cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ግጥምና ምጥን ሀሳቦች

ኢትዮጲያዊነትን የሚያንፀባርቅ ድንቅ ቻናል ነው፡፡ ይቀላቀሉን፡፡ @Hasabawian ለአስተያየትዎ @abiye12

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 481
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from አቦል
“ቸርች ውስጥ የተከለከሉ መዝሙሮች” የምትል ስንኝ፤ ¹ነገረ ኤልያስ መልካ( ፀሀፊ ዮናታን ጌታቸው) የሚል አርዕስት ባለ፞ው ልጥፍ ስር ከሶስት ቀን በፊት አነበብቤ ቀልቤን ገዛው። በ'ርግጥ ፅሁፉ ለኔ ሞጋችም፤የወደድኩትም ነበር። Secularism(specially secular songs(good songs))፤በወንጌላውያን አማኞች(aka Protestant) ዘንዳ ዘመን የተሻገረ አሟጋችነቱ አልተቋጨም። // ይሄንን ያነሳሁበትም ጉዳይ እንደ አንድ ወንጌላዊ አማኝ ሰለባ ስለሆንኩኝ ነው። ጉዳዩ ይቆየኝ'ና፤ ነገር መፈትፈቱንም ትቼ ወደ ፅሁፌ ልግባ።  ከሁለት ቀን በፊት በየኔ ዜማ Album፤አስመሪኖ truck inspired ሆኜ ስለ ፀሀይቱ ባራኺ አባሻዉል ዝተባህል ዘፈኗ ጥቂት ነገር ብዬ ነበር። እዛው ፅሁፍ ላይ አብርሃም አፈወርቂ'ን(ሰማይ) እንደ መግቢያ ተጠቅሜ ሌላ ቀን በሰፊው እንደምመለስበት ተናግሬ(ቃል ገብቼ ) ነበር። ይሄም ፅሁፍ ስለ አብርሃም አፈወርቂ አንዳንድ ጉዳዮችን እያወሳ ያወራል። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨                          ሰማይ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ (...በሙዚቃ ጥበብ ሚስጥር ባሳለፍነው ድብቅ ፍቅር ሰማይ ይዤ ናፍቆኝ መጣሁ አብርሃምን ያየው አጣሁ...) ሁለት አስርት የኩርፊያ አመታት፤የወንድማማቾችን ፈገግታ ተከረቸም አበጁለት። ሀያ አመት ጎረምሳነቱን የጨረሰ ወጣት እድሜ ነው። በፅሁፌ አመታትን ማንሳቴ በቂ ምክንያት አለው ለአሁኑ ግን ገታ ላ'ርገው'ና ሌላ ሀሳብ አንስቼ ልመለስ። አንድ ወዳጄ የኪነትን አቅም ሊቋቋም የሚችል ሀይል የለም ይላል። ኪነት...ስሜት ምትዘየርበት የጠቢብ መንገድ ነች። ኪን ግጥም ነች። ኪን ሙዚቃ ነች። ኪን..... ቃላት መፅሄት ቅፅ አንድ ላይ(የሄኖክ በቀለ አምድ) “ኪነትን የማያውቅ ጨካኝ ህዝብ” የሚል አርዕስት ያለው ፅሁፍ እንዲህ ይለናል። ቦታ ቋሚ እውነት አይደለም ይፈርሳል ይታደሳል። ጊዜ ግን መኳንንት ነው፤ ይጠይቃል እንጂ አይጠየቅም። ፀሀፊውም  ወረድ ብሎ አሁን ያለንበትን ዘመን Dystopian ዘመን እንደሆነ አረዳን። ምቾት ባይሰጠውም ለቃሉ የሰጠው አቻ ትርጉሞች እኚህ ናቸው....