cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

6 ማዕዘን

ወቅታዊ፣ ሀገራዊ፣ ታሪካዊ፣ አስተማሪ፣ አዝናኝ እና ቁምነገራዊ ጉዳዮች ብቻ የሚስተጋባበት ቻናል ነዉ። ✍ It is a channel where only current, national, historical, educational, entertaining and serious issues are echoed.

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
201
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
+330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ምንድነው? #Ethiopia | በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ፣ በጨቅላ ወሸፃናት እንዲሁም ታዳጊዎች ላይ የሚከሰት በጣም የተለመደ የቆዳ ሽፍታ ሲሆን ይህም ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከዳይፐር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የውጨኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲሆን በዋነኝነትም መቀመጫዎች፣ የታችኛው የሆድ ክፍል፣ ብልት አካባቢ እና የላይኛው ጭን አካባቢ ላይ በብዛት ይስተዋላል። በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) እነማን ላይ ይከሰታል? ዳይፐር dermatitis እድሜያቸው አንድ ሳምንት ከሞሉ ጨቅላ ህፃናት ጀምሮ ሚከሰት ቢሆንም, ነገር ግን ከፍተኛው የመከሰቱ አጋጣሚ እድሜያቸው ከ9 እስከ 12 ወራት ባሉ ህፃናት ላይ ይበልጥኑ ይስተዋላል። በተሰሩ ጥናቶች መሰረት ከአራት ልጆች መካከል አንዱ ላይ የሚከሰት ሲሆን በፐርሰንት ሲቀመጥ ስርጭቱ ከ7 እስከ 40 በመቶ ይደርሳል ይህም እንደ የዳይፐር አጠቃቀም፣ የሽንት ቤት ሥልጠና፣ የንጽህና አጠባበቅ እና የሕፃናት አስተዳደግ ልምምዶች ሊለያይ ይችላል። በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) ለምን ይከሰታል? 1) ከመጠን በላይ እርጥበት - በዳይፐር አካባቢ ውስጥ ያለው የእርጥበት መጠን መጨመር በዋነኝነት ሽንትን እና ሰገራን አምቆ ስለሚዝ ውስጣቸው ባለው ኬሚካል አማካኝነት የውጨኛውን የቆዳ ክፍል (stratum corneum)በመጉዳት ለሽፍታው ተጋላጭ ያደርጋል። 2) ፍትጊያ (Friction) - የውስጠኛውን የቆዳ ክፍል ተጋላጭ በማድረግ ከዳይፐሩ በሚኖራቸው ፍትጊያ ኬሚካሎቹ አልፈው በመግባት የቆዳ መቆጣትን ከማባባስ አልፎ ለኢንፌክሽን ተጋላጭ ያደርጋል። 3) የቆዳ ፒኤች መጨመር እና የቆዳ ማይክሮባዮም ለውጥ -ሽንት በራሱ አሲዳማ ስለሆነ ቆዳ ላይ ያለውን አሲድ ይበልጥ ከፍ በማድረግ በቆዳው ላይ የሚገኘውን ጠቃሚ ባክቴርያዎች በማጥፋት ጎጂ ለሆኑ ባክቴሪያዎች (S.Aureus, Strep.Pyogens, Candida Albican)፣ ተጋላጭ በማድረግ ችግሩን ያባብሱታል ። 4) አመጋገብ - ጡት የሚጠቡ ጨቅላ ህጻናት ፎርሙላ ከሚመገቡት ጨቅላዎች ባነሰ ለዳይፐር dermatitis ተጋላጭ ናቸው። 5) የቅርብ ጊዜ ተደጋጋሚ የአንቲባዮቲክ ሕክምና - በቅርብ ጊዜ ሰፋ ያሉ-ስፔክትረም ያላቸውን አንቲባዮቲኮችን መጠቀም ጨቅላ ሕፃናትን ለተቅማጥ እና የፈንገስ ኢንፌክሽን የመያዝ እድላቸውን በመጨመር ለዳይፐር dermatitis አጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል። 6) ዳይፐርን በጊዜው አለመቀየር 7) ለረጅም ጊዜ የቆየ የተቅማጥ ህመም በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) ምልክቶቹ ምንድናቸው? ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የውጨኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ይህም መቀመጫዎች፣ የታችኛው የሆድ ክፍል፣ ብልት አካባቢ እና የላይኛው ጭን ጨምሮ የሚታይ በጣም የቀላ (Intense Erythema), ሲዳሰስ ሸካራና ከቆዳ ከፋ ያለ (Macules and Papules) ፣እርስ በርሳቸዉ የተያያዙ ትናንሽ ዕብጠት (Coalesce plaques) አንዳንዴም ቅርፊት (Scaling) ሚመስል ነገር ሊኖራቸው ይችላል። ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር ተያይዞም ያለማቋረጥ ማልቀስ ፣ ምቾት ማጣት ፣ለማከክ መሞከር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ህክምናው ምንድነው? የዳይፐር dermatitis ህክምና በዋነኝነት አጠቃላይ የቆዳ እንክብካቤ, ዳይፐር ምርጫ, እና የውጨኛው የቆዳ ክፍል ላይ የሚቀቡ መድሀኒቶችን በዋናነት ይይዛል ፩ ዳይፐርን ቶሎ ቶሎ መቀየር - ዳይፐርን ቶሎ ቶሎ መቀየር ቆዳው ከሰገራ እና ከሽንት የሚኖረውን የተራዘመ ጊዜ በመቀነስ ዳይፐር dermatitis የመፈጠሩን ዕድል ይቀንሰዋል። ፪ ያለ ዳይፐር የእረፍት ጊዜያቶችን መስጠት - ዳይፐር dermatitis ያለበት ህጻን ያለ ዳይፐር የእረፍት ጊዜ (ለምሳሌ በቀን ጥቂት ሰዓታት) እንዲቆይ ማድረግ፣ ይህም ቆዳ በቀጥታ ለአየር እንዲጋለጥ ያስችላል። ፫ ቀስ ብሎ በለስላሳው ቦታውን ማጽዳት - የዳይፐር ቦታው ለብ ባለ ውሃ እና በትንሽ መጠን ወይም በፊዚዮሎጂክ ፒኤች ባላቸው ንፅህና መጠበቂያዎች መፀዳት አለበት. እንደ አማራጭ ከሽቶ-ነጻ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የህጻናት መጥረጊያዎች መጠቀም ይቻላል ነገር ግን በዚህ ወቅት ቆዳው ይበልጥ ሽፍ ካለ አለርጂክ ሊሆንባቸው ስለሚችል ቶሎ ማቆም ያስፈልጋል ፤ ከነዚህም መካከል እንደ methylisothiazolinone ያሉ መከላከያዎች የአለርጂ ንክኪ dermatitis ሊያስከትሉ ይችላሉ። ፬ ጎጂ ምርቶችን ማስወገድ -በተለምዶ ቦታው ላይ የሚደረጉ ከበቆሎ የሚሰሩ ግን ለሌላ ጥቅም የሚውሉ Poweders ለምሳሌ cornstarch or talcum powder ከፍተኛ የሆነ የመተንፈሻ አካል አደጋ ሊያመጡ ስለሚችሉ ባንጠቀም ይመከራል። ከነዚህም በተጨማሪ እንደ ቤኪንግ ሶዳ እና ቦሪ አሲድ ዱቄቶች Percutaneous Absorb ስለ ሚደረጉ ሌሎች አካላት ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ፭ የዳይፐር ምርጫ - በሕፃናት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው ከሁሉ የተሻለው የዳይፐር ምርጫ አከራካሪ ጉዳይ ነው.ነገር ግን የተራቀቀ የዳይፐር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሆን ዳይፐር (Disposables ) ዳይፐር dermatitis በሚታከምበት ጊዜ ብንጠቀማቸው ይመከራሉ ምክንያቱም ከፍተኛ የመምጠጥ አቅማቸው ቆዳውን ለሽንት እና ለኬሚካሎች የመጋለጥን ዕድልን ስለሚቀንስ ነው። ፮ ቆዳ ላይ ሚቀቡ መከላከያ ቅባቶች-ከቀላል እስከ መካከለኛ ለሆነ ዳይፐር dermatitis ክሬሞች እንዲሁም ቅባቶች እንደ መጀመሪያ ሕክምና ያገለግላሉ። እያንዳንዱን ዳይፐር በምንለውጥበት ወቅት እነዚህን ቅባቶች መጠቀም ይኖርብናል። እነዚህ መከላከያዎች በዋነኝነት ኬሚካሎቹ እንዲሁም እርጥበትን ከቆዳ ጋር እንዳይገናኙ ያደርጋሉ። ከነዚህ መከላከያዎች መካከል ፔትሮላተም፣ ዚንክ ኦክሳይድ ወይም ሁለቱንም ያካተቱ ይገኙበታል። አንዳንዶቹ ደግሞ ላኖሊን፣ ፓራፊን ወይም ዲሜቲክኮን (የሲሊኮን ዘይት) ይይዛሉ። Dr. Ephream Adane
إظهار الكل...
