cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Kahlil ጂብራን •

"ውበት የበለጠ ደምቆ የሚታየው . . . በሚመለከተው ዓይን ሳይሆን፥ ሊያየው በሚናፍቀው #ልብ ውስጥ ነው፡፡" / የሊባኖሱ ባለቅኔ. . .'ካህሊል ጅብራን' / • • • • • • • • • • ♥ ♥ ♥ The lovely poet KHALIL GIBRAN read more @tobiyan --------------- see more @tobiyan

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
928
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በውቄ አልወጣም ተራራ ደመናን ልዳብሰ ቀስተ ደመናውን ቁልቁል ልቀለብስ አልዋስም እኔ ካቡነ ተክሌ ክንፍ ከያዕቆብ መሰላል፤ እኔ መውጣት ሳስብ ሰማዩ ዝቅ ይላል:: ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
إظهار الكل...
የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች 68. ሚካኤል ተው ተብት በኩፍር ሳትቀጣ ይበቃሃል የሚል ከአላህ አዋጅ መጣ እንዴት ያለች ንፋስ የሆነች ባላንጣ በጥፊ ብትመታው በአፍንጫው ደም መጣ ጉዞው ተቃረበ እሩሁ ልትወጣ:: 69. ጉግሣና ራስ ( ወ )ሎሌ፣ አጼ ዮሐንስ ሚካኤል፣ ምኒልክና አጼ ቴዎድሮስ ዘውዲቱና ፈረንጅ ተፈሪ ድረስ በብልሃት ገዟት አልጋው እንዳይፈርስ መጨረሻው ከፍቶ ጣሉት እንደርኩስ:: 70. የአላህን ትተው በውሻ የሚመሩ በሐበሻ መሬት ግፍን የሚሠሩ ቁመታቸው አጭር መልካቸው የሚያምሩ አይነግሡም ብላችሁ አትወዳደሩ ሃምሳ ዓመት ይነግሣል እግረ ውትርትሩ:: 7 1 .ባሕር ወዲያ ማዶ ዘር መጣ ሊጠቅም ግድግዳው የሚያምር በሽንጥ የሚጠቅም ቅጠሉ ለስላሳ ቁመቱ ረዣዥም እሱን ያልተከለ እንዴት ይለጅም ሸዋ በተለየ ያለሱ አይቆምም:: 72. ሥራቸው ባለጌ አህያ የሚበሉ ባሕር ወዲያ ማዶ ክፉ ሰዎች አሉ፣ ሐበሻን ለመውረር ሐሳብ ያስባሉ የኋላ የኋላ መምጣት ይመጣሉ አምስት ዓመት ገዝተው ወዲያው ይሄዳሉ:: 73. ድንጋይ ዱቄት አርገው መንገድ የሚያበጁ ገመድን ዘርግተው መብራት የሚያበጁ አህያ የሚያርዱ አሞራ የሚፈጁ መጡ እየተማሩ ሐበሻን ሊያበጁ ማማሩን አማረች ግን ብዙ ሰው ፈጁ:: 74. እግሩ እንደ ሙቀጫ የሚንከባለል ቢሄድ አይታክተው አቀበት ቁልቁል ጭቃ ካለው መንገድ መሄድ የማይችል ገደል የሚያንሸራትተው የሚንከባለል ይህንን የገዛ ካለፈው ምንም አይል:: 75. በገዛ እጁ ነድፎ ፈትሎ የሚሠራ ሰውን የሚያስገርም የሚሠራው ሥራ ልብሱ ተፈላጊ ሰውን የሚያኮራ ልብሱን ላይሸከሽክ አስተውሎ የሚሠራ በዚህ አይግረምህ ሌላ አለ የሚሠራ:: ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
إظهار الكل...
በዕውቀቱ ስዩም ህልም አለህ ይላሉ ራዕይ ያዘለ ኮከብ አለህ አሉ ትንቢት የታደለ ህልምህን ንገረኝ ኮከብህን አሳየኝ ተርጉሜው ልፅናና መነሻዬን ልወቅ መድረሻዬን ላጥና ባንተ ዕጣ ፈንታ ውስጥ ርስት አለኝና። _______________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
إظهار الكل...
✍ መገንሽ በስውር ስትወርጂ ኖሮ ላፈር ገላሽ ከጥፋትሽ:ገኖ፣ አንቺን ሚጠጥትሽ ባል-ሰማ ነው አሉ፣ባል አወቀ ጭንቅሽ። 'ሰቢ ፯ ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ ከአባል የተላከ #yeneta #ሼር
إظهار الكل...
