cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

EBS TV

worldwide news🌍

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 776
المشتركون
+424 ساعات
+127 أيام
-130 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም ' ማለታቸው ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " ብለዋል። ከመንግስት ጋር በታንዛንያ የሰላም ንግግር ሲያደርጉ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) ተዋጊዎችን " በድርድር ተስፋ ሳትቆርጡ ፤ መተማመንን ለመገንባት ጥረት አድርጉ " ብለዋቸዋል። አሜሪካ ይህን ያለችው ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ በአምባሳደሯ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት ነው። በአዲስ አበባ ፤ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካን ግቢ በነበረ መርሀ ግብር የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር። Video Credit : US Embassy Addis Ababa / Ethiopia Insider @tikvahethiopia
1390Loading...
02
#SouthEthiopiaRegion በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል። በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም። ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል። የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል። ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። @tikvahethiopia
1130Loading...
03
#ProsperityParty #TPLF ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል። ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል። ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል። ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል። " ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል። ከዚህ ባለፈ ፦ - " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። - ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል። - የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል። - ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል። - የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ #ProsperityParty #TPLF @tikvahethiopia
1000Loading...
04
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል። አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው። ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው።  ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው። የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው። ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። " Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና፦ " ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር። አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። " Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው። ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል።  ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው። የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል። አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። " Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ? ፕ/ር መራራ ጉዲና ፦ " በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው። መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ። አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም። Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል። መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል። መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። " Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው። ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። " #TikvahEthiopiaFamilyAA #ቲክቫህኢትዮጵያ #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ? @tikvahethiopia
770Loading...
05
#Tigray ከማረት ከተስረቁት 2 መኪኖች አንደኛዋ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ። ማሕበር ረድኤት ማሕበር (ማረት) በመጋቢት እና በያዝነው ግንቦት ወር አንድ ላንድክሩዘር V8 እና ላንድክሩዘር ማርክ 2 መኪናዎችን ተዘርፏል። የድርጅቱ ንብረት የሆነች በሰሌዳ ቁጥር 35 - 2723 የተመዘገበችው V8 መኪና መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተሰርቃ ሳትገኝ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታ ነበር። ይህች መኪና ሳትገኘ ከቀናት በፊት ላንድ ክሮዘር ማርክ 2 መኪና ተዘርፋለች።  ፓሊስ የድርጅቱ መኪኖች ያየና ያገኘ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ በያዝነው ሳምንት የተሰረቀችው ላንድክሩዘር ማርክ2 መኪና ከመቐለ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አክሱም ከተማ በፓሊስ ተይዛለች። የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ መኪናዋ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 በፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋልዋን አሳውቋል። ፖሊስ መኪናዋን ያገኘው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል ነው። በሰዓቱ መኪናዋን የያዛት ሹፌር ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ማክሸፉን አሳውቋል። ከነሹፌሩ በተጨማሪ " የኔ ንብረት ናት " የሚል አመልካችም በፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል። የአክሱም ከተማ ፖሊስ " መሰል ስርቆት ከጦርነቱ በኋላ መታየት የጀመረና በትግራይ ያልተለመደ ነው " ያለ ሲሆን " ማንኛውም ወንጀለኛ ከህዝብ አይንና ጀሮ መደበቅ አይችልም ብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ስለ መኪኖቹ ስርቆት ከማሕበር ረድኤት ትግራይ (ማረትረት) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።                                             @tikvahethiopia            
1040Loading...
