cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

በዚኽ ቻናል ጽሑፍ የሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
11 246
المشتركون
+3924 ساعات
+2537 أيام
+92930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ጥያቄ? ብፁዕ ማለት ምን ማለት ነው? ጳጳስ ለምን ብፁዕ ይባላል?
إظهار الكل...
የኦሲኤን ቴሌቪዥን እውነታዎች ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምሥረታ ጋር የቤተክርስቲያን መዋቅር ለማፍረስ በመናፍቃንና ፖለቲከኞች እርዳታ የተመሠረተ ነው። ከስምምነቱ በኋላ + ከኢኦቲሲ ቲቪ ጋር በአንድ ቦርድና በአንድ ሥራ አስኪያጅ እንዲመራ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የወሰነው በቋሚ ሲኖዶስ ተሽሮ በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን ሥር እንዲሆን ተደርጓል። + ለተቋሙ 8 ሚሊዩን ብር በጀት  የተለቀቀ ሲሆን ገንዘቡ በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን አንቀሳቃሽነት ያለ ምንም ሰነድ ሲባክን ቆይቷል። + ኦሲኤን 2 ካሜራ አንድ ኮምፒዩተር የተመዘገበ ሀብት ያለው እና 2 ካሜራ ማን 1 ኤዲተር 2 ጋዜጠኞች አንድ ዳይሬክተር በድምሩ 6 ሠራተኞች ቢኖሩትም ከ50 በላይ የቀድሞ የኦሮምያ ቤተክህነት ደጋፊዎች እና የቀሲስ በላይ ዘመዶች የቤት ሠራተኞችና ጥበቃ ማይቀር በሠራተኝነት ተመዝግበው ያለ ፔሮል ደመወዝ በጥሬ ገንዘብ ከባንክ ዝውውር ውጪ በስማቸው ወጪ ሲደረግ ቆይቷል። +ከኢኦቲሲ ጋር ሲዋሀድ በቋሚነት ትቀጠራላችሁ በሚል ብዙዎች ስማቸው ብቻ ተመዝግቦ ደመወዝ ሣይከፈላቸው እንደ ሠራተኛ እንዲመዘገቡ ተደርጓል። + ከጠቅላም ቤተክህነት የተሠጠው የሥራ ቦታ ለፓርኪንግና ስቶር በማከራየት ገቢው ለሊቀ አእላፍ በላይ ሲቀበል ቆይቷል። + ቴሌቪዥን ጣቢያው ከስብከት እና መግለጫ ውጪ አንድም መደበኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የለውም + ቴሌቪዥን ጣቢያው ባሉት ሁለት ካሜራዎች ቅዳሜና እሑድ የሠርግ ቀረጻ ሥራ በማከናወን ሠራተኞች የግል ቢዝነስ ይሠሩበታል። በአጠቃላይ ተቋሙ የግል እንጂ የቤተክርስቲያን ያልሆነ ሠራተኞቹ የተባሉትም ከሙያው ጋር የማይገናኙ የበላይ መኮንን ዘመዳ ዘመዶች ናቸዉ። + ቋሚ ሲኖዶስ አጣሪ በመድብም ቄስ በላይ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይጣራ ቀርቷል ይኸው አጀንዳ ሲኖዶሱ የሚወያይበት ይሆናል ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እውነታውን እንዲያውቁ ቢደረግ።
إظهار الكل...
👍 15🤔 2👎 1
ሲኖዶስ ሲኖዶስ ማለት ጉባኤ፣ አንድነት፣ ኅብረት፣ ማለት ነው፡፡ “አሐተኔ፣ ርክብ” የሲኖዶስ ተለዋጭ ቃላት ናቸው፡፡ ርክበ ካህናት የሚለውን ርክበ ጳጳሳት በማለት ሲኖዶስ ጋር በትርጉም ይመሳሰላል።  ይኹን እንጂ ርክበ ካህናት ሲባል ጳጳሳትን ብቻ የሚወክል ሳይሆን ካህናት የወል መጠሪያ ቢሆንም  ትርጉሙን ለጳጳሳት ብቻ ተሰጥቷል።  በሕገ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜው ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት፡- “ቅዱስ ፓትርያርክ፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚገኙበት ዐቢይ ጉባኤ ሆኖ ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ሕግ አውጪና ወሳኝ አካል ነው”። (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 2. 2)፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ደግሞ ሲኖዶስ (ጽርእ) ግሪክኛ መኾኑን ጠቅሰው “ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ ዩጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር እከባ ስብስብ) መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ (ገጽ 875)  ቅዱስ ሲኖዶስ “ብሂል (ትርጉም) ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የጽርዕ (የግሪክ) ሆኖ ትርጉሙ ዐቢይ ጉባዔ ጳጳሳት ወይም የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ጉባኤ ማለት ነው።  (Synod's Ecclesiastical Assembly) አቡነ መልከ ጴዴቅ (ሊቀ ሥልጣናት ሃብተ ማርያም ወርቅነህ) ያልታተመ ጽሑፍ። (ገጽ 1) ብሂል (ትርጉም) ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የጽርዕ (የግሪክ) ሆኖ ትርጉሙ ዐቢይ ጉባዔ ጳጳሳት ወይም የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ১৭৭ ১৯৮ ১৫: (Synod's Ecclesiastical Assembly) ሲኖዶስን ቅዱስ ያሰኘው የተሰበሰበት ዓላማና የቤተ ክርስቲያን በየበላይ መዋቅር መኾኑ ነው።  ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የአንድነት መገለጫ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ የሐዋርያት መንበር ወራሽ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን ኅብረታዊትና ጉባኤያዊት መሆን ማሳያ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት አስፋፊዎች እንጂ የመንደር ተወካዮች ስብስብ ማለት አይደለም።  አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ትውፊት እና አስተዳደር በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የሚመክሩበት ጉባኤ ነው።  የቅዱስ ሲኖዶስ አጀማመር በሐዋርያት ዘመን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተነሣው ጥያቄ ወይም ችግርን ለመፍታት በተደረገ ጉባዔ ነው።  ይኽውም ቤተክርስቲያን ከይሁዲነት ወደ ክርስትና ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና በመጡ አማኞች መካከል የባሕል ልዩነት ስለነበር ይኽንን መከፋፈል ለማስቀረት የተደረገ ጉባዔ ነው። በአራቱም መአዘን ለአገልግሎት ተበትነው የነበሩ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም መንበር በነበረው አረጋዊው ቅዱስ ያዕቆብ መሪነት በ50 ዓ.ም ሐዋርያት ከያሉበት መጥተው ጉባዔ አደረጉ።  “አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።” ሐዋ.15:1 በዚኽ ጥያቄ መሠረት “ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።” በማለት ስለመጀመሪያው ጉባኤ (ሲኖዶስ) ይነግረናል። ሐዋ.15:6 ከሐዋርያት ቀጥሎ የተነሡ ሐዋርያነ አበው በአብያተ ክርስቲያናት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ይሠበሰቡ ነበር። ሲኖዶስን የፈጠረው ችግር መኖር ነው። ችግሮችን ለመፍታት ነው።  የቅዱስ ሲኖዶስ ዋነኛ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የአንድነቷ መገለጫ ነው፡፡ በየጊዜው በሚወለዱ ክስተቶች ዶግማዊ ቀኖናዋ ሥርዓቷ ትውፊቷ እንዲሁም አስተዳዳሯ እንዳይፈታ መጠበቂያ ነው፡፡ በዚህም በመሠረት እምነቷ ላይ ጥያቄ ሲነሣ ማብራሪያ መስጠት አዳዲስ አስተምህሮዎች ሲመጡ በዶግማዊ መሠረት ማረቅ ማቅናት የጾም የጾሎት ሥርዓትን መሥራት ልጆቿን የሚመሩ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መሾም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋነኛ ተግባራት ናቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባርና ኃላፊነት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነቶች መካከል፡:-  ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት ይመራል፤ ይጠብቃል፡፡ ሕጎችንና ደንቦችን ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ይሽራል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አጠቃላይ የምጣኔ ሀብትና የሙዓለ ንዋይ አስተዳደር ደንቦችን ያወጣል፡፡ ዓመታዊውን የቤተ ክርስቲያን በጀት ያጸድቃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን  አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲሁም የተቋማትን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል፡፡ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በማስፋፋት ምእመናን እንዲበዙ ያደርጋል፤ የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያስተምራል ያስፋፋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትንና የሚኖራትን ግንኙነት ከሃይማኖትና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር እየገመገመ ያስፋፋል ያጠናክራል፡፡ (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17) መ/ር ንዋይ ካሳሁን
إظهار الكل...
👍 7
30:35
Video unavailableShow in Telegram
Crews battling fire at historic St. Theodosius Orthodox Cathedral in Cleveland
إظهار الكل...
መቶ ዓመት ያስቆጠረው በኦሃዮ ግዛት ክሊቪላንድ Cleveland የራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሊመርጠ የ30 ቀን ጾም አውጀዋል። ሦስት እጩዎች ቀርበዋል። ምርጫው የዩክሬን ኦርቶዶክስ መገንጠልን ተከትሎ ፓለቱካዊ ጫና እንዳለ ገልጸው እመቤታችን ትረዳቸው ዘንድ ነው ሱባኤ የያዙት። ኦርቶዶክሳውያን በዓለም ደረጃ በሁሉም ሀገር ራሽያን ሳይጨምር ከፍተኛ ውጥረት ላይ ናቸው።
إظهار الكل...
38👍 4
"ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ" ሉቃ.22:31
إظهار الكل...
👍 14 8