cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ገድለ ቅዱሳን

@Gedelat ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡ በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
6 665
المشتركون
+224 ساعات
-77 أيام
+230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

[ ስንክሳር ግንቦት - ፳፰ - ] .mp33.02 MB
🕊 [ †  እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ገዳማዊት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ] 🕊  †  ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ  †   🕊 ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት:: አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች:: አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ : አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች:: በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም : የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች:: ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::" ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን : ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት : ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች:: በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች : ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች : ማንንም ሰው ሳታይ : በፍጹም ተጋድሎ ለ ፴፰ [38] ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር : የሌሊቱ ቁር [ብርድ] ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት:: ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ :- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው:: ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ ፴፰ [38] ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም:: እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም:: አንድ ቀን ግን [ማለትም ግንቦት ፳፰ [28] አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ:: አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች:: አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን:: 🕊 [ † ግንቦት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት [ ገዳማዊት ] ፪. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት ] ፫. አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ ፬. አባ ጌርሎስ [ ጻድቅና ሰማዕት ] ፭. ፵፭ "45" ሰማዕታት [ የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት ] ፮. ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን ፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ] ፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ ፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት] " ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: " [፩ዼጥ.፫፥፫]  (3:3) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የቅዱስ_ኤጲፋንዮስ_ሥጋው_ወደ_ቆጵሮስ መመለስ፦ ይህም እንዲህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ወደ መንበረ ሢመቱ እንደማይደርስ ትንቢት እንደተናገረለት ወደ ቆጵሮስ ሳይደርስ በመርከብ ውስጥ ሳለ ግንቦት ዐሥራ ሰባት ቀን ዐረፈ። በዐረፈም ጊዜም በመርከብ ጭነው ወደ ቆጽሮስ ከተማ አደረሱት። ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ መጡ ከሳቸውም ጋር ወንጌሎች መስቀሎች መብራቶችና ማዕጠንቶችም የሐዋርያት ጉባኤ ከታላቂቱ ቤተ ክርስቲያን እስኪያደርሱት በዝማሬ በማኅሌት በሚገቡት ጸሎቶች ሁሉ እያመሰገኑ ሥጋውን ተሸክመው ካህናቱም መቃብሩን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሊያዘጋጁ ወደዱ። ቀድሞ ስለ ክፉ ሥራቸው ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አውግዞአቸው የነበሩ ሁለት ዲያቆናት ተቃወሟቸው። ስለዚህም አርባ ቀን ተቀመጠ ነገር ግን ሽታው እንደ ሙታኖች ሽታ አልተለወጠም እንደ አንቀላፋ ሰው እንጂ። ❤ ከዚህም በኋላ አንድ ደግ ዲያቆን ወደ ቅዱስ ሥጋ ቀርቦ "አባቴ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ አንተ ባለሟልነት እንዳለህ እኔ አውቃለሁ። ብትፈቅድስ ክፉዎች ተቃዋሚዎችን ልታሸንፋቸው ትችላለህ" አለ። የቅዱስ ኤጲፋንዮስንም እጅ ይዞ ምድርን መታባት በዚያንም ጊዜ ሁለቱ ዲያቆናት በግምባራቸው ተደፉ። ለመሞትም ደረሱ ወደ ቤታቸውም ወስደዋቸው ሞቱ። ❤ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ካህናቱ በሚጣፍጡ ሽቱዎች ገንዙት። በከበሩ ልብሶችም ጠቅልለው ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ ጨምረው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ቀድሞ በሕይወቱ ሳለ እንደሚሠራው ከሥጋው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት_28_ስንክሳር።                           ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰአሉ_ለነ_አብርሃም_ይስሐቅ_ወያዕቆብ_አበወ ሕዝብ ወአሕዛብ ወዘመሐይምናን መክብብ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ"። ትርጉም፦ የምዕመናን ሹሞች የአሕዛብና የሕዝብ አባቶች #ቅዱሳን_አብርሃም_ይስሐቅ_ያዕቆብ ፈጽማችሁ ለምኑልን አማልዱ፡፡ #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በሰዓታት_ላይ፡፡                          ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለአመተ_ክርስቶስ_መንበርተ_ዓለም መኒና። እንተ ረሰየት ይእቲ ንቅዓተ ኰኵሕ መካና። ሠላሳ ወስምነ ዓመታት እስከ ኮና። ይቤሉ ነጋድያን ሶበ ምውተ ረከብና። ውሳጤ በዓት በህየ ቀበርና"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_28።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ71፥15 ወይም መዝ 4፥4። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ2፥1-21 ወይም ሉቃ 9፥18-23።                                                  ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አሌ ሎን ለከናፍረ ጒሕሉት። እለ ይነባ ዓመፃ ላዕለ ጻድቅ። በትዕቢት ወበመንኖ"። መዝ 30፥18 ወይም መዝ 50፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥29-ፍ.ም፣ ያዕ 2፥19-ፍ.ም እና የሐዋ.ሥራ 5፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥22-39 ወይም ማቴ 9፥9-18። የሚቀደሰው የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አማኑኤ በዐልና የበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። @sigewe https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886 https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
إظهار الكل...
