cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ከሣቴ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

የዱከም ም/ፀ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እናየደ/ቁ/ቅ/ማርያም አቢያተክርስቲያናት የከሳቴ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ትክክለኛ(official) የቴሌግራም ቻናል በቻናሉም....... 👉 ✞ መዝሙራት ✞ 👉 ✞ ስብከቶች ✞ 👉 ✞ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ✞ 👉 ✞ መንፈሳዊ መፃህፍት✞ 👉 ✞ ብሒላተ አበው ✞ 👉 ✞ መንፈሳዊ ምክሮች ✞ ✞ ይሰጣሉ ✞

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
203
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
+130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
አባት አይሰደብም! .... አባት አይሰደብም! ... አይደለም ቆብ ደፍቶ .. በትረ ሙሴ ጨብጦ .. መስቀል አንግቶ ፥ ለወትሮው ሽበት ጣል ያረገበት ሰው ይከበራል፡፡ ይህንን የምለው ብሏል እንዲሉኝ አልያም ወገንተኝነት ኖሮብኝ አይደለም፡፡ " የኛ ሰፈር " ናቸው ብለው እንደሚያስቡት ነገሩን ከዘር ለማገናኘትም ፥ "የኛ ሰፈር " አይደሉም ብለው ከሚጠሏቸውም ወገን ሳልሆን እውነት የመሠለኝን .. የተሰማኝን .. የራሴን እውነት እጽፋለሁኝ፡፡ .... አቡነ ገብርኤል ይባላሉ ፥ የምዕራብ ሸዋ(አምቦ) ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ በቅዱስ ፓትረያርኩ ሐምሌ 13 ቀን በአንብሮተ እድ ከሌሎች ስምንት ኤጲስ፡ቆጶሳት ጋር የተሾሙ ናቸው፡፡ .. ሲኖዶሱ አምኖባቸው ፥ የሾማቸው፡፡ ስለዚህ የሁላችንም አባት ናቸው፡፡ እንደነ አቡነ ኤርምያስ ፣ እንደነ አቡነ ናትናኤል .. እንደነ አቡነ ሩፋኤል(እህህህህ) .... በለንደን ኤርፓርት የታየው በጣም የሚያሳፍር ነው .. ክው የሚያደርግ ፥ ለቤተ ክርስቲያንም ብዙ ጥሩ ያልሆነ ገጽታ የሚያላብስ ነው ፡፡ ሰው አያጠፋም .. ጳጳስ አይከሰስም አይደለም፡፡ ያጠፋሉ .. ይወቀሳሉ ... ለሁሉም ግን ስርአት አግባብ አለው፡፡ በዚያ ልክ .. የተወለዱበትን አካባቢ የሚጠቅስ .. ግለሰባዊ ስድብ ተገቢ አይደለም፡፡ ተገቢ ያልሆነው እሳቸው ስለሆኑ ሳይሆን .. ማንም ቢሆን ተገቢ ስላልሆነ ነው፡፡ ሁላችንም አባቶቻችንን ከነ ጥፋታቸው ፣ ከነ ስህተት እና ጉድለታቸው ማክበርና መቻል አለብን፡፡ ዛሬ ንቀትን ፣ ስድብን አስለምደን ፥ አስተምረን .. ሌላ ጊዜ አክብሩልን ብንል ማንም አይሰማንም፡፡ ______ ✍ ቃል ፥ ኪ ዳ ን
إظهار الكل...
👍 1 4
ዱከም መድኃኔ ፥ ዓለም በ1980 ይህንን ይመስል ነበረ፡፡ እዚሁ ፌስቡከ ላይ የተገኘ .. ምስል ነው፡፡ ... በሃገር፡ውስጥም ከሃገር ውጪም ያላችሁ የመድኃኔዓለም፡ወዳጆች .. በቤቱ ያደጋችሁ .. እንኳን አደረሳችሁ!! .... ግን ከሁላችንም ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡ .. የቀደሙ አባቶችን መዘከር ፣ ታሪካቸውን መጻፍ ፣ ያሉትን መንከባከብ ይጠበቅብናል፡፡
إظهار الكل...