06
" ሞተዋል !! " - ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩ የመጨረሻው ሁለት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተከሳሾች መሞታቸውን ማረጋገጡን በጉዳዩ ላይ የተቋቋመው ችሎት አስታውቋል። ርያንዱካዮ በሚል ስም ብቻ የሚጠራው እና ቻርለስ ሲኩብዋቦ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ጉዳይ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ችሎት ሲፈለጉ የነበሩ የመጨረሻዎቹ ተከሳሾች ናቸው። በብሔራዊ ደረጃ ግን አሁንም ድረስ ከ1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በመፈለግ ላይ ናቸው። 2ቱ ግለሰቦች ከ30 ዓመት በፊት 800 ሺ ቱትሲዎችን እና ለዘብተኛ ሁትዎችን በጨረሰው የዘር ፍጅት ላይ ተሳትፎ አላቸው በሚል ለሩዋንዳ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በእ.አ.አ 1995 ክስ ቀርቦባቸው ነበር። ሲኩብዋቦ በእ.አ.አ 1998 በቻድ መሞቱን እና በዛው መቀበሩን እንዲሁም ርያንዱካዮ ደግሞ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከሸሸ በኋላ ከዛም ወደ ዛየር ተሻግሮ ኪንሻሳ ላይ በ1998 ሕይወቱ ማለፉን ፍ/ቤቱ አስታውቋል። በሩዋንዳው የዘር ፍጅት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ሲፈለጉ የነበሩ ተከሳሾች ሁሉ መለየታቸውንም ችሎቱ አስታውቋል። #ቪኦኤ #RwandaGenocide @tikvahethiopia
1090Loading...
07
#Ethiopia ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡ ከተመሩት ረቂቅ አዋጆች መካከል አንዱ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ነው። የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አዋጁ በስራ ላይ ከዋለ 6 አመት ያስቆጠረ መሆኑንና አሁን ካሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር ማጣጣም ማስፈለጉን ገልጸዋል። የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉንም ባካተተና ብዝሀነትን በጠበቀ መልኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ፦ ➡ የደሞዝ ጭማሪ፣ ➡ የደሞዝ እርከን፣ ➡ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ማትጊያና ማበረታቻ ስርአት፣ ➡ የሰራተኞች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ ስራ ስምሪት እና ነጻ ገለልተኛ ስርአት መገንባት፣ ➡ የመንግስት ሰራተኛነት ውል ማቋረጥና ማራዘም የሚሉና ሌሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 13/2016 ሆኖ በሙሉ ደምጽ ለሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡ ሌሎች ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመሩ ረቂቅ አዋጆች ምንድናቸው ? በዚህ ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Ethiopia-05-14-8 @tikvahethiopia
1561Loading...
08
#Ethiopia የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። አዲሱ አዋጅ የግል ፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰው ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች አሻሽሏል የተባለ ሲሆን የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል ተብሏል። አዋጁ ምን ይዟል ? - ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ ይችላል። NB. በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት " መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው "። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው " ለመንግስት እና ለህዝብ " ነው። - የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልበታል። - የወል ወይም የመንግስት ይዞታ ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር ይቀጣል። - ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። - ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል። - ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። ምንጭ፦ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @tikvahethiopia
1390Loading...
09
በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ገንዘብ ? በየዩኒቨርሲቲዎች " ለሥራ ኃላፊዎች የሚከፈል ክፍያ " በሚል የሚመዘበረው ገንዘብ  ከፍ ያለ ነው። ሰዎቹ ከመንግሥት በጀት / አካል ውጭ ተጻጽፈን በሚመጣልን ድጋፍ ፕሮጀክት እየሰራን ብር ይከፈለናል ነው የሚሉት። ክፍያው ግን እጅግ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ግልጽነት የጎደለው፣ ብዙ ጥርጣሬንም የሚያጭር ነው። መንግሥት ደመወዛቸውን እየከፈላቸው እያለ " ላስተባበሩበት " በሚል እዛው ግቢያቸው ውስጥ ለሚሰራ ስራ የሚከፈላቸው ብር ብዛት የሚገርም ነው። ለአብነት፦ ሰሞኑን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚፈጸም አይን ያፈጠጠ የለየለት የህዝብ ሀብት ምዝበራን በተመለከተ በተሰራጨው የፋና ምርመራ ዘገባ ላይ ዶ/ር ተመስገን ቶማስ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ብቻ የተከፈላቸው ገንዘብ በርከት ያለ ነው። ዶክተሩ ምንም እንኳን " ቁጥሩም እኮ ሳይገለጽ መነጋገር እንችላለን " ቢሉም አይገለጽ ያሉት ቁጥር ግን ይህንን ይመስላል። ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 1) ➡ 11,700 ብር (ሰንድ 2) ➡ 23,212 ብር (ሰንድ 3) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 4) ➡ 7,800 ብር (ሰንድ 5) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 6) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 7) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 8) ➡ 15,600 ብር (ሰንድ 9) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 10) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 11) ➡ 22,000 ብር (ሰንድ 12) ➡ 17,500 ብር (ሰንድ 13) ➡ 23,400 ብር (ሰንድ 14) ➡ 39,000 ብር (ሰንድ 15) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 16) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 17) ➡ 19,500 ብር (ሰንድ 18) ➡ 14,644 ብር (ሰንድ 19) ➡ 21,450 ብር (ሰንድ 20) እኚህ ሁሉ በሰኔ ወር 2013 የተከፈሉ ናቸው። ዶክተሩ ግን እስቲ ልየው 😳 በሰኔ ወር ነው የተከፈለው ? ብለው ይጠይቃሉ ዶክመቱም ይሰጣቸዋል፤ በኃላም ዶክመንቱን ያገላብጡና " እስቲ 2013 የሚለው የታለ ? " ሲሉ ድጋሜ ይጠይቃሉ " ይኸው ! " ይባላሉ ፤ በዝምታ ከተዋጡ በኃላ " እ ! " ብለው ዶክመንቱን መልሰዋል። ዶ/ር ተመስገን በተለያየ ጊዜ የተባከ ክፍያ የፋይናንስ ባጀት ስለሌለ በአመቱ መጨረሻ ባጀት ሲያገኝ ገብቶ ነው እንጂ በአንዴ የተላከ አይደለም ብለው ተከራርክረዋል። ሌላው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሐንስ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ሲሆን " እኔ ብዙ ፕሮጀክት ስለምሰራ ነው። ቀንም ማታም ቅዳሜና እሁድም በፕሮጀክት  ላይ ሰራው ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ ለዛ ነው የተከፈለኝ ባይ ናቸው። ዳይሬክተሩ በቀን 18 ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም 13,650  ብር እንዲገባላቸው የታዘዘበት ዶክመት የተገኘ ሲሆን በቀን 23 / 2013 ዓ/ም 15,600 ብር እንዲገባላቸው ታዟል በተመሳሳይ ቀን 19,600 ብር እንዲገባላቸው ተደርጓል። ሌሎችም በርካቶች ናቸው ነው ያሉት። ዶ/ር ተመስገን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዶክተር ሀብታሙ አበበ ጋር የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ስም በክፍያ ዶክመት ላይ " ፕሮጀክት " ተብሎ ተገኝቷል። በአጠቃላይ በዋቸሞም ሆነ በመሰል ተቋማት በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ብር እጅግ ብዙ ፣ ከደመወዛቸው እጥፍ፣ ግልጽነት የጎደለው ነው። ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎችስ ? @tikvahethiopia
1250Loading...
10
" በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " - ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የትምህርት ሚኒስቴር እና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው መገምገሙን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምር እና የ14 የአፕላይድ አጠቃላይ 22 ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር መገምገሙ ተነግሯል። በግምገማው ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፤ የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ይገባል ብለዋል። አስፈጻሚ መ/ቤቶች እና የስራ ሀላፊዎች በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ፤ " በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " ብለዋል። ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡ @tikvahethiopia
990Loading...
