cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሄለን በርሄ

helen berhe official page

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
439
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...

إظهار الكل...

++ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ++ "መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም" ቅዱስ ባስልዮስ "በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ "ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ "የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው" ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ "እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD) "ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD) ‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡ የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ~ኢትዮጵያ~
إظهار الكل...
إظهار الكل...
አስደንጋጭ እና አስደናቂ ታላቅ ተአምር | ቃጥላ ጽዮን ማርያም | 2014 አዲስ አበባ | @Axum Tube / አክሱም ቲዩብ

ስለተመለከታችሁን እናመሰግናለን ቪዲዮውን ሼር በማድረግ እናንተ ያገኛችሁትን እውቀት ለሌሎች አሳውቁ። ይህንን የአክሱም ቲዩብ ዝግጅት ዳውንሎድ አድርጎ ድጋሚ በሌላ ቻናል ላይ መጫን በጥብቅ የተከለከለ ነው። Copyright © Axum Tube Like, Comment and Share this video. ለቻናላችን አዲስ የሆናቹ ሰዎች አክሱም ቲዩብን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰቡን ተቀላቀሉ።

https://www.youtube.com/channel/UCUj5aUlwytXfTAK33Zx_8KQ?view_as=subscriber?sub_confirmation=1

=========Follow us on=========== Facebook:

https://www.facebook.com/AxumTube

Instagram :

https://www.instagram.com/axumtube

Telegram:

https://t.me/Z_Tube

Twitter:

https://twitter.com/axumtube

Tik Tok:

https://www.tiktok.com/@axumtube

Pinterest:

