cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ተዋህዶ ነው እምነቴ

ተዋህዶ እምነታችን     #ድንግል_እናታችን አንድዬ አባታችን     #ኢትዮጵያ_ሀገራችን ኦርቶዶክስነቴ      #አርማ_ምልክቴ አሜን ነው የኔ ቃል   #እግዚአብሄር_ያውቃል 🙏 https://telegram.me/ortodox_youth any Comment @Alador_Astu_15 ለመቀላቀል ከስር ሰማያዊውን ይጫኑ https://t.me/joinchat/AAAAAEMa9Loe1nISP8O-ew

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
1 287
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

T የወራት ስያሜ ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ የሚከተለውን ይመልከቱ፡፡ ፩. የወሩ ስም - መስከረም የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሴ እና ከረም ትርጉም - መሴ-አለፈ ፣ ክረምቱ መሸ፤ ከረም- ክረምት፤ ክረምት አለፈ። ፪. የወሩ ስም - ጥቅምት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ጠቀመ ትርጉም - ሠራ፤ ጠቃሚ ጊዜ። ፫. የወሩ ስም - ኅዳር የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀደረ ትርጉም - አደረ-ሰው በወርኃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል። ፬. የወሩ ስም - ታኅሳስ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀሠሠ ትርጉም - መረመረ- በመኸር ወቅት የሰብል ምርመራን ያመለክታል ፤ ሰብዐ ሰገል በታኅሳስ ወር የተወለደውን ጌታችንን ማሰሳቸውን ፣ መፈለጋቸውንም ያመለክታል። ፭. የወሩ ስም - ጥር የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ነጠረ ፣ አጥረየ ትርጉም - ነጠረ - ጠረረ- ብልጭ አለ፤ ነጻ፤ የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል ፤ አጥረየ - ገዛ (ከብቱም ምርቱም የሚሸጥበት የሚገዛበት ወቅት) ፮. የወሩ ስም - የካቲት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ከተተ ፣ ከቲት ትርጉም - መክተቻ (እኅልን ወደ ጎተራ) ፯. የወሩ ስም - መጋቢት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መገበ ትርጉም - በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት) ፰. የወሩ ስም - ሚያዝያ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሐዘ ትርጉም - ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሠርግ መሆኑን ሲያጠይቅ) ፱. የወሩ ስም - ግንቦት የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ገነበ ትርጉም - ገነባ፤ ሠራ፤ ቆፈረ፤ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል) ፲. የወሩ ስም - ሰኔ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሰነየ ትርጉም - አማረ (አዝርዕቱ) ፲፩. የወሩ ስም - ሐምሌ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሐመለ ትርጉም - ለመለመ ፣ ሐመልማል ሆነ ፣ ለቀመ (ለጎመን) ፲፪. የወሩ ስም - ነሐሴ የግእዝ ሥርወ ቃሉ - አናሕስየ ትርጉም - አቀለለ፤ ተወ (የክረምቱን እያደር መቅለልን ያሳያል) ፲፫. የወሩ ስም - ጳጉሜ/ን ሥርወ ቃሉ - ኤጳጉሚኖስ (ግሪክ) ትርጉም - ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ 📌 የኢትዮጵያ የዓመቱ ወራት ሥፍረ ሰዓት በቤተክርስቲያናችን ፩. መስከረም .. የቀኑ ርዝመት ..12 የሌሊቱ ርዝመት ..12 ፪. ጥቅምት ..የቀኑ ርዝመት ..11 የሌሊቱ ርዝመት ..13 ፫. ህዳር ..የቀኑ ርዝመት ..10 የሌሊቱ ርዝመት ..14 ፬. ታህሣሥ ..የቀኑ ርዝመት .. 09 የሌሊቱ ርዝመት ..15 ፭. ጥር ...የቀኑ ርዝመት ..10 የሌሊቱ ርዝመት ..14 ፮. የካቲት .. የቀኑ ርዝመት ..11 የሌሊቱ ርዝመት..13 ፯. መጋቢት.. የቀኑ ርዝመት..12 የሌሊቱ ርዝመት..12 ፰. ሚያዝያ.. የቀኑ ርዝመት.. 13 የሌሊቱ ርዝመት ..11 ፱. ግንቦት .. የቀኑ ርዝመት ..14 የሌሊቱ ርዝመት ..10 ፲. ሰኔ .. የቀኑ ርዝመት ..15 የሌሊቱ ርዝመት ..09 ፲፩. ሐምሌ .. የቀኑ ርዝመት ..14 የሌሊቱ ርዝመት ..10 ፲፪. ነሐሴ .. የቀኑ ርዝመት ..13 የሌሊቱ ርዝመት ..11 📌ምንጭ 📚 መዝሙረ ማኅሌት ወቅዳሴ (በመምህር አፈወርቅ ተክሌ የቅኔ መምህር)፤ 📚ኅብረ አትዮጵያ (ዲያቆን ቴዎድሮስ በየነ 1999 ዓ.ም)፤ 📚ከሊቃውንት አስተምህሮ @ortodox_youth @ortodox_youth
إظهار الكل...
