cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

SOZO YOUTH

ብ.እ.ት [ ብቸኝነት » እጮኝነት » ትዳር ] » YOUTUBE [ SUBSCIBE ] [ https://www.youtube.com/channel/UCKPvVauc9ByQSxrWRu-fNnQ ] » TIKTOK ⬇️ [ FOLLOW ] [ https://vm.tiktok.com/ZSHdkv89/ ] For comment: @inbox_sozo P.O.BOX 387 /1033 ADDIS ABABA

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
7 825
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በወጣቶች የሚነሱ ጥያቄዎች በሚል እርስ ብሩስ እና ካሮል ብሪትን ተፅፎ በአለማየሁ ማሞ የተተረጎመው መፀሀፍ በወጣቶች ተዘውትረው የሚነሱ ርዕሶችን ስለትዳር ፣ ስለትጭጭት(ፍቅር) ፣ ቅድመ-ጋብቻ ግብረ-ስጋ ግኑኝነት ፣ እንዲሁም የብዙ ወጣቶች ጥያቄዎችና ከክርትያናዊ መልሶቻቸው ጋር ይዞ ቀርቧል ፣ ትማሩበታላችሁ። አንቡት! ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
በወጣቶች የሚነሱ ጥያቄዎች-1.pdf4.89 MB
👍 20 7
ኢየሱስ-አዳኝ! “ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” — ማቴዎስ 1፥21       ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
SOZO YOUTH

ብ.እ.ት [ ብቸኝነት » እጮኝነት » ትዳር ] » YOUTUBE [ SUBSCIBE ] [

https://www.youtube.com/channel/UCKPvVauc9ByQSxrWRu-fNnQ

] » TIKTOK ⬇️ [ FOLLOW ] [

https://vm.tiktok.com/ZSHdkv89/

] For comment: @inbox_sozo P.O.BOX 387 /1033 ADDIS ABABA

6
📖በእግዚአብሔር ወይስ በሰው እንታመን? ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ " እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል። " - ኤር17፥5-8                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
SOZO YOUTH

