cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዝማሬ_መላእክት

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
185
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

7.03 KB
3.80 MB
“የትዕቢት መጀመሪያ ሰውን ከእግዚአብሔር ትለየዋለች” /ሲራክ 10፡12/ ሳጥናኤል ከቀደመ ክብሩ ተዋርዶ ዲያብሎስ የኾነው “ይኽ ሕዝብ ፈጣሪውን አጥቶ ተጨንቋል፡፡ እኔ ፈጠርኋችኁ በማለትም ፈጣሪነትን በእጄ ልያዝ” ብሎ በታበየ ጊዜ ነው፡፡ ዲያብሎስ ዲያብሎስ የኾነ አስቀድሞ ዲያብሎስ ኾኖ ስለተፈጠረ አይደለም፡፡ በትዕቢት ከመውደቁ በፊት የዐሥሩ ነገደ መላዕክት የአጋዕዝት አለቃ ንዑድ ክቡር መልዐክ ነበርና፡፡ ከዚኽ ክብሩና ሹመቱ ያዋረደው ትዕቢቱ ነው፡፡ እሳቱ ወደማይጠፋ ትሉ ወደማያንቀላፋ እሳት የጣለው ትዕቢቱ ነው፡፡ ወደ ዘለዓለማዊ ሐሳር የጣለው ትዕቢቱ ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ኹሉ የሚየሳምም ደግሞም የሚገድል ክፉ ደዌ ነው፡፡ ወንጌላዊው፡- “በሰው ዘንድ የከበረው በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የተዋረደ ነው” እንዲል /ሉቃ.16፡15/ ውስጣችን በትዕቢት የተሞላ ከኾነ በአፍአ ብንመጸውትም፣ ብንጸልይም ምጽዋታችን ወይም ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ርኵስ መሥዋዕት ነው፡፡ ትዕቢት ካለብን ውስጣችን ንጽሕ የለውም፡፡ ስለዚኽ ሰው ንጽሕናውን እንዲያጣ የሚያደርገው ዝሙት ወይም ማመንዘር ብቻ አይደለም ማለት ነው፤ ትዕቢት ጭምር እንጂ፡፡ እንደዉም ትዕቢት ከዝሙት ወይም ከማመንዘር በላይ እኛን ያቆሽሻል፡፡ ለምን? ምንም እንኳን ዝሙት ንስሐ ካልገቡበት ሥርየተ ኀጢአት የሌለው በደል ቢኾንም በዝሙት የቆሸሸ ሰው ንስሐ ለመግባት ቅርብ ነው፡፡ በትዕቢት የታመመ ሰው ግን እንዲኽ እንደ ዘማዊው ያለ ዓቅምን አያገኝም፡፡ ስለዚኽ ትዕቢት እጅግ አደገኛ ደዌ ዘነፍስ ነው ማለት ነው፡፡ ከትዕቢተኛ ሰው በላይ ጐስቋላ ሰው የለም፡፡ የፈለገ ያኽም ብዕል (ሃብት)፣ የዚኽን ዓለም ዕውቀት ቢኖሮውም ከትዕቢተኛ ሰው የባሰ ጐስቋላ ሰው የለም፡፡ በንግሥና ወንበር ቢቀመጥ፣ በሰዎች ዘንድ እጅግ “የተከበረ” ቢኾንም ከዚኽ ሰው በላይ ጐስቋላ ሰው የለም ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዚኽን ከንቱ ደግሞም ኀላፊና ጠፊ ዓለምን ነገር ይዞ ከመታበይ በላይ ምን አላዋቂነት አለ? ነገ የሚጠወልገውን የመስከረም አደይ አበባን (የዚኽን ዓለም ክብር) ይዞ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ነው ጐስቋላ? ሕልምን ይዞ እውኑን ዓለም ከሚያጣ ከዚኽ ትዕቢተኛ ሰው በላይ ማን ጐስቋላ ሰው አለ ልትሉኝ ትችላላችኁ? አኹን በወርቅ አልጋ ላይ ስለተኛ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ድኻ አለ ልትሉኝ ትችላላችኁ? (ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ገብረ እግዚአብሔር ኪደ )
إظهار الكل...
ከወጣብኝ የፓሊስ ማደኛ ይልቅ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ይቀድማል። በአስቸኳይ ሼር ይደረግ. የተዋህዶ ልጆች ትኩረታችንን በነገው የቅዱስ ሲኖዶስና የአዲስ አበባ ከንቲባዋ ውይይት ላይ እናድርግ። የቤተክርስቲያን ህልውና ተከብሮ የማየት ህልማችንም እውን እንዲሆን እናድርግ።የእኔም የፓሊስ የማደኛ ወረቀት እንዲወጣ ያደረገው የነገው አጀንዳ ጉዳይ ነው። እርሱን በሰፊው እንመለስበታለን አሁን ግን ሁላችንም ትኩረታችንን ወደ ነገው ስብሰባ እንመልስ። #ሼር @Ortodox_Ringtones
إظهار الكل...
ምስጢረ መለኮት ዘማሪት የማርያም ብሥራት @zemeriwochu @zemeriwochu
إظهار الكل...
Mestire melkot.m4a3.47 KB
​​✞ ይበራል በክንፉ ✞ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (2) ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ አዝ__________ በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ አዝ__________ በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ አዝ__________ ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር ይስማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ ታላቁት በረከት በውስጤ አፈሰሰ አዝ__________ ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ •➢ ሼር // SHARE @zemeriwochu
إظهار الكل...
