TheDeepThingsOfGod
الذهاب إلى القناة على Telegram
Glorious Church the bride of Christ. Rapture ready!
إظهار المزيد1 810
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
1 810
አንድ ሰው ለ 'ፌዝ ቡክ' I mean ለ ፌስ ቡክ😂 ለ Instagram ወይንም ለስልኩ የሚሰጠውን ጊዜና ትኩረት በትንሹ ለሦስት ወር ለእግዚአብሔር ቃልና ለጸሎት ቢሰጥ ጥቁሩ ወደ ነጭ ይለወጣል።
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
መለወጥ ከባድ አይደለም። ችግሩ መንገዱ ቀላል መሆኑ ነዉ፤ ነገሮች ከልተወሳሰቡ ዋጋ የሌላቸው የሚመስለን ከሆን ለውጥ ከባድ ነዉ ምክንያቱም የለውጥ መንገድ ውስብስብ አይደለም።
የለውጥ መንገድ 'አእምሮን ማደስ' ነዉ። አእምሮውን የሚያድስ ሰው አጠቃላይ ሕይወቱ በቀላሉ ይለወጣል። አእምሮአችንን የማናድስ ከሆነ በፍጹም ለውጥ ማየት አንችልም።
አእምሮ የሚታደሰው በምንድነው? የሰዎችን አእምሮ በእውነት ለማደስ የምችልና ዘላቂ ለውጥ ለመፍጠር የሚችል 'የእግዚአብሔር ቃል' ብቻ ነዉ። የሚያስፈልግህ፣ የሚያስፈልግሽ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ።
በሕይወትህ፣ በሕይወትሽ መለወጥ የምትፈልገው፣ የምትፈልጊው ነገር አለ? አዎ! ከሆን ምላሻቹ ፤ መድሃኒቱ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ። ችግራችሁን ወይም መለወጥ የምትፈልጉትን ነገር አታስቡ፣ አታውሩ፤ በዚህ ፈንታ የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ፣ አሰላስሉ፣ አውሩ፤ ይሄንን ያለማቋረጥ ቢያንስ ለ ሦስት ወር ማድረግ የቻለ ሰው: ሕልም እየመሰለው ነገሮች ሁሉ ይለዋወጣሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ፈጽሞ እንደሚለውጥ እኔን ጨምሮ የተለወጡ ሰዎች ሁሉ ምስክር ናቸዉ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
“ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4:4
1 810
"እውነትን ተጠቀሙ"
የምታነቡትን ተጠቀሙ : እውነትን ተጠቀሙ
በአእምሮአችሁ ውስጥ አጽኑት: አድራጊዎች ሁኑ: የጸሎታችሁ ክፍል አድርጉት: ለሌሎችም እንድደርስ አድርጉ : በራሳችሁ ሕይወት ተግባራዊ አድርጉት : ምን ያህል ተጨማሪ ብርሃን እንደሚያስፈልጋችሁ ለማወቅ ስሩ።
ራሳችሁን እንደዚህ ብላችሁ ጠይቁ " በገባኝ እውነት ብርሃን እየተመላለስኩ ነዉ?" "ሕይወቴን እየለወጠው ነዉ?"
➤ወንጌላዊ ኢቫን ሮበርት
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
"እውነትን ተጠቀሙ"
የምታነቡትን ተጠቀሙ : እውነትን ተጠቀሙ
በአእምሮአችሁ ውስጥ አጽኑት: አድራጊዎች ሁኑ: የጸሎታችሁ ክፍል አድርጉት: ሌሎችም እንድደርስ አድርጉ : በራሳችሁ ሕይወት ተግባራዊ አድርጉት : ምን ያህል ተጨማሪ ብርሃን እንደሚያስፈልጋችሁ ለማወቅ ስሩ።
ራሳችሁን እንደዚህ ብላችሁ ጠይቁ " በገባኝ እውነት ብርሃን እየተመላለስኩ ነዉ?" "ሕይወቴን እየለወጠው ነዉ?"