ብ.እ.ት [ ብቸኝነት » እጮኝነት » ትዳር ] » YOUTUBE [ SUBSCIBE ] [

https://www.youtube.com/channel/UCKPvVauc9ByQSxrWRu-fNnQ

] » TIKTOK ⬇️ [ FOLLOW ] [

https://vm.tiktok.com/ZSHdkv89/

] For comment: @inbox_sozo P.O.BOX 387 /1033 ADDIS ABABA

25👍 19
ለፍቅር ያሰብኩት የቸርች ሰው ጎዳኝ 》ሰላም ቤተሰቦቼ ዛሬ ይዤ የመጣሁት ርዕስ ከብዙ ክርስቲያን እህቶች እና ወንድሞች በተደጋጋሚ የሚደርሰኝ ጥያቄ ነው። ትንሽ ለማመን ቢከብድም ብዙ ክርስቲያን ወጣቶች ልባቸው የሚጎዳው አብሯቸው ከሚያመልኩ ወጣት አቻቸው ጋር ሊጀምሩ ባሰቡት የፍቅር ግንኙነት ነው። የፍቅር ጥያቄ አቅርበው እምቢ የሚባሉ እንዳሉ ሆነው እሺ ተብለው የፍቅር ግንኙነት የጀመሩ ወጣቶች በጣም በሚገርም ሁኔታ በማማረር እና በከባድ ፈተና ያሳልፋሉ።[ሁሉም ባይሆኑ አብዛኛዎቹ ማለት ነው] 》አንድ አመት ሙሉ እጮኛሽ ነኝ ብሎ አብሯት ቆይቶ ስለ ሰርግ እና አንዳንድ ነገሮች ማውራት እና ማቀድ ከጀመሩ በኋላ ግንገት በነጋታው "ግንኙነታችን እዚህ ጋር ይብቃ" ብሎ ጥሏት የሚሄድ ሰው ቸርች ውስጥ አለ።[ሁሉም እንዲህ አይነት ባህርይ አላቸው እያልኩ አይደለም።] 》ሌላው በጣም ያስተዋልኩት ነገር ከየቸርቹ[ሙሉወንጌል፣ቃለህይወት፣ህይወት ብርሀን፣መሰረተክርስቶስ. . .] አንዳንድ ወንድ ይዛ/ይዞ ፍቅረኛዬ ነው የሚል ሰው ቸርች ውስጥ አለ።[ይታያችሁ ይህ ሰው የአንድነት ፕሮግራም ሊያዘጋጅ ነው ወይስ ትዳር ሊመሰርት?] 》ምን እያልኩ እንደሆነ በዚህ ምክንያት የተጎዳችሁ በደንብ ይገባችኋል ብዬ አስባለሁ። እና በቸርች ልጅ ተጎዳችሁ ማለት ሁሉም የቸርች ልጅ እንደዛ መጥፎ ይሆናል ማለት አይደለም።  ስለዚህ ለምን ከዚህ ሁሉ አንደኛዬን ክርስቲያን ካልሆነ ሰው ጋር ግንኙነት አልጀምርም እነሱ እንደሆኑ እንክብካቤውን እና ማፍቀሩን ተክነውበታል የሚል አቋም ላይ ከመድረሳችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁን ነገር ልነግራችሁ እወዳለሁ። 1. ትክክል አይደለም በሉ 》በምታመልኩበት ቸርች ውስጥ የተጎዳችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም ልክ እንደ እናንተ በተመሳሳይ ሁኔታ ብሎም በተመሳሳይ ሰው የሚጎዱ እንደሚኖሩ አትርሱ። ስለዚህ ዝም ማለቱ አማራጭ ስለማይሆን ስለጉዳዩ በደንብ ብትጮኹ መልካም ነው ወይም ለምታምኑት ወጣት መሪዎች በዚህ ጉዳይ ግንዛቤ እንዲሰጡ፣ ሆን ብለው ከግንኙነት ወደ ግንኙነት የሚዘሉ ወጣቶችን ቸርች እንድታስጠነቅቅ እና ይዛ እንድትመክራቸው አሳውቁ። [ይህ ሀሳቤ ይቀልዳል እንዴ ሊያስብል ይችላል። ግን እመኑኝ ሞክሩት አውቃለው አንዳንድ ቦታ ወጣት መሪዎች ናቸው ጎጂዎቹ።] 2. ምሬታችሁን ለጌታ አሳውቁ 》መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት በቆዩበት ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን የላከላቸው እንዴት ይመስላችኋል? በምሬት ወደ እግዚአብሔር መጮኸ ሲጀምሩ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ በቁጥቋጦው ውስጥ ተገልጦ "የህዝቤን ጩኸት ሰምቻለው" ነበር ያለው። ስለዚህ ተጎድታችሁ ዝም ማለቱ ተገቢ አይደለምና ምሬታችሁን ለእግዚአብሔር አሰሙ።[እንደሰው ስላልሆነ ባልጠበቃችሁት መንገድ ያክማችኋል።] 》ደግሞ ሰይጣን በበቀል እንድትነሱ እና ሰው እንድትጎዱ ሊያሳስባችሁ ይችላል። ይህን ጊዜ በቀል የእናንተ ሳይሆን የእግዚአብሔር እንደሆነ አውቃችሁ ለእርሱ አሳልፋችሁ መስጠት መልካም ነው። 3. ብቁ ማንነት አትጠብቁ 》ቀጥሎ ወደ ህይወታችሁ የሚመጣው ሰው መልዐክ እንዲሆን አትጠብቁ። ሰው ነው እና አንዳንድ ጉድለቶች ይኖሩታል። አንዳንዴ ታዲያ ይህን ጉድለቱን ስታዪ ሊጎዳኝ ነው የመጣው እያልሽ መጥፎ ሀሳብ ወደ ውስጥሽ ካስተናገድሽ በጣም ልትጎጂ ትችያለሽ። ስለዚህ በጎ በሆነ አመለካከት ራሳችሁን አስታጥቁ።                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