_ይበራል_በክንፉ_Yiberal_Bekinfu_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.mp36.43 MB
Bahraneacheru.m4a2.97 KB
+ እኔ ግን እኔ አይደለሁም + አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ቅድስና ደረሰ:: ይህንን የንስሓ ሕይወት መኖር ከጀመረ በኁዋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው:: ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ:: ይህች ሴትም እየሳቀች :- አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :- "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላት:: ክርስትና የወደቀ የሚነሣበት የረከሰው የሚነጻበት ሕይወት ነው:: የትናንት ታሪክ የሌለው ጻድቅ የነገ ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛም የለም:: የቅዱሳን ታሪክም ንስሓ የገቡ ኃጢአተኞች ታሪክ ነው:: በዚህ መስመር ያለፉ ሁሉ ትናንትን እየተዉ ሌላ ማንነትን ይለብሳሉ:: ትልቁ ፈተና ሰዎች ተነሥተህ እያዩህም እንኩዋን መውደቅህን አለመርሳታቸው ነው:: ፈጣሪ "ከእንግዲህ አትበድል" ብሎ ይቅር ቢልህም ሰዎች ግን ይቅር አይሉህም:: "ድመት መንኩሳ ዓመልዋን አትረሳ" እያሉ እየተረቱ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ ይገፉሃል እንጂ እንድትለወጥ አይፈቅዱልህም:: ሳውል አሳዳጅ ነበረ ዛሬ ግን ሐዋርያ ነው:: ብዙ ክርስቲያኖች ግን እርሱን ለማመን ተቸግረው ነበር:: ከመመረጡ ጀምሮ "ኸረ እርሱ አይሆንም" ብለው ለፈጣሪ ምክር የሠጡም ነበሩ:: ከተመረጠ በኁዋላም ለመቀበል ተቸግረው ከሐዋርያት አሳንሰው ያዩት አልጠፉም:: እርሱም በትሕትና "ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ቢልም : "ጭንጋፍ" ብሎ ራሱን ያለ ጊዜው ከሚወለድ ጽንስ ጋር አነጻጽሮ ዘግይቶ የተጠራ መሆኑን ቢናገርም ከሐዋርያት በምንም የማያንስ ሐዋርያ ነበረ:: እነርሱ በትናንት ማንነቱ ሊያዩት ቢሹም እርሱ ግን "እርሱ አልነበረም" እርሱ መኖር አቁሞ በእርሱ ይኖር የነበረው ክርስቶስ ነበረ:: አንዳንድ ሰዎች የማያምኑህ ከክፋት ተመልሰህ መልካም ስትሆን ብቻ አይደለም:: በጣም መልካም ስትሆንላቸውም አያምኑህም:: ስታከብራቸው ምን አስቦ ነው? ብለው ይጠራጠራሉ:: መልካም ስታደርግላቸው "ምነው ደግነት አበዛሽ? ተንኮል አሰብሽ እንዴ? "ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው" "there is no free lunch” ብለው ሊሰጉ ይችላሉ:: መልካም የሚያደርግላቸውን ሁሉ ሊያርድ የሚያሰባቸው የሚመስላቸው ሰዎች አሉ:: ፍቅር የትግል ስልት የሚመስላቸው ጨብጠውህ ጣታቸው እንዳልጎደለ የሚቆጥሩ ዓይነት ተጠራጣሪ ሰዎች አሉ:: ዮሴፍ የገጠመው ይህ ነበር:: በሃያ ብር ሸጠው ግብፅ ያወረዱት ወንድሞቹን ይቅር ብሎ በፍቅር ተቀበላቸው:: አባታቸውን ያዕቆብን አስመጥቶ በክብር በግብፅ እንዲኖሩ አደረጋቸው:: ከዓመታት በኁዋላ አረጋዊው ያዕቆብ ሞተ:: ይሄን ጊዜ የዮሴፍ ወንድሞች ድንገት ስብሰባ አደረጉ: "አባታችን ከሞተ በኁዋላ ቢበቀለንስ?!" ብለው ስጋታቸውን ተመካከሩ:: ስለዚህ ዶልተው መጡና እንዲህ አሉት :- አባታችን ከመሞቱ በፊት እንዲህ ሲል ተናዝዞ ነበር:: እባክህን የወንድሞችህን በደል ይቅር በል:: (ዘፍ 50:15-21) ዮሴፍ ይኼን ሲሰማ አለቀሰ:: ይቅርታን አድርጎም አለመታመኑ አመመው:: እርሱ ለእነርሱ ድሮም ክፉ አልነበረም:: አሁን ደግሞ ላደረሱበት በደል እንኩዋን ፈጣሪውን የሚያመሰግን ሆኖአል:: "እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው" ነበር ያለው:: ምንም በደል ቢደርስበት እነርሱ አልተለወጡ ይሆናል እንጂ እርሱ ግን ትናንት የሚያውቁት ዮሴፍ አይደለም:: "እኔ ግን እኔ አይደለሁም" አላቸው::"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29) ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
إظهار الكل...
አባቴን እጠላዋለሁ እኔ ላይ፣ እናቴ ላይ እንዲ እንዲ አድርጓል (መልካም አዲስ ነገር) @ApostolicSuccession
إظهار الكل...
2.09 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.