cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

#ካሴት

https://telegram.me/nebi11alex #ካሴት የሚወደድ አዝናኝና አስተማሪ ግጥሞች😃፣ወጎችና ቀልዶች😀👌 ለፍቅራችን ይቀላቀሉና ያበዱ ወሬዎች እንደወረደ 👌 👌 እና የቤት ውስጥ ፊንሽንግ(የጅብሰን፣የቀለም ፣የግድግዳ ጌጦች)የመሳሰሉትን ሰራዎችን ይጎበኙ፤👌 በስራዎቻችንም ይደሰታሉ። ትእዛዝ (ፍላጎትዎን) ፥+2519 11104022 ይደውሉ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
177
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

📌 #አዳምጡኝ ⚡️እራሱን የሚወቅስ ሰው ፤ባለፈ ማንነቱ፤ ሁሉን አዎቂ ነኝ የሚል ብቻ ነው። ባለፈ ማንነት እራሳችሁን አትውቀሱ፤ ለሚመጣው ማንነታችሁ፤ ሌሎችም የራሳቸው እውቀት እንዳላቸው ተረድታችሁ ፤ተለወጡ እንጂ። ቧንቧ ከፍታችሁ፤ ሲፈስ ኖረና፤ ዛሬ ነቅታችሁ ብትዘጉት፤ ያ ሁሉ የፈሰሰው ውሀ ብላችሁ በመፀፀት ፤ወደሁዎላ ትውስታ በሚባል ወጥመድ አትታሰሩ የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም።ይልቁን የዛሬን ተስፋ ከሌሎች ጋር ተከፋፈሉ። አንድ ሰው ብቻውን ምንም ነው። ውቅያኖስ መሀል የተላከ የእንባ ዘለላ የሚያክል ጠብታ ነው። ስለዚህ በዙሪያችሁ ላሉት አካፍላችሁ መስፋት እንጂ፤ በጠብታ ውስጥ ብቻችሁን ከፍ ማለት ፍፃሜው ውድቀት ነው። 🌻በህይወት ስትኖር ለሰዎች ፍቅርህን እና እውቀትህን ለግስ ፤ ሰው ያለ ሰው ባዶ ነው።በምድር ላይ ምንም ጠቢብ ቢሆን እውቀቱ በዝቶ ቢከብርም እራሱን በራሱ ኦፕራሲዮን ያደረገ ማንም የለም። እኔ ብቻ አውቃለሁ የሚል ሰው መኖሩን እንጂ እንዴት መኖር እንዳለበት የማያውቅ ነው።
إظهار الكل...
የራስን ሕይወት መቆጣጠር እና መምራትን የሚያዳብሩ 10 ነጥቦች ሰዎች እቅዳቸውን በሚገባ ለማሳካት ራሳቸውን መቆጣጠር እና መምራት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ፍላጎትን እና እቅድን ባለማጣጣም እንዲሁም መመሪያቸውን በአግባቡ ባለመተግበራቸው የቀን ውሏቸው እና የሕይወት ስኬታቸው ወጣ ገባ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ራስን የመቆጣጠር እና የመምራት አቅምን ለማሳደግ የሚጠቅሙ 10 ምክሮችን አቅርበናል፡፡ 1. በተግባር የሚገለፅ አመለካከት ራስን ማየት በነጻነት የምንሰራቸውን ስራዎች ሃላፊነት እንድንወስድባቸው ያደርገናል፡፡ በመሆኑም ሊተገበር የሚችል አስተሳሰብን ማስፈን እና አስቀድሞ አቅዶ የዕለት ውሎን መምራት ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ ይህም ራስን በራስ ለማረም ይረዳል፤ ያልተፈለገ ጭንቀት እንዳያጋጥም ያደርጋል፡፡ 2. ግብ ማስቀመጥ አንድ ሰው ሲኖር የሕይወት ግብ ሊኖረው ይገባል፤ ግቦች ደግሞ ምርጫን ይወስናሉ፤ ግብን በውል ለይቶ ያስቀመጠ ሰው ያሳካዋል፡፡ የተዘበራረቀ ግብ ያለው ሰው ደግሞ ለቀውስ ይጋለጣል፤ ይህ ደግሞ ለጭንቀት እና ለሌላ ህመም ይዳርጋል፡፡ በመሆኑም በጊዜ የተገደበ፣ የተመጠነ፣ ሊለካ እና ሊሳካ የሚችል ግብን ማስቀመጥ ራስን ለመቆጣጠር እና ሕይወትንም በዚሁ መልክ ለመመራት አቅም ይፈጥራል፡፡ 3. ራስን መገምገም ራስን መገምገም ከተወሰነ ጊዜ በፊት የተከናወኑ ድርጊቶችን ወይም ስራዎችን መልሶ በማየት ምላሽን ለአዕምሮ መመገብ ነው፡፡ የተቀመጠውን የሕይወት ግብ ለማሳካት ቀድሞ የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም በቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ለማካተትም ይረዳል፡፡ ይህ ዓይነቱ ተግባር ሰዎች ባህሪያቸውን ራሳቸው እንዲያርሙ ያግዛቸዋል፡፡ 4. መነቃቃት ሰዎች አንድ ዓላማ ባስቀመጡ ቁጥር ያንን ለማሳካት የራስ ተነሳሽነት እና ትጋት ያድርባቸዋል፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የተቀመጠው የሕይወት ስኬት ግብ እና የእለት ውሎ አቅጣጫ ለስራ የሚያነሳሳ እና ቁርጠኝነትን የሚጨምር ጥቅም ሊኖረው ይገባል፡፡ ሰዎች የግቡ ስኬት ተደምሮ ውጤት እንደማይኖረው ካወቁ የስራ መነቃቃታቸው ይቀዘቅዛል፤ ስለሆነም የሚቀመጠው ግብ መነቃቀትን የሚፈጥር መሆን አለበት፡፡ 5. በራስ መተማመን መነቃቃትን ወደ አዕምሮ ለማምጣት በራስ መተማመን መኖር አለበት፤ በራስ መተማመን ለዓላማ ስኬት ዓቢይ መንገድ ነው፡፡ ሰዎች በራሳቸው ካልተማመኑ የሕይወት ስኬት ግቡን አይመታም፤ ይህ ደግሞ ራስን መቆጣጠር እና መምራትን ማጎልበት አልተቻለም ማለት ነው፤ በእጃቸው ያለውን ቀሪ ስራ ለማሳካት ይከብዳቸዋል በተጨማሪም ጭንቀትን ያመጣባቸዋል፡፡ በመሆኑም በርካታ ችግሮች ሊያጋጥሙ ቢችሉም እንኳ በራስ የመተማመን መንፈስ እቅድን ማሳካት ተገቢ ነው፤ ጥቀሙም ራስን የመምራት ጥበብን እስከ ማጎልበት ይደርሳል፡፡ 6. ተስፋን መሰነቅ ተስፋ ሰዎች ልቦናዊ አቅም በመፍጠር የሕይወት ጉዟቸው የተሳካ እንዲሆን የማስቻል አቅም አላት፡፡ በሂደት የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን በመጋፈጥ ለግባቸው ስኬት ወደ ፊት እንዲራመዱም መሪውን ታስጨብጣለች፡፡ የግሪኩ ፈላስፋ ፕሌቶ “አንድ ነገር ብቻ ተስፋ አድርግ እሱንም በሚገባ አሳካው” ብሎ ነበር፡፡ ስለዚህ ሰዎች ራስን በመቆጣጠር ያስቀመጡትን አንድ ዓላማ በልኩ ለመፈፀም ተስፋ የግድ ያስፈልጋቸዋል፡፡ 7. ጫናዎችን ማስወገድ አንዳንድ ጊዜ ያልተፈለጉ ፍላጎቶች ሕይወትን ለመምራት በሚደረገው ጥረት ላይ ያልተፈለገ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን የፍላጎት ቅጥ ማጣት ጫናዎችን በመቅረፍ የሕይወት ስኬት ጉዞን ወደፊት ማስቀጠል ይገባል፡፡ 8. ለምን እና እንዴት የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ በሕይወት ውስጥ ለምን የሚለው ጥያቄ በአጠይቆቱ ሩቅ ለማሰብ እና ስራን የሚከናወንበትን ዓላማ አውቆ ለማከናወን ይጠቅማል፡፡ በሌላ በኩል እንዴት የሚለው ጥያቄ ደግሞ ሩቅ የታሰበውን ግብ የማሳኪያ መንገዶችን ለማፈላለግ ፋይዳ አለው፡፡ ጀርመናዊው ኒቼ በአንድ ወቅት “በለምን ጥያቄ ላይ የተመሰረተ ህይወት ያለው ሰው እንዴት የሚለውን ጥያቄ በተግባር እየመለሰ ለህይወቱ ትርጉም ያለውን ስራ ይሰራል” ብሎ ነበር፡፡ በመሆኑም ሕይወትን የመምራት አቅምን ለማጎልበት ለተቀመጡት ግቦች ለምን የሚለውን ጥያቄ አስቀድሞ እንዴት እንደሚሳኩ ሁልጊዜም በመጠየቅ እና ምላሹን በተግባር በማከናወን መኖር ያስፈልጋል፡፡ 9. ራስን መቆጣጠር እንደ ባህርይ መገለጫ ዛሬ የሚሰራ ሥራ ለነገው እቅድ አስተዋጽኦ አስቀምጦ ያልፋል፡፡ ፕሮፌሰር ራችሊን እንደሚሉት ራስን መቆጣጠር የሰው ልጅ የባሕርይ አንድ መገለጫ ነው፤ አንድን ስራ ለማቆም ወይም ለማስቀጠል በራስ መወሰን መቻል የሚያሳየው የግለሰቡን ባህርይ ነው፡፡ በመሆኑም ለአወንታዊም ሆነ ለአሉታዊ የሕይወት ውጣ ውረዶች ራስን መቆጣጠርና የባሕርይ መገለጫ በማድረግ መጓዝ መልካም ነው ተብሏል፡፡ 10. ራሱን የሚተካ ወይም የሚያስቀጥል ግብ በሕይወት ኡደት ውስጥ አንድ ግብ ከተሳካ በኋላ ወይ መተካት ወይም ደግሞ ተሻሽሎ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም አንድ የህይወት ግብ እንደተሳካ መደበላለቆች እንዳይፈጠሩ አስቀድሞ ራሱን የሚተካ ወይም የሚያስቀጥል ግብ ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎች ራሳቸውን የመምራት እና የመቆጣጠር ስኬታቸው ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ ለመምጣቱ ማሳያ ነው። @dailyheroes @dailyheroes
إظهار الكل...
إظهار الكل...
አልጋህ ላይ ተኝተህ አጉል አትቆዝም፡፡የመኝታ ሰዓት ካለቀ ተነስ፡፡መነሳትህ ካልቀረህ አነሳስህን የጀግና አድርገው፡፡አትንቀራፈፍ፡፡እግርህ ወለሉን ፈጥኖ ይርገጥ፡፡ልብህ ለፈጣሪ ምስጋና ይስጥ፡፡ቀኑን ቀደም ብለህ በወኔ ጀምረው፡፡ + እስክትዘጋጅ አትጠብቅ፡፡ "ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም!" አትበል፡፡ተነስና just አድርገው፡፡ + "ከየት መጀመር እንዳለብኝ አላውቅም!" አትበል፡፡just ደስ ካለህ ነገር ጀምረው፡፡ + ይጠቅመኛል የምትለውን ነገር በጠዋቱ ጀምረው፡፡ያልጀመርከውን ነገር አትጨርሰውም፡፡ስለዚህ አሁን ጀምረው! በወኔ ጀምረው! በእምነት ጀምረው! + ጀምርና መንገዱ መንገዱን ይመራሃል፡፡አንዱ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ያደርስሃል፡፡እምነት ካለህ? ሁሌም መንገድ አለ፡፡ግን በመጀመርያ ጀምረው፡፡Hey ተነስ! ንቃ! ጀምረው፡፡ #መልካም_ቀን 𝐆𝐎𝐎𝐃 𝐃𝐀𝐘!
إظهار الكل...