| #ከእንቅልፋችን_እንንቃ | " ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" (ሮሜ  13:11 )  》ከእንቅልፍ እንንቃ ሲባል ባጭሩ እንቅልፍ አራት ደረጃዎች እንዳሉት ሳይንሳዊ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር በማየት የኛን ሁኔታ ስንመለከት:-                                            ደረጃ_1: አይን መጨፈን የሚጀመርበት 》ንቁ ሆነን ስናከናውናቸው የነበሩ ነገሮችን ማከናወን የምናቆምበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ጊዜ በቀላሉ ለመንቃት የሚቻልበት ደረጃ የመሆኑን ያህል በፍጥነት ወደ ቀጣዩ እንቅልፍ ደረጃ የሚታለፍበት በመሆኑ ብዙ በዚህ ደረጃ የመቆየት እድል የለውም፡፡ ይህን ከመንፈሳዊ እንቅልፍ አንጻር ስናየው በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ አማኝ ቀደም ሲል  በንቃት የሚጸልየውን ጸሎት  በፍቅር ለእግዚአብሄር የሚያቀርበውን አምልኮ እንዲሁም በመሰጠት ያነበው የነበረውን የእግዚአብሄር ቃል  ለማንበብ ሃይል የሚያጣበት እና በሃጢያት ላይ ማመቻመች የሚጀምርበት ደረጃ ነው፡፡ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?( ገላ.3፡1 )   ደረጃ_2: ቀላል እንቅልፍ 》 በዚህ ደረጃ አይንን ከመጨፈን ባለፈ ወደ ቀላል እንቅልፍ የሚገባበት ደረጃ ሲሆን በዚህም የልብ ምት እና ሰውነት ሙቀት የሚቀንስበት ወቅት ሲሆን በዚህም ሰውነታችን ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ለመግባት ዝግጅት የሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ልባችን ለክርስቶስ የነበረውን መቃጠል (ፍቅር) የሚያጣበት እና ያለን መንፈሳዊ መነቃቃት የሚቀዘቅዝበት ደረጃ ነው፡፡ …የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና። እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፡፡ (ራእ.2፡4-5)                                                   ደረጃ_3_እና_4: ከባድ እንቅልፍ 》 በዚህ ወቅት ሰውነታችን ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የሚገባበት በመሆኑ በዙሪችን እየተከናወኑ ያሉ ነገሮችን ማስተዋል አንችልም፡፡ ንቁ በሆንበት ጊዜ የሚታዘዙን ጡንቻዎቻችን ፓራላይዝድ የሚሆኑበት የእንቅልፍ ደረጃ ነው፡፡ በዚህ የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ከመንፈሳዊ አለም ያለን ቁርኝት የሚቋረጥበት እና ለመንፈሳዊ ነገር ባዳ የምንሆንበት ይልቁንም ስንጸየፋቸው የነበሩ አለማዊ ልምምዶች  ምንም እንዳለሆኑ ተቆጥረው በቤተ ክርስቲያን ስፍራ የሚይዙበት ፣ ከአለም ጋር መዳቀልና መቀላቀል የተለመደ የሚሆንበት ደረጃ ነው፡፡ ወገኞች ሆይ በየትኛውም የመንፈሳዊ የእንቅልፍ ደረጃ  ላይ እንገኝ ያው እንቅልፍ ላይ በመሆናችን እንንቃ እንመለስ! ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ (ሮሜ.13፡11)                 ✍ አገልጋይ Alex መልካም ምሽት!                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
SOZO YOUTH

