cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Birew(ለዓለም ብርሃኑ)

ናትእናሴና። https://t.me/joinchat/AAAAAEZFxCLVn_dR7I952w https://www.youtube.com/watch?v=3wTpmD6_XSo&t=704s https://www.youtube.com/watch?v=w_DrEn3gZTE&t=208s

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
145
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት 1. ጥሩ አድማጭ መሆን ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡ 2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡ 3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡ 4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡ 5. አቀማመጥን ማስተካከል ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡ 6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡ 7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡ 8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡ 9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡ ተግባቦት የብዙ ሰው ችግሮ ነውና #share በማረግ ለሌሎች እነዚህን ቁልፍ ነገሮች እናሳውቅ ፔጃችንን #Like በማረግ በየቀኑ አዕምሮዎን በመልካም ሀሳብ ይመግቡ (በዘመነ ቴዎድሮስ) ©zepsychologist #ለሀገራችን ቸር ሳምንት ይሁንልን
إظهار الكل...
ስልካችን ቢበላሽ እንዴት አድርገን ስልክ ቁጥሮቻችንን እናገኛለን ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ይዘን ቀርበናል እባኮትን ይህንን የማያውቁ እህት ወንድሞቻችን እንዲያውቁ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup መያዝ አለብን እንዴት Buckup እንያዝ? Step By Step 1:-contact ዉስጥ መግባት 2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን 3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ እሱን መጫን\ 4:-ከዛ Export to Storage ወይም export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ እሱን መጫን በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ FileManager መክፈት 5:-Phone Storage ወይም Memory Storage መክፈት 6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ 7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ Coppy ማረግ ይቻላል 8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል 2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት በሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ አንደምንችል 1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየሁችሁ Memory Card ላይ Coppy ማድረግ አለብን 2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት 3:-ከዛ setting botton ዉስጥ መግባት 4:-inport/ export ዉስጥ መግባት 5:-Import from Storage ማድረግ 3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንደምንችል፡፡ እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን በጂሜይል / Gmail / ላይ ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር አገናኝተን የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ አድራሻችንን እዛ ላይ ማኖር ያስችለናል። በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን እንዳይጠፉብን ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን ድንገት ቢጠፉብን እንኳ ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን ውስጥ 1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት አድራሻ / 2:-Contacts/ የሚለውን መጫን 3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ / Restore contacts/የሚለውን በመጫን የስልክ አግራሻችንን ጂሜይል ላይ ለማኖር እንችላለን መረጃው ከተመቻችሁ የInformation Technologyን ፔጅ ላይክ እና ሼር በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩ!! ▬▬ Share ▬▬▬▬ ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። here it is https://t.me/Information_Science_Technology በተጨማሪም የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድርጉ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
إظهار الكل...
Information Science and Technology

Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.

ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች 1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system) 2 የስክሪን መጠን (Screen Size) 3 ሲፒዩ(CPU) 4 ራም(RAM) 5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type) 6 የምስል ጥራት (Image Quality) 7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life) 8 ብራንድ (Brand) ኮርi3 ፣ ኮርi5፣ ኮርi7 ምንድናቸው? በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ 1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች ምርጫ ነው፡፡ ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡ 2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ • 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡ • 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡ • 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡ • 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡ ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡ 3. ሲፒዩ(CPU) የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡ • AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች ሲሆኑ Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡ • Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡ 4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡ 5.የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች አሉ( HDDrive እና SSDrive) ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት የዩትብ ቻናላችንን ሳብስክራቭ ያድርጉ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
إظهار الكل...
አንዳንድ የኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ 1. #RAM (Random Access Memory) ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል:: (1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል:: : 2. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot) ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን:: : 3. #Heat_sinker ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም #Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል:: : 4.#Fan ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው:: #CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን:: : #CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው::ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው:: #CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም : 1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው:: : 2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል:: : 3. #Regster ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው:: #Port (ፓርት) : port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው:: መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ:: የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ # ኤሌክትሪክ # ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው:: #Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል) power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው:: የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል:: #ሞደም (Modem):-ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው:: : #ኪቦርድ Keybord:-መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት.ቁጥሮች.ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::
إظهار الكل...
ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል። ✅ እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ። ✅ የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ። ✅ ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ። ✅ ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ። ✅ ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ። ✅ ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ። ✅ የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና። ❇ በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ። ❇ የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ። ❇ መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ። ❇ ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ። ❇ አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም። ❇ መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!! አንብበው ለወዳጅዎ ካላካፈሉት እንዲሁም የተሰማዎትን ካልፃፉ ሲበዛ እራሥ ወዳድ ነዎት ማለት ነው!!!! ምርጥ መጣጥፎች እንዲደርስዎ ከፈለጉ ላይክ ሼርርርር ያድርጉ።
إظهار الكل...
ጠቃሚ ምክር ለእርስዎ! 🚹🚺 ይሄን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት እንደማንበብ ነው! ✅ በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ። ✅ ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ። ✅ የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። ✅ ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ። ✅ የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ። ✴ ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ። ✴ ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ። ✴ ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ። ✴ እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ። ✴ ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። ✴ በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ። ✴ የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ። 🌀 ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! 🌀 መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ። 🌀 ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ። 🌀 ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ። 🌀 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ። 🌀 ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ። 🌀 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !! 🌀 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ። ✅ ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል። ✅ እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ። ✅ የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ። ✅ ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ። ✅ ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ። ✅ ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና
إظهار الكل...
ፕሮጀክት ቀረፃ ======== አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- A) ማውጫ (Table of contents) ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ B) አጭር መግለጫ (Executive Summary) ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው የሚገቡ ሃሳቦች ☞ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር ☞ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ ☞ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ ☞የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ ☞ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም ☞ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡ C) መግቢያ (Back Ground) ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡- ☞ ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ ☞ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው ☞ ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡ D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale) ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡ E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective) ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):- ☞ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ ☞ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ ☞ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት ☞ የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት ☞ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡ G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):- ☞ ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ ☞ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር ☞ የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡ H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):- ☞ ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡ ☞ ያገባኛል ባዮች (stakeholders):- የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡ I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):- የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቸና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡ J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):- ☞ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡ ☞ ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡ K) ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation): ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡- ☞ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ ☞ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት ☞ የግምገማ ዕቅድን ☞ ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ L) የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability): ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
إظهار الكل...
የደም አይነት እና የአመጋገብ ስርአት (የወዳጅዎን የደም አይነት ያውቃሉ? እንግዲያውስ ሼር ያድርጉት) የሰው ልጅ ደም በቀይ የደም ሕዋሳት ላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች መሠረት በማድረግ ኤ (A) ፣ ቢ (B) ፣ ኤቢ (AB) እና ኦ (O) ተብሎ በአራት ይከፈላል፡፡ የተመገብነው ምግብ በአንጀታች ውስጥ ከተፈጨ በኋላ በደማችን አማካኝነት ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ይሠራጫል፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ምግባችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ከደማችን ጋር ኬሚካላዊ ግንኙነትና ውሕድ ይፈጥራሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከደማችን ዓይነት ጋር የሚስማማ ምግብ ከተመገብን የምግብ የመላም ሂደት ሊፋጠን፣ አላስፈላጊ ክብደት ልንቀንስ፣ የላቀ ጉልበት ሊኖረን እንዲሁም የበሽታ የመከላከል ዓቅማችንም ሊዳብር ይችላል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም ከእያንዳንዱ የደም ዓይነቶች ጋር የሚጣጣሙ የምግብ ዓይነቶችን እንጠቅሳለን፡፡ 1) የ ኦ (O)ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት ይህ የደም ዓይነት ከሌሎች ቀድሞ የነበረ ጥንታዊ ሲሆን ከእንስሳት አዳኞች የተወረሰ የደም ዓይነት ነው፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ዓሣ፣ የባህር ምግብ፣ ቀይ ስጋ፣ ጨው፣ ዶሮ፣ ሲኳር ድንችና የመሳሰሉትን ምግቦች እንዲያዘወትሩ ይመከራል፡፡ በዚያውም ልክ እንቁላል፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣ ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማራቅ አለባቸው፡፡ 2) የ ኤ (A) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት ይህ የሰው ልጆች ወደ እርሻ ሲገቡ በተፈጠረው የአመጋገብ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የደም ዓይነት ነው፡፡ በዚያ ዘመንም የሰው ልጆች ለመኖነት ፊታቸውን ወደ አትክልቶች በማዞራቸው ምክንያት በጊዜ ሂደት እጅግ የዳበረ የምግብ ማላም ስርዓትን አዳበሩ፡፡ በአንጀታችው ውስጥ የሚገኙት የባክቴሪያዎች ዓይነትና ቁጥርም እጅግ ተበራከተ፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ፖም፣ አቮካዶ፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባቄላ፣ እርጎ፣ የስንዴ ዳቦና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ነገር ግን እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በተገቢው መንገድ ለማብላላት አንጀታቸው አልዳበረም፡፡ 3) የ ቢ (B) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት የጥንቶቹ አዳኞች ወደ ሒማሊያስ ተራሮች በመሰደድ እንስሳትንም በማላመድ የአርብቶ አደር ሕይወትን መምራት ሲጀምሩ የተፈጠረ የደም ዓይነት ነው፡፡ ቀይ ስጋ፣ ዓሣ፣ እርጎ፣ ዓይብ፣ ወተት፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ወይንና አናናስ ተስማሚ ከሚባሉት ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ ዶሮ፣ ስንዴ፣ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል፡፡ 4) የ ኤቢ (AB) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት ኤቢ የደም ዓይነት በቅርብ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ከዓለም ህዝብም በአምስት ፐርሰንቱ ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ስጋንና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል፡፡ ፍራፍሬዎችና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ሀብሀብ እና ወይን፣ እንደ ቱና እና ሰርዲን ያሉ የባህር ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን ከበቆሎ፣ የበሬና አሳማ ስጋ እነዲሁም ከአልኮሆልና ቡና መራቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የወዳጅዎን የደም አይት ያውቃሉ? እንግዲያውስ ሼር ያድርጉት በየእለቱ ጤና ነክ ጠቃሚ መረጃዎችን እናቀርባለን እንወያያለን እንዲሁም ለሚነሱ ሞያዊ ምላሽ እንሰጣለን። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን Dr.beza
إظهار الكل...
ስልኮትን ፓተርን ረስተውት ስልኮ አልከፍት ብሎታል? እንዴት ስልኩን እንደገና መክፈት እንደሚቻል ..... ስልኮትን ፓተርን ረስተውት ስልኮ አልከፍትብሎታል? የተረሳውን ፓተርን አጥፍተን እንዴት ስልኩን እንደገና መክፈት እንደሚቻል እናያለን። ግን አንድ ማወቅ ያለቦት ነገርቢኖር Install ያደረጉት አፕሊኬሽን እንዲሁም የመዘገቡት ስልክም ካለ መጥፋቱ የማይቀር ነው። እነዚህን 6 ስቴፖችይጠቀሙ Step 1:- ስልኮትን switch off ያድርጉትናለጥቂት ሰከንዶችይጠብቁ። Step 2:- ከዛም እነዚን ቁልፎችማለትም ድምፅ መጨመሪያውን( ),Home key, power በተኑን በአንድ ላይይጫኗቸውና ስልኮትን ያስነሱት። Step 3:-ከዛም የተለያዩ ኦብሽኖችይመጡሎታል። Step 4:- ከዛም "Restore factorydefaults" ወይም "Delete all userdata" የሚለውን ይምረጡ። Step 5:-ከዛም "Reboot system now"የሚለውን ይምረጡ። Step 6:- ከዛም ስልኮት Reboot አድርጎ እስኪጨርስ ይጠብቁ። ከዚያም ስልኮት እንደ አዲስ ይከፈታል።
إظهار الكل...