11
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ? በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲፈጸም እንደቆየ የተነገረለት እጅግ በጣም የለየለት የህዝብ ገንዘብ እና ሀብት ምዝበራን የሚያሳይ የ " ፋና ቴሌቪዥን " የምርመራ ዘገባ ከሰሞኑን ለህዝብ ተሰራጭቶ ነበር። 👉 በአበል መልክ የሚመዘበረው ገንዘብ ፦ የተቋሙ ገንዘብ በአበል መልክ ይመዘበራል። ለአብነት ሁለት የፋይናንስ ቡድን መሪዎች ከፍተኛ አበል ለራሳቸው ከፍለዋል። አቶ መሰረት ለማ የተባሉት ግለሰብ በ6 ወራት ብቻ የ1 ሺህ 496 ቀን ይህ ማለት 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል ተከፏላቸዋል። አቶ ደስታ ደቦጭ የሚባሉት ደግሞ የ940 ቀን አበል ወስደዋል። ➡️አቶ ደስታ የስንት ቀን አበል ወሰዱ ? ሲባሉ " የ790 ቀን ነው የወሰድኩት " ብለዋል። ወስደዋል እንዴ ? ተብለው በመርማሪ ጋዜጠኛው ሲጠየቁ " #አልወሰድኩም " ሲሉ ቃላቸውን አጥፈው ተናግረዋል። ➡️አቶ መሰረት የ1 ሺህ 496 ቀን አበል ወደ አካውንቶ ገብቷል ? ተብለው ሲጠየቁ " ይሄ ስህተት ነው የተሰሳሳተ ነው " ሲሉ መልሰዋል። የተቋሙ ፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዮሐንስ ፥ " እኔ ለረጅም ወራት ፍቃድ ላይ ነበርኩኝ የህመም ፍቃድ ላይ ከመጣሁ በኃላ ነው እንደዚህ አይነት ነገር እሰማ ነበር " ብለዋል። አቶ ደስታ ግን በዚህ አይስማሙም፤ አቶ ማርቆስ ታመው ቤት የተቀመጡት 2 ወር ብቻ እንደነበር የወጣው ደግሞ የ5 ወር መረጃ እንደሆነ ገልጸዋል። 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ አጋልጠዋል። ቀደም ሲል " እኔ አበል አልወሰድኩም " ያሉት አቶ ደስታ 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ እሱ እያለ ነው የተከፈሎት ? ተብለው ሲጠየቁ " ምኑን ? እንደ ስራ ባህሪ የተከፈለኝ ነገር ሊኖር ይችላል " ሲሉ መልሰዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ሀብቶሙ አበበ (ዶ/ር) ፥ " በሰነድ የተረጋገጠ ነው ብሎ የውጭ ኦዲት ያመጣውን ያክል አስመልሰናል ሰራተኞቹ ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል፤ በዲስፒሊም እየተጠየቁ ናቸው የኛ ኦዲት ያመጣውን የትራዛክሽኑን ቼክአፕ በህግ እንዲጣራ ክትትል እየተደረገ ነው " ብለዋል። የፋይናስ ስርአታቹ ክፍተት ያሉት ይመስላል ሲባሉ " በፍጹም በፍጹም !! " ሲሉ መልሰዋል። 👉 ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ስለወጣበት ፕሮጀክት ፦ ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግልጽነት በጎደለው መልኩ ተፈጽሟል። በዚህ ጉዳይ ፕሬዜዳንቱ እና የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እርስ በእርስ የሚያወዛግብ ምላሽ ነው የሰጡት። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ያለ ሰነድ ከእውቅናቸው ውጭ ገንዘቡ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይገልጻሉ። ክፍያ ሲፈጸም ሰነድ እጃቸው ላይ እንደሌለ እና እሳቸውም እንዳልተሳተፉ ተናግረዋል። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ " እኔ እኮ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠኝም ፤ እንደሚንቀሳቀስ አያለሁ እሰማለሁ " ብለዋል። ገንዘቡን እኔ አላንቀሳቅስም ነበር ብለዋል። ፕሬዜዳንቱ ግን የኦክስጂን ፕሮጀክት በጀቱ ሲመራ የነበረው በፋይናንስ ነው ሲሉ መልሰዋል። የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እኔ ሳላውቅ ነው ክፍያው የተፈጸመው ሲሉ ተናግረዋል። የቀድሞ ም/ፕሬዜዳንት ፀደቀ ላምቦሬ (ዶክተር) ፤  የአካውንቱ ጉዳይ በዋነኝነት የሚመለከተው ፕሬዜዳንቱን እንደሆነ ገልጸዋል። ▪️ለኦክስጅን ማምረቻው መሳሪያውን ያቀረበው ያለጨረታ ያለፍቃድ ያለውድድር 240 ሚሊዮን 988 ሺህ ብር ተሰጥቶታል። ለድርጁ ሙሉ ክፍያ ቢከፈልም ዝርጋታው ግን አላለቀም ስራውም አልተሰራም። ከተጀመረ 2 ዓመት አልፎታል። የምርመራ ዘገባውን ይመልከቱ👇 https://youtu.be/wREkP5S8zNM?feature=shared (አዘጋጅ ፦ ጋዜጠኛ አፈወርቅ እያዩ) @tikvahethiopia
970Loading...
