cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Sexual purity

For God hath not called us unto uncleanness, but unto holiness. 1Thessalonians 4:7 ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4 : 7

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
4 785
المشتركون
-224 ساعات
-117 أيام
-6930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

02:09
Video unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ🇪🇹በቅርቡ ግብረሰዶማዊነት ፣የጾታ መቀየር፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የቀረበን ሰነድ ፈርማለች። 😭 ይህም ሰነድ በዚህ አንድ ወር ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ይጠበቃል።🤯 ለዚህም መቃወሚያ Petition በትንሹ 50,000 ፊርማዎችን ለማሰባሰብ በዚህ Link እንሳተፍ። 🇪🇹Say NO!! ታሪክ የማይረሳውንና  እስከትውልድ ጥግ  በመልካሞቹ የሚዘከረውን ይህን movement በደስታ ተቀላቀሉ!!! Petition ለመፈረም https://keap.page/gq193/.html Tiktok https://vm.tiktok.com/ZM66xSPCn/ Telegram Group join ለማድረግ https://t.me/+ZtUngZzXFUIzOTZk
إظهار الكل...
13.71 MB
👍 18 3😭 3😁 1
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
There is nothing true about "Safe Abortion", in every #abortion two persons are #harmed and one definitely #dies. If it kills one and harms the other, It is #NOT safe. It is #EVIL. #AbortionIsEvil #PalahEthiopia
إظهار الكل...
👍 45👏 8 7🔥 6👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
6.07 KB
“ጌታን መቀበል እፈልጋለሁ፤ ከሱስ መላቀቅ ፈለጋለሁ እባከሽን እርጂኝ፡፡” ሰላም እንዴት አላችሁ፡፡ ዛሬ ከረጅም ጊዜ በኋላ እንደገና በአንድ ህሳብ ላይ ለመነጋገር መተናል፡፡ምናልባት ብዙዎቻችን በተለያየ ሁኔታ ገጥሞን ሊያውቅ ይችላል በተለይ ሴት እህቶች ላይ የተለመደ እነርሱን የማጥመጃ መንገድ ሆኖ ብዙዎችን ወደኋላ ያደረገ ጉዳይ ነው፡፡ በቅርቡ አንድ ሰው ለ አንዲት እህት ይደውላል፡፡ ሰላምታ ከጠያቃት በኋላ እሷ የምትሰራበት መስሪያ ቤት እንደሚሰራ ፤ አብዛኛውን ግዜ የመስክ ሰራ ላይ እንደሚውል እንዲሁም ስልኳን ከሰዎች እንደወሰደ ጌታን መቀበል እንደሚፈልግ እና እሷም በዚህ አብራው በመሆን እንድታግዘው ይጠይቃታል፡፡ በተደጋጋሚም ይደውላል፡፡ እንዲሁም በቴሌግራም እንድታወራው ይሞክራል፡፡ ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ተኩላ ነዉ ታዲያ የብዙ አሰናካዮች (ተኩላዎች ብላቸው ይቀለኛል) የማጥመጃ መንገድ ናት፡፡ “እባክሽን ጌታን መቀበል እፈልጋለሁ፤ወደጌታ ቤት መመለስ እፈልጋለሁ፤ ከሱስ መላቀቅ እፈልጋለሁ” የምትል ማባበያ አለቻቸው፡፡አንድ ወዳጄ እንዲህ ይላል “ጨው ውሀ ልትቀዳ ወንዝ ወረደች፡፡” አንዳንድ እህቶች በየዋህነት እንደዚህ አይነቱን ለማቅናት ብዙ ሲዳክሩ ተመልክተናል፡፡ እንዲሁም ለራሳቸው የሚሰጧት የማፅናኛ ቃል አለቻቸው፡፡ “በእኔ ምክንያት እኮ ቤ/ክ መሄድ ጀምሯል፤መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ ጀምሯል፤ ጥሩ ልብ አለው እኮ፤ ደግሞ ሲያሳዝን” እያሉ በከፍተኛ ፍጥነት ራሳቸውን አልጋ ላይ አግኝተዋል፡፡በኔ ምክንያት ጥሩ እየሆነ መጣ፤ ካሉት ሰው በላይ በህይወታቸው ራሳቸውን