cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የሰለምቴዎች ቻናል

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 351
المشتركون
+424 ساعات
+107 أيام
+10830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

◆▮ውይይት▮◆ "ኢየሱስ ለምን ትል ተባለ" ? ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ዘከረ
إظهار الكل...
record.ogg64.58 MB
ፈጣሪ ነገሮችን እያየ ለምን ይናገራል? ከሆነ ጥያቄአችሁ እግዚአብሔር፦ “በእውነት ቤትህ የአባትህም ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ” ብሎ የተናገረው ቃል በሌላ ጊዜ “ይህ አይሆንልኝም በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም” ብሎ ሁኔታውን አይቶ ለውጦታል ፦ 1ኛ ሳሙኤል 2፥30-34 ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *”በእውነት ቤትህ የአባትህም ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ”I said indeed that” አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና "”ይህ አይሆንልኝም። እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ"፥ ክንድህን የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል*። እግዚአብሔር፦ “ከሰውም በሚወጣ ፋንድያ በፊታቸው ትጋግረዋለሁ” ብሎ የተናገረው ቃል ”ከከብት በሚወጣ ፋንድያ በኩበት ትጋግረዋልህ” ብሎ ሁኔታውን አይቶ ለውጦታል፦ ሕዝቅኤል 4፥12-15 እንደ ገብስ እንጐቻም አድርገህ ትበላዋለህ፥ *"ከሰውም በሚወጣ ፋንድያ በፊታቸው ትጋግረዋለሁ"።…እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥንብና አውሬ የሰበረውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም አልሁ። እርሱም፦ እነሆ፥ "በሰው ፋንድያ ፋንታ ኩበት ሰጥቼሃለሁ" በእርሱም እንጀራህን ትጋግራለህ አለኝ*። እግዚአብሔር፦ “ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርም” ብሎ የተናገረው ቃል “በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ” ብሎ ሁኔታው አይቶ ለውጦታል፦ ኢሳይያስ 38፥1-5 በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ታመመ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *"ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና"* ቤትህን አስተካክል አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ። ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ። የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ። ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው። የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *"ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ"*። እንግዲያውስ እነዚህ ሦስት ናሙናዎች የሚያሳዩን ፈጣሪ የሰዎችን ሁኔታ እያየ መናገሩ ብቻ ሳይሆን የተናገረውን ኤዲት ማድረጉን ይገልጻሉ። በሰፈሩት ቁና መሰፈር እንዲህ ነው። ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
إظهار الكل...
👍 1
ሠበቡ አን-ኑዙል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*። وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا “ሠበብ” سَبَب ማለት “ምክንያት” ማለት ሲሆን የሰበብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አስናብ" ነው፤ “ኑዙል” نُزُل ማለት “አወራረድ” ማለት ነው፥ ቁርኣን የወረደበት ምክንያት "ሠበቡ አን-ኑዙል" سَبَب النزول ወይም "አስባቡ አን-ኑዙል" أسباب النزول ይባላል፤ ይህ የአወራረድ ምክንያት"circumstances of revelation" ነቢያችን"ﷺ" በተላኩበት ጊዜ ሰዎች በጥያቄ ሲመጡ አላህ "ይጠይቁሃል" "በላቸው" በማለት መልስ ይሰጣል፦ 25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*። وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا ይህን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ካየን ዘንዳ ሚሽነሪዎች ይህንን ካለመረዳት፦ "ቁርኣን በነቢያች"ﷺ" ኤዲት እንደተደረገ ይናገራሉ፦ 4፥95 *ከምእመናን ተቀማጮቹ አይተካከሉም፥ የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር። በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ፡፡ ለሁሉም አላህ መልካሚቱን ገነት ተስፋ ሰጠ፡፡ ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ*፡፡ لَّا يَسْتَوِى ٱلْقَٰعِدُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ غَيْرُ أُو۟لِى ٱلضَّرَرِ وَٱلْمُجَٰهِدُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ ۚ فَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلْمُجَٰهِدِينَ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ عَلَى ٱلْقَٰعِدِينَ دَرَجَةًۭ ۚ وَكُلًّۭا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلْحُسْنَىٰ ۚ وَفَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلْمُجَٰهِدِينَ عَلَى ٱلْقَٰعِدِينَ أَجْرًا عَظِيمًۭا ይህ አንቀጽ አንድ ቢሆንም ሁለት ሃረግ ሆኖ ነው የወረደው "ከምእመናን ተቀማጮቹ አይተካከሉም" የምትለዋ አንቀጽ ወርዳ ሳለ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ዘይድን ጠርተዉት ሲጽፍ ዐብዱላህ ኢብኑ ኡምሚ መክቱም መጥቶ ስለ እውርነቱ አማረረ፤ አላህም፦ "የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር" የሚለው ሃረግ አወረደ፦ ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4593: አል-በራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ከምእመናን ተቀማጮቹ አይተካከሉም" የምትለዋ አንቀጽ ወርዳ ሳለ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ዘይድን ጠርተዉት ሲጽፍ ዐብዱላህ ኢብኑ ኡምሚ መክቱም መጥቶ ስለ እውርነቱ አማረረ፤ አላህም፦ "የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር" የሚለው ሃረግ አወረደ*። عَنِ الْبَرَاءِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ ‏{‏لاَ يَسْتَوِي الْقَاعِدُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ‏}‏ دَعَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم زَيْدًا فَكَتَبَهَا، فَجَاءَ ابْنُ أُمِّ مَكْتُومٍ فَشَكَا ضَرَارَتَهُ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ ‏{‏غَيْرَ أُولِي الضَّرَرِ‏}‏ ይህ የሆነው አንቀጹ በወረደበት ጊዜ እንደሆነ ኢማም ሙስሊም ዘግቦታል፦ ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 20, ሐዲስ 4677: አል-በራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ከምእመናን ተቀማጮቹ አይተካከሉም" የምትለዋ አንቀጽ በወረደች ጊዜ ዐብዱላህ ኢብኑ ኡምሚ መክቱም ለነቢያችን"ﷺ" ሲናገር "የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር" የምትለዋ ሃረግ ወረደች*። عَنِ الْبَرَاءِ، قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ ‏{‏ لاَ يَسْتَوِي الْقَاعِدُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ‏}‏ كَلَّمَهُ ابْنُ أُمِّ مَكْتُومٍ فَنَزَلَتْ ‏{‏ غَيْرُ أُولِي الضَّرَرِ‏}‏ ዐብዱላህ ኢብኑ ኡምሚ መክቱም ከመምጣቱ በፊት "ከምእመናን ተቀማጮቹ አይተካከሉም" የሚል ቃል ከወረደና ከተጻፈ በኃላ ዐብዱላህ ኢብኑ ኡምሚ መክቱም ለነቢያችን"ﷺ" ሲናገር "የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር" የምትለዋ ሃረግ ስትወርድ እዛው ላይ ተጽፏል፦ ሱነን ነሣዒ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 3103: አል-በራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *ነብዩም"ﷺ" የግመል ቆዳ ወይም ሰሌዳ አምጣልኝ እና "ከምእመናን ተቀማጮቹ አይተካከሉም" የምትለዋ አንቀጽ ጻፍ" አሉ፤ ዐምር ዐብዱላህ ኢብኑ ኡምሚ መክቱም በጀርባቸው ነበር፤ ያ እኔ ይመለከታልን? ሲል "የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር" የምትለዋ ሃረግ ወረደች*። عَنِ الْبَرَاءِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم ثُمَّ ذَكَرَ كَلِمَةً مَعْنَاهَا قَالَ ‏"‏ ائْتُونِي بِالْكَتِفِ وَاللَّوْحِ ‏"‏ ‏.‏ فَكَتَبَ ‏{‏ لاَ يَسْتَوِي الْقَاعِدُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ ‏}‏ وَعَمْرُو بْنُ أُمِّ مَكْتُومٍ خَلْفَهُ فَقَالَ هَلْ لِي رُخْصَةٌ فَنَزَلَتْ ‏{‏ غَيْرُ أُولِي الضَّرَرِ ‏}‏ ‏.‏
إظهار الكل...