ጠዋት ጠዋት ትዳር ያምረኛል! (ዘውድዓለም ታደሰ) ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ሚስት ማግባት ያምረኛል። በቃ አለ አይደል ልክ እንደ አማርኛ ፊልም ሚስቴ ቀድማኝ ተነስታ ሸሚዜን ለብሳ በዚያ ውብ እግሯ ቤት ውስጥ ሽር ጉድ ብላ ሚገርም ቁርስ ከጁስ ጋር ሰርታልኝ በልቼ ምናምን ቡናዬን ጠጥቼ። የተተኮሰ ልብስ ራሷ መርጣ አምጥታልኝ እሱን ለብሼ እስከበር ድረስ ሸኝታኝ ከንፈሯን ስሜ ቀኔን ረሃ ሆኜ ብጀምር ደስ ይለኝ ነበር። But ... life is not like z movie my brother!! ሁሉም ወንድ ሊያገባ ሲወስን የሚታየው ከላይ የገለፅኩት አይነት ህይወት ነው። በርግጥ እህቶችም የሚሰሩን ሿሿ ቀላል አይደለም። ብራዘር ድንገት ቺክህ የወንደላጤ ቤትህ ከመጣች በምቾት ታጨናንቅሃለች። ትንከባከብሃለች። በአንድ ድስት ሰባት አይነት ወጥ ስትሰራ “አረረረ ጆርዳና in the house ” ምናምን ብለህ ትቀውጠዋለህ። እየተሽከረከረች ያቺኑ አንድ ክፍል ቤትህን ታፀዳለች። እንደ ስፓይደር ማን ግድግዳው ላይ ተራምዳ ሁሉ ኮርኒስህን ልትወለውል ትችላለች። አንተ እያወለቅክ አልጋህ ስር የጣልከውን ካልሲ ፈገግታ ከፊቷ ሳይጠፋ (በሆዷኮ ይሄ በስባሳ እያለችህ ነው) አውጥታ አጥባ እንደቋንጣ ታሰጣልሃለች። በቃ ምን አለፋህ ከሷ ጋር መኖር ሰቨን ስታር ሆቴል አዘግቶ መዝናናት እንዲመስልህ ታደርግሃለች። ባራት እንቁላል አምስት አይነት ወጥ ሰርታ ስታበላህ እነዚህ አድሃሪና ቡርዧ የሆቴል ቤት ባለቤቶች ሲበዘብዙህ እንደኖሩ ይሰማሃል! እሷን ማግባት ትመኛለህ። ትዳር ማለትኮ .... እያልክ ለጓደኞችህ ማብራራት ትጀምራለህ። የሙሽራ መኪና ስታይ አይንህ ይንከራተታል። እንተዋወቃለን ወይ? የሚለው ፕሮግራም ቋሚ ደምበኛ ትሆናለህ። በቃ ፋይናሊ ሽማግሌ ትልካለህ። እናትና አባቷ በየቀኑ «አንቺ ልጅ አግብተሽ አትፋቺንም እንዴ?» ሲሏት እንዳልኖሩ እየተጀነኑ ምን አለው? ማን ነው? ምናምን ብለው በመከራ ይፈቅዱልሃል! ከዛ መልአኳ እጮኛህ ስለሰርግ ትጀነጅንሃለች። እንደጀነጀነችህ ግን አትባንንባትም። በስታየል ነው ምታሰምጥህ። አለ አይደል «እኔኮ ሰርግ አሎድም ግን እነማሚ እንዳይከፋቸው አነስ ያለች አንድ መቶ ሰው ብቻ ጠርተን ቀለል አርገን እንደግስ .. ግን ካልተመቸህ ይቅር» ትልሃለች! አረ ጣጣ የለውም ምናምን ብለህ እድሜ ልክህን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሰልፈህ የቆጠብካት ፍራንክህ ላይ ትፈርድባታለህ! እናቱ ቀለል ያለ ያለችውን ሰርግ የአንድ ሺ ሰው ካርድ በማሰራት ትጀምረዋለች ቀለል አርጋ የሃያ ሺ ቬሎ፣ ቀለል አርጋ ሜካፕ ሰላሳ ሺ፣ ቀለል አርጋ ሊሞ ሃምሳ ሺ፣ ወዘተ ብላ በአንዴ ከአበዳሪ ሐገራት ተርታ አውጥታህ ኢኮኖሚህን በጠረባ ትጥለዋለች። የሰርግህ ቀን በሰው መኪና እንደታቦት አደባባይ ሲያዞሩህ ይውሉና አንተ የማታውቀውን አንድ ሺ ሰው ሆድ ሞልተህ እጅህን