👍 1
በስኬት ተበቀሉ! አንዳንድ ጊዜያት አሉ። ሁሉም ሰው ፊቱን ያዞርባችኋል፣ ማንም የምታደርጉት ነገር አይጥመውም፣ ማንም ወድቀትን እንጂ ከፍታን አይመኝላችሁም፣ ልፋታችሁ ለማንም ትርጉም አይሰጥም። በእርግጥ ይሔ ጊዜ እጅጉን ልብ ሰባሪ ነው፣ ሁኔታው በጣም ያሳምማል። ነገር ግን ምንም እንኳን ህመሙ ቢበዛና ስቃዩ ቢደራረብም እውነታውን ተቀብሎ ወደፊት ከመጓዝ በቀር ሌላ አማራጭ አይኖርም። የተባለውን ሁሉ መስማት ስትጀምሩ የማትፈልጉትን ሰው መሆን ትጀምራላችሁ፣ ለእናንተ ህይወት ግድ የሌላቸውን ሰዎች መከተል ስትጀምሩ ለከባዱ ያለመፈለግ ስሜት እራሳችሁን ታጋልጣላችሁ። ከሁኔታዎች መማር ካልቻላችሁ በሁኔታዎች ውስጥ ተቀብራችሁ ትቀራላችሁ። የብዙዎች ትልቁ አጀንዳ የሰዎች እነርሱ ለሚያደርጉት ነገር የሚሰጡት ምላሽ ነው። ሰው ወደደው አልወደደው፣ ለሰው ተመቸው አልተመቸው እያሉ ብዙ ያስባሉ፣ ብዙ ይጨነቃሉ። አብዛኛው የሰው ልጅ በባህሪው ብዙ ሰው የወደደውን ነገር አለመውደድ አይችልም። በጅማሬው አትወደዱም በሒደቱ መሃል ግን ከእናንተ በማይተናነስ ሁኔታ የምትሰሩትን ስራ የሚወድላችሁ ሰው ታገኛላችሁ።  መናቃችሁን ተዓምር አታድርጉት፣ መገፋታችሁን አታካብዱት፣ በሰዎች መተቸትንና መጠላታችሁን እንደ ትልቅ ዱብዳ አትቁጠሩት። የተደረገባችሁን የትኛውንም አሉታዊ ተፅዕኖ በስኬት ተበቀሉት፣ አንገት ያስደፋችሁን ንግግር ቀና በማለት እንዳሸነፋችሁት ማሳየት መልካም ነው፣ በናቋችሁ ፊት ክብራችሁን ጨምራችሁ፣ በሸሿችሁ ፊት ዋጋችሁን ጨምራችሁ፣ ለተቃወሟችሁ ልካችሁን በሚገባ ገልጣችሁ ተገኙ፣ በስኬት ተበቀሉ። ምንም ጥቅም እንደሌላችሁና እንኳን ለሰው መትረፍ ይቅርና ለእራሳችሁም ብቁ እንዳልሆናችሁ ደጋግመው ከሚናገግሯችሁ ሰዎች ጋር ብዙ የቃላት ግብግብ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ነገሮችንም ብዙ ማወሳሰብና ይበልጥ ልብ ሰባሪ ማድረግ አያሻም። ይሔንን ወሳኝ ነገር ብቻ ማድረግ ተገቢ ነው። ስሜታችሁን በመቆጣጠር፣ ውስጣችሁን አዳምጡ፣ በተወረወሩባችሁ የጥላቻና የንቀት ድንጋዮች የማይበገር ጠንካራ ማንነትን ገንቡበት፣ እራሳችሁን በንቃት ጠብቁ። ልዩ ሀሳብ እንዳላችሁ የምታምኑ ከሆነና የመረጣችሁት መንገድ ለሰው አይን እንደሚያጋልጣችሁ ካወቃችሁ አስቀድማችሁ ለማይመቸው ጉዟችሁ ተዘጋጁ። መርዛቸውን ረጭተው ሊያሽመደምዷችሁ ከሚፈልጉ ሰዎች ዞር በሉ። ! የማይረባ ትርፍ ቃላትን በመናገር ክብርንና ተደማጭነትን ለማግኘት አትሞክር። የመረጡትን ህይወት ለመኖር የዋህነትም ሆነ አብዝቶ ለሰዎች ስሜት