➤ወንጌላዊ ኢቫን ሮበርት
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
መስቀሉን እንመልከት።
የክርስቶስ መስቀል የኃጢአት ስርየት ያገኘንበት መሆኑ እውነት ነዉ። ነገር ግን መስቀሉን የኃጢአት ስርየት ያገኘንበት ብቻ አድርጎ ማቅርብ ትክክል አይደለም! የኃጢአት ውጤትም በመስቀሉ ከእኛ ተወስዷል።
በመስቀሉ ኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ሁሉ ከእኛ ላይ ተወስዷል!
ክፉ የሆነ ነገር ሁሉ፣ የትኛውም የመንፈስ፣ የነፍስና የስጋ ስቃይ ሁሉ ከእኛ ተወስዷል፤ ይሄ ብቻ አይደለም ሞታችንም ተወስዷል፤ ምንጩ ከደረቀ ወንዙ መፍሰስ ያቆማል! ኃጢአታችንን በመስቀል ለተሸከመ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ሃይል ለዘላለም ይሁን፡ አሜን።
በመስቀሉ የሚያምን ከኃጢአት፣ ከአመጽ፣ ከክፋት፣ ከፍርሃት፣ ከጭንቀት፣ ከድካም፣ ከበሽታ፣ ከእርግማን፣ ከማጣት፣ ከድህነት፣ ከሞት ለዘላለም ነጻ ወጥቷል! ሃሌሉያ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
መዝሙር~ነገን አልፈራውም
~ዘማሪት Samrawit Caesar
ተባረኩ! በዚህ መዝሙር እምነታችሁን ከፍ አድርጉ!😍
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
የክርስቶስ መስቀል?
የመስቀል እውነት እያንዳንዱ ክርስትያን ማወቅ የሚገባው እውነት ቢሆንም፤ መስቀል ላይ የሆነውን ነገር እጅግ ብዙ ክርስቲያኖች በሙላት አልተረዱትም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መስቀል ስናገር ሰዎች አንገታቸው ላይ በክሪ ስለሚያንጠለጥሉት ከእንጨት ወይም ከሌላ ነገር ስለተሰራ ትንሽዬ እቃ አይደለም የሚያወራው።
መስቀል ላይ የሆነው 'መስዋዕት' ነዉ። እኛም ስለመስቀል ስንናገር እያወራን ያለነው ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ፣ በአንተና ፣ በአንቺ ምትክ ለእግዚአብሔር ስላቀረበው መስዋዕት ነዉ።
የክርስቶስ መስቀል 'መስዋዕት' እንደሆነ የሚያመለክት ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያለ ቢሆንም አንዱን እንመልከት፡ “እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።”
— ዕብራውያን 7፥27
በዚህ ንባብ ውስጥ ጸሃፊው ኢየሱስ ክርስቶስን ከብሉይ ካህናት ጋር በንጽጽር በማቅረብ ኢየሱስ ያቀረበው መስዋዕት አንደሆነ ይነግረናል።
ይህም መስዋዕት አንዴ ለሁሌ የቀረበ መስዋዕት በመሆኑ የብሉይ ካህናት እንደሚያደርጉት በየዕለቱ የሚቀርብ እንዳልሆነ ያስረዳል።
ሌላው በጣም የሚያስገርመው ካህኑም መስዋዕቱም እራሱ ኢየሱስ መሆኑ ነዉ። መስዋዕት ሆና የቀረበው መስዋዕትም፤ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበውም ካህን እራሱ ነዉ። ይሄ ኢየሱስን ከካህናት ሁሉ የበለጠ ያደርገዋል! ክብርና ሃይል ይሁንለት።
#የክርስቶስ #መስቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
🔥እየጸለይኩ እግዚአብሔር እንደዚህ አለኝ!🔥
መንፈሴን አፈሳለሁ ትንቢት ይናገራሉ!
መንፈሴን አፈሳለሁ ራዕይ ያያሉ!
መንፈሴን አፈሳለሁ ሕልም ያልማሉ!
መንፈሴን አፈሳለሁ ድንቆችን ያደርጋሉ!
መንፈሴን አፈሳለሁ ምልክቶችን ያደርጋሉ!