በሰው ስቃይ የፋፋ፣ ፍትህና ርትዕን የገፋ፣ጥዩፍም ንቁፍም(Dystopian)።  ፀሀፊው The live of other's(“das leben der andren) በተሰኘ የጀርመን ፊልም ላይ በፅሁፉ አውድ(context) ዳሰሳን አቀረበልን።(እኔም ይሄንን ሁሉ ስዘበዝብ ስለ ኪን ብሎም ስለ አብርሃም(ሰማይ) የጀመርኩትን ፅሁፍ አውድ(context) ረስቼ ስላልሆነ በትዕግስት አንብቡልኝ።) ፊልሙ ላይ “ዊስለር” የተባለ ልበደንዳና የስታሲ ሰላይ ለስላሳ የጆሮ ማዳመጫ ካደረገበት(ሊሰልለው) “ደራሲ ድሬይማን” ቤት በሚለቀቅ “sontana for a good man” በሚል ሙዚቃ ሲያለቅስ ይታያል። ተሰላዩ ደራሲም ዊስለር(ሰላዩ) እንደሚያደምጠው ባያውቅም እንዲህ ይላል.….can any one who hered this music, i mean truly heard it really a bad person?(ይሄንን ሙዚቃ የሚያደምጥ፤ማለቴ ከልቡ ይሄንን ሙዚቃ የሚያደምጥ መጥፎ መሆን ይቻለዋልን?) ኪነት ልብን ያራራል። ኪነት ልትገድለው ካሰብከው ሰው ጋር የጋራ ህልም፣ የ ጋራ ህመም ፣ የጋራ ስቃይ ፣ የጋራ ፍላጎት፣ የ ጋራ ተስፋ እንዳለህ ይነግርሃል። ይህንን እያወክ እንዴትስ ልትጨክንበት ትችላለህ? ጠላቴ ያልከው ሰው አንተ የምትወደውን ሙዚቃ እንደሚወድ ማወቅ፣ አንተ የምትወደውን መፅሀፍ እንደሚሳሳለት መረዳት፣ የወገንነት ስሜት እንዴት አይፈጥርብህም? በፊልሙ ማብቂያም “ዊስለር” እንዲሰልለው በታዘዘው የ“ድሬይማን” ህይወት ሲነካ'ና ያልተጠበቀ መልካምነት ሲያሳየው ይታያል። ለምን? ኪን የሚገባው ህዝብ ስስ ነዋ።(ቃላት መፅሄት ቅፅ ፩) አብርሃም ከያኒ ብቻ አይደለም ለ'ኔ። ወደ ራሷ ኪን ይጠጋብኛል።  ሰማይ እያለ ሲያዜም ጠንከር እላለሁ። ምስጢር ፍቕሪን፣ ትምኒተይን ስሰማ አካሌ ይባባል። መለይ ሲል ከአውዱ 'ወጣለሁ። በ አባቷ ወገን ነው መኖር ምትችለው ተብላ ባፍላነቷ  ከ'ናቷ ያለውዷ ጦርነት የለያትን መለይ የምትባል cousinኔን አስታውስበታለሁ። ከ ሃያ ምናምን ዓመታት በኋላ ከኛ ከቤተሰቦቿ ስትገናኝ ያለቀሰችው ውል ይልብኛል። ብበዘሊናዮን ሲያቀነቅን ምናቤ ያፈቅራል። አይዞህ ባይ እያሻኝ የምናቤን እንስት አጆሂ እላታለሁ። አብርሃም በኔ ቤት ስሜቶቼን ምስልበት የድምፅ ቀለም ነው። ድባቴዬን ማባርበት ዛር። ከአብርሃም የተዋወኩት በምጠላው ሳይሆን በጣም እጠላው በነበረ ሰው ነው። ሰማይን ሲያደምጥ ጆሮዬ ውስጥ ገባ። ሰማይን ማድመጥ ጀመርኩኝ የትርጉም ችግር እያለብኝ። ከዛም ሰው ጋር ተወዳጀሁ ምን እንደሚልም ነገረኝ። የማላቀው ክራር ገራፊ ከዚህ ሰው አወዳጀኝ።  