cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡" "በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"                  መጽሐፈ ሰዓታት የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
4 136
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+67 أيام
-2930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ረቡዕ –አልዓዛር አልዓዛር ክርስቶስ ያስነሣው የማርያምና የማርታ ወንድም ነው፤ የስሙም ትርጓሜ እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፲፩፥፯-፵፰)፤ አልዓዛር የሞተው መጋቢት ፲፯ ነበር፡፡ እህቶቹም ክርስቶስ እንዲመጣ መልእክት ልከውበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በ፬ኛው ቀን ማለትም  መጋቢት ፳ መጥቶ ከሞት አስነሥቶታል፤(ዮሐ.፲፩፥፵፬)፡፡ ፋሲካውንም በወዳጁ በአልዓዛር ቤት ያከብር ዘንድ  ከቀደ መዛሙርቱ ጴጥሮስንና ዮሐንስን አስቀድሞ ላከ፤ ከዚያም በአልዓዛር ቤት ሆኖ የሐዲስ ኪዳንን ሥርዓት ምሥጢረ ቁርባንን ሰርቶ ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው፤ አልዓዛር ከተነሣ በኋላ በሐዋርያት ኤጲስ ቆጶስነት ተሸሞ ፵ ዓመት አገልግሎ ግንቦት ፳፯ ቀን ዐርፏል (ስንክሳር ግንቦት ፳፯)፡፡    ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw #ሼር
إظهار الكل...
ማክሰኞ ቶማስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ትንሣኤው ሐዋርያት ተሰብስበው በነበረበት በዝግ ቤት ገብቶ ሲገለጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ ሐዋርያትም የጌታችንን ከሙታን ተለይቶ መነሣት ቢነግሩት ‹‹እኔ ሳላይ አላምንም›› አላቸው፡፡ በሚቀጥለው ሳምንትም ጌታችን ቶማስ በተገኘበት በድጋሜ  ተገለጠላቸው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን ‹‹ጣትህን ወደዚህ አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን›› ብሎ በጦር የተወጋ ጎኑን ፥ በችንካር  የተቸነከረ እጁንና እግሩን እንዲዳስሰው በማድረግ ትንሣኤውን  አረጋገጠለት፡፡ ቶማስም ሲዳስሰው እጅ ከእሳት እንደገባ ጅማት ስለተኮማተረ ‹‹ጌታዬ አምላኬም›› ብሎ መሰከረ፡፡  በኋላ ግን ፈውሶታል፤ ኢየሱስም ‹‹ስለ አየኸኝ አምነሀል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዐን ናቸው›› አለው፡፡  ምንም አንኳን ድርጊቱ የተፈጸመው በዳግም ትንሣኤ ቢሆንም የሐዋርያው መታሰቢያ ሆኖ ዕለተ ማክሰኞ ‹ቶማስ› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ (ዮሐ. ፳ ፥ ፳፬ -፴) ወስብሐት ለእግዚአብሔር
إظهار الكل...
👍 4
ሰኞ ማዕዶት ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል:: +ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ *ከባርነት ወደ ነጻነት *ከጨለማ ወደ ብርሃን *ከሞት ወደ ሕይወት *ከኃጢአት ወደ ጽድቅ *ከሲዖል ወደ ገነት *ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል:: +አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች:: +ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና:: =>አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን:: =>+"+ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ:: በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ጴጥ. 3:18)
إظهار الكل...
✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ ✞ ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/        የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል የነገራችሁን እዩተሰ ተፈፅሟል በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/            /አዝ===== ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ❖ @meazahaymanot❖   ❖ @meazahaymanot ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
إظهار الكل...
***        እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም               አደረሰን! አደረሳችሁ! “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም፤ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ዲያብሎስን አሰረው፤ አዳምን ነጻ አወጣው፡፡ ሰላም! ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ኾነ፡፡
إظهار الكل...