መጨነቅ አያስፈልግም። በህይወትህ አንድ አስገራሚ ነገር እንዲፈጠር ከፈለክ አላማህን ለማሳካት ያለህን ቆራጥነት ለሁሉም ሰው ማሳየት ይኖርብሃላል። የምትኖረው የራስህን ህይወት ነው፣ የሰው ልጅ ለውድቀትህ ምክንያት ቢሆን እራስህን ቀና የምታደርገው እራስህ ነህ። በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ላለማግኘት ዝግጁ መሆን፣ ተቀባይነቱ እስኪመጣ ድረስ ደጋግሞ መጠየቅ፣ ደጋግሞ መሞከርና ሳያቋርጡ እስከመጨረሻው መጓዝ ጠንካራ ልብ ይጠይቃል፣ የተለየ ሰው መሆንን ይፈልጋል። ማንም ሰው ሀሳብህን እንዲደግፍ አትፈልግ፣ ማንም ሰው በህልምህ እንዲደነቅ አትጠብቅ። ለማስደነቅም ሆነ ለማስገርም የሀሳብህን ወደ ምድር መውረድ መቻል የሚያሳይ ፍንጭ ስጠው፣ ማንም ባያምንበት፣ ለእርሱ እውንነት ማንም ከጎንህ ባይቆም አንተ ብቻህን እውን ልታደርገው ዝግጁ እንደሆንክ በተግባር አሳይ። የማይገባ ባህሪ ባሳዩህ ሰዎች ላይ መናደድ አቁም፣ ይልቅ ያ ባህሪ የሚገባው ላንተ እንዳልሆነ ከፍታህን ጨምረህ፣ እራስህን አሻሽለህና ስኬትን ተጎናፅፈህ ማሳየቱ የአሸናፊነት ድልን ያጎናጽፍሃል ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 @Sixangles @fastsix
إظهار الكل...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
የወጋየሁ ንጋቱ 81ኛ ዓመት የልደት በዓል እየታሰበ ነው #Ethiopia | የስመ ጥሩው ተዋናይ የወጋየሁ ንጋቱ 81ኛ ዓመት የልደት ቀን ግንቦት 28 2016 ይታሰባል ። በተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ሀሣብ አመንጪነት በማህበራዊ ድረ ገፅ እና በልዩ ልዩ የመገናኛ አውታሮች ቀኑ የሚታሰብ ሲሆን የወጋየሁ ንጋቱ ታሪክም በአጫጭሩ ተደርጎ ከምሥል ጋር ታጅቦ ይቀርባል ። ተዋናይ ወጋየሁ በበርካታ ቴአትሮች ላይ ከመተወኑ ባሻገር ፍቅር እስከ መቃብር ልቦለድን በሬድዮ በመተረክም ይታወቃል። ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የወጋየሁን የግል ማስታወሻ ደብተሮች እና ምስሎች እንዲሁም የተወነባቸውን ቴአትሮች የሚያሳዩ የቪዲዮ ሊንኮችን ያሰባሰበ ሲሆን ስብስቦቹም በልደቱ ቀን ለዕይታ ይቀርባሉ ። ተወዳጅ ሚድያ የሀገር ባለውለታ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የልደት ቀንን እያሰበ በማህበራዊ ድረ ገፅ ንቅናቄ ከጀመረ 7 ዓመቱ ነው።
إظهار الكل...
ተግባራዊ ሊደረግ ነው‼️ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው‼️ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ለመተግበር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል። በዚህ ወቅት አስፈጻሚ አካላት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት እንደሚኖርባቸው የአዲሰ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ አዋጁ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና አስተዳደር የተረጋጋ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የአከራይና የተከራዮችን ጥቅምና መብቶችን ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስፈጸም እንደሚረዳ ተገልጿል። መንግስት የነዋሪውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በርካታ የልማት አመራጮችን ሲፈጽም ቆይቷል ያሉት ሃላፊው፥ የግል ቤቶች ያልተገመተ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር አዋጁ የተከራይና የአከራይ መብቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እንዲመራ ያስፈልጋል ብለዋል። በመሆኑም አስፈጻሚ አካላት አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። @Sixangles @fastsix
إظهار الكل...
👍 3👎 1
ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (ኤዲኤችዲ) (Attention Deficit hyperactivity Disorder)-ADHD ************ ኤዲኤችዲ ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው። አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡ ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡ የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች  አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው  በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ  የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ  የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው  በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ  ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው  በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ ላይ ለመውጣት የሚታገሉ  እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው  ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት የሚመስላቸው  በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡ ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል ። ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት(Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡ ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡ መልእክቱ ለሁሉም እንዲደርስ #Share ያድርጉት በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386 በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ)
إظهار الكل...
ዶ/ር ዮናስ ላቀው(DrYonasLakew)

ያለ አእምሮ ጤና፤ጤና የለም!!!!

አንድ አባት ለገዳምቸው እርዳታ ለመሰብስብ አስበው መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፍ ሌላ በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸውን ኩራዝ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ ይዘዋል አንድ ቀን ምሽት እኚህ አባት ደከማቸውና ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያም እርዳታም ቢጠይቁም መንደርተኛው ሁሉ ፍቃደኛ አልሆነም ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጎድጓዳ ቦታ ያገኙና እዚያ ውስጥ ገብተው አደሩ ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ቀንዲላቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው። ለመተኛት ጋደም እንዳሉ አውሬ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን በላባቸው። ጠዋትም ተመሰገን ብለው መንደርተኛውን ተሰናብተው ሊሄዱ ሲሉ አንድም ሰው አጡ ለካንስ በዚያህ ምሽት ዘራፊ ሽፍቶች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ነበር ያደሩት እሳቸውም በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ፋኖሱንም ነፋስ ባያጠፋው ኖሮ የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውም አውሬ ባይበላው ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር። ወደጆቼ እኚህ ለነፍሳቸው በመድከም ስለእኔ ስለእናንተ ብሄር ሀይማኖት ሳይመርጡ ስለሀገር ቀን ከሌለት እያነቡ የሚይፀልዩ የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ገዳም ያሉ አባቶች ዛሬም የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው ከአውራዊት እና ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብ ይዘዋል። ወንጌል የሚወዱ ፍለጋ ሳይሰደዱ ፣ እናት ቤተክርስቲያን ለዘመናት የጠበቀቻቸውን ልጆቿን ሳታጣ አለሁልሽ እንበላት ልጅነታችን ታድያ ለመቼ ሊሆን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ትጣራለች ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለተጨማሪ መረጃ:- የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444 በመደወል ድጋፍ ማድረግ ይቻላል፡፡
إظهار الكل...
😢 2
"ባህታዊ ቤት አልሰራም አለ ለአፈር ሰው ለአፈር ሰው እያለ"
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢኦተቤ ፈተናዎች በዝተውብኛል አለች‼️ #Ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ *** ቅዱስ ፓትርያርኩ ግንቦት 21 ቀን 2016 በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተናገሩት 👉ለተጨማሪ መረጃዎች join us& invite to others👇👇👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
إظهار الكل...
😢 3