👍 3
00:27
Video unavailableShow in Telegram
መዳረሻ ( መጋቤ ሥርዓት ቀሲስ ጥበቡ መንግስቱ፡) ... ባለሞገሱ አባታችን በዐለ ንግሱ እስኪቃረብ .. ጥንተኞቹን እናስታውሳለን፡፡ የኃላው ከሌለ የለም የፊቱ .. ይባል የለ? .. መጽሐፉ ይገለጥ .. ታሪክም! ... ከዚህ በቪዲዮው ላይ የምታይዋቸው አባት ናቸው .. ከላይ ስማቸውን ያነሳኹት ፥ መቸም ዱከም ላይ ያለፈ ያገደመ ሁሉ የረር ተራራ ሆቴልን ያውቃል፡፡ የርሱ ባለቤት ናቸው .. የደብረ መዊዕ መድኀኔ ፥ ዐለም ጥንታዊ አገልጋይ፡፡ .. በታሪካዊው ደብር ደጃፍ የተመላለሱ ... ታቦተ መድኃኔ ዐለምን ቅዱስ ብለው ያጠኑ .. ክብረ ክህነት ወአሰረ ክህነታቸው የተጠበቀ ፥ በወር በወር ሁሉ .. የመድኃኔ ዐለም እለት የማይቀሩ .. እንዲሁ እንደምታዩት መልኩን የሚያደርሱ .. የሚያወድሱ ናቸው፡፡ በተለይ የዱከም መድኀኔ ፥ ዐለምን ታሪክ .. ከነግሱ የሚያውቁ ናቸው፡፡ በሕይወት ያሉ ትልቅ መዝገብ ናቸው፡፡ ... እድል ቀንቶኝ .. የዱከም መድኃኔ ዐለምን አመሠራረት .. በደብሩ ስላገለገሉ በሕይወት ያሉ እና የሌሉ ባለታሪኮች መጣጥፍ ነገር የማዘጋጀት ሕልም አለኝ፡፡ እንደው እሳቸውን የምትቀርቡ ሰዎች ካነበባችሁት ... አድርሱልኝ፡፡ ብዙ ታሪክን የሚያውቁ ናቸውና .. ........ እኚህ ታላቅ ሰው ... የደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ሕንጻ ሲሰራ .. የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴው ሊቀ መንበር ሆነው ያንን ግዙፍ ሕንጻ ያስፈጸሙም ናቸው፡፡ ... መድኃኔ ዐለም እድሜ ሰጥቷቸው .. ዘወትር በመቅደሱ .. ቅዱስ እንዳሉ ቢኖሩ ምኞቴ ነው፡፡ ____ መጋቢት 24 - 2016 ✍ቃል ፥ ኪዳን
إظهار الكل...
6.94 MB
👍 2
ዱከም መድኀኔ ዐለም ፥ እና የዱከም ሰው ... እንደዛሬው እዚህም እዚያም የበቀሉት ፎቆች ሳይኖሩ ...  የዱከም ሰው .. ከየትኛውም ስፍራ ላይ ሆኖ ቀና ካለ ፥ በወይራ እና ባርዛፍ ተጨፍርጎ .. ኮረብታማው ስፍራ ላይ ቀይ ቆርቆሮዎቹ አይን የሚገቡ ደብር ያስተውላል፡፡ ደብር ቅዱስ ፥ ደብር መዊዕ .. ጥንታዊው ዱከም መድኃኔ ዐለም፡፡ ገበያተኛው ከገበያው ሲመለስ ... የየረር ሰው .. የነጮ .. የጎጌቾች መንደር ነዋሪዎች .. ወደሐሙስ ገበያ ሲመጡም ሲመለሱም .. መሳለሚያው ጋር ፥ ከሐዲዱ ጣገብ .. እጅ የሚነሱት የሚሳለሙት ነው .. ዱከም መድኀኔ ፥ ዐለም፡፡ .... ጥቅምት እና መጋቢት .. የዱከም እና የገጠራማዋ ቀበሌዎቿ ሰዎች .. ጧፍ ዘቢባቸውን ሸክፈው ፥ ላመቱ ያደረሳቸው ደግሞ ለከርሞ እንዲያደርሳቸው