዘለል ተግባራዊ ህልውና ያለው ነው። በምናብ መኖር፣ በሃሳብ ማደግ ደስ ይላል፣ ተጨባጭ ግን አይደለም። ነገን እያለምክ በዛሬ ውስጥ ታስረህ አትቅር። ያሰብከውን ሁሉ ማድረግ የምትችለው ነገ ሲባሉ በነበሩ ዛሬዎች ውስጥ ነው። ሃሳባዊው ነገ በትንሹ ሊያስፈልግህ ይችላል፣ የህይወትህ መርህ ሊሆን ግን አይችልም። ማየት የሚገባህን የምታየው ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም፤ ሃሳብህ እውን የሚሆነው አሁን እንጂ ቦሃላ አይደለም። መኖር የምትፈልገውን ህይወት በተሰጠህ ዛሬ ውስጥ ኑረው። ህይወትህን አንተው በሃሳብህ ሙሉ ካላደረካት አትሞላምና ለምትወዳቸው ሰዎች ፍቅርህን ለመግለፅ፣ የምታስበውን ስራ ለመጀመር፣ መሆን የምትፈልገውን ሰው ለመሆን ነገን መጠበቅ አቁም። የዛሬ ሃላፊነትህን ተወተህ ሃሳባዊውን ነገ ሙሉና ተጨባጭ አድርገው። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
إظهار الكل...
👍 21🔥 4🥰 2👏 2 1🙏 1
ዋጋቢስ አትሁን! ፨፨፨///////፨፨፨ መልካም በተባሉ ነገሮች መማረክ፣ ጥሩ በሰራው መደነቅ፣ የሰዎችን ህይወት ማድመቅ ብሎም ማድነቅ ክፋት የለውም የእራስን መርሳትና ማደብዘዝ ግን ትልቅ ክፍተትን ከብዙ ችግር ጋር ይፈጥራል። የየለት አጀንዳህ የሰዎች ህይወትና አኗኗር ከሆነ ለእራስህ ጊዜ ሊኖርህ አይችልም። የእነርሱን ትንሽ አጀንዳ በማጉላት ከተጠመድክ ያንተው ትልቅና ወሳኝ አጀንዳ አስታዋሽ ያጣል። ይህ አስታዋሽ ያጣው ወሳኝ አጀንዳህም ቀስ በቀስ ስር እየሰደደ ውድቀትህን ሲያፈጥንና ችግሮችን ሲደራርብብህ ልትመለከት ትችላለህ። የሰው ህይወት የሰው ነው፣ ያንተም ህይወት ያንተ ነው። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንደተባለችው ሴት አትሁን። በሰው ቤት ሄደህ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን ከመሞከርህ በፊት መጀመሪያ የራስህን ቤት አቅና፣ የራስህን ጎጆ በሚገባ ገንባ። ክብርህ በቤትህ ነው፣ ዋጋ የሚኖርህ ለራስህ በምትሰጠው ዋጋ ልክ ነው። የማይመለከተውን እየተነተነ ለሚመለከተው ጉዳይ ጊዜ ያጣ ብዙ ሰው አለ፣ የራሱን ችላ እያለ የሌሎችን የሚፈተፍት ብዙ ሰው አለ፣ ዋናው ትኩረቱ እራሱ መሆን ሲገባው ትኩረቱን ሌሎች ላይ ያደረገ ብዙ ሰው አለ። አዎ! ጀግናዬ..! ዋጋቢስ አትሁን! መራሩን እውነት ለመሸሽ አትዋደቅ። አንተ ለራስህ ዋጋ ካልሰጠህ ማንም ዋጋ ሊሰጥህ አይችልም። በየመንገዱ ለምታየው ነገር አስተያየት በመስጠት አትጠመድ፣ በአላፊ አግዳሚው አትማረክ፣ የእራስህን ጉዳይ የማትከታተል ለሰው ጉዳይ የምትዋደቅ፣ ለመወደድና ትኩረት ለማግኘት ላገኘሀው ሰው ሁሉ ድክመትህንና ከእርሱ ያነስክ እንደሆንክ የምታወራ አሳፋሪ ሰው አትሁን። ሰው አይደለም እቃ እንኳን የውድነቱ ማሳያ የዋጋው ጭማሬ ነው። ዋጋህ ካልጨመረ ማንም ሊያነሳህ እንደማይመጣ እወቅ። ይሔንን አስታውስ፦ "ዛሬ የእለት አጀንዳህ አንተ ነህ።" ዓለምን የማትሰማበት፣ ከጫጫታዋ ዞር የምትልበት፣ በማይረቡ አዳዲስ አጀንዳዎቿ የማትታለልበት፣ የማይጠቅምን የመረጃ በር የምትዘጋበት፣ አኗኗሪ መሆንህ የሚያበቃበት፣ ነዋሪነትህ የሚጀምርበት ጊዜ ዛሬ ነው፣ ከዛሬም አሁን ያለህበት ሰዓት ነው። በቅድሚያ የእራስን ሸክም ማራገፍ ስልጣኔ ነው። ሁን ተብሎ የሚሰራን ድራማ የህይወት አጀንዳ ማድረግ ቅለትና ብክነት ነው። አለም አዳዲስ አጀንዳ አታጠም፤ አዳዲስ ወሬ አታጣም። ያንተ በእርሷ ጊዜያዊ ድራማ መታለል ዋጋ ከማስከፈሉም በላይ ያንተንም ዋጋ እያሳነሰ ዋጋ ቢስ እንደሚያደርግህ እወቅ። አዎ! ፈተና ከተባለ እራስን ከማስረሳት በላይ የሚፈትን ነገር አይኖርም። ትኩረትህ ወደ ውጭ በሆነ ልክ ውስጥህ ባዶና ጥቅም አልባ እየሆነ ይመጣል፣ አይንህ አካባቢውን ብቻ መመልከት ከጀመረ የሚያስፈልገውን ነገር ማግኘት ያቅተዋል። ሁላችንም ጦርነት ውስጥ ነው። እራስን የመግዛት ጦርነት። ዓለም በዛኛው ወገን ልትገዛን ትጥራለች እኛም በነቃን ቁጥር በዚህ በኩል እራሳችንን ነፃ ለማውጣት እንታገላለን። በየቀኑ የሚመጡ የአለም ክስተቶች ለእራሳችን ጊዜ እንዳይኖረን፣ በእነርሱ ጉዳይ መጠመድና መብከንከን ዋነኛው ተግባራችን እንዲሆን እያደረጉን ነው። የሌላውን ስናደምቅ የእኛ ሲፈዝ፣ የሌላውን ስናሳምር የእኛ ሲበላሽብን መመልከት የየለት ተግባራችን ኋኗል። ህይወትህ ላይ ጠብታ ያክል ነገር የማይጨምር የአለምን ጋጋታ መከተልህ ማብቂያው አሁን ነው፣ መጨረሻ የሌለውን ጊዜያዊ አጀንዳ የመስማቱ ፍፃሜ አሁን ነው። በጊዜያት ለማይቀረው፣ በህይወት እስካለህ ድረስ አብሮህ ለሚኖረው ለእራስህ ጊዜ መስጠት ጀምር፤ ዓለም ካንተ ቦሃላ ነችና አራስህን ቀዳሚው የህይወት አጀንዳህ በማድረግ ለዓለም ጠቃሚና ከዓለም ተጠቃሚ ሆነህ ተገኝ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
إظهار الكل...
👍 15 4👏 4🥰 3🔥 1
✝✝ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፣ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ✝✝ "ምድር ጸዳች ሐሴት አደረገች  በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች።" እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! 💒✞❖ መልካም በዓል! 💒✞❖ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን! ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
إظهار الكل...
🥰 15 10👍 3🙏 3🔥 1
ከፍርድ ተቆጠቡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/2GmfpRhWHgE?si=KOdGj-snzJ8kqb5e
إظهار الكل...