ብ.እ.ት [ ብቸኝነት » እጮኝነት » ትዳር ] » YOUTUBE [ SUBSCIBE ] [

https://www.youtube.com/channel/UCKPvVauc9ByQSxrWRu-fNnQ

] » TIKTOK ⬇️ [ FOLLOW ] [

https://vm.tiktok.com/ZSHdkv89/

] For comment: @inbox_sozo P.O.BOX 387 /1033 ADDIS ABABA

ትዕዛዝ ቢጤ ለወንድሞች 》ከፍቅር አጋርህ ጋር ያለህ ቅርርብ መልካም እንዲሆን እነዚህን የፍቅር ዘዴ ለአጋርክ አሳይ!! 1: እንድትለወጥ በምትነግራት ጊዜ ሁሉ የምትጠቀምባቸውን ቃላት ለስለስና ይቅር ባይነት የሞላባቸው መሆናቸውን አረጋግጥ:: °°° እጮኛህ ቁጣ በተሞላባቸው ቃላት ከጮህክባት አትለወጥም:: "እጮኛዬ አይወደኝም::" በማለት ራሷን ታሳምናለች:: እንዴት ልትለወጥ እንደምትችልና የተሻለች የፍቅር አጋር እንደምትሆን ልታስብ አትፈልግም:: በዛ ፈንታ ታለቅሳለች ወይም መልሳ ትጮህብሀለች:: 》ቃሎችህ ለስለስና ይቅር ባይነት የሞላባቸው ከሆኑ ግን ፍቅርህ ይሰማታልና ለመለወጥ ዝግጁ ትሆናለች:: " የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች    ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች። " (መጽሐፈ ምሳሌ 15:1) 2: ለመናገር ቁጣህ እስኪበርድ ጠብቅ:: ለምሳሌ የሆነ ነገር ተነጋግራቹ በተባባላቹበት ጊዜ አላከናወነችውም እንበል:: ወዲያው ስለሁኔታው እንደሰማክ አትናገራት:: እንዴት መለወጥ እንዳለባት ልትነግራት ይህ ጥሩ ጊዜ አይደለም:: ቁጣህ እስኪበርድ ድረስ ጠብቅ ተቆጥተህ እያለህ ብትናገር ቃሎችህ ለስላሳና ይቅርታን የተሞሉ ሊሆኑ አይችሉም:: 3: በምትናገርበት ጊዜ "አንቺ" እንዲህ አደረግሽ ወዘተ... ከማለት "ይሰማኛል" በል:: 》ቀጥሎ በዚህ መንገድ እንዴት እንደምትናገር የሚያሳይ ምሳሌዎች ተጠቀም:: 》 "በተቀጣጠርንበት ቦታ በጊዜ አትገኚም(ትቀርያለሽ) ምክንያቱም ትዝ አልልሽም::" ከማለት ይልቅ በመጀመርያ አንተ ራስህ ቀጠሮ አክባሪ ሁን ከዛ  " በተቀጣጠርንበት ቦታ በጊዜ ስትገኚ ለእኔ ያለሽ ፍቅር እና ክብር ትልቅ እንደሆነ ይሰማኛል::" ብትል መልካም ነው:: 》 "እኔን ስታናግሪ ትህትና የለሽም ምክንያቱም አስተዳደግሽ ልክ ያልሆነ ጋጠወጥ እና ባለጌ ነሽ:: "አትበል ይህ ነቀፋ ነው:: ይህ ይጎዳታል እንጂ እንድትለወጥ አያደርጋትም:: በዚህ ምትክ  " ረጋ ብለሽ ስታወሪኝ እና ነገሮችን ሰከን ባለ መንገድ ስታስረጂኝ እጅግ እንደምታፈቅሪኝ እና ለእኔ ያለሽን መልካም ስሜት የሚያሳይ ይመስለኛል::" ብትል እጅግ የተሻለ ነው::            ጌታ ዘመናቹን ይባርክ!!!            ፍቅራቹ ያለገደብ ይባረክ!!                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
ድንግልናዬን መጠበቅ ያለብኝ ለምንድን ነው? ••• ከፅሑፉ በፊት እስቲ የአንዳንድ ሰው የግል አመለካከት ምን እንደሚመስል እንመልከት። “ከየአቅጣጫው የሚመጣው ተጽዕኖ ‘የፆታ ግንኙነት ምን እንደሚመስል ሞክሬ ባየው’ ብዬ እንዳስብ ያደርገኛል።”​—ኬሊ “የፆታ ግንኙነት ሳልፈጽም እስካሁን መቆየቴ ያሳፍረኛል።”​—ጆርደን “ዘንድሮም ድንግል ነሽ?” ••• እንዲህ ያለው ጥያቄ ሽምቅቅ እንድትዪ ያደርግሽ ይሆናል። በብዙ ቦታዎች አንዲት ወጣት ድንግል ከሆነች ችግር እንዳለባት ተደርጋ ትታያለች። ከዚህ አንጻር በርካታ ወጣቶች ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያሉ የፆታ ግንኙነት እየፈፀሙ ነው። ፍላጎታችሁና እኩዮቻችሁ የሚያሳድሩባችሁ ተጽዕኖ ••• ክርስቲያን ከሆንሽ መጽሐፍ ቅዱስ ‘ከዝሙት እንድትርቂ’ የሚሰጠውን ማሳሰቢያ ታውቂያለሽ።        [ 1 ተሰሎንቄ 4:3 ] ••• ያም ሆኖ የፆታ ስሜትሽን መቆጣጠር አስቸጋሪ ሊሆንብሽ ይችላል። ••• አንድ ወጣት እንዲህ ሲል በግልጽ ተናግሯል፦ “አንዳንድ ጊዜ ከፆታ ግንኙነት ጋር የተያያዙ ሐሳቦች ያለ ምንም ምክንያት ወይም ሳልፈልግ ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ።” አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ ያለው ስሜት በተፈጥሮ ያለ ነገር ነው። ••• ይሁንና ድንግል በመሆንሽ ጓደኞችሽ ነጋ ጠባ የሚያሾፉብሽና የሚነዘንዙሽ ከሆነ ሁኔታው ከባድ ነው። ለምሳሌ፣ √ አንድን ወጣት እኩዮቹ ‘የፆታ ግንኙነት የማትፈጽም ከሆነማ ወንድ ነኝ አትበል’ የሚሉት ቢሆንስ? √  አሊያም ደግሞ አንዲትን ወጣት ጓደኞቿ ‘የፆታ ግንኙነት ካልፈጸምሽ ምኑን ሴት ሆንሽው’ ቢሏትስ? ••• ሔርመን እንዲህ ብላለች፦ “እኩዮቻችሁ የፆታ ግንኙነት መፈጸም የሚያስደስትና ሁሉም ሰው የሚያደርገው ነገር እንደሆነ ይናገራሉ። ከዚህም ከዚያም ጋር ካልተኛችሁ ከሰው የተለያችሁ እንደሆናችሁ አድርገው ይቆጥሯችኋል።” ••• ይሁንና ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት ከመፈጸም ጋር በተያያዘ እኩዮችሽ የሚደብቁሽ ነገር አለ። ለምሳሌ ያህል፣ ••• ከወንድ ጓደኛዋ ጋር የፆታ ግንኙነት የፈጸመች ማሪያ የተባለች አንዲት ወጣት እንዲህ በማለት ታስታውሳለች፦ “ድርጊቱን ከፈጸምኩ በኋላ በኀፍረትና በጥፋተኝነት ስሜት ተዋጥኩ። ራሴን ጠላሁት፤ የወንድ ጓደኛዬንም ጨርሶ ላየው አልፈለግኩም።” ••• አብዛኞቹ ወጣቶች ባያውቁትም እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት መፈጸም ብዙውን ጊዜ የስሜት ሥቃይ የሚያስከትል ከመሆኑም ሌላ አስከፊ መዘዞች አሉት! ይቀጥላል. . .                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
ጥቂት ሰው እንፈልጋለን! ••• በተዘጋጀ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሀሳብ መስጠት እና በማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ በውስጥ መስመር @inbox_sozo ላይ አሳውቁን። [ፕሮግራሙ የቪዲዮ ቀረፃ ስለሚኖረው ለጊዜው አ.አ ለሆናችሁ ቅድሚያ እንሰጣለን።]                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
ምን አይነት ወንድ ለመሆን ታስባለክ?               》እግዚአብሔር ለአብርሀምም የወደፊት ህይወቱን በተለያየ መንገድ ሲገልፅለትና ሲያሳየው ነበር:: ከምንም በላይ አብርሀም ሁሉን ነገር ትቶ እግዚአብሔር ወደተናገረው ስፍራ ጨርቄን ማቄን ሳይል ወቷል:: 》እግዚአብሔር በህይወትህ ይሆናል የሚልክ ነገር ልክ እንደ አብርሀም ቢዘገይብህ ምን አይነት አባት የምትሆን ይመስልሀል? 》አብርሀም ከአምላኩ ጋር እለት እለት ይነጋገር እና ይፀልይ ነበር:: በዚህ ፀሎት ስፍራው ከእግዚአብሔር ጋር የማይቋረጥ ህብረት ያደርግ ነበር:: ከእግዚአብሔር ብዙ ትዕዛዝ ተቀብሏል:: እግዚአብሔር የሚስቱን ስም የአብርሀምን ስም ቀይሯል በአጠቃላይ ቤተሰቡን ከመሀንነት እና ፍሬ ከሌለው ማንነት አንስቶ ለብዙዎች አባትና ፍሬያማ አድርጓቸዋል:: ወደፊት ምን አይነት አባት መሆን ትፈልጋለህ? 