cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አል ቡርሃን islamic channel

አላማችን በውቀት ላይ የተመሰረተ ትውልድ መፍጠር ነው አንባቢ እንሁን እስልምናችን ሙሉእ ነው:: ንፅፅር ተከታታይ እስላማዊ ፅሁፎች አነቃቂ መልክቶች ይቀርቡበታል. @abuburhann ለአስተያያት @AlburhanBot

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
185
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እሱ አምላክ አለኝ እያለ እንዴት አምላክ ትሉታላችሁ❓❓❓❓ 1. ዩሐንስ ወንጌል(7፥28)“እኔ በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት #የላከኝ እውነተኛ ነው ” 2. የማቲዮስ ወንጌል(15፥24)“ከእስራኤል ቤት ለጠፉ በጎች በቀር #አልተላኩም” 3. ዩሀንስ(7፥15-16)“አይሁድም። ይህ ሰው ሳይማር መፅሐፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር። ስለዚህ #እየሱስ_መለሰ ፤ እንዲህም አላቸው። ትምህርቱስ #ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።” 4. ዩሐንስ (8፥26)“ ‘#የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለአለም እናገራለሁ’ አላቸው። 5. ዩሐንስ(12፥44)“በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም” 6. ዩሐንስ(17፥3)“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን #የላከውንም_እየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ህይወት ናት” 7. የዬሐንስ ወንጌል (13፥16)“እውነት እውነት እላችኋለው #ባሪያ_ከጌታው አይበልጥም ፣ #መልዕክተኛም_ከላኪው #አይበልጥም” 8. ዩሐንስ(11፥41-42) “ ድንጋዩንም አነሱት እየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንስቶ አባት ሆይ ስለ ሰማሀኝ አመሰግንሀለው። ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ አወኩ ፤ ነገር ግን አንተ #እንደላከኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለቆሙት ህዝብ ተናገርሁ አለ”ሸሸሸ ለአምላክ አምላክ አለዉዴ⁉️ አምላክ ላኪ ወይስ ተላላኪ⁉️ ወገኖች ወደራሳችሁ ተመለሱ❗️
إظهار الكل...
✍ትግስዕት ትግስዕት_ድምፅ የሌላቸው ቃላቶች ናቸው። ትዕግስት ያለውን ሰው አክብረው~~ትልቅ ደርጃ ሲድርስ ያኔ ስታየው ከሱ ብዙ ነገር ትማራለክ;; @abuburhann
إظهار الكل...
እንደሞተች አይውቅም።ህይወቷ ከአካሏ የተለየ ቢሆንም አጠገቡ ስላለች በእረጋታ ተቀምጧል።የፊቱ ቁስል ትዝ ሳይለው ከመች ከመች ተነስታ ታቅፈኛለች ብሎ በጉጉት ይጠብቃታል።😪😪😪🇯🇴🇯🇴🇯🇴🇯🇴 ህመም! ዑመር አል-አውዷህ #GazaUnderAttack 🇯🇴🇯🇴🇪🇹 ↳ https://t.me/ALIF_MIDIA
إظهار الكل...