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ምን ያህል ቢከፋ ምን ያህል ቢያሳምም፣ ለአላዘር መሞት የክርስቶስ እንባ በጉንጩ ሚዘምም፣ ፡ እንዴትስ ቢያንስ ነው እንዴትስ ቢጣጣል፣ በመግደል መሸነፍ እስከመቼ ድረስ ኖሮ ያልጠገበ በሞቱ ይቀጣል፣ ፡ ወረርሽኙ ሲነግስ ተጠንቀቁ ብለው የነተረኩኑ፣ ገዳይ ሲያሰፈስፍ ሜንጫ ሲሳልብን ስለምን ጨከኑ፣ ወይንስ ገዳይ መሸነፉ እንዲገባው ብለው ሟች ላይ ተዋገኑ፣ ፡ ምን ያህል ቢከፋ ምን ያህል ቢያሳምም፣ ለአላዘር መሞት የክርስቶስ እንባ በጉንጩ ሚዘምም፣ ፡ ሞትማ ህመም ነው የአምላክን እንባ ቋት የደነቆለ፣ ልቡን ያሳዘነ የወዳጁ በድን ስላቆለቆለ፣ አፈር ተምሶለት ባፈር ስለዋለ፣ ፡ እሱ ከታመመ እኔንማ እሰቡኝ፣ ማች ስቆጥር የምውል መግደል መሸነፍ ነው ብለው ከትበውኝ፡፡ ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
إظهار الكل...
ሚስት-- ላንተ ስል ከአለም እንደምጣላ ታውቃለሃ? ባል-- ግንኮ ሁሌ ከኔ ጋር ነው ምትጣዪው ሚስት-- ምክያቱም የኔ ዓለም አንተ ነሃ፡፡ 😂❤️😂❤️😂❤️😂❤️😂❤️😂 ________________________________ ለወዳጅዎ ያጋሩ @thiolophy
إظهار الكل...
🔰Online ስራ መስራት እንፈልጋለን ላላችሁ ይሄን⬇️ ቦት ተጠቀሙ፤ ሞክሬው ሰርቷል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i392939044 1⃣. ቦቱን Start በሉት። 2⃣. Join Channel የሚል ይመጣል #Join በሉት። 👉 @askAnythingEthiopia 👈 🔆ለተለያዩ ሰዎች በላካችሁ ቁጥር፤ በየአንዳንዱ ሰው 1ብር ይከፍላችኋል።✅ ❗️ቦት ውስጥ ከገባችሁ ብኋላ join channel የሚል አለ እሱን join ማለት አለባችሁ እንጂ ቦቱን ብቻ ስለተቀላቀላችሁ አይቆጥርላችሁም
إظهار الكل...
አንድ ነገር ላስቸግርህ? 🙏 ❇️ Online ስራ መስራት እንፈልጋለን🤔 ላላችሁ ይሄን⬇️ ቦት ተጠቀሙ፤ ሞክሬው ሰርቷል። 💡ስለ ቦቱ ቀለል አርጌ ለመንገር ያህል:- ከታች ያለውን ሊንክ ነህተሽ ሁለታችንም ትርፋማ እንሁን🤷‍♂️🤷‍♂️ የሚሰራው በመጀመሪያ ሊንኩን start ብለህ Ask Any Things bot ውስጥ ተቀላቀይ በመቀጠል invite ሚለወን በመንካት share ሚለወን እየነካህ በ 1 ሰው 50 ሳንቲም የከፈልሀል ጊዜው አሁን ነው::💁🏿‍♂ መርሳት የሌለብህ ነገር ግን👇 #bot_start_ብለህ_join_channel_ሚለውን_መንካት_ይኖርብሀል
إظهار الكل...
Start
Join channel
የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም - - - - - - - - - - - - - - - - “በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡ የዚህ አመለካከት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡ የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡ 2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡ 3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡ - - - - - - - - - - - - - - - - - በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ! Dr. Mehret Debebe 📖 📖 📖 📖 📖 📖 @thiolophy @thiolophy @thiolophy #ማንበብ_ምናልባት_ምናልባት_የተሻለ_ሰው_ሊያረግ_ይቻላል
إظهار الكل...