12
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " መንግሥት የሰውን ሞት ትኩረት እየሰጠው አይደለም " ሲል እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሰጠው ቃል ወቅሷል። ድርጊቱን ማስቆም እንዳለበትም አጥብቆ ጠይቋል። እናት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ምን አለ ? Q. ፓርቲው አሁናዊ የኢትዮጵያ የጸጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እንዴት ይገመግመዋል ? በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?  እናት ፓርቲ ፦ " አገራዊ ሁነቱ የውድቀት አፋፍ ላይ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ጥበቃ በታች የመጨረሻ የሚባለውን ሰቆቃ እያየች ነው። ሰው በሰላም ወጥቶ የማይገባባት፣ የሰው ሞት የእንስሳትን ሞት ያህል የማያስጨንቅበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። በሌላ ጎን ሞቱ አለ፤ በሌላ መንገድ ደግሞ ሞቱን የሚንቅ አለ። ‘ይሄ በለውጥ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥም ነውና እኔ ትክክለኛ ስራዬን እየሰራሁ ነው ፤ ከእኔ ስንፍናና ጉብዝና የሚገናኝ አይደለም ' ብሎ የሚያምን፣ ለሕዝብ ሞት እውቅና የማይሰጥ ስርዓት ነው ያለው። " Q. መፍትሄው ምንድን ነው ? እናት ፓርቲ ፦ " የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ፣ ከፍተኛ መከፋት ውስጥ ወድቋል። እናም መንግሥት እሰጥ አገባውን አቁሞ ወደ ድርድር መምጣት አለበት።  ድርድሩ ደግሞ ቄስ፣ ሼይኽ በመላክ አይሆንም። ምክንያቱም ይሄ ስርዓት እንዲህ አይነት እሴቶችን የሚያከብር ይመስላል እንጂ አይቀበልም። የሚቀበለው ባለዶላር ፤ ባለዩሮዎችን ነው። ስለዚህ እነሱ በተገኙበት ለ “ ሸኔ ” እንደተደረገው ቁጭ ብሎ መነጋገሩ የተሻለ ነው። " Q. “ መርጦ አልቃሽ ናችሁ ” የሚል አስተያዬት ለፓርቲያችሁ ይሰጣል ፤ ለዚህ ምላሻችሁ ምንድን ነው ? " በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ትግራይ፣ በተለይ አማራ፣ በሃይማኖት ደግሞ ኦርቶዶክስ በፍጹም ታርጌት ተደርጎ ይገደላል። ይሄ ማለት ኦሮሞ ውስጥ ያለው ኦሮሞ አይገደልም ማለት አይደለም።  በእስልምናውም በክርትናውም ነባር በሆኑት ተደጋጋሚ ግድያ ይደረጋል። በዛ ምክንያት ሞቅ ብሎ ተሰምቶ ሊሆን ይችላል። ሞቅ ብሎ የተሰማው ግን በተግባር የተደረገ ነው። አልተደረገም ብሎ የሞገተን አካል የለም፤ ሊኖርም አይችልም፤ እውነት ነውና። " Q. እንደ ፓርቲ ደረሰብን የምትሉት ጫና ምንድን ነው ? እናት ፓርቲ ፦ " በአመራሮች ላይ እስራት እየተፈጸመ ነው። ለአብነትም የወልዲያና አካባቢው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ደርበው ከዋሽ አርባ በእስር እየማቀቀ ይገኛል።  ምርጫ ቦርድ የተሻለ ነበር በዘመነ ብርቱካን፤ አሁን ‘ለምን’ ብሎ የሚጠይቅ የለም። ስብሰባ መሰብሰብ፣ በአካል ማግኘት አይቻልም። ፓለቲካ ላይ መስራትን በእሳት እንደ መጫወት ነው ያደረገው ስርዓቱ። " Q. በቀጣይ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ ምን አይነት ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ? ለህዝብ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ እየተዘጋጃችሁ ነው ? እናት ፓርቲ ፦ " ዝግጅት እያደረግን ነው። እውነትም ምርጫ አለ ወይ ? የሚለው ጥያቄ በሁላችንም አዕምሮ የሚመላለስ ቢሆንም እያደር የምንገልጻቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። በምርጫ ተሳትፈን ማሸነፍ ነው በቸኛው አማራጫችን። " 📱 ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተከታታይ የሌሎች #በህጋዊ_መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን ሁሉ ሀሳብ ያቀርባል። በተለይም ፦ - ስለሀገራዊ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳይ ያላቸውን ግምገማ - ስለዜጎች የሰብዓዊ መብት ፣ - ስለብልሹ አሰራር - ስለኑሮ ሁኔታ - ስለቀጣዩ ምርጫ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ ስላላቸው ዝግጅት በዋነኝነት ያነሳል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
1230Loading...