#የሸዋል ፆም ፍች (ትንሹ ዒድ) በአቡ ሀይደር በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡ በተወሰኑ (ሁለት ወይም ሶስት) ብሔሮች ዘንድ ከረመዷን ዒድ (ዒዱል-ፊጥር) ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም ይጾሙና ሰባተኛውን ቀን እንደ ዒድ ያከብሩታል፡፡ ምክንያቱን ጠይቄ ለማወቅ እንደሞከርኩት ይህን ይመስላል፡- የዒዱል-ፊጥር ቀን ደብዘዝ ብሎ በደንብ ሳይሞቅ የምናሳልፈው ቀኑ አንድ ቀን ስለሆነና በነጋታው ተመልሰን ወደ ሸዋል ጾም ስለምንገባ ነው፡፡ ስለዚህ ባሉት ተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም በመጾም ሁለቱንም (ረመዷንንም ሸዋልንም) እንጨርስና ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ በደንብ ዒዱን እናከብራለን፡፡ እንበላለን እንጠጣለን፡፡ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ ዘመድ እንጠይቃለን፡፡ ብዙ ቀናቶች አሉንና፡፡ ከዚህ ምክንያት መረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ብቻ በመሆኑ በሰፊው ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር ለመዘያየር የማይበቃ መሆኑ ነው እንጂ የሸዋል ዒድ አለ ብለን አይደለም የሚል ነው፡፡ ማስተካከያ፡- 1ኛ/ የኢስላም ሃይማኖት እንዳስተማረን ከሁለቱ ዒዶች (ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ) ውጪ፡ ሙስሊሞች ሌላ ዒድ የላቸውም፡፡ የአላህ መልክተኛ ከደነገጉት ውጪ አዲስ ስርአትን መደንገግ በሃይማኖቱ ላይ መጨመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቢድዐ ይባላል፡፡ የሸዋል ወር 8ኛው ቀን የሸዋል ፆም መፍቻ ዒድ ቢሆን ኖሮ፡ በዒድ ቀን መፆም ሐራም ነውና በዚህ ቀን አትፁሙ የሚል ትእዛዝ በሐዲሥ በሰፈረ ነበር፡፡ ግን የለም፡፡ 2ኛ/ የሸዋል መጀመሪያ ቀን ዒዱል ፊጥር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዒድ ደግሞ የመደሰቻ፣ የመብያና የማብያ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጫ ቀን ነው፡፡ ግን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ነው መብላትና ማብላት፣ መዘየርና መደሰት የሚቻለው ያለው ማነው? የሸዋልን ሁለተኛና ሶስተኛ ቀናትስ መብላትና ማብላት፣ መዘያየር አይቻልም? ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከላይ የቀረበው ምክንያት አጥጋቢ አይደለም፡፡ 3ኛ/ የሸዋል ስድስት ቀናት ጾም በመጀመሪያዎቹ የሸዋል ቀናቶች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሸዋል ሙሉ አንድ ወር 29/30 ነው፡፡ ስለዚህ ከወሩ ውስጥ የሚመቸውን ቀን መርጦ በማከታተልም ሆነ በማፈራረቅ ሸዋልን መጾም ይቻላል፡፡ እናም የደስታውን ቀን ማርዘም የሚፈልግ ከዒዱል-ፊጥር በኋላ ያለውንም ቀን መጠቀም ይቻላል፡፡ በቀሩት ቀናት ደግሞ ሸዋልን መጀመር ይቻላል፡፡ 4ኛ/ ከዒዱል-ፊጥር ማግስት ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ስድስት ቀናት የጾመ ቤተሰብ በቀጣዩ ቀን በመብላትና ቀኑን እንደ ዒድ ቆጥሮ ሲያሳልፈው፡ ከመሐከላቸው አንድ ሰው ጾሙን ባለመጨረሱ (ቀዷእ ቢኖርበት ወይም ዘግይቶ ቢጀምር) እነሱ የሚበሉበትን ቀን ቢጾመው የቤተሰቡ አካላት ይቃወሙታልን? በዒድ ቀን እንዴት ትበላለህ ይሉታልን? አዎ! ከሆነ ምላሹ፡ ሰዎቹ ቀኑን ዒድ አድርገው ይዘውታል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዲነል-ኢስላም ላይ የተጨመረ ፈጠራ ‹‹ቢድዓህ›› ይባላል፡፡ አላህና መልክተኛው ከዒዱል-ፊጥር እና ከዒዱል አድሓ ውጪ የበዓል ቀን አልደነገጉልንም፡፡ የሸዋል ዒድ የሚባለው መሰረት የለውም እና እንደ-ዒድ አድርገው የሚይዙ ሰዎችን ቢድዓ መሆኑን ማስተማርና ማስገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡ 4. ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር፡- ከዒዱል ፊጥር ማግስት ጀምሮ በተከታታይ የሸዋልን ስድስት ቀናት የጾመ ሰው በቀጣዩ ቀን መብላት መጠጣት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሰውየው ጾሙን እስካጠናቀቀ ድረስ መብላት መጠጣት ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቀኑ ላይ ሲበላም ሆነ ሲጠጣ ቀኑን ዒድ ነው ብሎ እንዳይመለከተውና እንደ-ዒድ አድርጎ እንዳይዘው ነው፡፡ የዒዱል-ፊጥር ቀንንም በአግባቡ ሊያከብረው ይገባል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡ Ustaz Abuhyder
إظهار الكل...
ፊዳከ አቢ ወኡሙ ያ ረሱለላህ አንድ ቀን እንዲህ ሆነ… ረሱል ሰ,አ,ወ ቢላልን(ረ•አ) ጠርተው ያ ቢላል አሰላቱ ጃሚአ ብለህ ህዝቤን ሰብስብልኝ አሉት ያኔ ቢላል ረ,ዐ ወዲያውኑ አሰላቱ ጃሚአ ብሎ ህዝቡን ሰበሰበ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ወደ ሚንበር ላይ ወጡና እሚገርም ቁጥባ ማድረግ ጀመሩ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ይጠይቃሉ ሰሀባወች ይመልሳሉ ። ረሱል ሰ,ዐ,ወ የእኔ ነብይነት ለእናንተ እንዴት ነበር ??? በደንብ አስተምሬአችሆለሁን ? ሀቃችሁን ሁሉ ተወጥቻለሁ ወይን? ብለው ጠየቁ። ሰሀባወችም አንቱማ በጣም ረሂም አባት ነበሩ እንዲሁም መካሪ ወንድም እናት ነውት እኮ ለእኛ አሎቸው በሉ እንግዲያውስ በአለህ ይዧችሆለሁ ምናለልባት የበደልኩት ሰው ካለ ነገ አኼራ ላይ እንዳይጠይቀኝ ዛሬ ላይ ይኸው የበደልኩት ካለ ንብረቱን የወሰድኩበት ሰውም ካለ የመታሁት ዛሬ ነውና እድሉ ይምጣ እና ይበቀለኝ ብለው አሉ። ሁሉም ፀጥ አሉ ማንም አልተነሳም አሁንም ለ2ኛ ጊዜ ደገሙና በአላህ ይሁንበት የበደልኩት ይምጣና ይበቀለኝ ይሄው አለሁ ሁሉም ፀጥ አሉ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያመእሸረል ሙስሊሚን እስኪ ማነው እኔን መበቀል እሚፈልግ ትላንት በእኔ የተከፋ አለን? ፀጥ አሉ ። ለ3ኛ ጊዜ ደገሙና በአላህ ይሁንባችሁ ይኸው እኔ እዚህ አለሁ የበደልኩት ሰው ይምጣና ይበቀለኝ ሲሉ ይህኔ በእድሜ የገፋው ኡካሻ(ረ• አ) የሚባሉ ሰሀባ ተነሱና ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ ወላሂ ያረሱለላህ በአላህ ይሁንባችሁ እያልሉ ደጋግመው ባይጋብዙ ኖሮ ወላሂ እኔ ለእዚህ ጉዳይ እምቆም አልነበርኩም ። በእርግጥ አንድ ቀን ከእርስዎ በደል ደርሶብኛል ፊዳክ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ☞ ከእለታት አንድ ቀን አንቱ ጋር ጦርነት ላይ አላህ የማሸነፍን እድል ሰጥቶን ወደየቤታችን ልንመለስ እያልን ሳለን ያንቱ ግመል ከእኔ ግመል አጠገብ ለአጠገብ ሆነው ነበር። እናም እኔ የእግረዎትን ጡንቻ ለመሳም ከግመሌ ወረድኩ ወደ እግረዎ ዝቅ ስል በእጅዎ የያዙትን አለንጋ ዝቅ ሲያደርጉ ወገቤን እስከ ሆዴ ጭምር መቱኝ ሆን ብለው ነው የመቱኝ ወይስ አለንጋውን ከፍ ለማድረግ አላቸው? ☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ አሉ ኧረ አውቄ እማ ከመምታት አላህ ይጠብቀኝ አላወኩም አሉት ። እና አሁን ምን ትፈልጋለክ ሲሉት እኔማ እምፈልገው የመቱብኝ ቦታ መምታት ነው አላቸው ለረሱል (ሰዐወ) ☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ ቢላልን ጠሩትና ያ ቢላል በል ከፋጡማ ረ,ዐ ቤት ሂድና አለንጋዋን አምጣ ብለው አሉት። ቢላልም ሄዶ ያ ፋጡማ ቢንት ረሱል ሰ,ዐ,ወ ረሱል ሰ,ዐ,ወ አንቺ ጋር ያስቀመጡትን አለንጋ ላኪ ብለውሸል አላት። ያ ቢላል ዛሬ የሀጅ ቀን ወይም የዘመቻ ቀን አይደለም ምን ሊያደርጉት ነው አለችው። ቢላልም ቀጠለና ያ ፋጡማ አልሰማሽም እንዴ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የደረሰባቸውን የተባሉትን አልሰማሽምን? ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ከዚህ አለም አየሞቱ ወደ እዛኛው አለም እየተሸጋገሩ እኮ ነው ። ያ ፋጡማ አልሰማሽምእንዴ መሄዴ ነው እና በቀል ካላችሁ ተበቀሉኝ አሉ እኮ ታዳ ማነው ነብዩን እሚመታ እሳቸውን እሚገርፍ? ያ ቢላል ማነው ሀሰን እና ሁሴንን ውሰድ እና በረሱል ቦታ ይገረፉው እነሱ እያሉ ረሱል ሰ,ዐ,ወ አይገረፉውም አለች አለንጋውን ለረሱል ሰ,ዐ,ወ ወስዶ ሰጣቸው ተቀበሉና ያ ኦካሻ በል ወገቤም ሆዴም የሄው ምታኝ አሉት ኦካሻም ሊመታቸው ተነሳ ያኔ አቡበከር ረ,ዐ ቆሙ ኡመርም ረ,ዐ ተነሱ ያ ኦካሻ እኛ እያለን ረሱልን እንዳትነካብን አሉ ። ይሄው እኛ ቆመናል እኛን ግረፍ አሉት ። እሳቸውን እንዳትመታብን ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑት ጀመር። ረሱል ሰ,ዐ,ወ እንቢ ያ አቡበከር እንቢ ያ ኡመር አላህ ሱ,ወ ለእኔ ያላችሁን ቦታ አውቋል አይቷል ወዶታል እና ተቀመጡ አሉ ። ምታኝ ያ ኦካሻ ሲሉት አልይ ኢብን አቡጣሊብ ረ,ዐ ተነሳና ያው እኔን እንደፈለክ ወገቤም ሆዴም አደራ ብየሀለሁ ረሱልን እንዳትነካብኝ እኔን እንደፈለክ አርገኝ አለ። ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ አልይ አላህ ንያህንም ለእኔ ያለህን ቦታ ወዶታል ቁጭ በል አሉት ። የዛኔ የፋጡማ ረ,ዐ ልጆች ሀሰንና ሁሴን ተነሱ እና ያ ኦካሻ የረሱል ሰ,ዐ,ወ የልጅ ልጆች መሆናችንን አታውቅምን? ነብዩን እንዳትነካ እኔን እኔን ግረፍ አማና ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑ ጀመር ። ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ቁረተል እዩኒና አይደለም ተቀመጡ አሎቸው። ☞ያ ኦካሻ እምትመታኝ ከሆነ ምታኝ አሉት። ያረሱለላህ እርስዎ እኮ የመቱኝ ሆዴ ክፍት ሆኖ ነው እንዴት አድርጌ ከእነ ልብስዎ ልምታወት ይህኔ ይኸው ሆዴ በለው ገለጡለትና ምታኝ አሉት ። ይህኔ ሰሀባዎች በእንባ ተራጩ ። ያ ኦካሻ አይከብድህም አታፍርም ነብዩን ልትመታ ነው? እያሉ ይጮሀሉ ። የነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሆድ በሚያይ ሰአት በሚገርም ሁኔታ ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ እያለ ይስማቸው እየላሳች ይጮሀል ። ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ኦካሻ ወይ ምታ ወይ አፉው በል አሉት። አላህ የውመል ቂያማ አፉዉ እንዲለኝ አፊው ብየዎታለሁ እኔ እኮ ልመታወት ፈልጌ አይደለም ቆዳየ ከቆዳወ ጋር አንዲላተም እንዲገናኝ ብየ ነው። ረሱል ሰ,ዐ,ወ ተናገሩ ጀነት ውስጥ የእኔ ጎደኛ የሆነን ሰው ማየት እሚፈልግ ካለ ወደ እዚህ ሽማግሌ ይይ አሉ። እንዳለ ሰሀባዎች የኡካሻን ግንባር እየሳሙ የረፊቅል አእላ ባለቤት እያሉ ያለቅሳሉ ኦካሻም ያለቅሳል ሰሀባዎች ይህን ያህል ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ያፈቅሯቸው ነበር ። እኛስ?