የወርቅ ጥላቸውን ይዘው ደጁ ይገኛሉ፡፡ ባለእጁ ገበሬም አህያውን የጤፍ ጆንያ አስደግድጎ ከተፍ ይላል .. የዱከም መድኃኔ ዐለም .. ገረገራው በሰዎች የተሞላ ነው .. በዛሬ ተረኛ ቋሚዎች .. የዘለዐለም እረፍት አድራጊ ሙታኖች .. ዙሪያው ተከቧል፡፡ የዱከም ሰው መነሻውም መዳረሻውም .. በሰንሰል እና በቆንጥር .. በወይራ ዛፎች ስር ነው፡፡ የዘለዐለም እረፍተ ቤቱ ነው፡፡ ቢከፋው .. ሆድ ቢብሰው .. ሰው ባሌለበት ሰአት ከደጀ ሰላሙ ሂዶ ሕሊናውን ያሳርፋል፡፡ ... ዐረፍተ ዘመን ገቶት ፥ ቀን ጠርቶት ቢያርፍ .. የበድን ፥ የነፍሱ ታዛው ነው፡፡ መድኀኔ ዐለም፡፡ .... ዘጠና አመት ሊደፍን የተቃረበው ደብር .. አያሌ ሰዎች ያፈራ እና እያፈራ ያለ ደብር ነው፡፡ የከተማዋ ግርማ ሞገስ .. ከመሆኑ ባሻገር ... የወይራ ዛፎቹን ያህል በእድሜ በእውቀታቸው .. በክህነታቸው አርኣያ የሆኑና የነበሩ ሰዎች ያሉበት ነው፡፡ .. መጋቤ ሥርዓት ጥበቡ (ዛሬም አይደለም በአመቱ .. በወርኀ በዐሉ የማይቀሩ .. በማኅሌቱ ፥ በስብሐተ ነግኁ በ'ሳታቱ .. የሚሳተፉ .. ) ፥ ወላዴ አእላፍ መምሬ አቤ ( ነፍስ ይማር) ፣ መምሬ አሰፋ ( ነፍስ ይማር ፥ የቤተሰባችን ንስሐ አባት የነበሩ ..) ፥ አባ በርሱማ (ነፍስ ይማር ፥ ደወሉ ስር የመነኑ ... ለሰአታት ደወል እየደወሉ .. አባታቸው መድኃኔ ፥ ዐለም የጠራቸው ) ፥ መምሬ ተስፋዬ ( የነ መልዐከ ስብሐት አብርሃም አባት .. ያቆይልን) ... ፤ የቅርብ ጊዜዎቹ ( ከደብሩ አንጋፋነት እንጂ .. መቆየትስ ቆይተዋል .. ) የኔታ ርዕሰ ደብር አክሊሉ ፥ የኔታ ናሁሰናይ .. መልአከ ሕይወት እስጢፋኖስ .. የኔታ ጸጋዬ ... የነዚህ ሁሉ ደብር ፥ እነኚህን ሁሉ ያፈራ ደብር ፥ ደብር ቅዱስ .. ደብር መዊዕ .. ዱከም መድኃኔ ዐለም ነው፡፡ ..... ልጁቹ ግን የታላችሁ .. ከደብሩ ትልቅነት አንጻር .. የምስረታው ዐመት ይከበራል? ... 80ኛ አመቱ ፥ 85ኛ አመቱ ተከብሯል?? ... እኒያን ትልልቅ ዋርካዎች .. ያሉትን አስታውሳችኃል? አስታውሰናል? .. ያረፉትን .. ዘክረናል?? መቃብራቸውን አጽድተናል፡፡ የደብሩን ታሪክ በመጽሔት ተዘጋጅቷል?? ... ወይስ ለዚህም በየሶስት አመቱ የሚቀያቀረውን ሰበካ ጉባኤ .. አሊያም እግር ጥሎት የሚመጣ አለቃ ነው የሚጠበቀው? የሚወቀሰውስ!! ይህ ታሪካዊ .. አንጋፋና ቅዱስ የሆነ ደብር .. ርዕሰ አድባራት መባል ያለበት ነው .. ከቆይታው ብዛት፡፡ .. ይህ እንግዲህ የኛ .. የዱከም ተወላጆች ስራ ነው .. ኃላፊነት ነው፡፡ መጋቢት 27 በጥንተ ዕለቱ በዕለተ ዐርብ ከደጁ ያገናኘን፡፡ .... ✍ ቃል ፥ ኪ ዳ ን
إظهار الكل...