ታዲያ “can any one who hered this music, i mean truly heard it really a bad”?  ማለት ለኔ አይደለምን? አብርሃም ጥቅምት 7/2006 ኤርትራ ምፅዋ በ አርባ ዓመቱ ይቺን አለም ጥሏት ሄዷል(ቀረባት)። መንዛዛት እንዳይሆንብኝ ሰማይ የሚለው'ን lyrics ትግረኛውን ወርስ በሆነ የአማርኛ  ትርጉም አስቀምጬ ፅሁፉን እቋጫለሁ( ውርስ ትርጉሙን ካወላገድኩት ከወዲሁ ይቅር በሉኝ🙌)  ሙዚቃውንም ከዚሁ ፅሁፍ በታች አኖረዋለሁ። «..ሰማይ... ኩሉ ሓላፋይ'ዩ ኢለ ገሚተ ስግር ጋሻ ውሕጅ ጠሚተ እጽዕር ኣለኹ ብተስፋ ነዛ ሕማቕ እዋን ክሓልፋ እጽዕር ኣለኹ ብዓቕመይ ቃልሲ'ስ መናብርተይ ናይ ቀደመይ ንግዚኡ'ኳ እንተሓየለኒ እስዕሮ እምበር ኣይስዕረንን ጸገመይ ተስፋ'ዩ ደገፈይ ተስፋ እዩ ሓይለይ ደጋጊመ እጽዕር ክሳብ ዝሰምረለይ ይጥዓም ይሕሰም ፍሽኽታ ኣመለይ) (....ሁሉ አላፊ ነው ብዬ ስለገመትኩኝ እንግዳ ጎርፍ ብመለከትም ተሻገርኩኝ። እየጣርኩም ነው በተስፋ፣ ይህቺን መጥፎ ጊዜ ላልፋት፣ እየጣርኩ ነው ባ'ቅሜ። መታገልስ አብሮኝ ኗሪ ነው ከቀድሞም፣ ለጊዜው አየለብኝ እንጂ በረታ፣ ሆኖም እረታዋለሁ እንጂ አይረታኝም። ተስፋ ነው ድጋፌ ተስፋም ነው ሃይሌ ደጋግሜ እለፋለሁ እስከሚሰምርልኝ ይክፋም ይድላም(ይጣም፞ም፞ ይምረር) መሳቅ ነው አመሌ።) ፍሽኽታ ኣመለይ ኩሉ ጸይረ'የ ፍሽኽታ ኣመለይ ፍሽኽታ ኣመለይ ይጥዓም ይሕሰም ፍሽኽታ ኣመለይ ፍሽኽታ ኣመለይ ኣይሕለልን ክሳብ ዝሰምረለይ ፍሽኽታ ኣመለይ እስዕሮ እምበር ኣይስዕረንን ጸገመይ ) (...መሳቅ ነው አመሌ ሁሉን ችዬ መሳቅ ነው አመሌ መሳቅ ነው አመሌ ይጣም ይምረር መሳቅ ነው አመሌ መሳቅ ነው አመሌ አልንበረከክም እስከሚሰምርልኝ መሳቅ ነው አመሌ እረታዋለሁ እንጂ ችግሬ አይረታኝም..) ናብራ ከቢዱኒ እንዳማረርኩ፣ ጥዕና ዘይብሉ ምስ ረኣኹ፣ ኣጸናኒዐያ ንነብሰይ፣ ኣረጋጊአዮ መንፈሰይ። ለካ ወሃቢ እምበር ኣይኮንኩን ሓታቲ፣ ተጸባዪ ኣይኮንኩን ተመጽዋቲ፣ ጥዕና ኣይትኽልኣኒ ምስ ተስፋ፣ እምረር እምበር ህይወት ከሰንፋ፣ ሙኻነይ እነኹ ኣሚነ፣ ዝሓዝክዎ ሒዘስ ኣመስጊነ። ኑሮ ከብዶኝ እያማረርኩ፣ ጤና የለሌውን ተመለከትኩ። አፅናናኋት ነፍሴን፣ አረጋጋሁት መንፈሴን። ለካ ሰጪ እንጂ አይደለሁም ጠያቂ፣ ተመፅዋች አይደለሁኝ ጠባቂ። ጤናን አይሳኝ ከተስፋ ጋር ሂወትን ላሸንፍ ምንም ቢመር መሆኔን አለሁኝ አምኜ የያዝኩትን ይዤ አመስግኜ...)
إظهار الكل...