✥ #አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ ✥ ✥በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው :- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ✥በሃይማኖት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ከጠየቃችሁኝ አንደኛው ትሕትና ሲሆን ሁለተኛውም ትሕትና ነው:: ሦስተኛው ደግሞ ትሕትና ነው :- #ቅዱስ_አውግስጢኖስ ✥ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር:- #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ✥ሰዎች ወደ ተራሮች ከፍታ ይወጣሉ ወደ ኃይለኛው የባሕር ሞገድና ወደ ውቅያኖስ ስፍሐት ይቀዝፋሉ : የከዋክብትን ክበባዊ ዑደት ያደንቃሉ [ግሩምና ድንቅ የሆኖ የተፈጠረ] ሰውነታቸውን ግን ሳያደንቁ ያልፉታል:: #ቅዱስ_አውግስጢኖስ ✥"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ ክርስቲያን ሆኜ ልኑር ክርስቲያን ሆኜ ልሙት ዳግም ልትፈርድ ስትመጣም ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ" #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ✥የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን✥ @tewahedo_new_emenete @tewahedo_new_emenete
إظهار الكل...
ዘመቻ 1 ። ይህን ምስል profile picture በማድረግ ድርጊቱን ለአለም ማሳወቅ ። facebook Telegram Instagram Viber ... በሁሉም ላይ መለጠፍ። ቢያንስ ለ 15 የኦርቶዶክስ አማኝ መልክቱን እናዳርሰው ። #ኦርቶዶክስ_የኔ_ናት ! @tewahedo_new_emenete
إظهار الكل...
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 " ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ፡፡ " 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌿🌿🌿🌿 እንኳን ለምንናፍቃት ጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም አደረሳችሁ፡፡ 🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂 ጾሙን የበረከት፣ የምህረት እና የአንድነት ያደርግልን፥ መዓቱን በምህረት ይለውጥልን ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ በፀሎታችሁ አስቡኝ፡፡ 🌺መልካም ጾም🌺
إظهار الكل...
ሐዋርያትም ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በሱባኤው መጨረሻ በነሐሴ አሥራ ስድስት ቀን ጌታችን ጸሎታቸውን ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ /ረዳት/ ቄስ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬሰናይ /ዋና/ ዲያቆን አድርጐ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያናችንም ሥርዓት ሠርታ ከሰባቱ ዓበይት አጽዋማትተርታ አስገብታ ይህን ታላቅ የበረከትና የምሥጢር መግለጫ ጾም እንድንጾም አድርጋናለች፡፡ ሐዋርያት ያዩትን ድንቅ ምሥጢርየእመቤታችንን ትንሳኤና ዕርገት ለማየትና ከሐዋርያት አበው በረከትለመሳተፍ ጌታችን “ልጆቼ” ይላቸው ለነበሩ ሐዋርያት አምሳል ሕፃናትና ወጣቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ አረጋውያንም የጻመ ፍልሰታን መድረስ በናፍቆት እየጠበቁ በየዓመቱ በጾም በጸሎት ያሳልፉታል፡፡ የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት መታሰቢያ /በጾመ ፍልሰታ/ ወቅት ብዙዎች ከቤታቸው ተለይተው በመቃብር ቤት ዘግተው፣ አልጋና ምንጣፍትተው፣ በመሬት ላይ ተኝተው ዝግን ጥሬ እፍኝ ውኃ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት በመትጋት በታላቅ ተጋድሎ ይሰነብታሉ፡፡ በሰሙነ ፍልሰታም እመናን ለእመቤታችን ያላቸውን ጽኑና ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩበት ነው፡፡ ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው፣ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ እርሷም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጅዋ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷንትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ” ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡ ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን- አሜን ፡፡ ሁሉም እንዲያውቅ ሼር የበረከት ፆም ያርግልን ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† @tewahedo_new_emenete @tewahedo_new_emenete
إظهار الكل...