👍 3
+ ተራ የማይደርሰው ተጠማቂ + "ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው ሰውዬውም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡ ብሎ መለሰለት" ዮሐ.5:5-7 ይህንን ጥያቄና መልስ ሳይ በሽተኛውን ማናገር ያምረኝና እንዲህ በል ይለኛል :- አንተ በሽተኛ ግድ የለህም የተጠየቅከውን ብቻ መልስ:: እመነኝ ጠያቂህ ተራ ጠያቂ አይደለም:: የሚጠይቅህ ሲያደርቁህ እንደኖሩት ሌሎች አሰልቺ ጠያቂዎች አይደለም:: ጥያቄውም የሌሎችን ሰዎች ዓይነት ጥያቄ አይደለም:: ከፊትህ የቆመው የመጠመቂያውን ውኃ ብቻ ሳይሆን በዓለም የሞላውን ውኃ የፈጠረ አምላክ ነው:: "ወደ መጠመቂያው የሚያኖረኝ ሰው የለኝም" አልክን? የተጠየቅከውን መልስ እንጂ! ወደ መጠመቂያው መግባት ትወድዳለህን? ብሎ ማን ጠየቀህ? የጠየቀህ ማን እንደሆነ ባታውቅ እንኩዋን ጥያቄውን እንኳን በደንብ ስማ እንጂ! ሰው የለኝም አትበለው : ስለመጠመቂያው ወረፋ አትንገረው : ስንት ሰው ቀድሞህ እንደዳነ አትቁጠርለት:: የጠየቀህ ግልፅ ጥያቄ ነው:: ልትድን ትወዳለህን? እግዚአብሔር ፊት ስለ ችግርህ ክብደት ለምን ታወራለህ? ምን እንደሌለህማ እሱም ያውቃል:: አዎን እድን ዘንድ በለው:: ችግርህን ትተህ የምትፈልገውን ንገረው:: የችግርህ መወሳሰብና ሥር መስደድ ለእሱ የሚከብድ አይደለምና መዳን እንደምትሻ ብቻ በእምነት ንገረው የሚል ተግሣፅ በበሽተኛው በኩል ወደ እኛ ደረሰ:: 🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌 መጻጉዕ (በሽተኛው) ቤተ ሳይዳ ከመጣ 38 ዓመት ሆነው:: ዳዊትና ሰሎሞን 40 40 ዓመት ነግሠው እንኳን ብዙ የምሬት ቅኔ ተቀኝተዋል:: ይህ ሰው አልጋ ላይ ሆኖ አርባ ዓመት ሊሞላው ሲል ምንኛ ተንገሽግሾ ይሆን? ልብ በሉ ጌታችን በቤተልሔም ሲወለድ ይህ በሽተኛ በአልጋው ላይ ነበረ:: እረኞች ከብዙ መላእክት ጋር ሲዘምሩ እሱ የአንድን መልአክ መውረድና ውኃውን ማናወጥ እየጠበቀ ስድስተኛ ዓመቱን ደፍኖ ነበር:: ጌታችን የሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ ላይ ደርሶ ወደ መጠመቂያው ሥፍራ ሲመጣም ይህ ሰው አልጋው ላይ ነው:: መጠመቂያዋን 38 ዓመት በተስፋ ሲጠብቅ ቆይቶ ሳይጠመቅባት ቀረ:: ጌታ ሆይ የማይደርሰኝን ወረፋ ከመጠበቅ አድነኝ:: እንድፈወስበት ባልፈቀድክበት ሥፍራ ዕድሜዬን እንዳልጨርስ ጠብቀኝ:: ወደ ሐዲስ ኪዳንዋ ቤተ ሳይዳ ወደ ቤተክርስቲያን ከመጣሁ ብዙ ዘመን አስቆጠርኩኝ:: ግን እስካሁንም ድረስ ከኃጢአት አልጋ ላይ አልወረድሁም:: መነሣት እፈልጋለሁ ግን አቃተኝ:: ልቤ እንጂ እግሬ ጸንቶ መቆም አልቻለም:: ፈረቃ የሌለብህን የሕይወት ውኃ አንተን ሊጠጡ ሲመጡ በዓይኔ እየተቀበልኩ ብዙዎች ጠጥተውህ ሲድኑ በዓይኔ እየሸኘሁ አልጋዬ ላይ ቀረሁ:: እኔ እንደተኛሁ ስንቱ ቀድሞኝ እንደዳነ ባየህልኝ:: ከእኔ በኁዋላ መጥተውስ ከእኔ በፊት ስንቶች ዳኑ? ስንቱ ከኃጢአት አልጋ በንስሓ ተነሥቶ ያንተን ሥጋና ደም ተቀብሎ ተፈወሰ? የቤተ ሳይዳው ሐኪም ሆይ ወደ አንጋፋው በሽተኛህ ወደ ጽኑዕ ሕመምተኛህ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ይሆን? ያን ሕመምተኛ "ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበረ" አውቀህ ያናገርከው ሆይ እኔን የምታናግረኝ መቼ ይሆን? እኔስ ብዙ ዘመን እንደሆነኝ አታውቅምን? ሰው የለኝም : ልብ የለኝም : ኃይል የለኝም : አቅም የለኝም ብዬ ብሶቴን የምነግርህ መቼ ይሆን? "ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ" ዮሐ.5:8-9 አንተ ተነሥ ብለኸው የማይነሣ ማን ነው? እንኳንስ ከአልጋ ከመቃብርም ተነሥ ያልከው ይነሣ የለምን? ግዴለህም እኔንም ተነሥ በለኝ:: ተነሥ ኃይልን ልበስ ያልከኝ እንደሆነ እንኳንስ "ሸክሜም ቀሊል ነው" ያልከው አንተ ያዘዝከኝ የራሴን ሸክም ቀርቶ የወንድሜን ሸክምም ተሸክሜ የአንተን ሕግ እፈጽማለሁ:: (ገላ. 6:2) 🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌🛌 "ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ... ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፡ አለው" ይላል:: በሽተኛው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ እንደሔደ ሳነብ አንድ ነገር ልቤን አስጨነቀው:: ይህ ሰውዬ 38 ዓመት ሙሉ የኖረው በቤተ ሳይዳ ነው:: ክርስቶስ ድንገት ፈውሶት ሒድ ሲለው እሺ ብሎ ከዚያ መጠመቂያ ሥፍራ ከወጣ በኁዋላ ወዴት ሔደ? የሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛው ሆይ እውነት ወዴት ሔድህ? ከመጠመቂያው መውጣትህን ሰምተን አድንቀናል:: ከዚያስ ወዴት ሔድክ? ዙሪያ ገባው አልተለወጠብህም? መንገድስ አልጠፋብህም? ወደ ዘመዶች ቤት ሔድክ እንዳልል "ሰው የለኝም" ስትል ሰምቼሃለሁ:: አልጋህንስ የት አደረስካት? መቼም ሰባብረህ እንደማትጥላት የታወቀ ነው:: አልጋ ለታመመ ብቻ ሳይሆን ለጤነኛም ያስፈልጋልና አራት እግር እያላት ጥላህ ያልሔደችውን ዘመድህን መቼም በክብር ማስቀመጥህ አይቀርም:: ለማንኛውም እዚያው ምዕራፍ ላይ ኢየሱስ ይህንን በሽተኛ ዳግም በመቅደስ አገኘው ይላል:: ዮሐ. 5:14 ጌታ ከመጠመቂያ ቦታ አድኖ ያስነሣውን ሰው በመቅደስ ቆሞ አገኘው:: ይህ በሽተኛ እግሩ ሲጸናለት የሔደው ወደ ፈጣሪ ደጅ መሆኑ ያስመሰግነዋል:: ጌታ በመጠጥ ቤት ቢያገኘው ኖሮ ያሳዝን ነበር:: እግርህን ያጸናሁልህ ለዚህ ነው ወይ ብሎ ባዘነበት