إظهار الكل...
إظهار الكل...
አል ቡርሃን islamic channel

አላማችን በውቀት ላይ የተመሰረተ ትውልድ መፍጠር ነው አንባቢ እንሁን እስልምናችን ሙሉእ ነው:: ንፅፅር ተከታታይ እስላማዊ ፅሁፎች አነቃቂ መልክቶች ይቀርቡበታል. @abuburhann ለአስተያያት @AlburhanBot

ሸዋል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ “ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም” እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ “ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም” እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያ ሆዬ ወደ አንቺ ሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ። የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦ 1ኛ ወር ሙሐረም 2ኛ ወር ሰፈር 3ኛ ወር ረቢዑል-አወል 4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ 5ኛ ወር ጀማዱል-አወል 6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ 7ኛ ወር ረጀብ 8ኛ ወር ሻዕባን 9ኛ ወር ረመዷን 10ኛ ወር ሸዋል 11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ 12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦ 9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር “ሸዋል” ነው፥ “ሸዋል” شَوَّال ማለት “ማንሳት” ወይም “መሸከም” ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን”ﷺ” እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦ ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78 አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏ የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦ 6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አሊያም ሠላሳ የረመዳን ቀን እና ስድስት የሸዋል ቀን በአስር ምንዳ ሲባዛ 360 ቀናት ይሆናሉ፥ 36×10= 360 ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ በጸሐይ አቆጣጠር 360 ቀናት መሆኑ ቅቡል ነው። አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት” ይለናል፦ 59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሰራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው። ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር @abuburhann ወሠላሙ ዐለይኩም
إظهار الكل...
ዒድ ሙባረክ! እንኳን ለ1442ኛው ለዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኻል አዕማል!
إظهار الكل...
የዘካተል-ፊጥር ህግጋት ★★★★★★★★★★★★★★ 1/ ዘካተል-ፊጥር የጾሙም ያልጾሙም አዋቂና ህጻናትም ላይ በሙሉ ግዴታ ነው 2/ የሚሰጠውም ለአቅመ ደካማ/ሚስኪኖች ብቻ ሲሆን አንድ ሰው የቲም ወይም የአካል ጉዳተኛ ብቻ ስለሆነ ዘካተል-ፊጥር ይግባዋል ማለት አይደለም! 3/ የቲምም ይሁን አካል ጉዳተኞች በቂ መተዳደሪያ ካላቸው ዘካ አይሰጣቸውም! 4/ ዘካተል-ፊጥር በእህል(1 ቁና) እንጂ በብር ወይም በልብስና መሰል ነገሮች አይሰጥም የተራቡ የሚበሉት ምግብ እንጂ የታመሙ የሚታከሙበት ወይም እዳ ያለባቸው የሚከፍሉበትም ገንዘብ አይደልም! አንድ ቁና በኪሎ ግራም ሲሰላ ከ2.5 እስከ 3 ኪሎ ነው ተብሏል። 5/ የዘካተል-ፊጥር ማስረከቢያ የተመረጠው ወቅት የረመዷን የመጨረሻው ቀን ጸሐይ ከጠለቀችበትና ነገ ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ወቅት ጀምሮ እስከ ቀጣዩ/ የዒድ ቀን ሰላት እስኪጀመር ያለው ጊዜ ላይ ሲሆነ ካስፈለገ ከዒድ ቀን አንድ ወይም ሁለት ቀን አስቀድሞ መስጠትም ይቻላል ከዒድ ሰላት ከዘገየ ወይም ከረመዷን 28ኛው ቀን በፊት ከሆነ የተሰጠው ወቅቱን አልጠበቀም ምንጭ ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ አደም
إظهار الكل...
ያ ሰላም ምነኛ ያማረ ስግደት ማንኛውም ቦታ ወደ አምላክ ለሰጋጆች የተገባ ነው ...! ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡[ ሱረቱ ሐ ሚም አል-ሰጅዳህ - 37 ] ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ [ ሱረቱ አል-ነጅም - 62 ] የኢትዮ ሙሥሊሞች በአብዮት የኢድ አደባባይ ። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.