Repost from አቦል
ዘመስግን'ዩ ዕጉስ ዝዕገስ'ዩ ሓያል ዘዋህልል'ዩ ለባም ይኣኽለኒ ምባል ዝፈልጥ'ዩ ሃብታም ክበሃል ሰሚዐ እንተስ ኣሚነሉ እንተስ ክጸናናዕ ግን ተሰማሚዐ ድሓን ክሓልፍ'ዩ እንዳበሉኒ እኳ ብዓይነይ ርእየ ኣቤት እወ ክንደይ ድዩ ሓሊፉ) (...አመስጋኝ ነው ታጋሽ 'ሚታገስ ነው ሃያል፣ 'ሚቆጠ፞ብ ነው ልባም፣ ይበቃኛል ማለት የሚያውቅ ነው ሃብታም ሲባል ሰምቼ አምኜም ይሁን ፥ ለመፅናናት ግን ተስማምቼ ደህና ያልፋል እያሉኝ'ኳ ባይኔ አይቼ አቤት ስንቱ ነው ያለፈው?...) እወ ሙኻን ሕስብ ተበልክዎ ስፍሓት ህይወት ከም ዝተረዳእክዎ ነቲ ጽቡቕ ዝበለጸ 'ለዎ ነቲ ሕማቕ ዝበኣሰ 'ለዎ ነቲ ጣዕሚ ዝጠዓመ 'ለዎ ነቲ ሕሰም ዝመረረ 'ለዎ ጫፍ ጽቡቕን ሕማቕን ዓቂነ ከለልዮ ወላ እንተፈቲነ ኣበይ ከይክእሎ ኣነ ሰብ 'ዚ ኣነ (..አዎ ሁነትን ሳስበው፣ ስፋቱን ጥልቀቱንም ስረዳው፣ ለጥሩ(ለመልካምም) የበለጠ አለው። ለመጥፎውም የባሰ አለው። ለጣፋጩ የጣፈጠ አለው። ለኮሶውም የመረረ አለው። የጥሩ'ና የመጥፎ'ን ጫፍ ለክቼ ልለየውም ብፈተንም መች ሊሆን ሰው ነኝና...) ዓለም ከም ባሕሪ'ያ ከም ዝበሃል ክሕምብስ ዘይክእል ንኸይጥሕል ሓቢርና'ዶ ጸገምና ነቃልል ክንበላሓት ዝያዳ ክንጋደል ስለ'ቲ ሽግር ትወልዳ ንጥበብ ብኣካል ብመንፈስ ንራኸብ ህይወት ከነማሓይሽ ክንላዘብ) (...ዓለም በባህር እንደምተመሰል፣ እንዳይሰምጥ፤መዋኘት ግን የማይችል አብረን ችግራችንን እናቃልል? መላ በሉ እንግዲህ እንጋደል(survival) (እንጎብዝ ችግራችንን ለመቅረፍ ሰው በዓለም እንዳይሰምጥብን፣ ችግር ጥበብን እንደ'ምትወልድ፣ በአካል በመንፈስ እንጋመድ። ህይወትን እንዲሻሻል እንዲል ለዘ፞ብ) ክሳብ ዝኾነለይ ክሳብ ዝሰምረለይ ውቅያኖስ'ዩ ዓቕለይ ትስፉው'ዩ ጠመተይ ኣይዕገትን'የ ሰማይ'ዩ ደረተይ) (...እስከ'ሚሆንልኝ እስከ'ሚሳካልኝ ውቅያኖስ ነው አቅሌ ተስፋ ነው እይታዬ(ወደፊቴ) አልታገትም(አልደናቀፍም) ሰማይ ነው ደረቴ..) ክሳብ ዝኾነለይ ክሳብ ዝሰምረለይ ኣይጽንቀቕን'ዩ ሓይለይ ትስፉው'ዩ ጠመተይ ኣይሕለልልን ሰማይ'ዩ ደረተይ) እስከ'ሚሆንልኝ እስከ'ሚሳካልኝ አይጨለጥም ሃይሌ ተስፋ ነው ወደፊቴ አልረታም ሰማይ ነው ደረቴ ሰማይ ሰማይ ሰማይ ሰማይ'ዩ ደረተይ (..ሰ..ማ..ይ   ሰ ማ ይ ሰማይ ሰማይ ነው ደረቴ..) ©ናታን ኤርሚያስ Share to your loved ones ለሚወዷቸው ያጋሩልን . @nathanErmias @nathanErmias
إظهار الكل...
