cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

إظهار المزيد
Advertising posts
30 157المشتركون
+7824 hour
+2117 يوم
+55130 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
የተዋሕዶ ልጆች

የሰሙነ ሕማማት ድንቅ መጽሐፍ በብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ "Thine is The Power and the Glory" አማርኛ አቻ ትርጉም: "ለከ ኃይል" @Ethiop_tewahido @Ethiop_tewahido @Ethiop_tewahido

👍 14 1🔥 1
🩸"ዓለምን ለማዳን"🩸 ዓለምን ለማዳን የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው /፪/ ጌታችን ተሰቅሎ ሲያዩት መላዕክት በዝማሬ ፈንታ አለቀሱለት ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው አምላኩን እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው /፪/     አዝ===== ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም ለጠላቱ የሚሞት በጭራሽ አይኖርም ጠላቶቹ ሳለን ለእኛ የሞተው ክርስቶስ ልዩ ነው ወደር የሌለው /፪/     አዝ===== እውርን ቢያበራ የሞተን ቢያነሳ በመመስገን ፈንታ ሆነበት አበሳ ሰማያዊው ዳኛ ሊፈረድበት ተከሶ ቀረበ ከጲላጦስ ፊት /፪/     አዝ===== የጸሎተ ሐሙስ ዕለት እራት የሆነው አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ፍቅር አስገድዶት ለእኛ የሞተው መልካሙ እረኛችን መድሃኒዓለም ነው /፪/ በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
25👍 7🙏 2
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ሰኞ ✅መርገመ በለስ ✅አንጽሖተ ቤተ መቅደስ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
10👍 2
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ሰኞ ፩. መርገመ በለስ (በለስ የተረገመችበት) ዕለት ነው። አንድምታ፡ ወንጌሉ እና ግብረ ሕማማቱ ላይ እንደተገለጸው ☞በለስ የቤተ እስራኤል እና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌ ናቸው ፡፡ ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ ስለዚህም እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡ ☞በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት "ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡" በማለት ፈጸማት ፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት ፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡ ☞በለስ ኃጢአት ናት ፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ "በአንቺ ፍሬ አይገኝ" ማለቱም "በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር" ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በአምላካችን እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ ፪. አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተከናወነበት ዕለት ነው። ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ ገርፎም አስወጣቸው...'' እንዲል። (ማቴ ፳፩፡፲፫) ምስጢሩ :- ☞ቤተመቅደስ የሆንን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም በማለት ሊቃውንት ይገልጹታል። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
👍 12🙏 5 1
በሰሙነ ሕማማት ባሉ ቀናት የግዝት በዓላት(12፣ 21 ወይም 29) ቢያጋጥሙ እንኳ ስግደት ይሰገዳል!! ያዳምጡት! @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
👍 24 10🥰 3
እብኖዲ፣ ትስቡጣ ፣ ማስያስ ፣ ታኦስ ፣ ናይናን እና ኪርያላይሶን ትርጉማቸው ምንድን ነው??? @Ethiopian_Orthodox በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ ኪርያላይሶን ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዚእነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡ ፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ ናይናን-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ እብኖዲ-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው። ታኦስ-የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ ማስያስ-የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው። ትስቡጣ-«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው። አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ – ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው። አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ-የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ @Ethiopian_Orthodox የ፵፩/41 ስግደት ምን እየተባለ ይሰገዳል? አንድ ክርስቲያን በጾም ጊዜ ከጸሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ ፵፩/41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ:- ፲፪/12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ፲፪/12 ጊዜ በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ፲፪/12 ጊዜ ኪርያላይሶን ፭/5 ጊዜ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ(አምስቱ የጌታ ችንካሮች) እነዚህም ቢደመሩ ፵፩/41 ይሆናሉ፡፡ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
🙏 17👍 10 2🔥 2
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፪ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
👍 20 8🙏 5
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፩ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
إظهار الكل...
👍 11 6🙏 4
🩸 ሰሙነ ሕማማት 🩸   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዕለተ ትንሣኤ በፊት  ያለውን ሳምንት "ሰሙነ ሕማማት" በማለት ታከብረዋለች። "ሕማማት" የሚለው ቃል "ሐመ"  ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን የዚህ ስያሜ  መነሻም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፣ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት  ከአዳም እስከ ክርስቶስ የነበረው የዓመተ ፍዳ  የዓመተ ኩነኔ ወቅትም የሚታሰብበት ስለሆነ "ሰሙነ ሕማማት" ተብሏል።   በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን  በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር፣ በተሰዓትና በሠርክ  ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ስለ ጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል  የሚያዘክረውን  ምዕራፍ  ከቅዱሳት  መጻሕፍት በማንበብና  በመጸለይ  ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ  ያሬድ በመጨረሻው  ሳምንት በየዕለቱ በጌታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ  ላይ  የተፈጸመውን  ነገረ  መስቀል  በተመለከተ  ያዘጋጀውን  መዝሙር  ይዘምራሉ፤  አብዝተው  ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡   ጌታችንና  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ሕማማትን መቀበሉ ስለምን ነው ቢሉ፡- ☞ፍቅሩን  ለመግለጽ፡-  ለፍጥረቱ  ይልቁንም  ለሰው  ልጆች ያለውን  ፍቅሩን  ይገልጽ  ዘንድ(ዮሐ  ፫÷፲፮)  ምንም  በደል ሳይኖርበት  ነፍሱን  አሳልፎ ሰጠ(ዮሐ  ፲፭÷፲፫) ☞የኃጢአትን ፍዳ ከባድነት ለማሳየት፡- እርሱ  ጻድቅና ንጹህ ሆኖ ሳለ ሰውን ወዶ ይህን ያህል  መከራ ከተቀበለ ሰው ኃጢአት በመሥራት  ቢመላለስ  የኃጢአትን  ውጤት  ከባድነት  ያስተምረናል፡፡  ራሱ  ጌታችንም  ከጲላጦስ  ግቢ እስከ ቀራንዮ አደባባይ መስቀል ተሸክሞ ሲንገላታ  ላለቀሱለት የኢየሩሳሌም  እናቶች  <<በእርጥብ  እንጨት የሚያደርጉ ከሆነ በደረቀውስ እንዴት ይሆን>> በማለት ገልጾለታል፡፡ (ሉቃ  ፳፫÷፳፪) ☞ቤዛ ለመሆን፡- በኦሪት ዘመን ሰዎች  ለሠሩት  ኃጢአት ኃጢአታቸውን  ለማስተሰርይ  ነውር  የሌለበትን  በግ  ቤዛ እንዲሆናቸው መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ይህ ግን ከአዳም የተሰወረውን ኃጢአት ማስቀረት ስላልቻሉ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሁኖ መጣ <<እነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ>>(ዮሐ ፪÷፳፮) ☞እርግማናችንን  ለማስቀረት፡-  <<በእንጨት  የሚሰቀል  ሁሉ  የተረገመ  ነው  ተብሎ  ተጽፏልና  ክርስቶስ  ስለ እኛ እርግማን  ሆኖ  ከሕግ  እርግማን  ዋጀን>>(ገላ  ፫÷፲፫)    በማለት  ቅዱስ  ጳውሎስ  እንደጻፈው  እርግማናችንን  ተሸክሞ ሕማማትን  መቀበሉ  የቀድሞው  ኃጢአት  ምንም  ያህል  ከባድ  ቢሆን  በታላቅ  መስዋዕትነት  እንዳስቀረልን ሊያስተምረን ነው፡፡ (ዘዳ  ፳፩÷፳፫) ☞የድኅነታችንን ክቡርነት /ውድነት/ ሊያስረዳን ፡- ድኅነታችንን  የእግዚአብሔር ልጅ ደሙን እስኪያፈስለት ድረስ እጅግ ውድ መሆኑን ሊያስተምረን፡፡ (ራዕ ፭÷፱) @Ethiopian_Orthodox   ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም  ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡  በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት : ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው:: በመስቀል መባረክ፣ ማማተብ፣ መሳቅ፣ መሳሳም፣ ከሴት ጋር መገናኘት(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 593)፣ ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም፣ ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም:: "እግዚአብሔር ይፍታህ" አይባልም(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600)፤ ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት(12፣21 እና 29) እንኳ ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው፤ መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው።(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 578)    ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም። ጸሎቱ ውዳሴማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ሕማማትና መዝሙረ ዳዊት ናቸው። የቅዱሳን መልክአ መልክእ አይጸለይም። ስናጠቃልለው የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ፡ 1.  እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል፣ መሳሳም 2.  ሩካቤ ሥጋ ማድረግ 3.  መስቀል ማሳለም እና መሳለም 4.  ክርስትና ማስነሣት 5.  ለሙታን ፍትሐት ማድረግ 6.  ክህነት መስጠት 7.  የላመ የጣመ ምግብ መመገብ 8.  መሳቅ መጫወት መጨፈር 9.  አብዝቶ ጠግቦ መመገብ 10. መስከር ወዘተ ናቸው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሣዕና ይከናወናሉ፡፡ @Ethiopian_Orthodox የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች: ፩.  አለመሳሳም ፡- ከላይ እንዳየነው በሰሙነ  ሕማማት  የኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  እምነት  ተከታዮች መስቀል  እንደማይሳለሙት  ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን  ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ  አልሰመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ  እንስቀለው ፤እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡  በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ ፪. ሕፅበተ  እግር፡- ጌታ በፍጹም ትህትና  የደቀ  መዛሙርቱን  እግር  ያጠበበት፣  ከሐዋርያት  ጋር  ግብር  የገባበትና የክርስትና  ህይወት  ማሕተም የሆነውን  ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት  ነው። ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ  ዕለተ  እናንተ  ለወንድማችሁ  እንዲሁ  አድርጎ  ለማለት  የደቀ  መዛሙርቱን  እግር  በማጠቡ  ምክንያት  የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ፫. ጉልባን እና ቄጠማ ፡- ጉልባን ከባቄላ ክክ፣  ከስንዴ  ወይንም  ከተፈተገ  ገብስ  ጋር  አንድ  ላይ  ተቀቅሎ  የሚዘጋጀና የጸሎት  ሐመስ  እለት  የሚበላ  ንፍሮ  ነው፡፡  የጉልባን  ትውፊት  እስራኤላውያን  ከግብጽ  ተሰደው  በሚነጡበት  ጊዜ በችኮላ  ስለነበር  አቡክተው  ጋግረው  መብላት  ያለመቻላቸውን  ሁኔታ  ያመለክታል፡፡  ያን  ጊዜ  ያልቦካው  ሊጥ  እያጋገሩ ቂጣ  መብላት  ንፎሮም  ቀቅለው  ስንቅ  መያዝ  ተግባራቸው  ነበር፡፡  ይህን  ለማሰብ  በሰሙነ  ሕማማት  ቂጣና  ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ [በጸሎተ ሐሙስ ዕለት በስፋት የምናየው ይሆናል።] ቄጠማ (ቀጤማ)፡-  በቀዳም  ስዑር  ቀሳውስቱን  ዲያቆናቱ  ቃጭል  /ቃለ  አዋዲ/  እየመቱ  "ገብረ  ሰላመ  በመስቀሉ ትንሳኤሁ  አግሃደ" የሚለውን  ያሬዳዊ  ዜማ  በመዘመር  ጌታ  በመስቀሉ  ሰላምን  እንደሰጠ  እና  ትንሳኤውንም እንደገለጠልን  በማብሰር  ቄጤማውን  ለምእመናን  ይሰጣሉ፡፡  ምእመኑም  ለቤተ  ክርስቲን  አገልግሎት  የሚውል  ገጸ በረከት  ያቀርባሉ  ቀጤማውንም  በራሳቸው  ያስራሉ፡፡  ይህም  አይሁድ  ጌታችንን  እያሰቃዩ  ሊሰቅሉት  ባሉ  ጊዜ  የእሾህ አክሊል  ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ  እለት  ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለምዕመናን ትልቅ ብስራት ነው።
إظهار الكل...
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads:

https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

👍 31 12🙏 4😱 2