የህይወት ልጓም (Samuel Geda) 📄📄📄 አንድ የሥነ-ሕይወት (Biology) መምህር ለተማሪዎቹ፤ 'አባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ የሚለወጥበትን ዑደት' እያስተማራቸው ነው። ለጥቆም፤ "በሚቀጥሉት ሰዓታት ከአባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ የተቀየረው አካል፡ ከዕጭ-ሽፋኑ (cocoon) ውስጥ ለመውጣት ትግል የሚያደርግበት ጊዜ ነው፤ ሂደቱን ከመመልከት ውጪ ታዲያ ማንም ቢራቢሮውን ለመርዳት እንዳይሞክር!" ብሎ በማስጠንቀቅ፡ ተማሪዎቹን ጥሎ ከቤተ-ሙከራው ይወጣል። ተማሪዎቹም የሚሆነውን ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ ጀመር፤ ልክ መምህሩ እንዳላቸውም ቢራቢሮው ከእጭ-ሽፋኑ (cocoon) ውስጥ ለመውጣት ይታገል ጀመር። ይሁንና ከተማሪዎቹ አንደኛው ልጅ የቢራቢሮውን ትግል ዐይቶ ያዝንና ከመምህሩ ትእዛዝ በተቃራኒ- ብራቢሮውን ከእጭ-ሽፋኑ ሊያወጣው ይወስናል። 'ትግሉን ባቀልለት' ሲልም የእጭ-ሽፋኑን ይሰብረዋል፤ ይሁንና እንደጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ከደቂቃዎች በኋላ ቢራቢሮው ይሞታል። ፧ መምህሩም የተማሪዎቹን ሁኔታ ሊያይ ሲመለስ የተፈጠረውን ነገር ይነግሩታል። ይህን ጊዜ መምህሩ የእጭ- ሽፋኑን ለሰበረው ተማሪ፡ ሁኔታውን ያስረዳው ጀመር፤ "ቢራቢሮውን የገደልከው እርሱን ለመርዳት በማሰብህ ነው፤ ምክንያቱም ከእጭ-ሽፋኑ ለመውጣት ትግል ማድረጉ፡ አንተ እንዳሰብከው ቢራቢሮውን የሚጎዳ ሳይሆን ለክንፉ ጥንካሬና እድገት የሚረዳው ነበር። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነውና። አንተ ግን ትግሉን በማቋረጥህ ወይንም በመከልከልህ ምክንያት ቢራቢሮው ሊሞት ችሏል።" * * * ይህ ህግ በህይወታችንም ይሠራል። ከትግል ውጪ ወደ ህይወታችን የሚመጣ (ምንም ዐይነት) ስኬት የለም። አንዳንዴ ወላጆቻችን ከሃዘኔታ ስሜት ተነስተው የትግል ህይወትን ከኛ በማራቃቸው ጎድተውናል፡ እንዳንጠነክርና እንዳናድግም አድርገውናል። ብዙውን ጊዜ ትግል ምቹ ሜዳን ስለማይፈጥርልን አንወደውም። የምንፈልገው ስኬት ሁሉ ያለ ትግል ሰተት ብሎ እንዲመጣ ነው። ስኬቱን እንፈልጋለን ትግሉን ግን አንፈልገውም። ፧ አንድ ቢራቢሮ ቢራቢሮ ለመሆን-- ከእንቁላል ወደ እጭ (larva)፤ ከእጭ ወደ ሙሽሬ (pupa)፤ ከሙሽሬ ወደ አባጨጓሬ፤ ከአባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ፤ ከቢራቢሮነት መብረር እስከቻለባት ደቂቃና ሰአት ድረስ ያለውን *ትግል* ማለፍ የግድ ብሎታል። ልክ እንዲሁ፤ በህይወት ለማደግ/ለመለወጥ (ምንጊዜም) በትግል ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። ስኬት መፈለግህ ጤነኛና ብሩህ አእምሮ የመያዝህ ምልክት ነው። ይሁንና ስኬታማ ለመሆን ጥንካሬና እድገት የግድ ይሉሃል፤ እነርሱ የሚገኙት ደግሞ በትግል ውስጥ ነው። ይኸውልህ፤ የህይወት ትልቁ ልጓም ምንድነው ካልን- ትግል ነው። ነጻነት ያለው ሰው ለመሆን እንጂ ነጻ ለመሆን መፈለግ የለብንም። ፈጣሪም ቅርፅ የሚሰጠን በትግል ውስጥ እያቀለጠ ነው። ምናልባት ልጓም- እርምጃን የሚገታ፣ እረፍት የሚያሳጣ፣ ምቾት የሚነሳ፣ ገደብ የሚጥል፣ ከመንገድ የሚያስቀር፣... ሊመስል ይችላል። ይሁን እንጂ፤ ልጓሙ- ከግብ የሚያደርስ፣ የተገራ ማንነትን የሚያላብስ፤ ብቁና ስልጡን የሚያደርግ፣ ወደ ዓላማ-መርና መርኽ-ገዝ ህይወት (Self actualization/ realization) የሚያሳድግ፣ ጥንካሬን የሚሰጥ፣ ከሁሉ በላይ፡ ከራስ አልፎ ለሌላው የሚቆረስ ስብእና ባለቤት የሚያደርግ--ነው። ስለዚህ ትግል ማለት የስኬት ተቃራኒ ሳይሆን የስኬት አካል ነውና- ትልቁን የህይወት ልጓም- ትግልን አንጥላው! ሰናይ ዕለት! 📄📄📄 Credit to ፦ Samuel Geda 📖@thiolophy @thiolophy @thiolophy #ማንበብ_ምናልባት_ምናልባት_የተሻለ_ሰው_ሊያረግ_ይቻላል
إظهار الكل...