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ግንቦት_፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን #ለቅዱስ_አማኑኤል_ዓመታዊ_የንግሥ በዓል #ለአርስተ_አበው_ቅዱሳን_ለአብርሃም፣ #ለይስሐቅና_ለያዕቆብ_ለመታሰቢያቸው_በዓል፣ ተጋዳይ ለሆነች ዓለምን ንቃ ለተወች፤ አባ ዳንኤል ስርሷ እንደተናገረ የዓለምን ፍላጎት ሁሉ ድል ለነሣች፤ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት አንዴ ወደ ገዳም ይዛ በሔደች ሽንብራና የጽዋ ውኃ ሳያልቅባት በተሰነጠቀ ዐለት ውስጥ ስትጋደል ለነበለች #ለቅድስት_አመተ_ክርስቶስ_ለዕረፍት_በዓል፣ #ለአባ_ጳኵሚስ_ገዳም ለሆነ በዕረፍቱ ጊዜ ሥጋው አጋዘን ተሸክመው ወደ ሚቀበርበት ቦታ ላመጡቱ #ለአባ_መርቆሬዎስ_ለዕረፍት_በዓልና ለታላቁ #ለቆጵሮስ_አገር_ሊቀ_ጳጳስ_ለቅዱስ_ኤጲፋንዮስ #ሥጋው_ወደ_ቆጵሮስ_ለደረሰበት_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ከሚታሰቡ፦ በሰማዕትነት ከዐረፉ #ከአባ_ጌርሎስና #ከአርባ_አምስት_ልጆቹ፣ #ከአባ_ስንጣና_ከሰማዕት_አጋቦስ_ከመታሰቢያቸው ረድኤና በረከትን ያሳትፈን።                                 ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_አመተ_ክርስቶስ፦ አባ ዳንኤል እንዲህም አለ "በረሀም ሳለሁ በሌሊት ተነሥቼ በጨረቃ ብርሃን ተጓዝኹ በተራራ ላይ የተቀመጠ ሰውንም አየሁ ጠጉሩም ሁለመናውን ሸፍኖታል በልቤም ወደርሱ ሔድሁ። በአየችኝም ጊዜ ወደ ተሠነጠቀው አለት ውስጥ ገባች "ሰው ሆይ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ በረከትህን እንድቀበል እማልድሃለሁ" አልሁ እጅግም አብዝቼ ለመንሁ። ከዚህም በኋላ "አባት ሆይ አልወጣምና ይቅርታ አድርግልኝ" አለችኝ። እኔም "ስለምን አልኋት" እርሳም "እኔ ሴት ነኝ ራቁቴን ስለሆንኩ" አለችኝ። ይህንንም ሰምቼ የለበስኩትን ዐጽፍ ጣልሁላት ለብሳም ወጣች በአንድነትም ጸለይን። ❤ ከዚህ በኋላ "እናቴ ሆይ ከዓለም ወደዚህ ስለመውጣትሽ ይኸንን የተሠነጠቀ ዐለት እንዴት እንዳገኘሽ ንገሪኝ አልኋት"። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችልኝ በወላጆቼ ቤት ድንግል ሁኜ በኢየሩሳሌም የምኖር ነኝ ሁል ጊዜ የሚጎበኘኝ ከእኔ ጋራ የሚነጋገር አንድ መነኰስ ነበር። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ወደርሱ ሔድኹ በእግዚአብሔር ፊትም ኃጢአቴን እየታመነ ሲአለቅስ አገኘሁት። ደጅንም በአንኳኳሁ ጊዜ አልከፈተልኝም እየተጸጸተ ልቅሶን አበዛ እንጂ። በዚያን ጊዜ በልቤ እንዲህ አልኩ እኔስ ስለ ጒስቍልናዬና ስለ ኃፍረቴ የማላለቅስና የማልጸጸት ለምድነው ወደ ማደሪያዬም ፈጥኜ ሔድኹ ማቅ ለበስኩ በዘንቢልም ሽምብራ በጽዋ ውኃን ያዝሁ። በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ዘንድ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ "አቤቱ ጽኑዕ ኃያል ለዘላለሙ ድንቅ የሆንክ የጠፋትን የምታድን የወደቁትንም የምታነሣቸው ወደ አንተ የሚጮኹትንም የምትሰማቸው የታመነችብህ ባሪያህን ታድናት ዘንድ ይቅርታህንና ምሕረትህን ላክ። ከምግባር ድኃ የሆንኩ ባሪያህን ጐብኘኝ ንስሐዬንም ተቀበል። ለረጅም ዘመን ስንቅ ይሆነኝ ዘንድ ይህን ሽምብራና ይህን የጽዋ ውኃ ባርከው ስለ ነፍሴ ድኅነት የአሰብኩትን እንዳላቃልል ለሆዴ ምግብ ስለሚአሻኝ"። ❤ ከዚህ በኋላ ነፍሴን በእግዚአብሔር ላይ በመጣል ወጥቼ ወደ በረሀ ሔድኹ እስከ ኤርትራ ባሕርም ደረስኩ። ከዚያም ወደዚህ በረሀ መጥቼ ይህን የተሠነጠቀ ዐለት አገኘሁ ይህ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ መኖሪያዬ ነው አልሁ። "እንሆ በዚህ በረሀ ውስጥ ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነኝ ያለ አንተ ሰው አላየሁም። ይህም የዘንቢል ሽምብራና የጽዋ ውኃ ሠላሳ ስምንት ዓመት ከእርሳቸው ስመገብ አልጎደሉም ልብሴ ግን አለቀ ነገር ግን ይህ ቦታ ስለ ልብስ መከለያ ሆነኝ። የበጋ ፀሐይ ትኵሳትም አላስቸገረኝም ቊር ቢሆንም በዕድሜዬ ዘመን ሁሉ አላስጨነቀኝም"። ከዚህ በኋላም ከዘንቢል ካለው ሽምብራ እንድመገብ ማለደችኝ ከሽምብራውም በላሁ ከውኃውም ጠጣሁ። ግን አልጐደለም እግዚአብሔርንም አመሰገንሁት ልብሴንም ልተውላት ወደዱሁ እርሷም "ከዚህ የተሻለ አምጣልኝ" ብላ ይህን እምቢ አለችኝ። ❤ ከዚህ በኋላም ከእርሷ ዘንድ ሔድኩ ወደ ገዳም ደርሼ ስርሷ ለአበ ምኔቱ ነገርኩት። "እርሱም ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው አንዱን ይስጥ ብሎ ጮኸ ፈቃደኞች የሆኑም አመጡለት ያን ጊዜም ይዤ ሔድኩ ለአመተ ክርስቶስ ልሰጣት ብዙ ደከምኩ እርሷን በመፈለግ ዞርኩ አላገኘኋትም። ከጥቂት ቀኖች በኋላም አረጋውያን ወደ እኔ መጡ እንህም አሉኝ "ወደ ኤርትራ ባሕር የሚያደርሰውን መንገድ ይዘን በጣኔዎስ በረሀ ስንጓዝ ከዋሻ ዘንድ ሴት ተቀምጣ አይተን ከእርሷ በረከት ለመቀበል ሮጥን ሽሽታ ከዋሻው ገባች ወደ ዋሻውም አፍ ቀረብን ግን አላየናትም። ሽምብራ በዘንቢል ውኃም በጽዋ አግኝተን በላን ጠጣን ያን ጊዜም አለቀ እስከ ንጋትም አደርን። ❤ በነጋም ጊዜ በረከቷን ለመቀበል ቅድስቲቱን ፈለግናት ሙታም አገኘናት ጠጒሯም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል። በዚያም ሰገድን በበዓቷም ውስጥ ቀበርናት የዋሻውንም አፍ በደንጊያ ዘጋን የቅድስቲቱን በረከት እንድንቀበል አድሎናልና እግዚአብሔርን እያመሰገን ወደ በዓታችን ገባን"። በሰማሁም ጊዜ አስቀድሜ ያገኘኋት እንደሆነች አወቅሁ የነገራችኝንም ሁሉ ነገርኳቸው። ጠላት ዲያብሎስን ድል ያደረገው ዘንድ ክፉዎች አጋንንትንም ደካማውን ድኃ የሚረዳ የተመሰገነ እግዚአብሔርን ፈጽመን አመሰገን ነው። ለእግዚአብሔር ይስጋና ይሁን እኛንም በዘመች ቅድስት አመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከተበም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_መርቆሬዎስ፦ አባ እንጦንዮስ እንዲህ አለ "ለእኔ ገዳም አለኝ ይኸውም የወንድማችን የመርቆሬዎስ ዕረፍቱ ቀረበ" እያሉ ወደእኔ መነኰሳት የመጡበት ነው እኔም በረከቱን ለመቀበል ወደርሱ በሒድኩ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ሳትለይ በተመሥጦ ላይ አገኘሁት። ከመነኰሳቱ ጋራ በእርሱ ዘንድ ሦስት ሌሊቶች ኖርን በሦስተኛዪቱም ዕለት ነፍሱ ተመልሳ ዐይኖቹን ገለጠ በአየንም ጊዜ "ከእኔ ዘንድ ምን ሰበሰባችሁ" አለን እኛም የሆነውን ሁሉ ነገር ነውና ከዚህም በኋላ ያየውን እንዲነግረን ለመነው እርሱም የሚያስፈራ ሰው ወደርሱ መጥቶ ነፍሱን እንደወሰደ የኃጥአንን ሥቃይ እንዳሳየው የጻድቃንንም ዋጋቸውንና ተድላቸውን እንዳየው ነገራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወዮ ብሎ በማልቀስ በግምባሩ ከምድር