cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethiopian pilots (ambitious)👩‍✈️✈️

✈✈We aimed to inspire young students and to provide latest information about aviation✈✈

إظهار المزيد
Ethiopia5 347لم يتم تحديد اللغةالنقل4 518
مشاركات الإعلانات
2 987
المشتركون
+324 ساعات
+117 أيام
+2530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ትላንትና ማክሰኞ #ከሀዋሳ ወደ #አዲስ_አበባ በመብረር ላይ እያለ የደኅንነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ክስተት በገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር #ET154 ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥልቅ የሆነ የደኅንነት ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ትላንት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከፍተኛ ጭስ መከሰቱን፣ ነገር ግን በመንገደኞች ላይም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ ምን ዓይነት እክል ሳይፈጠር ቦሌ ኤርፖርት በሰላም ማረፉ መገለጹ ይታወሳል። አውሮፕላኑ ውስጥ ለጊዜው በምን ምክንያት እንደተነሳ ያልታወቀው ጭስ መንገደኞችን ከፍተኛ ድንጋጤና ፍርኃት ውስጥ አስገብቷቸው ነበር። የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ባስተላለፉት የደኅንነት ጥንቃቄ ዕርምጃ መሠረት ሁሉም ተሳፋሪዎች በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመውን የአየር መሳቢያ የፊት ጭምብል (oxygen mask) እስከማድረግ ደርሰው ነበር። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የበረራ ደኅንነት ክፍል እክል የገጠመው አውሮፕላን ቀጣይ በረራ እንዳያደርግ በማገድ በበረራ ወቅት ያጋጠመውን የደኅንነት ክስተት እንደሚያጣራ ሪፖርተር ጋዜጣ ስማቸው ያልተገለጹ የተቋሙን ምንጮች ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። እኚሁ ምንጮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አየር መንገዱ በሚሰጠው የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት ላይ የደኅንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ክስተቶች ደጋግመው መከሰታቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን አጠቃላይ የደኅንነት ፍተሻ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ/ም ላይ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ሲበር የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት ከማረፊያው አስፋልት ውጪ የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል። ሌላው የመንገደኞች አውሮፕላን በተመሳሳይ በአርባ ምንጭ አውሮፓላን ማረፊያ ከማረፊያ መስመሩ (ራንዌይ) የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ተስምቷል። በአጠቃላይ በአንድ ዓመት 4 የደኅንነት እክሎች የተመዘገቡ መሆኑን ጋዜጣው ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ጠቁሟል። ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲበር የነበረውን ጨምሮ እክል ያጋጠማቸው አውሮፕላኖች ' #Q400 ' በመባል የሚታወቁት አየር መንገዱ በአገር ውስጥ እና ወደ ጎረቤት አገሮች ለሚደረጉ በረራዎች የሚገለገልባቸው ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካሉት 178 አውሮፕላኖች መካከል 33 የሚሆኑት Q400 በመባል የሚታወቁት ለመካከለኛ ርቀት የሚጠቀምባቸው አውሮፕላኖች ናቸው። #ሪፖርተር @tikvahethiopia
إظهار الكل...
👍 14 1
إظهار الكل...
TikTok · Sera

41.6K likes, 2240 comments. “#ethiopianairlines #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ethiopian_tik_tok ”

2👏 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ ታይቷል። ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል። መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን ገልጿል። " በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል " ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቋል። @tikvahethiopia
إظهار الكل...
👏 8👍 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
👍 9 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
For those Who were asking me Marketing and Air hostess(Cabin Crew) applications are out Try from march 25 up march 29 Here is the link for full information https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies
إظهار الكل...
👍 12 1🔥 1
ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል የመንግስት ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ መልኩ ተከብሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይህን ቀን አስመልክቶ ወደ እንግሊዝ ለንደን በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ያደርጋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓለምአቀፍየሴቶችቀን
إظهار الكل...
👏 8👍 2 2🎉 1
Another brand new 737 MAX 8 is arriving tonight 👏(ET-BAI)
إظهار الكل...
👍 11 7😁 6
Repost from Addis መረጃ™
Photo unavailableShow in Telegram
በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸዉ ተነግሯል። ንብረትነቱ የኳታር አየር መንገድ የሆነዉ አዉሮፕላን ( ኳታር 6 ዩ) ከዶሃ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ በ 38,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ ቢሆንም በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አዉሮፕላኑ ወደ 40,000 ጫማ ወደላይ እንዲወጣ ተነግሮታል። በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 : 32 ገደማ በተመሳሳይ በ39,000 ጫማ ከፍታ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ዱባይ ሲጓዝ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ( ኢቲ 602) ጋር የተፋጠጠዉ የኳታር አዉሮፕላን ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተዘግቧል።ሁለቱ ካፒቴኖች ስለ ክስተቱ ሲነጋገሩ የተቀረጹት ቅጂዎች ሁለቱም በሞቃዲሾ ከሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ እንደተቀበሉ ያሳያል ተብሏል። በሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት ማስወገጃ ሲስተም (TCAS) ወዲያውኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፣ ይህም በታዘዘው ከፍታ ላይ ሌላ አውሮፕላን መኖሩን በማመልከቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንዲተርፍ ለማድረግ መቻሉ ዝግባዎች አመላክተዋል።ይህን ተከትሎ በሞቃዲሾ የሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሆኑትን ሙባረክ ኑር አሊን በቁጥጥር ስር እንዲዉል አደርገዋል። Via Capital @Addis_Mereja
إظهار الكل...
😱 24👍 8 3👎 1🔥 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ። ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል። " በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል። 1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦ * በሂሳብ፣ * በእንግሊዘኛ * በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ 2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ 3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4 4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ 5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል። " የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ [email protected] / [email protected] ያነጋግሩን " ብሏል። ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline @tikvahethiopia
إظهار الكل...
👍 13👏 4 1
Repost from Natnael Mekonnen
ዛሬ በመቐለ ምን አጋጠመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከቀኑ 8:00 መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ ጎማው አከባቢ ባጋጠመው ችግር በፓይለቱ ድንቅ ብቃት ሰዎችን ሳይጎዱ ሊያርፍ ችሏል።
إظهار الكل...