13
Media files
1660Loading...
14
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸውን እቃዎች ከብዙ አማራጮች ጋር ከዮናታን ቢቲ ያገኛሉ ! የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር ! አድራሻችን ፦ 1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ) +251957868686 2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት +251995272727 3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ ሀያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ) +251993828282
1140Loading...
15
#Amhara ➡️ “ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ሞተዋል። በተለይ ሕፃናት ተርበዋል ” - ደባርቅ የሚገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች  ➡️ “ በድርቁም ችግር አለ፤ ተፈናቃዮች ላይም ችግር አለ ” - የሰሜን ጎንደር ዞን በ2013 ዓ/ም ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን ፤ ደባርቅ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች እርዳታ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ የምግብ እጥረት እንደተጋረጠባቸው፣ በዚህም የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ ሁኔታውን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል “ ኬንዳውን (መጠለያውን) አፈረሱብን። በየመስሪያ ቤቱ ብንገባም ተቀባይነት አጣን ” ብለዋል። “ የትግራይ ተፈናቃዮች በየመስሪያ ቤቱ፣ በየመስጂዱ (በተለይ ሕፃናት፣ ሕሙማን፣ እናት አባት የሞቱባቸው) ናቸው ” ያሉ ሲሆን “ ባይሆን ለእነርሱ እንኳን እርዷቸው ብለን እንኳ ብንለምን ‘ ምንም የለም፤ ለእናንተ አይሰጥም ’ አሉን ” ሲሉ አማረዋል። “ ሕዝቡ ግን ረሃብ ሞተ። በተለይ ሕፃናት ፣ መድኃኒት ተጠቃሚዎች። ከ2016 ዓ/ም መስከረም ወር ወዲህ 4 ሰዎች ሞተዋል። ከዚያ በፊት ደግሞ 3 ሰዎቸ ሞተዋል። በአጠቃላይ 7 ሰዎች ሞተዋል ” ነው ያሉት። መጠለያውን ያፈረሱት ግንባታ ሊገነቡበት እንደሆነ ፣ የተፈናቃዮቹ ብዛት 403 አባውራ፣ በአጠቃላይ ደግሞ 1,244 መሆናቸውን፣ የተፈናቀሉት በ2013 ዓ/ም እንደሆነ ፣ የተፈናቀሉት ከመቐለ ፣ ከዓዲግራት ፣ ሽረና ሌሎች የተለያዩ ቦታዎች እንደሆነም አስረድተዋል። “ እኛ እዚህ ተቀባይነትን ካጣን ሌላ ቦታ ተቀባይነት ካገኘን ዜግነታችንንም ቢሆን ቀይረን ፈርመን አብረን እንሄዳለን ተረካቢ ድርጅት ካገኘን ” እስከማለት የደረሱት እኚህ ተፈናቃዮች ይህን የወሰኑት የሚረዳቸው ስላጡ መሆኑን ገልጸዋል። የእለት ደራሽ ምግብ እርዳታ እንዲሰጣቸውም አጥብቀው ጠይቀዋል። በተፈናቃዮች በኩል ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቅናቸው አንድ የሰሜን ጎንደር ዞን ባለስልጣን፣ “ የክልሉ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ‘ከእኔ ውጪ መረጃ እንዳይሰጥ’ ብሎ በክልሉ መንግስት አሳውጇል። እኔማ እንዴት ብዬ ልስጥህ። ‘መረጃ በአንድ ማዕከል ይሁን’ ብለው አቅጣጫ ስለሰጡ ” ብለዋል። እኝሁ አካል “ በድርቁም ችግር አለ። ተፈናቃዮች ላይም ችግር አለ። የሰላም ተመላሽ ላይም ችግር አለ። ይህን ለማለት ግን እቸገራለሁ። መረጃ ሰጥተናል ለክልሉ መንግስት ” ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ° ለተናቃዮቹ ለምን እርዳታ አልተደገላቸውም ? ° መጠለያውስ ለምን ፈረሰ ? በማለት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተቢበሪያ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታን ጠይቋል። ጉዳዩን #ከፍተኛ_የመንግስት_አካላት እንደያዙት እና እሳቸው ማብራሪያ መስጠት እንደማችሉ ከመግለጽ ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። #TikvahEthopiaFamilyAA @tikvahethiopia
1520Loading...