https://www.pinterest.com/AxumTube

እንኳን ለአጋዕዝተ አለም ቅድስት ሥላሴ ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ በረከት እና ምህረት በሁላችንም ላይ ይደርብን።አሜን አሜን አሜን 🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬
إظهار الكل...
በዓለም ላይ 3 አይነት ሰዎች አሉ። እነሱም:- 1. የተቀመጡ ሰዎች 2. የተሰረቁ ሰዎች 3. ባለ ራዕይ ሰዎች ✍ የተቀመጡ ሰዎች እነኚህ ሰዎች ሕይወትን በ TV ነው የሚያዩት። ትችትን፣ ነቀፌታን፣ ተግዳሮት የማይፈልጉ፣ አሸናፊነትንም ሆነ ሀላፊነትን አይወዱም ባጠቃላይ (Challenge Life) አይፈልጉም። ✍ የተሰረቁ ሰዎች ሌላውን መስሎ መኖር ምኞታቸው ነው። የራሳቸው የሆነ አቋምም ሆነ ማንነት የላቸውም። የተሰረቀ ሰው ራሱን ከሌላ ጋር እያወዳደረ ነው የሚኖረው! ✍ ባለራዕይ ሰዎች ነፃ እና ተፈጥሯዊ ሰዎች ናቸው። የበታችነት ስሜት አይሰማቸውም! መተባበር፣ ፍቅር እና ማህበራዊ ተቆርቋሪነት መገለጫቸው ነው። እነዚህ ሰዎች በቅድሚያ፦ 🔹 ማህበረሰቡን 🔹 በመቀጠል ቤተሰባቸውን 🔹 በመጨረሻም ራሳቸውን የሚያስከትሉ ናቸው። "እንዲህ አይነት ሰው ተስፋ እግዚአብሔርን የሚያምን እንጂ ተስፋ የሌለው ሰው አይደለም ጽኑ እምነት ያለው ፍቅርን በልቡ የታጠቀ ነው !"
إظهار الكل...
"#ሴተኛ_አዳሪ ስለሆንኩ ጧፉን ልነካ አልችልም!" ................................. እኛስ ከእህታችን ምን እንማራለን ?? ................. ምን ቢመሻሽም ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖትን ተሳልሜ ልምጣ ብዬ ወደ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ፤ ወርሃዊ በዓላቸው እንደመሆኑ መጠን መግቢያው በር ላይ ግርግር አለ፤ አንዲት ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ጧፍ የምትሸጥ ነጋዴ ጋር አንዲት ነጠላ የተከናነበች ወጣት ጧፍ ለመግዛት ቆማለች፤ እኔም አጠገባቸው ነኝ “ወንድም ይቅርታ አለችኝ’’ ወጣቷ፤ “አቤት” አልኳት “እኔ ስለማልገባ ነው ይህንን ጧፍ ስጥልኝ” አለችኝ፤ “እኔም ተሳልሜ ነው የምመለሰው ለሚገባ ሰው ስጪው” አልኳት፤ እሺ ለሚገባ ሰው አንተ ስጥልኝ አለችኝ፤ እኛ ስንነጋገር ተሽከርካሪ... ወንበሩ ላይ ያለችው ጧፍ ነ...ጋዴ ጧፉን እንደያዘች እጇን ዘርግታለች፤ እሺ ችግር የለውም እሰጥልሻለሁ ግን ለምን አንቺ አትሰጪም አልኳት፤ እኔ ሴተኛ አዳሪ ነኝ እንዴት በእጄ እነካዋለሁ ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ሲቀደስ የሚበራ አይደለም ? አረክሰዋለሁ ብዬ ነው አለቺኝ፤ ደነገጥኩኝ ፤ አንዳች የሆነ ፍርሃት ሰውነቴን ወረረኝ፤ከዚህ በኃላ መልስ አልሰጠዋትም፡፡ እሺ ብቻ ብዬ ጧፉን ከጧፍ ነጋዴዋ ተቀበልኩላት፤ ብሩን ስትከፍላት እግዚያብሔር ይስጥልኝ ብላ ስትመርቀኝ አስታውሳለሁ፤ አንገቴን አቀረቀርኩኝ እኔ ግን ንጹህ ሆኜ ነው ? ይህንን ጧፍ የያዝኩት እንዴት ያለሁ ደፋር ነኝ ፤ ለምን እኔም ካንቺ የባስኩኝ ኃጢያተኛ ነኝ ፤ እኔም አልነካውም አላልኳትም? ስል ራሴን ሞገትኩት፤ ‹‹አንተ ውሸታም ጧፍ አይደለም ከታቦቱ ጋር ስትጋፋ አላውቅህም›› ሲል ጭንቅላቴ ወቀሰኝ፤ እኔ ዞርም ብዬ አላየዋትም ምናልባት እሷ ግን እየተመለከተችኝ ከሆነ ብዬ ወትሮ አድርጌው የማላውቀውን ወደ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ስገባ ተንበርክኬ መሬቱን ሳምኩኝ ፤ አረማመዴንም አስተካከልኩኝ ፤ ምናልባት ንጽህናዬን ካረጋገጠሊኝ ብዬ፤ ወይ አምላኬ በስንቱ ታስተምረኛለህ? አቤት ይህን ጊዜ ዮሐንስ ሐጺር በኖረ ስል ተመኘሁ፤‹‹የጥበብ መጀመሪያ እግዚያብሔርን መፍራት ነው›› የሚባለው ትርጉሙ ለካስ ይህ ነው፤ በወንጌል ላይ ያለው ቀራጭ ትዝ አለኝ ፤ ጌታ ያመሰገነው፤ከዛ ቀራጭ ግን ይህቺ ሴት ትበልጣለች ፤ እርሱስ ወደ ምኩራብ ገብቶ ነው፤ ይህች ሴት ግን ደጀ ሰላሙ ጋር እንኳን አለቀረበችም፤ እንዲህ ያለ ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው፤ እንደዚህስ ያለ እግዚያብሔርን መፍራት እንደምን ያለ ፍርሃት ነው፤ በዚህ ዘመን አይቼውም ሰምቼውም የማላውቀው፤ወይ ግሩም። 🙏እስቲ በዚህ ፁሁፍ እስቲ እራሳችንን እንመርምር !!! ጌታ ሆይ ትሁት ልብን አድለን!