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ ፍልሰታ ማለት ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ከአንድ ቦታወደ ሌላ ቦታ ማዛወር የነበሩበትን ሀገር ለቆ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ መፍለስማለት ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሲባልም የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደገነት መፍለስን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱንለማመልከት የሚነገር ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራበሞት ከተለየች በኋላ እንደ አንድ ልጅዋ ሞታ መነሣቷንና ዕርገቷን ያዩዘንድ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 16 የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታከሰባቱ ዐበይት አጽዋማት አንዱ ሆኖ በቀኖና እንዲጾም ከተወሰነበት ጊዜጀምሮ ምእመናን ይጾሙታል፡፡ እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እምሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረውመሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባልወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረእግዚአብሔር ሆናለች፡፡ እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ12 ዓመት፣ መድኃኔዓለምን በማህጸንዋ ጸንሳ ዘተኝ ወር ፤ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከዮሐንስ ወልደነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናትጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ ነቢያት አስቀድመው ስለ እመቤታችን እረፍትና ትንሳኤ በምሥጢርተናግረዋል፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር /መዝ 136¸8/ “አቤቱ ወደ ዕረፍትህተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” ብሎአል፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ ሲል ነው፡፡ ይህም እመቤታችን እንደ ልጅዋትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው፡፡ ታቦት ያላትም ማደሪያውስለሆነች ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምትአለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜደረሰ የቀረ… ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ ወይኖችም አበቡመዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ” ሲል ስለእመቤታችን በምሳሌ ተናግሮአል፡፡ /መኃ 2¸1ዐ-13/ ወዳጁን ውበቱን ተነሺ ነይ እያለ የተጣራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ተጠሪዋም እመቤታችን ናት፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ማለት በስደትበአይሁድ የዘወትር ጠላትነት በልጅዋ መከራና ስቅላት ስምዖን በቤተመቅደስ እንደተናገረ ልቧ በሀዘን ሠይፍ የተከፈለበት በሀዘን ፍላጻየተወጋበት የመከራ ክረምት /ወቅት/ አልፎ የክርስቶስ ሕማሙ ፣ ሞቱ፣ቤዛነቱ ተፈጽሟል፡፡ ትንሣኤው በምድር ላይ ተገልጧል፣ ተሰብኳል ማለትነው፡፡ በምድራችን አበባ ታይቷል ማለት የሐዋርያት ድምፅ በምድር ሁሉደርሷል ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውምእስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ ብሎ ስለ ሐዋርያት የተናገረው በዓለም ያለውንመከራ ስድት ሲገልጽ ነው፡፡ /መዝ 18¸4/ የዜማም ጊዜ ደረሰ ያለው የመከራን ጊዜ ነው፡፡ ሸለቆችም በእህልተሸፈኑ በደስታ ይጮሃሉ፣ ይዘምራሉም ተብሏል፡፡ /መዝ 14¸13/ የመከርጊዜ ደረሰ የተባለው መከር የፍሬ ጊዜ በመሆኑ ክርስትና አፍርቷል ማለትነው፡፡ በለሱ ጐመራ ማለት ደግሞ በጐ ምግባረ ፍሬ ሳያፈሩ የነበሩ ሰዎችበጐ ምግባር መሥራት መጀመራቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በመጨረሻም ወይኖች አብበዋል፣ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል እንደተባለ በመላው ዓለምአብያተ ክርስቲያናት በሃይማኖት ማበብ መዓዛ ምግባራቸውን ማቅረብ ከጀመሩ በኋላ እመቤታችን ዐረፈች፡፡ እመቤታችን ጥር 21 ቀን ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያትየእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሣሥተው “ቀድሞልጅዋን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ፡፡ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል፡፡ እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለንብንተዋት እርሷንም እንደ ልጅዋ ተነሣች ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን; ኑ ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለውተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋኒያ የተባለው ጐበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄዶ የእመቤታችንን ሥጋ የተሸከሙትን አልጋ ሽንኮር ያዘ፡፡የአልጋውን ሽንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጁን ስለ ቆረጣቸው ከአልጋው ሽንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ ታውፋንያ በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በኅቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደ ቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ የእመቤታችን ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ተድላ ደስታ ወደ አለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቁ፡፡ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ትወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፅ ሕይወት በታች ካለ መቃብርየእመቤታችን የማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም ዘላለማዊ ወደሆነ መንግሥተ ሰማያት መላእክት እና ሰማዕታት እየሰገዱላት አሳረጓት፡፡ ንጉሥ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህትቆማለች” እንዳለ፡፡ /መዝ 44¸9/ ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ከሰማይወረደ፡፡ ሐዋርያት ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋም በታላቅ ክብርማረጉን ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ፡፡ የነሐሴም ወር በባተ/በገባ/ ቀን ዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት ኑ፤ሁለት ሱባኤ በመጾም እንለምን አለ፡፡ በጾም በጸሎት ሱባኤ ያዙ፤ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ፣ በውዳሴና በጽኑምሕላ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀው መካነ እረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌምሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡ ትንሣኤዋን ሌሎቹ ሐዋርያት አይተውለ እርሱ የቀረበት መስሎት ተበሳጭቶ “በመጀመሪያ የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ” ብሎ ከማዘኑ የተነሣ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤዋን እንዳላዩ ነግራው አጽናንታው ሄዶም ለሐዋርያትየሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው አዝዛው ምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን/መግነዟን/ ሰጥታው ዐረገች፡፡ ሐዋርያው ቶማስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱም “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴትይሆናል?” አላቸው፡፡ “አንተ እንጂ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንምን;” ብለው በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችን መካነመቃብር ይዘውት ሄደው መቃብሩን ቢከፍቱ ሥጋዋን አጡት፡፡ደነገጡም፡፡ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችን ተነሥታዐርጋለች” ብሎ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፡፡ ለማረጋገጫ ምልክት እንዲሆንየሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ ሰበኗን /መግነዟን/ ለበረከት ቆራርጠውከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡
إظهار الكل...
#መልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል_ከ7ቱ_ሊቀነ_መላእክት_አንዱ ነው <ሰባቱ ሊቀነ መላእክት እነማን ናቸው ቢሉ 1ኛ #ቅዱስ_ሚካኤል _ይሁዳ 9 2ኛ #ቅዱስ_ገብርኤል -ዳን 9፥21 3ኛ #ቅዱስ_ሩፋኤል_ መጸ ሐኖክ 10፥6 4ኛ #ቅዱስ_ዑራኤል _እዝራ ሱቱኤል 2፥1 5ኛ #ቅዱስ_ራጉኤል _ሄኖ 10፥6 6ኛ #ቅዱስ_ፋኑኤል _ጦቢት 12፥5 7ኛ #ቅዱስ_ሳቁኤል ናቸው። #ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን ት.ዳን3+25ሕዝ 9፥2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ (የሐዲስ ኪዳን አስተማሪ)እግዚእ ወገብረ (#እግዚአብሔር_አደረገ)ማለት ነው። ከግብሩ በመነሳትም #የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ለቅዱስ ገብርኤል ሌሎች የተፀውኦ ስሞችን ሰፕተውታል። ከእነዚህም መካከል ጥቂቶቹ 1️⃣ኛብስራታዊ (አብሳሪው)መልአክ #እመቤታችንንና_ዘመዷ_ኤልሳቤትና አብስሮአልና። 2️⃣ኛ የአርባብ አለቃ 3ቱ አለም መላእክት እየተባሉ የሚጠሩት #ኢዮር_ራማ_ኤረር የየራሳቸው ክፍል ሲኖራቸው በራማ ካሉት 3 ክፍሎች (የመላእክትከተሞች )አንዱ አርባብ እየተባለ የሚጠራው ሲሆን የዛ አለቃ ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ነው። 3️⃣ኛ ጽኑው መልአክ ንቁም በበኀላዌነ ንረከቦ ለአምላክነ በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ፀንተን እንቁም በማለት መላእክት አጽንቶአቸዋል። 4️⃣ተራዳዩ መልአክ ዳን 3፥19-27፣ዳን 8፥15 ዳን 9፥21-27 5️⃣ኛ ሊቀ መላእክ ከ7ቱ ሊቀነ መላእክት አንዱ ነውና 6️⃣ኛ #መኑ_ከመ_አምላክ (ማንእንደ አምላክ) ሀምሌ1️⃣9️⃣ እና ሊቀ መላአኩ በዓል ወደዚያ ወደጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውሀው ፍልሃት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ #ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቲን ሃይል #አቀዝቅዞታልና መ.ፀስንክሳር ሐምሌ 19 እና ድርሳነ ገብርኤል ሐምሌ 19 ቅዱስ ገብርኤል በአመት ውስጥ የሚከበሩ ሁለት አመታዊ (የንግስ) በዓላት አሉት ታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19። ሐምሌ 19 ቅዱስ እየሉጣና ልጇ ህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ያዳነበት እለት ነው። ገድሉ የተፈፀመው በዘመነ ሰማዕተት በወቅቱ #ቂርቆስና ኢየሉጣ የሚባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ቅዱሳን ነበሪ። ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም አንጌቤን ነው አባቱ ቆዝምሶ ይባላል። እናቱ ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገስት ነች ። #ዲዩቅልጥያኖስ በነገሰ #በ20ኛው ዓመት በክርስቲያኖች ላይ ቤተክርስቲያኖችም ቅዱሳት መጻህፍቶቻቸው ይቃጠሉ ክርስቲያኖችም ይገዱሉ የሚል አዋጅ አውጥቶ ነበርና በመፍራት እናት ስለልጇ ስትል ወደ ኢቆንዩን ሸሸች። መስፍኑ ብሔሩ አለእስክንድሮስ ክርስቶስ ካጂ ለጣኦት ሰገጂ አላት። እርሷ ግን አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው የማይሰማ አንተ ላቆምከው ምስል አልሰግድም አለች ንጉስሱም በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ ቢያስፈራራት ሀሳቧን ልትለውጥ አልቻለችም ህፃኑም ቢጠየቅ እንደ እናቱ መለሰላቸው። እሺ አለማለታቸውን ንጉስ ሲረዳ ለወታደሮቹ በብረት ጋን ውሃ አፍሉ ብሎ አዘዛየው የውሃው ፍላት እንደ ክረምት ነገድጓድ እስኪነደ ድረስ #42 ምዕራፍ ያህል ይሰማ ነበር። ወደውሃው ሊከቷቸው ባሉ ጊዜ ቅዱስ ኢየሉጣ ፈራች ነገር ግን አጠገቧ ያለው ህፃን #ቂርቆስ እናቴ አትፈሪ ዳግመኛ ሞት ንሞትም አላት። አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል ብሎ አፀናት ከዚህ በኋላ በፍፁም ልብ ተያይዘው ከእሳቲ ውሃ ጠብተዋል በዚህ ጊዜ አናንያን አዛሪያ ሚሳኤልን የረዳ ታላቁና ገናናው መላአክ ቅዱስ ገብርኤል በመካከላቸው ተጠኝቶ የፈላው ውሃ አቀዝቅዞላቸዋል። ከውሃ በውጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው አንዳች ሳይሆን #ምዕመናን አዩ። እነርሱበሚያመልኩት አምላክም አምነው ብዞዎቹ በሰማዕትነት አርፈዋል። #ቂርቆስ እየሉጣ ያወጣ ከእሳት ×2 #እኛንም አድነን ×2ገብርኤል ሊቀ መላእክት #ከእናታችን_ከቅድስት_ኢየሉጣና_ከሰማዕቱ_ቂርቆስ #ከታደጋቸው_ከቅዱስ_ገብርኤል_ረድኤት_ፍቅር_ያሳድርብን 💚💚💛💛❤አሜን አሜን አሜን✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 💚💚💛💛❤አሜን አሜን አሜን✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 💚💚💛💛❤አሜን አሜን አሜን✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ✍️ምንጮች መዝገበ ታሪክ ክፍል ሁለት ስንክሳር ድርሳነ ገብርኤል ነገር ቅዱሳን @ortodox_youth አገልግሎታችን በቅርቡ ሲጀምር ለብዙ ኦርቶዶክሳዊ እህት ወንድሞቻችን ይደርስ ዘንድ ወደዚህ ቻናል 10 ሰው በማሳተፍ አገልግሎቱን እንደግፍ።
إظهار الكل...