16
#EARTHQUAKE " ብዙዎቻችን በህይወት እንተርፋለን ብለን አልጠበቅንም ነበር " - አቶ ኦይታ ኡኖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ትናንት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ36 ደቂቃ ላይ ነው የተከሰተው። ክስተቱ በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል " ወይጦ ድልድይ ፖሊስ ጣቢያ " አካባቢ መከሰቱን ጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ይህ መጠን (4.8) ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ የሚባል እንዳልሆነና " መካከለኛ " የሚል ደረጃ የሚሰጠው እንደሆነ ገልጿል። የሚያስከትለው ውድመት እና ጥፋት እንደ አካባቢው ቅርበት እንደሚወሰን ፤ ከተማ ውስጥ ቢፈጠር ብዙ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስረድቷል። " ወይጦ " የተባለው አካበቢ የሚገኝበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ ብራይሌ ታዳጊ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ኦይታ ኡኖ ትናንት ሌሊት የመሬት መንቀጥቀጥ ማጋጠሙን አረጋግጠዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ ሁለት ጊዜ መከሰቱን እና ክስተቱም አስደንጋጭ እንደነበር ገልጸዋል። " ብዙዎቻችን በህይወት እንተርፋለን ብለን አልጠበቅንም ነበር " ብለዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ካሉት ስድስት ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር ውስጥ በስድስቱ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ አረጋግጧል። እስካሁም መረጃ በተገኘባቸው መዋቅሮች ጉዳት አልተመዘገበም። አሪ ዞንም የመሬት መንቀጥቀጡ መሰማቱን የዞኑ የመንግስት አሳውቋል። ጂንካን ጨምሮ በአራት ወረዳዎች እና 2 የከተማ መስተዳድሮች ክስተቱ ማጋጠሙን አረጋግጧል። በሁሉም መዋቅሮች የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ጠቁሟል። ባለፈው ሳምንት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን በወረዳ ሁሉም መዋቅሮች 3 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበር። የትናንትናው የመሬት መንቀጥቀጥም እስከ ዳውሮ ድረስ መሰማቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው። @tikvahethiopia
940Loading...