ላይ ተደፋ እንዲህም አለን "ወንድሞቼ ሆይ ወደ ሐራጺት ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ማደሪያ ሒዱ። ከእኔ ጋራ የነበረውን መለአክ መርቆሬዎስን መልሳችሁ በትንሽ በዓት ውስጥ ሲጋደል የኖረ ጊዮርጊስን አምጡት ሲል ሰምቼዋለሁና ይቺም ሥጋው አስቲቋጠር የተጋደለባት የጨው በረሀ ናት"። ወንድሞች መነኰሳትም በሔዱ ጊዜ ሙቶ አገኙት ወደዚህ ገዳምም አምጥተው ቀበሩት። ይህም ወንድም መርቆሬዎስ እንደ ደረቀ እንጨት እስቲሆን ሥጋውን እጅግ አሠቃየ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም ይሔድ ዘንድ ተሰናበተኝ። ደግሞ "ግንቦት ሃያ ስምንት ቀን ወደኔ ና ታገኘኛለህና" አለኝ። በቀጠረኝም ቀን ወደርሱ ሒጄ አገኘሁደትና "እኔ ወደ አባቶቼ እሔዳለሁ" ወደ አንተም ሦስት አጋዘኖች ይመጣሉ ሥጋዬም በጀርባቸው ላይ ጫን እነርሱም ወደ ቦታዬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ይመሩሃል። በዚያም በማደሪያዬ ውስጥ ድፈኑኝ" አለኝ። እንደ ቃሉም ሆነለት ከመቃብሩም ቍጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አባ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላሙ አሜን።
إظهار الكل...
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

👍 2
❤ ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታይ ተወዳጅ ቤሰቦቼ እንደምን ሰነበታችሁ። በዕለተ ቀኑ #ስለ_ቸሩ_መድኀኔዓለምና_ስለ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ሃሌ_ሉያ። #ሼር_ሼር_ሼር_በማድረግ_ተባበሩ። 👉 #በደቡብ_ጎንደር_ሀገረ_ስብከት_ለሚገኘው #ለሞክሺ_ደብረ_ኅሩያን_ርግብ_መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ለአግልግሎት የሚሆነ ንዋየ ቅድሳት በጣም ስለተቸገሩ በስማችሁ ገዝታችሁ አብርክቱልን። 1,የአንድ ተልኮ ቀዳስያን ነጭ ልብሰ ተክህኖ። 2, የኪዳን መስቀል ሁለት። 3, አንድ ባለ አበባ ስጋጃ ምንጣፋ። 👉 ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ሃሌ ሉያ ገዳም እዛ ለሚማሩ የአብነት (የቆሎ) ተማሪዎች ለተማሪዎቹ ቤት ተሠርቶላቸው ቆርቆሮ በጣም ስለተቸገሩ ክረምት ሳይገባ ቆሮቆሮውን እናልብስላቸው። #የይድረሱልኝ_ጥሩ_ነው። 👉 #የሚያስፈልገው_ቆሮቆሮ_30 የአንዱ ዋጋ=#600 ብር ጠቅላላ ዋጋ= #18,000 ብር። 👉 ለበለጠ መረጃ፦#0912127085፣   #0911414852። በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ ያላችን ለመርዳት የምትፈልጉ ምዕመናን በዚሁ ቁጥር #በቴሌግራም(#@Teamhokidusan) ማውራት ትችላላችሁ ከበረከቱም የምትሳተፉ ስመ ክርስትናችሁ አባቶች በጸሎት እዲያስባችሁ ላኩልን። @sigewe https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886 https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKw
إظهار الكل...
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል። ❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

Photo unavailableShow in Telegram
[ ያለ እምነት - ፮ - ] .mp311.90 MB