ነበር:: አሁን ግን ያዳነው ጌታ በመቅደስ አግኝቶት "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" አለው:: ይህንን የምታነብ ወንድሜ ሆይ ክርስቶስ አንተንስ አላዳነህም? "ኸረ እኔ ሽባ ሆኜ አላውቅም:: ማንም እኔን ከአልጋ አላስነሣኝም ትለኝ እንደሆን እመነኝ ክርስቶስ እንደ አንተ ያዳነውስ የለም:: እርሱ እኔና አንተን ተነሡ ብሎ ያስነሣን ከ38 ሳይሆን ከዘላለም የሲኦልና የኃጢአት አልጋ ነው:: እኛን የፈወሰን አልጋችንን አሸክሞ ሳይሆን እሱ ራሱ እኛን ከነአልጋችን ተሸክሞን ነው:: ካላመንከኝ ነቢዩ ኢሳይያስን ጠይቀው "እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ" ሲልህ ትሰማዋለህ:: ኢሳ. 53:12 የእኛን በደል ተሸክሞ ጀርባው ምን ያህል እንደ ቆሰለ ባየህ:: ይህንስ ጀርባዬን ታያለህ የተባለውን ሙሴን ብትጠይቀው ሳይሻል አይቀርም:: ያዳነህ አምላክ አንተንስ የት ነው የሚያገኝህ? እንደዚህ ሰውዬ መቅደስ ያገኝህ ይሆን? የትም ቢያገኝህ ግን ቃሉ አንድ ነው "እነሆ ድነሀል ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ" ከሠላሳ ስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኝነት የሚብስ ምን ሊመጣ ነው? ካልክስ እሱን ከማየት ይሠውረኝ ብትል ይሻልሃል:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጋቢት 10 2014 ዓ.ም. ተጻፈ ባሕር ዳር ኢትዮጵያ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ሥጋ የለበሰ ኹሉ መመኪያ ድንግል ኾይ! ነፍስ የተዋኻዳቸው ፍጥረት ኹሉ አክሊል የዓለም ኹሉ ቤዛ ነፍሴን ከክፉ ነገር ወደ ገሃነምም ከምትወስድ የጥፋት መንገድ አድኛት፡፡ 🙏 ሳትዘራ ስንዴ ያፈራች ዝናምም ሳይዘንምባት የወይን ፍሬ ያስገኘች ማረሻ ያልዞረባት እርሻ ድንግል ኾይ! የኦሪትና የነቢያት ቃል ዝናምን አጠጭኝ በሐዋርያት ወንጌል ቃል ፈሳሽነትም ሐዲስና ብሉይን እንዳፈራ አድርጊኝ፡፡ የኃይል መንፈስ የተመሉትን የተደነቁ የተመረጡትን ሐዋርያት ዋጋ እንድቀበል አድርጊኝ፡፡ ልቡና የሚገልጽ ዕውቀት የሚያበዛውን መንፈስ የተመሉ ሐዋርያትን ዕሴት እንድቀበል ማለቴ ግን በኔ ገድል በትሩፋቴ አይደለም በአንቺ ደግነት በንጽሕናሽም ነው እንጂ፡፡ በጸሎትሽም ረዳትነት ይኽንን ላገኝ እወዳለኹ ድንግል ኾይ! በሃይማኖት ጭንጫ ላይ የተመሠረተች መሠረቷ የማትፈርስ የነፋሳት ኃይል የጎርፍ ፈሳሽ የዝናምም ወጀብ የማይበረታ ፈሳሽ የዝናምም ወጀብ የማይበረታ ታቦት አጥር ቅጽር ኾይ እኔን ከጥፋት ጎርፍ በዓመፀኞችና በበደለኞች ላይ ከምትመጣው የመቅሠፍት ኃይል አድኝኝ፡፡" 🤲🤲🤲 አርጋኖን - አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
إظهار الكل...
👍 2
ሞት ያምራል ለካ?! ... መቸም በመጽሐፍም በአፍም ስለሞት ብዙ ተብለናል .. በተቻለም ለሞት ያለንን ግንዛቤ የሚያሻሻሉ ስብከቶች እና ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ ሞት እንደማያስፈራ ፣ .. እንደውም ወደ እግዚሐር የሚያደርስ ድልድይ እንደሆነ ስንሰማ አድገናል .. ዳሩ ግን .. ምን ሞት ወደእረፍት መውሰጃነቱ ቢንቆለጳጰስም ፣ ቅዱሳን ጻድቃን እንዲሁም ጌታቸው የቀመሰው ጽዋ ቢሆንም ፤ ሞት ያስፈራል .. ግርማው ያሸብራል፡፡ ሞት ነዋ! ... ፌስቡክ ላይ እንደወትሮዬ ሁሉ ስክሮል አደርጋለሁ .. ፓለቲካ ፣ መዝናኛ .. ልግጫም አይቀረኝም ፤ ያመጣልኝን ለአይኔ ሲሳይ አውላለሁ .. ዞሬ ስመለስ ፤ አንድ መልከኛ ቄስ ፎቶ ላይ .. ነፍስ ይማር የሚል ተለጥፎ አየሁ፡፡ ሳየው የማውቀው ይመስለኛል .. ስሙን ሳነበው ግን ጨርሶም ሰምቼው አላውቅም፡፡ በዚህ ደረጃ ስወዛገብ .. ትልልቅ የሚባሉ አባቶች እና መምህራን ሳይቀር .. ስለሞቱ ሐዘናቸውን የሚገልጽ ጽሑፍ አስከተሉ፡፡ አሁን ጭራሽ መልከኛውን ቄስ አለማወቄ አንገበገበኝ፡፡ መልአከ ጸሐይ ቀሲስ መኮንን ደስታ .. ! ... ካረፈበት ጊዜ አንስቼ አለማወቄን ለመበደል ... ብዙ ስለሱ የጻፉ እና ያወሩትን ሰዎች ማንበብ ያዝኩ .. ከላይ እንዳልኹት .. መልኩን ሳየው ያወቅኹት የመሠለኝ .. በአእምሮዬ ቄስ ማለት ፥ ካህን ማለት .. ብዬ ከሳልኹት ሰው ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ ነው፡፡ ... ብዙ ሳጣራ .. ከዛሬ 50 አመት በፊት በገነተ ኢየሱስ አካባቢ የተወለደ ነው ፥ ቀሲስ መኮንን ደስታ ... በዚያው ደብር የተማረ ለማዕረገ ዲቁና የበቃ ፤ ብሎም በሰሞነኝነት ያገለገለ ነው ... ይሄ መቼስ መመረጥ ነው ፥ ባደጉበት ደብር መቀደስ ማወደስ .. ለዚህ እኔም አንዱ ባለእድል ነኝ! ... በ1991 በቲዎሎጂ ዲግሪውን የያዘ ሲሆን ... እስከ ሚሊንየሙ ድረስ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ በስብከተ ወንጌል ኃላፊነት አገልግሏል፡፡ .. ከ2 ሺህ ዓ.ም አንስቶ ደግሞ በአዲሱ ሚካኤል በዚሁ የስራ ኃላፊነት እስከ 2008 ዓ.ም ቆይታ አድርጓል፡፡ በእኔ ማጣራት ... ከ2008  ዓ.ም እስከ አረፈባት ቀን ድረስ በሲያትል አካባቢ ስፓኬን ማርያም አስተዳዳሪ ሆኖ በማገልገል ላይ እንዳለ ጠንከር ባለ ሕመም የተነሳ ያረፈ እንደሆነ ማወቅ ችያለሁ፡፡ .... ቀብሩ ባደገበት .. ክርስትና በተነሳበት .. ቀድሶ ባቆረበበት ደብር ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ሲፈጸም ... አብሮ አደጎቹ .. ወዳጆቹ በሙሉ በእንባ ሲገለገሉ ማየት ይገርማል፡፡ .. ታቦታቱ ከመንበራቸው ወተው .. ቀብሩን ሰርጎ አስመስለውታል፡፡ ... ሊቃውንቱ አምመው ጠምጥመው ... ጳጳሳቱ ተገኝተው .. መምህራኑ ወምዕመናኑ ለየት ያለ የሽኝት አጀብ በማድረግ ክብራቸውን አሳይተዋል ፡፡፡ ይህን ያዩ ሰዎች ሞት ያምራል እንዴ እስኪሉ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡ ... ለእኔም ለካ የካህን ... የቄስ ሞት እንዲ ያምራል እንዴ እንድል አድርጎኛል .. እኔም የማዕረገ ክህነትን መያዜ እንዲያኮራኝ አድርጓል፡፡ ለመምህሩ ለካህኑ ለመልአከ ጸሐይ መኮንን ደስታ .. ተድላ ገነትን ያውርስልን!! ✍ቃል ፥ ኪ ዳ ን
إظهار الكل...
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
#በዐለ መስቀል መጋቢት 10 እንኳን አደረሰን እምገቦከ ውኂዘ ነቅዐ ማይ ዘቀደሶ ለፈያታይ ለነዳይ ምስካይ መስቀልከ እግዚኦ ለነዳይ ምስካይ
إظهار الكل...