በኢትዮጵያ ምድር ላይ #የከበደ_የመንፈስ_ቅዱስ ዝናብ⛈⛈⛈ ይሆናል። ይህንን የተናገረው እግዚአብሔር ነዉ።
እኔንም ይመለከተኛል የሚል Comment ላይ "ለእኔ ነዉ" ይበል!
1 810
የክርስቶስ መስቀል ላይ የሆነው ምንድነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቶስ መስቀል የሚለውን በጥንቃቄ ስንመረምር እጅግ በጣም የሚያስገርም መንፈሳዊ ልውውጥ እንደሆነ መረዳት እንችላለን፤ ይህ መንፈሳዊ ልውውጥ ብዙ ነገሮች በውስጡ ያሉት ቢሆንም የልውውጡ ጭብጥ ግን በዚህ መልኩ ይገለጻል፡
👇
መስቀል ላይ በሰው ልጆች አለመታዘዝ ምክንያት ኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሆነ፤ በምላሹም ነውርና ነቀፋ በሌለበት ፍጹም በሆነው በኢየሱስ መታዘዝ ጽድቅና የጽድቅ ውጤት ሁሉ ለሰው ልጆች ሆነ።
ይህ በእግዚአብሔር ጥንተ ውሳኔ መሰረት የተደረገ መለኮታዊ ልውውጥ ነዉ። ይህንን እውነት የሚያምን ሰው ሁሉ ምንም እንኳ ኃጢአተኛ ቢሆንም ፍጹም በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ መታዘዝ ምክንያት ጻድቅ ተደርጎ ይቆጠራል የጽድቅም ውጤት ሁሉ የእርሱ ይሆናል። በቀላል አማርኛ የቀረበ ቢሆንም እጅግ በጣም ጥልቅ ትርጉም ያለውና ሰፊ ነዉ። ይሄንን እውነት የመረዳትን ያህል ዋጋ ያለው ነገር ምንም የለም!
ከዚህ በፊት እንዳልኳችሁ የክርስቶስን መስቀል እውነት መረዳት፡ ፍለጋ ወደሌላው ወደ ክርስቶስ ባለጠግነት የሚወስደው መንገድ ላይ እግሮቻችንን የሚያስገባ፤ ከዘመናት በፊት በእግዚአብሔር ተሰውሮ የተጠበቀ የሚስጥር ስርዓት ነዉ/ኤፌ 3:8-9/።
እግዚአብሔር ይባረክ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻኛው ወደ እግዚአብሔር መንግስት የሚያስገባ በር....
#በራዕይ
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
የክርስቶስ መስቀል!
ይነበብ!!!
ከቀደመው ፍቅር ብንወድቅ እና የቀደመውን ተግባራችንን ማድረግ ብንተው፣ የነበረንን መንፈሳዊ ግለት ብናጣው: ወደ ቀደመው ጎዳና የሚመልሰን አንድ እውነት የክርስቶስ መስቀል ነዉ። የክርስቶስን መስቀል ስንመለከት እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ያስረዳል። ማድረግ ያለብንን ማድረግ እንድንችል ከፍቅር የተሻለ ግድ የሚለን የለም።
➤መጸለይ ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤መቀደስ ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤ወንጌል መስበክ ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤ማገልገል ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ብንጠራጠር መስቀሉን እንመልከት!
➤ጤነኛ መሆን ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤መሳካት ቢያቅተን መስቀሉን እንመልከት!
➤ብንጨነቅ መስቀሉን እንመልከት!
➤አቅርቦት ብናጣ መስቀሉን እንመልከት!
እግዚአብሔር በየትኛውም ጊዜ በሰው ልጅ ሕይወት ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ የሰጠው የክርስቶስ መስቀል በሚባል ቋንቋ ነዉ።
“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።”
— ዮሐንስ 15፥13
1 810
??ጥያቄ: ሽልማት ያለው!
መስቀል ስለምንድነው? መስቀል ላይ የሆነው በትክክል ምንድነው?
what's the cross? what's the cross all about? what exactly happened on the cross?
የእግዚአብሔር ልጆች መልሳችሁን ስጡኝ?
