cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መረጃ 24 ሰአት

ቶሎ ቶሎ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶት ላይክ እና ሼር አርጉ ፈጠን ፈጠን ብለን መረጃን አንለቃለን ላይክ ያርጉ ፈጠን በሉ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 017
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-87 أيام
-1230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በጀት‼️ ለ2017 ዓ.ም የቀረበው ወደ 1 ትሪሊየን ብር የሚጠጋ የመንግስት በጀት ለምክር ቤቱ ተላከ‼️ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2017 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ፤ የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ ተደርጓል። በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣ ለካፒታል ወጪዎች ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ነው። በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሰፊ ሥራዎች ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካላት የቆዳ ስፋት ከግማሽ በላይ የሆነው የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ለማድረግ፣ የደን ዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በአሁኑ ወቅት በተበጣጠሰ መልኩ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በክልል መንግስታት ፋይናንስ እየተደረገ እየተሰራ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተቀናጀና ተገቢውን ሀብት መመደብ በሚያስችል የፋይናንስ አሰራር ስርዓት መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ከዕሁድ'ለት ጀምሮ መቋረጡን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዕሁድ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከጎንደር ወደ ባሕርዳር እንዲኹም ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ እንደኾኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶቹ የተዘጉት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ባስቀመጡት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክልከላ ምክንያት መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ላለፉት አራት ቀናት ከባሕርዳር ወደ ኹሉም የጎንደር አካባቢዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልጸዋል። ከ10 ቀናት በፊት በሦስቱ የጎጃም ዞኖች ተመሳሳይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ እንደነበር ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል። አንድ ጊዜ ለአራት ወራት የተራዘመውና ባጠቃላይ ለ10 ወራት የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ለኹለተኛ ጊዜ ሳይራዘም ትናንት አብቅቷል። ኾኖም መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማብቃቱ በይፋ ያለው ነገር የለም።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከፍለው ለመማር የማይችሉ ተማሪዎች የባንክ ብድር እንዲያገኙ የሚረዳ ሕጋዊ አሠራር እንዲመቻች ተጠየቀ፡፡ በ2015 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባውና ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የሚያደርገው አዋጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከስምንት ወራት በፊት ወደ ሥራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝነት ለማሸጋገር ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ምንም እንኳ ተጠያቂነቱ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መንግሥት በገንዘብ የሚደግፋቸውም ቢሆኑም፣ ራሳቸውን በራሳቸው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የፋይናንስ፣ የአስተዳደር፣ የአካዴሚክ፣ የሰው ሃብት እና መሰል ነፃነት አዋጁ ያጎናፅፏቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ራስ ገዝ ሆኖ ሥራ በጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ከፍለው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ክፍያው በከፍተኛ መጠን እንደጨመረባቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ወደፊት ራስ ገዝ የሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ሲገቡ አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ከፍለው እንዳይማሩ ይገድባል የሚል ሥጋት እየተሰማ ነው፡፡ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ለተማሪዎች የሚሰጥ ብድር መመቻቸት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በተመሳሳይ፤ መንግሥት በውጭው ዓለም የተለመደውን ለተማሪዎች ብድር የሚቀርብበት አሠራር ሊያስብበት ይገባል ብለዋል፡፡
إظهار الكل...
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ? ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦ ➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ፣ ➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል። #የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram