cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

በብሂለ አበው ኩኑ ውሉደ ብርሃን

<<አንተስ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ የዚህን መፅሐፍ የትንቢት ቃል አትሰውር ዘመኑ ደርሷልና ፤ እንግዲህስ የበደለውን ይበድሉታል። ያሳደፈውን ያሳድፉታል ጻድቁም ይጽደቅ። ንፁሑም ንፅሑ ይሁን። እነሆ ፈጥኘ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱም እንደስራው ከፍየ ብድሩን እከፍለው ዘንድ የምሰጠው ዋጋ ከኔ ጋር ነው (ራዕ ፳፩ ቁ ፰-፲፪ ፤ ኢሳ ፵ ቁ ፲)>> መልዕክት ካለዎት @TemhrtTewahedoBot

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
Advertising posts
809المشتركون
-124 hour
-67 يوم
-2130 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#የስሜት_ቀንበር #በአንድ_ወቅት_እንዲህ_ሆነ። አንድ ባለ ጸጋ ሰው ብዙ ወርቅ ይዞ ወደ ገዳም በመሄድ በገዳሙ ውስጥ ላሉት መነኮሳት አባቶች እንዲከፋፈልለት ይጠይቃል:: የገዳሙ አበምኔትም ወርቁን ወደ አንድ ወገን እንዲቀመጥ ካደረጉ በኋላ የገዳሙን የጥሪ ደውል ይደውላሉ፡፡ የገዳሙ መነኮሳት ከተሰበሰቡ በኋላም ወደ ወርቁ እያመለከቱ እያንዳንዳቸው ለባለ ጸጋው ሰው ያላቸውን ፍቅር ይገልጡ ዘንድ ድርሻ ድርሻቸውን እንዲያነሱ ይጠይቋቸዋል። በዚህ ጊዜ ደጋግመው ቢወተውቷቸውም መነኮሳቱ ወርቅ ሳይሆን ድንጋይ እንደሚመለከቱ ሆነው በዚያው ቆመው ቀሩ፡፡ የመነኮሳቱ ባሕርይ ያን ባለጸጋ ሰው እጅግ ስላስደነቀው እንደ እነርሱ ይመነኩስ ዘንድ ጠይቆ በዚያው ቀርቷል። #ውድ_ወንድሜ_ሆይ! ዓለሙና ሥጋችን ስሜታችንን በብዙ ነገር ይማርኩታል። በመሆኑም ቁሳዊና የዓለም የሆኑት ነገሮች በሙሉ ከሆኑት ይልቅ እጅግ የሚያምሩና የሚስቡ ብቻ ሳይሆን መልካም ነገርን የሚያስገኙልን መስለው ይታዩናል፡፡ ይሁን እንጂ ነፍሳችን ከዚህ መሰናክል ከሆነባት ነገር በከፊል ተላቃ በሥጋችን ላይ መሰልጠን ስትጀምር ስሜታችንም አብሮ ነፃ ስለሚሆን ሁለቱም በአንድነት ከዓለማዊው ፍላጎትና አመለካከት ነፃ ስለሚወጡ በነገሮች ላይ አዲስ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ማዳበር ይጀምራሉ፡፡ ይህ ዓይነቱን ነገር በራስህ ገጠመኝ ታውቀዋለህ። እንበልና ከቤተሰቦችህ ተለይተህ ራቅ ወዳለ ሥፍራ በመሄድ ለረዥም ጊዜ ከቆየህ በኋላ የቤተሰብህ አባላት በሙሉ በታላቅ ፍቅርና ናፍቆት እያቀፉ ይስሙሃል፡፡ በዚህ ጊዜ ላንተ ባላቸው ፍቅር እጅግ ትመሰጣለህ፡፡ ከዚህ ተመስጦ ባሻገር ግን አቅፎ የሚስምህ እናትህ ይሆኑ አባትህ ወይም እህትህ ትሁን ወንድምህ፤ ወንድ ይሁን ሴት የምትለይበት ሁኔታ ብዙም አይታወቅህም። #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ @Weldeaman
إظهار الكل...
ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Weldeaman
إظهار الكل...