Eritrea music Abraham Afewerki - Semai/ሰማይ Official Audio Video
إظهار الكل...
እምነት መጥፎ ይሁን ጥሩ ማሰብህ አንተ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በእምነትህ ልክ ነው። 🔋መጥፎ ነገር ይከሰታል፣ ይህን ማድረግ አልችልም፣ እኔ ቆንጆ አይደለሁም፣ ድህነት እጣ ፈንታዬ ነው.... ባልክ ቁጥር ህይወትህን ጨለማ ውስጥ እየከተትክ ትመጣለህ። 🔋 በተቃራኒው ህይወትህን መለወጥ እንደምትችል ካመንክ ህይወትህን ትለውጣለህ። ✅ አንተን የሚገድልህም ሆነ የሚያድንህ እምነትህ ነው። Share @eiduka🦋
إظهار الكل...
📌 መቼም ቢሆን እጅ አትስጥ ✔️ በወደቅክ ቁጥር ተነስ ✔️ በተሳሳትክ ቁጥር አስተካክል። ✔️ ባልተሳካልህ ቁጥር እንደገና ሞክር። ✔️ ህይወት ልታሳዝንህ በሞከረች  ቁጥር በግድም ቢሆን ፈገግ በል፡፡     @eiduka 🦋
إظهار الكل...
🎚️ በህይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰም ነው። የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም። ✍️ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት። ስኬት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከሌሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም። Share -> @eiduka🦋
إظهار الكل...
2
አምና ወይ ታች አምና ውሃ የለበሰች አብረቅራቂ ገላ አካል የታቀፈች በነበር በነበር የቀራት ቁንጅና እድሜዋ ሳይከትም ቀረበች ለእርጅና እና.... ሽክርክር ስንጥቅጥቅ እድፍድፍ   የሚለው የገላዋ ጉድፍ ማን ነበረች እሷ? የሚል ቃል ያስነሳል ወትሮስ ውበት ሲሄድ ወዴት ይደረሳል መድረሻ እንደሌላት              የእርሷ መጨረሻ ደረስኩ ያለች ቀን ነው ሚሆናት መነሻ አይን እንዳላያት    ልብን እያቆመ          ቀልብን እያራቀ ዛሬ ዛድያ ምነው     ውበት ሚሉት ነገር ከአካሏ ራቀ ያን መሰል ከናፍር ቀማሹ እንዳልበዛ ምነው ዛዲያ ዛሬ የእርሷ ከንፈር ብቻ በእድፍ የተወዛ ጥሩ ወርቅ እያሉ ስምን እንዳልቸሩሽ ላንቺ እንዳላወጡ በአሽሙር በነገር ሎሚ ናት ይሉሻል ቅጥሽ በመጥፋቱ እንደ ሎሚ ቃና ተመጠሽ ተመጠሽ ጥፍጥናሽን ወስደው እድፋም ናት ይሉሻል ውበትሽን ንደው ወንድ ነኝ ባይ ሁላ ቆሞ እንዳልጠየቀ ለአንድ አዳር ምሽት ዛሬ እንዴት ይሮጣል ካንቺ ገላ ሽሽት የምትኳይበት...የምታግጭበት ብራብርሽ ጠፍቶ ገላሽን አውድቋል ጎዳና ላይ ወቶ ይኸውልሽማ... ፀሃይ ከ ጨረቃ በሚፈራረቀው በዚች ጠባብ አለም ለጊዜው ነው እንጂ ለዘላለም ብሎ ሚፈልገን የለም ያስለመድናቸውን አንዲቷን ባህሪ ድንገት ብትጠፋ ለምንን ጠይቆ የተፈጠረውን ለማጥፋት አይለፋ ይኸውልሽማ... የደረሰብሽን ይህ ሁሉ ታዝበሽ አሜን በይ ወደላይ ፍርዱ ፈጣሪ ነው     ሌላ ደጅ እንዳታይ። የገፉሽን ሁሉ አልፈሽ እራቂያቸው የናቁሽን ሁሉ በአካል ናቂያቸው ሁሉም ፈራሽ ገላ ቀኑን የማያውቀው እንዴት ሲል ያንቺን መልክ በአፍ አወደቀው ይኸውልሽማ... ናቂያቸው ናቂያቸው ናቂያቸው የገፉሽን ሁሉ ንቀሽ እለፊያቸው። ዮኒ      ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan @Hasabawian @Hasabawian
إظهار الكل...