እያጠላለፍክ ኬክ ትጎራረስና በአደባባይ ሃብቴ ሃብትሽ ነው ብለህ ፈርመህ ኮትህን አንጠልጥለህ ወደቤት ይዘሃት ትገባለህ! የመጨረሻው መጀመሪያ! እንዲል የድሮ ደራሲ the tragic part of your life begins: ጠኋት ከእንቅልፍህ የሚገርም የጀነሬተር ድምፅ ያነቃሃል! ብንን ስትል እያንኮራፋች ነው ካሁን አሁን ተነስታ ምርጥ ቁርስ ሰራችልኝ ብለህ ብትጠባበቅ እናቱ ተኝታ ህልም እየቀያየረች ታያለች። ምርር ሲልህ ትቀሰቅሳታለህ። ጠላትህ ቅይር ይበል በዚያ ሻካራ ድምጿ አፍጥጣ «ሰው ከእንቅልፌ ሲቀሰቅሰኝ ደስ አይለኝም» ብላ ተመልሳ ትተኛለች። በሆድህ “ እቺ ነገር ያቺ ነገር ነች?” እያልክ ፆምህን ወደስራ ስትወጣ በር ላይ ለሰርግ ብር ጎሎህ የተበደርከው ሰውዬ ከቦክሰኛ ልጁ ጋር ይጠብቅሃል ... ምፅ እኔ አፈር ልብላ! ማታ ቤት ስትገባ ካልሲዎችህ በር ላይ ተከምረው ይጠብቁሃል! እሱን አጥበህ ስትጨርስ ጨው እንደ Dead sea የበዛበት ሽሮ ወጥ ይቀርብልህና “ከበላህ ብላ ካልበላህ አፈር ብላ” ትባላለህ! በዘጠኝ ወሯም አንድ ጩኸታም ፈልፈላ ትወልድልሃለች። በየደቂቃው ዋኣኣይ ነው። በየሰከንዱ ኡኡ ነው። አናትህን ያዞረዋል። በመስኮት አውጥተህ ወርውረው ወርውረው ይልሃል። ለሊት ይነሳና ይቀውጠዋል። እሷ ምርር ሲላት ላሽ ትለዋለች። ቢቸግርህ ተነስተህ ጡጦ ትሰጠውና ተመልሰህ ተኝተህ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርግህ ጡጦውን ሻት አርጎት እንደገና ዋኣኣይ ይላል። በቃ ትነቅላለህ! ይሄ ሰውዬ ለምን አይተወኝም ግን ትላለህ። የሶስት ወሩን ልጅ “ና ልብ ካለህ ወጥተን እንነጋገር” ምናምን ሁሉ ልትለው ትችላለህ: በገባህ በወጣህ ቁጥር ያ በደጉ ግዜ ስንት ነገር ያሳየህ ጡቷ ላይ እንደአልቂት ተጣብቆ ሲመጠምጣት ደምህ ይፈላል። ዘመዶቿ አያልቁም ዛሬ አባቷ ፣ ነገ አጎቷ፣ ከነጎዲያ አክስቷ እየመጡ ጠብ እርግፍ ብለህ ታስተናግዳለህ። እሱ ሳይበቃቸው ምነው ጠቆርሽ? ምነው ከሳሽ? እያሉ ወፍራ ጆንሲናን ያከለችውን ሴትዮ ይጨቀጭቋታል። ፕራይቬት ላይፍ ብሎ ነገርህ ይናፍቅሃል! ብቸኝነትህ በአይንህ ውል ይልብሃል! ለሊት አንተ የልጅህን ዳይፐር ለመቀየር ስትታገል ፍሬንዶችህ ክለብ ሆነው ይደውሉልህና ዘፈን ይጋብዙሃል! ሲኦል ሆነህ ከመንግስ ተሰማይ ሚደወልልህ ያህል ትቀናለህ! ከዚያ ህይወትህን መለስ ብለህ በትካዜ ታስታውሰዋለህ። ከዚያም ሴትየዋ ከትዳር በፊት የነበራት ማራኪ ባህሪ የምርጫ ቅስቀሳ መሆኑ ይገባህና “All women are politicians ” ብለህ መፈላሰፍ ትጀምራለህ። መልካም ሶቅራጠስ!
إظهار الكل...
🔴ሁለት ነገር ቀናችንን ያበላሽብናል 1. ስለ ትናንት ማሰብና 2. ከሰው ጋር ውድድር 🟡ሁለት ነገር ቀናችንን ያስተካክልልናል 1. ያለንን ማመስገንና 2. ዛሬን መኖር 🟢ሁለት ነገር ነጋችንን ያሳምርልናል 1. እቅድ ማውጣትና 2. በቂ ምክንያት ማስቀመጥ •═•••🍃🌺🍃•••═•
إظهار الكل...