》ይስሀቅም እንደ አባቱ አብርሀም የፀሎት ህይወት ነበረው:: እለት እለት ከእግዜአብሔር ትዕዛዝን ይቀበል ነበር::በዛ የፀሎት ስፍራ አምላክ ይስሀቅን እና ቤተሰቡን ጎብኝቷል:: 》ይስሀቅ ታጋሽ ነበር:: ልጅ ለመውለድ ዘግይታ ለነበረችው ሚስቱ ከምንም በላይ ክብርና ትልቅ ፍቅር ነበረው:: አንዳች መጥፎ ነገር አልተናገራትም:: ከሌላ ሰው እንድትወልድ አልመከራትም:: አላንቋሸሻትም:: አልፈታትም:: ወደ ሌላ ሴት አልሔደም:: ነገር ግን በእግዜአብሔር ቃል ላይ ታምኖ በፅናት ይጠብቅ ነበር:: እግዜአብሔር የሰጣችሁ ተስፋ ሲዘገይ ምን ታደርጋላችሁ? 》ይስሀቅ አብዝቶ ወደ እግዜአብሔር ይቀርብ ነበር::                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...
ድንግል አላገባም 》ይህ አባባል አሁን አሁን ብዙ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ እና ሰይጣን ብዙዎችን ሊያስት የሚጠቀምበት ዘዴ ሆኗል። ለዚህም በብዙዎች ዘንድ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን አስቀምጧል። ከምክንያቶቹም መሀል ● ለወንዶች "ድንግል የሆነች ሴት ስለ ሩጋቤ-ስጋ ምንም እውቀት ስለማይኖራት ስትጋቡ በጣም ትቸገራላቹ" ● ለሴቶች ደግሞ "እስካሁን ድንግል ነሽ? ምን ነክቶሽ ነው ወደፊት ከምታገቢው ሰው ጋር የመጀመርያ ምሽትሽ በስቃይ የተሞላ እንዲሆን ትፈልጊያለሽ?በይ ተሸክመሽ ከምትዞሪ ቶሎ አስወግጂው።" °°°እነዚህን እና ሌሎችን እዚህ ግባ የማይባሉ ምክንያቶችን ያቀርባል። 》በጣም ማስተዋል ያለብን እነዚህን ሀሳቦች ራሱ ሰይጣን አካል ለብሶ አይናገራችሁም። ይህን ሀሳቡን አውቀው ይሁን ሳያውቁ በተለያየ መንገድ የሚያራምዱ ሰዎች አሉ። ስለዚህ ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ራሳችንን መጠበቁ እጅግ መልካም ነው። እስከ ጫጉላ ጊዜ ድረስ ንፅህናችንን ጠብቀን ራሳችንን ለትክክለኛው ሰው እንጠብቅ። አስተውሉ ድንግልና ብዙዎች እንደሚሉት የማያስፈልግ ነገር ቢሆን አምላክ ባልፈጠረው ነበር። ይልቁን ትልቅ ሚስጢር ያለው ነው። 》መፅሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን እንደ ንፅህት ክብሯን ጠብቃ ባሏን እንደምትጠባበቅ ሴት ይመስላል። እንደዚህ አይነት ክብራችሁን እንድትጥሉ ከሚያደርጓችሁ አይነት ሰዎች ፈፅሞ ራቁ። እስካሁን ይህን ውሸት ሰብኳችሁ ከሆነ ሁለተኛ እድል አትስጧቸው። □ አትሳቱ! ለሁሉም ጊዜ አለው። ••• በዙሪያችሁ ያሉ ጓደኞቻችሁ ይህን ተግባር(sex) ከማውራት አልፎ በየቀኑ ሊፈፅሙት ይችላሉ ያ ማለት እያደረጉ ያሉት ነገር ልክ ነው ማለት አይደለም። በእነሱ ደግሞ ትቀናላችሁ ብዬ አላስብም። እውነት ለመናገር በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው የሄዱ ወጣት ሴትና ወንዶች ይህን በማድረግ ተወጥረው ይሆናል ግን ማስተዋል ያለባችሁ በወጥመዳቸው መያዝ እንደሌለባችሁ ነው። ከምንም በላይ አላማችንን መዘንጋት የለብንም። በወደቀ ሞራል ተመርቆ መውጣት ቀሪውን ህይወታችንን ጭምር በተጨማለቀ ህይወት ያደርገናልና ተጠንቅቀን እንጓዝ። 》ብዙ ጊዜ ወድቀን ሊሆን ይችላል ማወቅ ያለብን ግን መነሳት እንዳለ ነው። ስጋ ለባሾች ነን በአንድም በሌላም የተሳሳተ ውሳኔ ወስነን ይሆናል ነገር ግን በስህተታችን ጎዳና ጉዟችንን መቀጠል የለብንም። ፃዲቅ ሰባቴ ቢወድቅ ሰባቴ ይነሳልና በሀጢያታችን ምክንያት ከቤቱ ከመራቅ ይልቅ በንስሀ ወደ እግሩ ስር መመለሱ እጅግ የብልህ ሰው ውሳኔ ነውና ጌታ ይርዳን!!                  ✅ ይቀላቀሉን ⤵️ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖     [ https://t.me/sozo_purity ]
إظهار الكل...