🌹🌹💖 " #ይድረስ _ለሄዋኔ " 💖🌹🌹 ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለእኔ ..................ይልቅስ ሄዋኔ ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ ከቻልሽ ነይልኝ ፡ካልሆነ እኔ ልምጣ ግን ልትመጪ ከሆነ ፡መንገድ ሳትጀምሪ ማንነቴን ሰምተሽ ፡ከቀረሽም ቅሪ ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ ቤት ማጀቴ ፡ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ ልብሴም ድሪቶ ነው ፡ፊቴም ውበት የለው ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ፡ያቆሰለው ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ ሳይረታሽ ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ፡ወደ እኔ ከመጣሽ እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ........በደስታ ፈንጥዤ በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡ 😊😊☺️😊 Share|| 👉 @eiduka🦋
إظهار الكل...
2
​​​​​​​ ❤️ እኔ #አንተን ከማጣ😘 ...እኔ አንተን ከማጣ....❤️ ደመናው ይቆጣ #ያዝንብ ፡ ሚስማር ከላይ ሲፈልግ ደጎራ ፡ ሲያሻው #ጥርብ ድንጋይ ፀሃይ ብርሃን ታቁም ፡ ስትፈልግ ትበተን ምድር ዱቄት ትሁን ፡ ሲያሻት ከስላ ትብነን ጨረቃም ትሠወር ፡ አትውጣ እድሜ ልኳን ። እኔ አንተን ከማጣ...😘 ስትፈልግ የሎጥ ሚስት ፡ ጎጃምኛ ትምታ😁 የፈርኦን ሠራዊት ፡ እስራኤልን ይቅጣ😊 የኤርትራም ባህር ፡ ይኑር በከፍታ ። እኔ አንተን ከማጣ... እፅዋት #ይድረቁ ፡ እንስሳት #ይለቁ ፕላኔቶች ሁሉ : ምድር ላይ ይውደቁ ። እኔ አንተን ከማጣ... ዳይኖሠር #ተነስቶ ፡ በምድር እሣት ይትፋ #ምፃት ነገ ይሁን : አለም ካለም #ትጥፋ ። እኔ አንተን ከማጣ... ምድረበዳው ያዝንብ : ኤርታሌም ይወርዛ #ብልፅግና ፓርቲ አስር ሺህ ዓመት  ይግዛ!😁 ሲፈልግ ተሻግሮ ፡ አለማትን #ይንዳ ። እኔ አንተን ከማጣ... ማወቅ ድብን ይበል : ባፍ ጢሙ ይደፋ #ክፉወች ወፍረው : መልካም አንገት ይድፋ ። እኔ አንተን ከማጣ.... ፈጣሪ አሲድ ይርጭ : ምድሪቱን ያጉርፋት ቁጣውን ያበርታ : አይዳኑ ፍጥረታት ። እኔ አንተን ከማጣ..... ማንም ምንም ይምጣ !🤗 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@eiduka🦋
إظهار الكل...
💛💛 ህይወትን የሚያስውቡ ውብ ሰዎች አሉ። ሳትፅፍ ያነቡሀል። ሳትናገር ይረዱሀል። ውለታን ሳይሹ መልካም ይውሉልሀል። በእነዚህ ሰዎች ውስጥ መኖር ህይወትህን ውብ ያደርገዋል።🤍 ☺️😊 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 𝐒𝐇𝐄𝐑 @eiduka @eiduka
إظهار الكل...