ሚዛናዊ ሁኑ፤ በሰፈራችሁት ቁና እንዳትሰፈሩ ተጠንቀቁ! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ምቾት የሚነሷችሁን ሰዎች ራቁ! ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro 🔶 ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇 ♦️

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction -Rebellion inaudio - Infraction - Majestic Vision inaudio - Infraction -Action motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

5👍 2🔥 1🥰 1👏 1
ልማድን በልማድ! ፨፨፨/////////፨፨፨ በእድሜያቸው የሸመገሉ ሰዎች በሚኖሩበት የአዛውንት መጦሪያ ቤት የሚሰራ የእነሱ ተንከባካቢ ባለሞያ ወጣት ስራውን በጣም ስለሚወደው ለእነዚህ አዛውንት የሚሰጠውን እንክብካቤ ከልቡ ነበር የሚያደርገው፡፡ ነገር ግን፣ ይህንን ስራውን እጅግ አስቸጋሪ ያደረገበት አንድ ነገር ነበር፡፡ ሁለት በዚያ የጡረተኞች ቦታ ጓደኝነት የፈጠሩ አዛውንት ማታ ማታ ከቤት ወጥቶ በአካባቢው ተዘዋውሮ የመመለስ የብዙ አመታት ልማድ ስላላቸው አብረው ያንን ያደርጋሉ፡፡ በመቆያ ቦታው ሕግ መሰረት ግን ይህንን ማድረግ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም ስለሸመገሉ አደጋ ሊደርስባቸው ስለሚችል ካለጠባቂ መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ ይህንን ልማዳቸውን ለማስቆም ብዙ ሞክሮ ያቃተው ወጣት ሰራተኛ በመጨረሻ አንድ የስነ-ልቦና አዋቂ አማከረ፡፡ አማካሪውም ወዲያውኑ፣ “እነዚህ አዛውንት ማታ ከቤት ለመውጣት ሲያስቡ በፍጹም ሳይዙ ወይም ሳያደርጉ መውጣት የማይችሉት ልማድ አላቸው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ወጣቱ ትንሽ አሰበና፣ “አዎን፣ ሁለቱም ኮፍያቸውን ሳያደርጉ በፍጹም መውጣት አይወዱም፡፡ ኮፍያቸው ከታጠበ እንኳን እስከሚደርቅ ጠብቀውና አድርገው ነው የሚወጡት” አለው፡፡ አማካሪውም፣ “እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ አየህ አንድን ልማድ ለማቆም ሌላ ልማድ መጠቀም አለብህ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ አለፍ አለፍ እያልክ ኮፍያቸውን ደብቅባቸው፡፡ ኮፍያቸውን ሳያደርጉ መውጣት ያለመቻል ልማዳቸው ወደ ውጪ ከመውጣት ልማዳቸው ስለሚጠነክር በዚያ ምክንያት ከመውጣት ታስቀራቸዋውና ቀስ በቀስ እቤት ሲያመሹ ሌላ ከቤት የማያስወጣ ልማድ ያዳብራሉ” ብሎ መከረው፡፡ ወጣቱ ይህንን ምክር ገና ተግባር ላይ ከማዋሉ ውጤታማ በመሆኑ በጣም ተገረመ፡፡ አዛውንቱ ኮፍያቸውን ባጡባቸው ቀናት እቤታቸው ቁጭ ብለው የድሮ ታሪክ ሲያወሩና የድሮ ፊልሞችን እየከፈቱ ሲመለከቱ በማምሸት ማታ ወደውጪ የመውጣትን አደገኛ ልማድ በሌላ ጤናማ ልማድ ለመለወጥ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር፡፡ ለወቅቱ “ጨለማ” የማይመች ልማድህ ምንድን ነው? እቤት መቀመጥ አለመቻል? ውጪ የመመገብ ልማድ? ከሰዎች ጋር ሳይሰባሰቡ አለመዋል? የወቅቱ ወረርሽኝ ላመጣብን “ጨለማ” የማይመጥነውን ከአንተ ጋር የከረመ ልማድህል ለመቀየር ቀላል ባይሆንም የማይቻል ግን አይደለም፡፡ ቀላሉ መንገድ ከዚያ ልማድህ የጠነከረ ሌላ ልማድ ማዳበር ነው፡፡ እቤት መዋልን እንድትወደው የሚያደርግ ልማድ ፍጠር፡፡ ከቤተሰብ ጋር ማሳለፍ፣ ማንበብን መልመድ፣ በሁለት ወር ውስጥ በአንድ አዲስ እውቀት ራስን ለማሰልጠን ማቀድ፣ የማትችለውን ምግብ ማብሰልን መልመድ፣ አንድን መጽሐፍ መምረጥና ከቤተሰብ አባላት ጋር በየቀኑ ማጥናትና መወያየት፣ ስፖርት መስራት . . .፡፡ መላው ብዙ ነው፡፡ አትርሳ፣ የሚያጠፋህም ሆነ የሚያለማህ ልማድህ ነው፡፡ ©ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
إظهار الكل...
