cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው። «السلفية منهجي» https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

إظهار المزيد
Ethiopia5 876لم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
2 568
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-67 أيام
-4230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

⠀ ⠀ الله أكبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله والله أكبر الله أكبر  ولله الحمد ⠀⠀
إظهار الكل...
وعليكم السلام ورحمة الله وبركاته 🌹تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🌹
إظهار الكل...
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته عيدكم مبارك تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን ‼
إظهار الكل...
🌴የረመዷን ልዩ  መልዕክት🌴           ቁ/15 ☄አማናን ያለመጠበቅ መዘዞች        ሀሙስ ረመዷን 18/1445ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ          ⬇ ⬇ ⬇ ⬇ 🔎  https://tinyurl.com/2bg44mc3       🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegrgam.me/ahmedadem ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
إظهار الكل...
የተራዊሕና ተሃጁድ አሰጋጆች ሆይ፥ 🔹ለሰዎች የአላህን ቃል ማሰማትና የቁርኣንን መልዕክት ማድረስ መቻል ትልቅ ዕድልና ጸጋ መሆኑን አውቃችሁ በስራችሁ ተደሰቱ፤ ስራን አላህ ዘንድ ዋጋ ከሚያሳጡ ተግባራትና ኒያዎችም ተጠንቀቁ። ♦️ከኋላችሁ ካሉ ሰጋጆች (ደካማ መኽሉቆች) ይልቅ ከፊታችሁ ያለውን ኀያሉን አላህን እያሰባችሁ አሰግዱ። የማንንም አድናቆት አትከጅሉ፣ የማንንም ወቀሳ አትፍሩ። ♦️የቁርኣን ንባብ ላይ ድምጻችሁን ስታሳምሩ ኒያችሁን ቀድማችሁ አሳምሩ። ድምጹ ሲያምር እንዲባልለት ፈልጎ ድምጹን የሚያሳምር ሰው የጀሀነም ማገዶ ይሆናል! ይልቅ የአላህን ቃል ባማረ ድምጽ ቀርቶ ሰዎች ይበልጥ የጌታቸውን ንግግር እንዲሰሙና እንዲመከሩበት ማሰብና መነየት ነው የሚገባው። በቁርኣን ድምጽን በማሳመር ክብርና ዝና መፈለግ፣ ድምጽን የሚያሳምሩትን ያክል ስራና ስነምግባርን አለማሳመር ውጤቱ ነገ አላህ ዘንድ መክሰርና እያደረ ሰዎች ዘንድም ከክብር በኋላ መዋረድ፣ ከመወደድ በኋላ መጠላት ነው የሚሆነው:: ♦️ የምታነቡትን ቁርኣን ተፍሲሩን ለማወቅ ጥረት አድርጉ፤ ሙሉ አቅሙ እንኳ ባይኖራችሁ አጫጭር የተፍሲር መጽሐፍትን አንብቡ፣ በሚገባችሁ ቋንቋ የተዘጋጁ ተፍሲሮችን አዳምጡ። ልብ የሚገሰጸው የሚነበበውን ሲረዳ ነውና። ከኋላችሁ ያሉ ሰጋጆችም ቀድሞ በሚያነበው አንቀጽ ከተገሰጸ ሰው አንደብት የሚወጣ ንባብ ይበልጥ ይገስጻቸዋል። ♦️ቀን ላይ በቂ ዝግጅት ማድረግን በመተው በተደጋጋሚ ትልልቅ ስህተቶችን መሳሳት የተሰጠን አደራ በአግባቡ አለመወጣት ከመሆኑም ባሻገር ሰጋጆች የልብ መረጋጋትን እንዲያጡ ያደርጋል። ይህ እንዳይሆን ቀን ላይ በቂ ዝግጅት አድርጉ። ይህን ከማድረጋችሁም ጋር ቁርኣን አሸናፊ ነውና ከተሳሳታችሁ ቆም ብላችሁ ለሚያርማችሁ ሰው ዕድል ስጡ! መሳሳት ነውር አይደለምና። ይሳሳታል ላለመባል እየጣራችሁና እየደጋገማችሁ ሰዓት አታባክኑ! ♦️አትዋሹ! ሳል ሳይኖር ሲሳሳቱ ማሳልና ያልተሳሳቱ ለመምሰል መሞከር ተገቢ አይደልም! ♦️የሰላትና የአስጋጅነትን ህግጋት ጠንቅቃችሁ እወቁ። ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮችን፣ የሰላት መስፈርትና ማዕዘናትን፣ ከኢማም የሚጠበቁ ነገሮችን ሳያውቁ ቁርኣን በቃል ስለሸመደዱ፣ ወይም ጥሩ ድምጽ ስላለ ብቻ ወደ ሚሕራብ መግባት (አሰጋጅ መሆን) ትልቅ ስህተት ነው። ኢማም ከኋላው ተከትለው በሚሰግዱ ሰዎች ሰላት መበላሸት ወይም መጉደል አላህ ዘንድ እንደሚጠየቅ ጠንቅቃችሁ እወቁ። ♦️ሚዛናዊ ሁኑ፤ ሩጫም ይሁን ዝግመት፣ ድምጽ ማነስም ይሁን መብዛት ሳይኖር  (በይነ ዛለኪ) የሆነ አካሄድ ሂዱ። አላህ ያግዛችሁ፤ ስራችሁንም ወዶ ይቀበላችሁ። ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረመዳን 16/ 1445ዓ.ሂ 💥 በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት   ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኘት 🌐https://t.me/zad_qirat ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
إظهار الكل...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

💫አንድ የሸሪዓ እውቀት ተማሪ (ጧሊበል- ዒልም) ሊላበሳቸው ከሚገቡ ስብዕናዎች መሐከል💫 - ኒይ'ያን ማስተካከል - ጊዜን በአግባቡ መጠቀም - እውቀት በመፈለግ ላይ መታገስ - የሚማሩትን ትምህርት መሸምደድ እና መከለስ - አስተማሪን ማክበር - ተራ ክርክርን መራቅ - መስከን፣ መረጋጋት እና መተናነስ - ባወቀው መስራት https://t.me/AbuUweis
إظهار الكل...
ጾምና ሙቀት 🔅ሙቀት በበረታበት ጊዜ እየተቸገሩ መጾም ምንዳን ከፍ ያደርጋል። ደጋግ የአላህ ባሮች ዱኒያ ላይ መቆየትን እንዲመኙና እንዲወዱ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከልም አንዱ ጾም በሚከብድበት ጊዜና ቦታ ላይ ችግሩን ተቋቁሞ መጾም ነው። 🔅አቡ አድ'ደርዳእ رضي اللہ عنہ "በሙቀት ጊዜ (በረሃ ውስጥ) ጥምን ተቋቁሜ መጾም፤ የሌሊት ሰላት ላይ የሚደረግ ሱጁድና እውቀትን አዋቂዎች ዘንድ ተንበርክኮ መማር ባይኖር ኖሮ ዱኒያ ላይ መቆየትን አልፈልግም ነበር" ሲሉ፤ ታላቁ ሰሓቢይ ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ رضي اللہ عنہ ደግሞ ምን ትመኛለህ ተብለው ሲጠየቁ "በጋ ላይ መጾም፤ በአላህ መንገድ እየታገልኩ ጠላትን በሰይፍ መምታትና እንግዳን በክብር ማስተናገድ " ብለዋል። 🔅ስለዚህ የዘንድሮ ጾም የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሙቀት በበረታበት ወቅት ላይ መሆኑ ይበልጥ ሊያስደስተን ይገባል። 🔅ከመሆኑም ጋር የሙቀትን ድካም የሚያቀንሱ ነገሮችን ማድረግ ይፈቀዳል። ለምሳሌ፥ በማንኛውም ሰዓት ገላን በቀዝቃዛ ውኃ መታጠብ፣ ፊት እና ጸጉር ላይ ውኃ ማፍሰስ፣ አፍን በውኃ መጉመጥመጥና መልሶ መትፋት፣ ከጸሐይ መሸሽ፣ አናትና ደረት ላይ የረጠበ ፎጣ ማስቀመጥ ወዘተ። 💥 የዱኒያው ቀላል ሙቀት የጀሀነሙን ከባድ ግለት አስታውሷቸው ከርሱ የሚድኑበትን መልካም ስራ ለመስራት ደፋ ቀና ከሚሉ ባሮች አላህ ያድርገን! 🔅ማታ ማታ ተራዊሕ ላይም ሙቀት አልችልም ብሎ ሰላት ትቶ ከመሄድ ይልቅ ታግሶና የጀሀነምን ግለት እያስታወሱ አላህን ከጀሀነም ጠብቀኝ ብሎ መማጸን በላጭና ብልሕነት ነው። ✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ረመዷን 10/1445 ዓ.ሂ @ዛዱል መዓድ   🔹🔸🔹🔸🔹🔸 💥 በተጨማሪም የተለያዩ       ትምህርቶችን ለማግኘት   ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ የኪታብ ደርሶችን ብቻ ለማግኘት 🌐https://t.me/zad_qirat ~~~~ 🔗https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
إظهار الكل...