ደጉ_መልአክ_ገብርኤልሊ_መ_ቴዎድሮስ_ዮሴፍDegu_Melak_GebrielTewodros_Yosef_2.mp36.73 MB
#ይቅርታ FORGIVENESS💐 #ይቅርታ የደስተኛ ህይወት ምልክት ነው። በደስታ የተሞላ የሚወደድ ህይወት ነፀ-ብራቅ #ይቅርታ ነው። #ይቅርታ የማይቋረጥ ፍቅር ስጦታ ነው። የሕይወት ደስታዋ #የይቅርታ_ህይወት ነው። መስጠት የሚወደድ ሕይወት የደስታ በረከት የይቅርታ ውጤት ሰማያዊ ፈገግታ ነው። #ይቅርታ ሕይወት ነው! #ይቅርታ ደስታ ነው! #ይቅርታ የነፍስ ክዳን ነው! #ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት ነው! @tewahedo_new_emenete @tewahedo_new_emenete
إظهار الكل...
🌼💐✝ተዋሕዶ✝💐🌼 👉ህልም ምንድ ነው? 👉 ህልምን በሶስት መልኩ እንከፍለዋለን ሀ=)ከመንፈስ ቅዱስ ለ=) ከስጋችን ሐ=) ከርኩስ መንፈስ ናቸው እስቲ በስፋት እንያቸው 👉 ሀ=) ከመንፈስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ተቆጥሮ የማያልቅ ፀጋዎችን ለሰው ልጆች የሚሰጥ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ደግሞ የህልም ፀጋ ነው። በህልም ውስጥ እግዚአብሔር ብዙ መልእክትን ለሰው ልጅች ያስተላልፋል ከነዚህ ውስጥ 1 =)ወደ ፊት ሚመጣው መከራ ለማሳየት እንደ ፈርኦን ዘፍ 41 15÷ጀምሮ የሚመጣውን መከራ በህልሙ እንዳሳየው ይህን አይነቱ ህልም ምናየው በኛ ላይም ቢሆን በቤተሰባችን ላይ ወይም ዙሪያችን ያሉት ወዳጆቻችን ላይ የመጣውን መከራ መቋቋም እንድንችልና በፆሞ በፀሎት እንድንዘጋጅ የሚያደርግ የማስጠቀቂያ ደውል ነው አንድም ከመንገዴ ወጥታችኋልና የተመለሱ ጥሪ ነው አንድም ከመናፍስት ውጋያ እንድናመልጥና ለነሱ እንዳንሸነፍ መሳሪያን በብዛት እንድንተጠቅም ነው ለምሳሌ ፦አንድ ሰው በህልሙ =)ዝንየ ቢመታው =)መናፍስት የመሰሉ ነገሮች ሲያሰቃዩት ቢያይ =)ከአስፈሪ እንሰሳት ጋር ሲሮጥ ቢያድር =)ሴት ከሆነች ወንድ ሲደፍራት ወንድም ከሆነ ሴት ስትደፍረው ቢያይ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ህልሞችን ቢያይ ፍችውና መፍትሔው አንድና አንድ ወደ ፈጣሪ ተመለስ ጥቅህን አሟላ ነው። እነዚህን በሌላ ርዕስ እስከነ ትርጓሜያቸው በስፋት እናያቸዋለን 2=) ለክብርና ለፀጋ መጠራታችንን የሚያሳይ ህልም ነው አንዲህ አይነቱ ህልም እግዚአብሔርን በፍፁም ልባቸው ለሚወዱ ከሚሰጣቸው ስጦታ መሀከል አንዱ ነው። ለምሳሌ ፦ አንድ ዲያቆን ወይም ለጨዋታና ለፌዝ ብሎ ወይም ለሌላ ነገር ብሎ ሰ/ተማሪ የሆነ ሳይሆን አምላክን ለማመስገን ሲል ብቻ ሰንበት ተማሪ ሆኖ የሚያገለግል አንድ አገልጋይ አልያም ቤተ ክርስቲያን የማይቀር ስለ ክርስቶስ መመስከርም ሆነ ማመስገን የማይሰለቸው አንድ ምእመን በህልም ላይ ቤተ ክርስቲያን ሲዘምር በቅዳሴ ሲገኝ አብሮ ሲቀድስ የመሳሰሉትን ቢያይ በሀይማኖቱ ጠንክሮ እንዲቀጥልና ከዚህ ብኃላም እሱ ያላሰበው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያዘጋጀለት መልካም ስጦታ እየጠበቀው መሆኑን የሚያጠይቅ ነው 3=) ከእግዚአብሔር መራቃችንን የሚያሳይ ህልም ነው ይህ መሰሉ ራስን በጭፈራ ቤት በኮንሰርት በዝሙት ቤት ወይንም በሌቦችና ነፍስ ገዳዮች መሀከል ሆኖ የሚያሳይ ነው ይህንን በቀጣይ ክፍል ለብቻው በስፋት እንመለስበታለን 👉ለ=) ከስጋ የሚታይ ህልም ስጋችን 4 ባህሪያት እንዳሉት የማይካድ ነው እነሱም እሳት ውሀ ነፋስና መሬት ናቸው እነዚህ ባሕሪያት አንዱ ከአንዱ እንዳይጣሉ እርስ በርስ እንዲስማሙ ተደርገው የተፈጠሩ ናቸው። ታዲያ በዚህ አነዋወር ሳለን የእሳት በሀሪ ከውሀ ሲበልጥ ወይም የንፋስ በሀሪ ከመሬት ሲበልጥ ህልሞችን እናያለን ማለትም ስንጨነቅ ስንፈራ ስንደሰ ቀኑን ከዋልን የቀኑን ውሎአችንን በማታው አዳራችን ልንደግመው እንችላለን ቀን የሆረር ፊልም አይተን ከሆነ ለሊቱን የተኛንበት እስኪ ሳቀቅ ድረስ ስናብድ እናድራለን ቀኑን ከወዳጆቻችን ጋር ስንደሰት ብንውል አዳሩን እንደዛው ሊሆን ይችላል ቀኑን ስናመሰግንም ብንውል እንደዛው 👉ሐ =) ከርኩስ መንፈስ ርኩስ መንፈስ በህልም ላይ ሚጫወተው ጨዋታ የዋዛ ሚባል አይደለም ለንደዚህ አይነቱ ጨዋታ አይነ ጥላ ፣ዛር ፣የቡዳ መንፈስ መሰሎቹ ዋነኛ ቢሆኑም የተቀሩትም ይህን የህልም መንገድ የሰውን ልጅ ማሸነፊያ ማድረጋቸው ማይቀሬ ነው በህልም ላይ ጥገኛ ሆነው ከሚያደርጉት ሴራዎች መሀል =) እነዚህ አጋንንት በህልም በግዴታ ሆነ በፍላጎት ከሰውን ልጅ ጋር ተራክቦ መፍጠር (ዝንየት) =) ፀበል ልንጠመቅ ስንል ሆነ ልንቆርብ ድንገት ያለ ቀኑ የወር አበባ ብቅ ማለት ከዚያም ወዲያው መሄድ =)ጥበባዊ በሆነ መንገድ የምንወዳቸውን ሰዎች እንድንጠላ ማድረግ =) መተኛት እስኪቀፈን ድረስ በህልም ከመጠን በላይ ማስፈራራት ይገኙበታል በቀጣይ ከላይ የጠቀስናቸውን በዝርዝር ምናይ ይሆናል። ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏 👉ይቀላቀሉን @tewahedo_new_emenete @tewahedo_new_emenete @tewahedo_new_emenete
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.