የሚጠቅሞት ነገር ነውና በትእግስት ያንብቡት ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ ። ---------------------------------------------------------------- #የዝንጅብል_ጠቀሜታዎች ዝንጅብል እጅግ ጠቃሚ በሆኑ ንጥረነገሮች እና የማደስ አቅም ባላቸው ውህዶች የታጨቀ ነው::ይህ ተወዳጅ ቅመም በመላው ዓለም በየእለቱ ቀዳሚና ተመራጭ የምግብ ማጣፈጫ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ዝንጅብል በተፈጥሮ በታደለው ኬሚካላዊ ይዘት ለጤና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ በረከቶችን ይሰጣል፡፡ በተለይ የዝንጅብል ሻይ (ቀሽር) ወይም የዝንጅብል ውሃ ሳይንስ ያረጋገጣቸው ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጤና ጥቅሞች ይሰጣል፡፡ 1. ለጉንፋንና ለጉሮሮ ሕመም ወሳኝ የተፈጥሮ መድኃኒት ነው፡፡ ለሆድ ቁርጠትም ተመራጭ ነው፡፡ በተለይ በወር አበባ መምጫ ቀናትና በወር አበባ ጊዜ እህቶታችንና እናቶቻችን የዝንጅብ ሻይ ብታዘወትሩ ይመረጣል፡፡ ቁርጠት ከማስታገሱ ባሻገር የወር አበባው ያለምንም መቆራረጥ በቶሎ እንዲፈስ ይረዳዋል፡፡ 2. ፀረ-ማቃጠል( Anti-inflammatory) ፡- የዝንጅብል ሻይ አዘውትሮ መጠጣት ብግነትን ወይም መመረዝን ይከላከላል፡፡ባክቴሪያዎች፣ኬሚካሎችና ደካማ የምገባ ስርዓት ብግነት በሰውነታችን ውስጥ እንዲከሰት ምክንያት ናቸው፡፡ ብግነቱ እየጨመረ ሲሄድ ደግሞ ዘላቂ ለሆኑ በሽታዎች ይዳርገናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ለመከላከል የዝንጅብል ሻይ ያዘውትሩ ምክራችን ነው፡፡ አልርጂክ እና የጡንቻ ሕመምን በቀላሉ ያባርራሉ፡፡ 3. የምግብ ያለመፈጨት ችግር ያለባችሁ የዝንጅብል ውሃ ወይም ሻይ ቀዳሚ ምርጫችሁ ብታደርጉት ውጤቱን በፍጥነት ታዩታላችሁ፡፡ ማቅለሽለሽን አስወግዶ የበላችሁት ምግብ በፍጥነት እንዲፈጭ ያደርጋል፡፡ ስለሆነም የምግብ ስርዓተ ልመትን ጤናማ በማድረጉ ዝንጅብል ሲበዛ ምስጉን ነው፡፡ በተለይ ማቅለሽለሽ እና ትውከት ለሚያስቸግራችሁ በፍጥነት ተግብሩት፡፡ በጉዞ ጊዜ ለሚያስመልሳችሁ ከጉዞአችሁ በፊት የዝንጅብል ሻይ እንድትጠጡ ይመከራል፡፡ 4. የደም ስኳር መጠንን ሚዛናዊ ያደርጋል ወይም ያስተካክላል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የስኳር ሕሙማን የደም ስኳር መጠናችሁን በፍጥነት ያሻሽላል፡፡ 5. የደም ቅባት ወይም የኮሌስትሮል መጠንን ያስተካክላል፡- የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት መጥፎ የተባለውን የኮሌክትሮል መጠንን በመቀነስ በዚህ ችግር ምክንያት የሚከሰቱ የልብና የስትሮክ በሽታዎችን ይከላከላል፡፡ 6. የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ጤናማ አመጋገብን ከዝንጅብል ሻይ ጋር አቀናጅተው ዘወትር የሚወስዱ ከሆነ ሸንቃጣ ለመሆን ብዙ ቀናት አይፈጅብዎትም፡፡ 7. ለሆድ ቁርጠት ብዙ አይነት እጽዋት እና ቅመሞች ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ጥሩ ናቸው፣ ቢሆንም ግን የዝንጅብልን ፈዋሽነት የሚስተካከል የለም:: በተለምዶ ሆዱን ለሚያቅለሽልሸው ሰው የዝንጅብል መጠጥ ይሰጣል:: ጥቂት ዝንጅብሎች ወይም የሚንት ቅጠሎችን በሚፈላ ውሀ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃወች በመዘፍዘፍ ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር መጠቀም ለሆድ ቁርጠት ማስታገሻነት ይውላል:: 8. የራስ ምታት/ሚግራይንስ(ከባድ የራስ ምታት) እንደ ቆንዶ በርበሬ፣ የካይኔ ቃሪይ እና እንደ ዝንጅብል ያሉ እጽዋቶች የራስ ምታትንና ሚግራይንስን ለማስታገስ ይጠቅማሉ:: በተለየ ደግሞ ዝንጅብል በሚግራይንስ ሰበብ የሚከተለውን የማቅለሽለሽ ችግር ለመከላከል ይጠቅማል:: እነዚህን 3 አይነት እጽዋቶች እንደተፈጥሯዊ መድሀኒት በሻይ ለመጠቀም፣ አንድ ኢንች የዝንጅብል ክታፊ ከአንድ የሻይ ማንኪያ ቆንዶ በርበሬ ጋር መጠቀም ይቻላል። @information_science_and_technology ▬▬▬ Share ▬▬▬▬ ለተጨማሪ እውቀት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። here it is https://t.me/Information_Science_Technology
إظهار الكل...
Information Science and Technology

Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.