👍 38 5👏 1😁 1
"ምን ላድርግ?" ፨፨፨//////፨፨፨ መቼ፣ እንዴት፣ የት፣ በምን ደረጃ እንደምትገኝ አታውቅም። ብዙ ብታቅድም፣ ብዙ ብታስብም ሃሳብና እቅድህ ሚዛን ሳይደፋ፣ ሳይሳካ ያልገመትከውና ያላሰብከው ስፍራ እራስህን ልታገኝ ትችላለህ። ስኬትን አቅደህ ወድቀህ ይሆናል፣ ብረሃንን አስበህ በጨለማ ተከበህ ይሆናል፣ ብዙዎችን ለማገዝ አስበህ ተረጂ ሆነህ ይሆናል፣ ችግር ለመፍታት እየተንቀሳቀስክ ችግር ውስጥ ተገኝተህ ይሆናል። ተጨባጩ ክስተት፣ ያለው እውነታ ከሃሳብና እቅድህ በብዙ እጥፍ ተቃርኖ ቢገኝ፣ እጅጉን ቢራራቅ ያንተ ግብረመልስ ምን ሊሆን ይችላል? ከመቀበል ባሻገር ቀጣይ እርምጃህ ምንድነው? አዎ! ጀግናዬ..! ያለህበት ሁኔታ ያልታሰበና ያልተመቸህ፣ አቅደሀው የማታውቀው፣ ለማመን የከበደህ ቢሆንም እንኳን የያዝከውን ይዘህ፣ የደረሰብህን ችለህ፣ ህመምህን ውጠህ እራስህን አንድ ጥያቄ ጠይቅ። ስለሁኔታው " ምን ላድርግ? " ብለህ ጠንቅ።  "ካለሁበት አስከፊ ሁኔታ ለመውጣት ምን ላድርግ? ምን ልስራ? እንዴት ልስራ? እንዴት ላድርግ? ኬት ልጀምር? ከማን ጋር ልጀምር? " ብለህ እራስህን ጠይቅ። ብልሆች በእራሳቸው መልስ ያላገኙለትን ጥያቄ የሚያምኑተንና የሚረዳቸውን ሰው ይጠይቃሉ። በአጋጣሚም ሆነ ሁን ብለህ የተገኘህበተን ስፍራ ማሻሻል፣ ማደስ፣ መቀየር ከፈለክ በሚገባ ትችላለህ። ሁሌም በችግር፣ ሁሌም ምቾት በማጣት፣ ዘወትር በምሬ፣ ዘወትር በለቅሶ እንድኖር የፈረደብህ አካል የለም። ለውጥ የሚባል ስጦታ ላንተም ህይወት ተሰቷ፣ ባንተም እጣፋንታ፣ ባንተም ኪስ ውስጥ ይገኛል። አዎ! የምታስበውን ለውጥ ለማምጣት ተቸግረሃል? ህይወት ዳገት እንደመውጣት ከብዳሃለች? ወኔህ ክዶሃል? ጉልበትህ ተብረክርኮብሃል? ከጥያቄዎቹ ጀርባ "ለምን?" ብለህ ዳግም እራስህን ጠይቅ። ከምክንያቶቹ ጀርባ የሚገለጥልህ ምክንያት፣ ማድረግ የሚገባህ ተግባር ይኖራል። ማድረግ የሚገባህን ባታውቅ አምላክህን ተማፀነው፣ "ምን ላድርግ?" በለው፤ ሰዎችን ጠይቅ፣ መርምር፣ ከልምዳቸው ተካፈል፣ እግራቸው ስር ወድቀህ ተማር። አንተ ያላሰብክበት ችግርህ፣ አንተ ችላ ያልከው ሸክምህ ያላንተ ፍቃድ በማንም የሚፈታ፣ በማንም የሚቀረፍ፣ በማንም የሚወርድ አይደለም። ከማትወደው የህይወት ዘይቤ ለመላቀቅ እራስህን አሳምን፣ ያለህበትን ሁኔታ በሙሉ ልብህ ተቀበል፣ ማድረግ ስለማትችለው ሳይሆን ማድረግ፣ መቀየር ስለመትችለው ብቻ ማሰብ ጀምር። የትኛውንም ያንተን ሸክም የመሸከሙ ሃላፊነት ያንተ ነው፤ ሲከብድህም የማውረድ፣ ፋታ የመውሰድ መብቱ አለህ። በፋታህ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብህ ደጋግመህ አስብ፤ ከብዶኛል እያልክ የሚቀልህ ነገር እንደሌለ አስታውስ። ከባድ ቢሆንም ትችለዋለህ፣ ታደርገዋለህ፣ እንደቀላሉ ታልፈዋለህ፤ ትሻገረዋለህ። በርታ! ተበራታ! ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
إظهار الكل...
👍 21 6🔥 2🥰 1
ስሜታችሁን ተቆጣጠሩ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/eYFQfciJH-o?si=bAz3-EAq29VyndQD
إظهار الكل...
በጥልቀት አስቡ፤ አንድ መጥፎ ውሳኔ ህይወታችሁን ለማበላሸት በቂ ነው! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ቆም ብላቹ አስቡ! ከቁጪት እራሳችሁን ታደጉ! @mikre_aimro ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro 🔶 ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇 ♦️

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction - Atlas main version inaudio - Infraction -Memories inaudio - Infraction - Rebellion motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

👍 3 1
ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉት!እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሰላም አደረሳችሁ! ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
إظهار الكل...
15🙏 7👍 3🥰 3🤔 1😢 1