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ!! አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱለሂ ወበረካቱህ የዲን መምህር፣ የኢስላም ወንድማቻን ኡስታዝ ሰላሓዲን ሻፊ ሐሰን ባደረበት  የኩላሊት ሕመም ምክንያት ቁርአንና የዲን ትምህርት ከሚያስተምርበት መስጂድ እና መድረሳ ርቆ ከ4 አመት በላይ ከሆስፒታል  ሆስፒታል በመዘዋወር እየተንከራተተ የኩላሊት እጥበት በማድረግ ላይ ይገኛል። የእጥበቱ ወጪ  ጎዳና ላይ በሚደረግ የእርዳታ ጥሪ ሲሸፈን የቆየ ሲሆን ይህ ሂደት ሕይወቱን ለማስቀጠል ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑ ወደ ውጭ ሐገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ–ተከላ ሕክምና በማድረግ ሕይወቱን ማትረፍ እንደሚችል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሐኪሞች ቦርድ ተወያይቶ ባቀረበው ምክረ–ሐሳብ  መሰረት አስፈላጊ ምርመራዎችን በሙሉ ጨርሶ በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው Acibadem "አኪባደም"  አንጋፋው አለም–አቀፍ ሆስፒታል፤ ታካሚው  የተጠየቀውን ገንዘብ የሚከፍል ከሆነ ሙሉ ሕክምናውን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በደብዳቤ ገልፇል። የጳውሎስ ሆስፒታል ቦርድ በይፋዊ ማስታወቂያ እንደገለፀው ታካሚ ሰላሀዲን  ይህንን የህክምና ሂደት በአንድ ወር ውስጥ ብቻ መጨረስ እንዳለበት እና ይህ ካልሆነ ግን እድሉ ለሌላ ታካሚዎች ይተላለፋል። ሆኖም ወንድማችን ኩላሊት የሚያጋራው በጎ ፈቃደኛ  ወንድም ቤኖረውም ከሀገረ ቱርክ የተጠየቀውን የጎዞ እና ማረፊያ ወጪ ሳያካትት ጠቅላላ የሕክምና ወጪ (22,500 USD) የአሜሪካን ዶላር ወይንም የኢትዮጲያ 1,350,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሀምሳ ሺህ) ብር ማግኘት ግን ለእርሱም ሆነ ለቤተሰቦቹ ከአቅም በላይ ሆኗል። ይህንን ለማሳካት ከአላህ ቀጥሎ የሁሉም ሙስሊም እርዳታ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ሁላችሁም የአላህን ምንዳ ጀነቱን ለማግኘት ስትሉ ኡስታዛችን እድሉ ሳያመልጠው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ  ሕይወቱን ለመታደግ ሰበብ ሁኑልን ስንል በአላህ ስም እንማፀናለን። ማሳሰቢያ ሕክምናውን አስመልክቶ መረጃውን ማጣራት የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተጠቀሱት አድርሻዎች በኩል ታካሚውንም ሆነ ቤተሰቦቹን ማግኘት እንደሚችል በትህትና እንገልፃለን። ሰላሀዲን ሻፊ ሀሰን 0926441317                      ንግድ ባንክ 1000430058375
إظهار الكل...