17
“ 20 እናቶች በደም እጦት ሕይወታቸው አልፏል ” - ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ከ60 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሕዝቦች የሚገለገሉበት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ባጋጠመው ከፍተኛ የደም እጥረት ሳቢያ በተለይ እናቶች ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል። ላጋጠመው የደም እጥረት ምክንያቱ የደም ባንክ አለመኖር መሆኑን የገለጸው ሆስፒታሉ በዚህም ደም የሚሹ ታካሚዎች ለሕልፈተ ሕይወት እየተዳረጉ መሆኑን አስረድቷል። የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ኢያሱ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያና ለሌላ አንድ ሚዲያ በሰጡት ቃል ፣ “ በ6 ወራት ውስጥ በተከሰተው የደም እጦት ሳቢያ 20 እናቶች ሕይወታቸው አልፏል ” ብለዋል። የደም ባንክ እንዲቋቋም ሆስፒታሉ ለጤና ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ደም ባንኩን ማቋቋም እንዳልተቻለ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ከደም እጥረቱ ባሻገር በሆስፒታሉ በርካታ የወባ ታካሚዎች በመኖራቸው መጨናነቅ እንደፈጠረ፣ ሆስፒታሉ የምርመራ ግብአቶችን ጨምሮ የኦክስጂን እጥረት እንደፈተነው ተመላክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቃቸው አንድ የጤና ሚኒስቴር ፒአር ባለሙያ ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ፣ “ እኔ የፒአር ባለሙያ ነኝ የሚመለከተውን ነው እንጂ የማገናኝህ መልስ አልሰጥህም ” ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች የተቋሙ አካላት ለጊዜው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
1110Loading...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
10:08
Video unavailableShow in Telegram
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም ' ማለታቸው ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " ብለዋል። ከመንግስት ጋር በታንዛንያ የሰላም ንግግር ሲያደርጉ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) ተዋጊዎችን " በድርድር ተስፋ ሳትቆርጡ ፤ መተማመንን ለመገንባት ጥረት አድርጉ " ብለዋቸዋል። አሜሪካ ይህን ያለችው ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ በአምባሳደሯ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት ነው። በአዲስ አበባ ፤ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካን ግቢ በነበረ መርሀ ግብር የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር። Video Credit : US Embassy Addis Ababa / Ethiopia Insider @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል። በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም። ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል። የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል። ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty #TPLF ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል። ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል። ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል። ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል። " ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል። ከዚህ ባለፈ ፦ - " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። - ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል። - የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል። - ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል። - የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ #ProsperityParty #TPLF @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል። አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው። ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው።  ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው። የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው። ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። " Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና፦ " ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር። አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። " Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው። ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል።  ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው። የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል። አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። " Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ? ፕ/ር መራራ ጉዲና ፦ " በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው። መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ። አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም። Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል። መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል። መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። " Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ? ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦ " የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው። ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። " #TikvahEthiopiaFamilyAA #ቲክቫህኢትዮጵያ #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ? @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ከማረት ከተስረቁት 2 መኪኖች አንደኛዋ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ። ማሕበር ረድኤት ማሕበር (ማረት) በመጋቢት እና በያዝነው ግንቦት ወር አንድ ላንድክሩዘር V8 እና ላንድክሩዘር ማርክ 2 መኪናዎችን ተዘርፏል። የድርጅቱ ንብረት የሆነች በሰሌዳ ቁጥር 35 - 2723 የተመዘገበችው V8 መኪና መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተሰርቃ ሳትገኝ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታ ነበር። ይህች መኪና ሳትገኘ ከቀናት በፊት ላንድ ክሮዘር ማርክ 2 መኪና ተዘርፋለች።  ፓሊስ የድርጅቱ መኪኖች ያየና ያገኘ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ በያዝነው ሳምንት የተሰረቀችው ላንድክሩዘር ማርክ2 መኪና ከመቐለ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አክሱም ከተማ በፓሊስ ተይዛለች። የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ መኪናዋ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 በፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋልዋን አሳውቋል። ፖሊስ መኪናዋን ያገኘው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል ነው። በሰዓቱ መኪናዋን የያዛት ሹፌር ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ማክሸፉን አሳውቋል። ከነሹፌሩ በተጨማሪ " የኔ ንብረት ናት " የሚል አመልካችም በፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል። የአክሱም ከተማ ፖሊስ " መሰል ስርቆት ከጦርነቱ በኋላ መታየት የጀመረና በትግራይ ያልተለመደ ነው " ያለ ሲሆን " ማንኛውም ወንጀለኛ ከህዝብ አይንና ጀሮ መደበቅ አይችልም ብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ስለ መኪኖቹ ስርቆት ከማሕበር ረድኤት ትግራይ (ማረትረት) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።                                             @tikvahethiopia            
إظهار الكل...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
Photo unavailableShow in Telegram