1 810
በመንፈሳችን ብንዝል፣ ነፍሳችን ብትጨነቅና ስጋችን ቢታመም...ይህንን ስናውቅና ስናምን ሁሉም ይለወጣል! እግዚአብሔር በክርስቶስ መስቀል በኩል ሌላ የከበረ ሕይወት አቅርቦልናል።
አሁን ያለህበት/ያለሽበት ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ ልሆን ይችላል።
ለዚህም ሁኔታ የሚረባ መፍትሔ ይዞ የመጣ ማንም የለም! ምን አልባትም ከሁኔታው የተነሳ በብቸኝነት፣ በፍርሃትና በተስፋ መቁረጥ ሸለቆ ውስጥ ሆነህ/ሽ ይሆናል፤ ነገር ግን መልካም ዜና አለኝ! የፈጠረህ/ሽ እግዚአብሔር በክርስቶስ መስቀል ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል!
አንድ ነገር ብቻ አድርግ/ጊ አይኖችህን/ሽን በክርስቶስ መስቀል ላይ አድርግ/ጊ። መስቀሉን በትኩረት መመልከት እንጀምር።
ምድረበዳ ውስጥ በእባብ ተነድፈው በፍርሃትና በተስፋ መቁረጥ ሞታቸውን ስጠባበቁ የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሙሴ የነሃስ እባብ ሰርቶ በዓላማ ላይ በመስቀል: የሚድኑበትን መንገድ አዘጋጀላቸው: ያንንም የተሰቀለ የነሃስ እባብ የተመለከተ ሁሉ ከሞት ዳነ በሕይወትም ኖረ! ይህ ለእኛ በምሳሌነት የቀረበ ነዉ። "የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያዩ ሁሉ ከየትኛውም ችግር ይድናሉ፣ በሕይወትም ይኖራሉ።"
“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።”
— ዮሐንስ 3፥14-15
Only @TheDeepThingsOfTheSpirit
Join the chariot
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
ሰላምና ፀጋ ይብዛላችሁ!
በየትኛውም ጊዜ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ በክርስቶስ መስቀል በኩል ተሰጥቶናል።
የክርስቶስ መስቀል የክርስትናን እምነት ከሌሎች ስሑት እምነቶችና ሐይማኖቶች ሁሉ የተለየ የሚያደርገው አንዱ እውነት ነዉ።
የክርስቶስ መስቀል ታሪካዊ ክስተት ብቻ አይደለም ያለፈው፣ የአሁኑና የወደፊቱ ትውልድ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚሆንበት ብቸኛው መንገድ ነዉ። የክርስቶስ መስቀል ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የታረቁበት መንገድ ከመሆኑም በላይ፤ የትኛውም ሰው በየትኛውም ዘመንና ቦታ በሕይወቱ የሚያስፈልገውን አቅርቦት ሁሉ እግዚአብሔር ያስቀመጠበት መንፈሳዊ ቦታ ነዉ። ለሰው ልጅ የሚያስፈልገው አቅርቦት ሁሉ መለኮታዊ በሆነ አሰራር በመስቀል ተለቋል።
የክርስቶስ መስቀል እውቀት፡ ፊለጋ ወደሌለው የክርስቶስ ባለጠግነት በሚወስደው መንገድ ላይ እግሮቻችንን የሚያስገባ፤ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም ተሰውሮ የነበረ የሚስጥር ስርዓት ነዉ።
የክርስቶስን መስቀል ሚስጥር የተረዳ ሰው በእግዚአብሔር አቅርቦት በሙላት ለዘላለም ይኖራል።
Only @TheDeepThingsOfTheSpirit
Join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TheDeepThingsOfTheSpirit
@TheDeepThingsOfTheSpirit
“...ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።”
— ገላትያ 6፥14
1 810
What drives your life? what are the motivations and motives behind our desire?
ለምን?
@TheDeepThingsOfTheSpirit
1 810
☝️☝️☝️this are some of the reactions after taking the vaccines.... what do youth think?
ሰዎች የኮቪድ ክትባት ከተቀበሉ በኃላ የተፈጠሩ የተወሰኑ ክስተቶች ናቸው፤ ምን ታስባላችሁ???