አንቺ ከሄድሽ ወዲ . . አንቺ ከሄድሽ ወዲ ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ እማላገኝሽን እማላገኝሽን አንቺን አምጣት አለኝ እሷን አምጣት አለኝ ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ አንቺ ከሄድሽ ወዲህ መሰለኝ መቃብር ያለሁበት ሰፈር ዘልዬ ቦርቄ ያደኩበት መንደር ደሞም ባከባቢው የሚወጣው ድምፀት የሚሰማው ጩኸት መሰለኝ የሲኦል ጫጫታ'ና ሁካታ፥ የአጋንንት ፉጨት የሐጣን ዋይዋይታ፥ የሐጥአን እሪታ... እንዲም አስባለሁ ሰፈርተኛው ሁሉ ሞልቶለት ሲዘክር ይመስለኛል የኔ የአርባዬ ተስካር የሰማንያ ተስካር ሙት አመቴን ማውሻ እኔን ማስታወሻ ደግሶ ማልቀሻ... አንቺ ከሄድሽ ወዲ አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ ሁሉ በኔ አየለ ህሊናዬ ዛለ ዋለለ ቆሰለ መላው ሰውነቴም ነደደ ከሰለ ከሰለ . . እንደው ባጠቃላይ አንቺ ከሄድሽ ወዲ ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!! ማይክል ሰለሞን (የቡዜ ልጅ)
إظهار الكل...
​🤔እናስተውል ጨለማ የንጋት ጀርባ ነው። 🔴ጥፋትም የምህረት መንገድ ነው። ሰው ሆኖ ልታጣው የማይገባው ሰዋዊ ማንነትህን ነው በልባችን ሊታተም የሚገባው ክብርና ፍቅር ናቸው የህይወት እርምጃችን እሾህ ቢበዛው እንደ ፅጌሬዳ ማህዛችን ሊያውድና ነገራችን የተዋበ እንዲሆን 🔵እናስብ ለመነሳት መውደቅ ለከፍታም ዝቅታ አለውና ዝቅታችን በቅንነትና በደስታ ይሁን ቀና ስንልም መቃናታችን ከፈጣሪ እንጂ በራሳችን እንደሆነ # አናስብ ሁሉም ከርሱ ለእርሱ ነውና በፈተናችን ሁሉ እንታገስ የነገዋ የማለዳ ፀሀይ ምን ብስራት ይዛ እንደምትመጣ አስበን እንዘጋጂ ♥️ዱብዳም ብታመጣም የሚቀበል ጥንካሬ ይኑረን ሊነጋ ሲል ይጨልማል ግን የነገን ማን ያውቃል ??? መልካም ቀን ይሁንላችሁ *....*...❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣....*...*
إظهار الكل...
🌸🌸🌸 ስላልሺኝ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ተወኝ አልሺኝ ተውኩሽ እንዳደገ ህጻን የእናት ጡት ወተት በግድ እንዳስተዉት ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ እርሳኝ አልሽኝ ረሳሁሽ ከነመፈጠርሽ ማስታውሰው የለም ባደጋ እንደመጣ የጭንቅላት ህመም ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ጥላኝ እንኳ ብትይ ነፍሴን የሚገድል ጠላት እንደመጥላት ከቃልሽ ላልወጣ ጠላሻለሁ መጥላት ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ የሚወደኝ ቢኖር ትዛዜን ይፈጽም በፍቅር መጽሐፍ የፍቅር አምላክ እንዲል ቃልሽ ትዛዜ ነው ያልሺው ይፈፀማል ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ሌላ ፈልግ ብትይ ሌላ ፍቅር ጀመርሁ አትሆነኝም ላልሺው ምትሆነኝ አገኘሁ ዞርበል ባልሺኝ ማግስት ሀገር ለቅቄአለሁ ላይኔ የጠላሁሽ ስላልሺኝ ነው እንጂ እኔ አፈቅርሻለሁ ፍቅር ማለት ለኔ የተፈቃሪን ቃል ትዛዙን ማክበር ነው መጽሐፉ እንደሚለው። shali6 @shali6
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.