cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

ይህ በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ (አዲስ አበባ) የሚገኘው የገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። እንኳን በደኅና መጡ!

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 328
المشتركون
+424 ساعات
+107 أيام
+2730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ነገ ጠዋት ይቀጥላል ።
إظهار الكل...
👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
" በሰማዕታት ሞት ሃይማኖት ትጠበቃለች ፣ እምነት ታድጋለች ፣ ቤተ ክርስቲያን ትጠነክራለች ። የሞቱት ሲያሸንፉ አሳዳጆቹ ደግሞ ተሸናፊዎች ይሆናሉ የሰማዕታት ሞት በራሱ ለሕይወታቸው ሽልማት ነው ። " ቅዱስ አምብሮስ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በስልሣ ሰባት ዓ.ም. በኔሮን ቄሣር እጅ ቁልቁል ተሰቅሎ  ሰማዕትነትን ለተቀበለበት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በስልሣ ሰባት ዓ.ም በኔሮን ቄሣር እጅ አንገቱን ተቆርጦ ሰማዕትነትን ለተቀበሉበት የክብር ቀን እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን መልካም በዓል የመሰረቶቻችን የሐዋርያት ጸጋና በረከት በኛ አድራ ትኑር ። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በዓል አሜን 🙏🙏🙏
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም እንደምን አደራችሁ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታዩቻችን እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ዛሬ ጠዋት ከቀኑ 4:00 ሰዓት ይጠብቁን 🙏
إظهار الكل...
፫- ሁለቱንም ጌታ ስማቸውን ለውጦታል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የዮና ልጅ ስምዖን ተብሎ ይጠራ ነበር። (ዮሐ. ፳፩፡፲፭) ጌታም ጴጥሮስ ብሎ ስያሜ አወጣለት። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። (ማቴ. ፲፮፡፲፯-፲፰) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ለአገልግሎት ሲጠራ ስሙ ሳውል ተብሎ ይጠራ ነበር። በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። (ሐዋ. ፱፡፬) በአገልግሎቱ ጽናት ጳውሎስ የሚል ስያሜ ተሰጠው። ፬- ሁለቱም ድንቅና ተአምራትን አድርገዋል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስላደረገው ድንቅ እንዲህ ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፏል፦ ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ። በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ። ጴጥሮስም። ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ አለው። ወዲያውም ተነሣ። በልዳና በሰሮናም የሚኖሩ ሁሉ አይተውት ወደ ጌታ ዘወር አሉ። (ሐዋ.፱፡፴፪-፴፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ታላላቅ ተአምራቶችና ድንቅ ስለማድረጉ፦ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር። (ሐዋ. ፲፱፡፲፩-፲፪) ፭- ሁለቱም ሙታንን አሥነስተዋል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጣቢታ የተባለችውን ብላቴና ስለማሥነሳቱ፦ በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች። በዚያም ወራት ታመመችና ሞተች፤ ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች። እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት። (ሐዋ. ፱፡፴፮-፵፩) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አውጤኪስን ከሞት ስለማሥነሳቱ፦ አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው። ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ። ብላቴናውንም ደኅና ሆኖ ወሰዱት እጅግም ተጽናኑ። (ሐዋ. ፳፡፯-፲፪) ፮- ሁለቱም የሰማዕትነት አክሊል አግኝተዋል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በስልሣ ሰባት ዓ.ም. በኔሮን ቄሣር እጅ ቁልቁል ተሰቅሎ ሕይወቱን አጥቷል (ሰማዕትነትን ተቀብሏል)። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በስልሣ ሰባት ዓ.ም. በኔሮን ቄሣር እጅ አንገቱን ተቆርጦ ሕይወቱን አጥቷል (ሰማዕትነትን ተቀብሏል)   የቅዱሳኑ በረከት ዘወትር ከእኛ ጋር ይሁን ወስብሐት ለእግዚአብሔር !! ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ምንጭ (ኅሩይ ወልደ ሥላሴ) ፲፱፻፺፭ SAINT PETER AND PAUL  (POPE SHENOUDA )
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ ፭ ቀን ጴጥሮስ ወጳውሎስ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልካሙን የክርስትና ገድል ተጋድለው ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ቀን በታላቅና በተለየ ሁኔታ ታከብራለች ። ክርስትናን በማስፋፋት ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታትን ጽፈዋል ። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምንት ምዕራፎችን የያዘ ሁለት መልእክታትን ሲጽፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንድ መቶ ምዕራፎችን የያዘ አሥራ-አራት መልእክታትን ጽፏል። ለአግልግሎት የጠራቸውም የክብር ባለቤት የሆነው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ዓሣ በማጥመድ ሥራ ላይ ሳለ ለዚህ ታላቅ አገልግሎት ሲጠራ (ማቴ ፬፦፲፰) ሐዋርያው ተከተሉት። (ማቴ. ፬፡ ፲፰-፳) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጌታ የተጠራው ወደ ደማስቆ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ ነው። ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ ፥ በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ። ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ። ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም። አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። (ሐዋ. ፱፡፩-፭)
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.