ኤዲቲንግ ማለት የነበረውን ሰርዞ ወይም ቀይሮ ሌላ መተካት እንጂ በነበረው ላይ መጨመር አይደለም። ግን እዚህ አንቀጽ ላይ ሁለቱንም ሀረግ የተወረዱ ኑዙል መሆናቸው አንባቢ ልብ ይለዋል። እንደሚታወቀው ቁርኣን ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ዓመተ-ልደት እስከ 632 ዓመተ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረደ፤ ለ 13 ዓመት 86 ሱራዎች በመካ ሲሆን 28 ደግሞ የወረዱት ለ 10 ዓመት በመዲና ነው፣ ይህ ወሕይ በ 40 ዓመታቸው ጀምሮ በ 63 ዓመታቸው ቀስ በቀስ ወረደ፤ ይህም ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ አወራረዱ “ተርቲል” تَرْتِيل ይባላል፦ ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፤ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏ 25፥32 እነዚያ የካዱትም *«ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا 17፥106 *ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*፡፡ وَقُرْءَانًۭا فَرَقْنَٰهُ لِتَقْرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍۢ وَنَزَّلْنَٰهُ تَنزِيلًۭا “አወረድነው” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “ነዝዘልናሁ” نَزَّلْنَاهُ ሲሆን “ነዝዘለ” نَزَّلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል በቁርኣን ዐረቢኛ ቋንቋ ቀስ በቀስ በተለያየ ጊዜ መውረድን ያመለክታል፤ እዚሁ አንቀጽ ላይ “ተንዚላ” تَنزِيلًۭا የሚለው የተንዚል አንስታይ መደብ ነው፤ “ተንዚል” تَنزِيل የሚለው ቃል 15 ጊዜ ለቁርኣን ተጠቅሷል፦ 26፥192 *እርሱም ቁርኣን በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَإِنَّهُ لَتَنزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِين
إظهار الكل...
◆▮ውይይት▮◆ "የአላህ ቅድመ እውቀት ? ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ጃቤህ
إظهار الكل...
record.ogg21.99 MB
👍 2
ንብ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ *"ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ"*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ ንብ በራሪ ነፍስ"insect" ናት፤ ከሶስት አፅቂዎች የምትመደብ ስትሆን ልክ እንደ ጉንዳን ካሉ "Hymenoptera" ቤተሰብ ትመደባለች፤ ይህቺ በራሪ ነፍስ በማር እና በሰም ምርቷ ትታወቃለች፤ በምድራችን ላይ ከ20,000 በላይ የታወቁ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩ እነዚህም በዘጠኝ ታዋቂ ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል፤ ምን አለፋን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ዝርያዎች ሊኖሯቸውም ይችላል። ንብ የራሷን ቤቶች የምትሰራው ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ነው፤ ይህንን ሥርአት ያሳወቃት ንድፍ አውጪው አምላካችን አላህ ነው፦ 16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ *"ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ"*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ ንብ አበባዎች ባሉበት ሁሉ ትገኛለች፤ የንብ አካላቷ በሦስት ክፍል ይከፈላል፤ አንደኛው ክፍል የምታሸትበት፣ የምትዳስስበት፤ የምትሰግበት፣ በግንባሯ በስተቀኝና በስተግራ ሁለት ቀጫጭን ነገሮች እንደ ቀንድ የሆኑ አሏት፤ ደግሞ በዚህ በገጿ ላይ ሁለት ትልልቅ ጠፍጣፋ ዓይኖች በግራና በቀኝ ሆነው ለማየት የሚያስችሏት በሌሎች ትንንሽ ዓይኖች የተሞሉ አሏት። ሁለተኛው ክፍል የአካሏ ክፍል ፀጉራሞች የሆኑ በአበባ ውስጥ ያለውን ኔክታር ማለትም ፈሳሽ ነገር ስትመጥ የአበባ ዱቄት የምታመጣባቸው ስድስት እግሮች፣ ሁለት ወፈር ያሉ ክንፎችና ሌሎች ሁለት ሳሳ ያሉ ክንፎች በጠንካሮች ሥር የሆኑ አሏት። በሦስተኛው የአካላት ክፍሏ እንደ አንጓ ክርክር ያላቸው መተንፈሻዎች የምትነድፍበትና የተበላሸውን የምታስወጣበት አሏት። ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ምግቧን ትብላለች፤ ይህንን የተፈጥሮ ሥርአት የነደፈላት አምላካችን አላህ ነው፦ 16፥69 «ከዚያም *ከ*ፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ الثَّمَرَات "ፍሬዎች" በሚለው ቃል ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መግባቱ ከፍሬዎች ሁሉ መካከል መብላቷን ያሳያል እንጂ ፍሬዎችን ሁሉ አያሳይም። ንብ ወለላን ቱቦ በመሰለው ምላሷ ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ቅሥም አውላ እየቀሰመች በሆዷ ውስጥ ባለ የማር ቋት ውስጥ ታጠራቅማለች፤ አምላካችን አላህ፦ "ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል" የሚለው ይህንኑ ነው፤ ከዚያም ተሸክማ ወደ ወደ ቀፎዋ ትወስደዋለች፤ ቀጥሎም ፈሳሽ የአበባ ወለላውን ወደ ሌሎች ንቦች ታዘዋውረዋለች፤ ወለላውን በአፏ ውስጥ ካሉት እጢዎች ከሚመነጭ ኢንዛይም ጋር እያዋሐደች ለአንድ ሰዓት ከግማሽ ያህል ታላምጠዋለች፤ ከዚያም ከሰም በተሠሩ ባለ ስድስት ማዕዘን ክፍሎች ውስጥ ታስቀምጥና እርጥበቱ እንዲተን በክንፎቿ ታራግባለች፤ የውኃው መጠን ከ18 በመቶ በታች ሲሆን ክፍሎቹን በሰም በስሱ ትሸፍነዋለች፤ በዚህ መልኩ የተሸፈነ ማር ሳይበላሽ ለዘመናት ሊቆይ ይችላል። ይህ ማር ምግብ ከመሆኑም ባሻገር በቫይታሚን ቢ፣ በተለያዩ ማዕድናት እና አንቲኦክሲደንትስ በተባሉ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ መድኃኒት ነው፤ ማር ቁስልን፣ የተቃጠለ የአካል ክፍልን፣ የዓይን ቆዳ መሸብሸብን እና በቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስልን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የጤና ችግሮችን ለማከም ዛሬ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ ንብ በአበባ ፈሳሹ ላይ ኢንዛይም ስለምትረጭ ማር ለስለስ ያለ የፀረ ባክቴሪያነትና አንቲባዮቲክነት ባሕርይ እንዳለው ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህንን ያገራላት አምላካችን አላህ ነው፤ በማር ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት እና ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት፦ 16፥69 *የጌታሽንም መንገዶች ላንቺ የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት*፡፡ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِن بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِّلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ ✍ ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሰላሙ አለይኩም
إظهار الكل...
فَسَتَذْكُرُونَ مَا أَقُولُ لَكُمْ ۚ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር(ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፡፡ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፡፡አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና ቃሪእ አቡበክር አል-ሻጥሪ
إظهار الكل...
10.21 KB
05:58
Video unavailableShow in Telegram
▯▩ መልሶቻችን▩▯ " በኢስላም ሴትን በወር አበባ ግዜ ግንኙነት ይፈቀዳልን "? "መልሶቻችን ክፍል4"       ◍ ከወንድም ዒምራን ቲክቶክ ያላችሁ ገብታችሁ ኮፒ ሊንክ ድዮት እና ላይክ አድርጉ https://vt.tiktok.com/ZSY459D1o/
إظهار الكل...
39.14 MB
👏 1
◆▮ውይይት▮◆ "ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ጅሀነም ከገቡ ኢሳና ሌሎች የአላህ ደጋግ ባርያዎች ይገባሉ? ◍ ወንድም ዒምራን          🅥🅢 ◍ ወገናችን ጃቤህ
إظهار الكل...
record.ogg33.28 MB
فَسَتَذْكُرُونَ مَا أَقُولُ لَكُمْ ۚ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር(ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፡፡ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፡፡አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና ቃሪእ አቡበክር አል-ሻጥሪ
إظهار الكل...
2051880898.mp31.84 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.