ማየት በማይፈልጉበት ቦታ ራሳቸውን ያገኙ ብዙዎች ናቸው ጨው ውሀ ልትቀዳ ወንዝ እንደወረደችው፡፡ ይልቅ የተሻለ እና ተጠያቂ የማያደርገን መንገድ አለ፡፡ አንድ ሰው ጌታን መቀበል ወይም ዳግም ወደ ጌታ ቤት መመለስ ከፈለገ ይህንን አገልግሎት የምታገለግል ቤ/ክ ለዚሁ አገልግሎት የተቀመጡነ የቤ/ክ መጋቢዎች ጋር እንዲገናኙ ማመቻቸት፤ የመጋቢዎችን ስልክ በመስጠት የቤ/ክ አቅጣጫን በማሳየት ልንተባበራቸው ይገባል፡፡ እንዲሁም ከሱስ ህይወት መላቀቅ ለሚፈልጉ ጥሩ ጥሩ የሱስ ማገገሚያ ቦታዎች እንዲሁም የህክምና ማዕከሎች ስላሉ ሄደው አገልግሎቱን እንዲያገኙ መንገር ተገቢ ነው፡፡ ይህንን ፅሁፍ ያነበባችሁ የራሳችሁን ታሪክ ልታካፍሉን ትችላላችሁ፡፡ 0983840757 - በቴሌግራም በፅሁፍ አስቀምጡልን፡፡ @sexualpurity @sexualpurity
إظهار الكل...
ይህንን ፀሎት ከአንድ መፀሀፍ ላይ አገኘውት ( የመፀሀፉ ርዕስ አሁን ትዝ አይለኝም) በጊዜው በጣም አስደንቆኝ ማስታወሻዬ ላይ ፅፌው ነበር፡፡ ምንአልባት አንድ ሰው ከጠቀመ ብዬ ላጋራችሁ አሰብኩ፡፡ ፀሎት 🧎ኦ ልበ ትሁትና የዋህ የሆንህ ኢየሱስ ሆይ ስማኝ አጥብቄ መወደድን ከመፈለግ አድነኝ፡፡ ከፍ ከፍ ማለትን ወይም መወደስን ከመፈለግና አድነኝ፡፡ ክብርን ከመፈለግ ምስጋናን ከመፈለግ አድነኝ ከሌሎች ይልቅ ቅድሚያ እንዳልፈልግ ጠብቀኝ ከሌሎች ይልቅ አዋቂ ሆኖ መገኘትን ከመሻት አድነኝ የሰዎችን ይሁንታና አዎንታን ከመፈለግ አድነኝ፡፡ 🧎ኦ ኢየሱስ ሆይ ዝቅ ዝቅ ማለትን ከመፍራት መናቅና መጠላትን ከመፍራት ተግሳፅን ለመቀበል ከመፍራት እንዳይበድሉኝ ከመፍራት ሰዎቸ እንዳይጠረጥሩኝ ከመፍራት ታደገኝ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሌሎች ከእኔ ይልቅ እንዲወደዱ ሌሎች ከእኔ ይልቅ ከብረው እንዲታዩ የመፈለግ ፀጋን ስጠኝ በዓለም ዓይን ሌሎች ከእኔ ይልቅ ልቀው ይታዩ እኔ ግን አንሼ ልገኝ ሌሎች ሲመሰገኑ ኔ ግን አንሼ ልገኝ አስታዋሽ ማጣትን እንድቀበል አስችለኝ መሆን የሚገባኝን ያህል በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኜ ከተገኘው ከእኔ ይልቅ ሌሎች ቅዱሳን እንዲባሉ መፈለግን ስጠኝ አሜን🙏 @sexualpurity
إظهار الكل...
እኛ ስሙኝ ስሙነኝ እማ እኛ 1ኛ- ሰለ ህይወት የምንሟገት በፍጥረት መጀመሪያ በታላቁ አምላክና ፈጣሪ የተመሠረተውን የሰው ልጅ ያልጀመረው በወንድና በሴት መካከል ብቻ የቆመውን ክቡር ጋብቻንና የምናከብር ደግሞም ለእንደዚህ ዓይነቱ ጋብቻ ብቻ እውቅና የምሰጥ፤ 2ኛ- የሰው ልጅ ከፈጣሪው እስትንፋሰ የተቀበለው በሕይወት የመኖርና የመተንፈስን መብት ከማህፀን ጀምሮ እንዳለው የምናምንና የምናከብርና ለእርሱንም የምናቀነቅን እንጂ አሁን በድህረ ዘመናዊት የራሳቸውን ማንነትና እዉቅናን ከመወለድ በኋላ ብለው እንደሚያስቡ ያልተወዛገብን፤ 3ኛ- ታላቁ ፈጣሪ ያስቀመጠውን ማንም ሰው ሊያበጀው ሊያሻሽለው የማችለውን የወንድን ማንነትና ልዩ ድርሻእንዲሁም የሴትን ማንነትና ልዩ ድርሻ የምናከብር ከዚህም የተነሣ በሁለቱ መስተጋብር የሚፈጠረውንና የሚገለጠውን የፈጣሪን ውበት የምናደንቅ በፈጣሪ የተሠጠንን የማይተካካና የማይወዳደር የወንድነትና የሴትነትን እጅግ ልዩ ውበት የገባን በፈጣሪ ያልተቸረንን ማንነት ከአደባባይ በመፈለግ የማንደክም የተፈጠርንለትን አላማ የገባን በማንም የማንደለልና የማንታለል የማንደናገር፤ 4ኛ- ፈጣሪ በወላጅና በልጅ መካከል ያስቀመጠውን የከበረ ሥርዓት የተገነዘብን ማንም የማይነጥቀን ለመስጠትም የማንደራደርበትን ልጅን የመምራት መንገድ የማሣየትን አደራ አሣልፈን የማንሰጥ የተዋልዶ ደህንነታቸው የተሣካ እንዲሆንላቸው እንጂ በመብት ሽፋንን የተዘጋጀላቸው ስውር መርዝ እንዳይጎነጬ እየቀደምን የምንደፋላቸው ነን። 5ኛ- ደግሞም አጥብቀን ውርጃን (abortion) ግብረሠዶማዊነትን (homosexuality)አክራሪ ሴታዊነትን(radical feminism ) እና የነዚህ ማስተግበሪያ የሆነውንና ከአምላካዊ የፍጥረት የአካሄድ ሥርዓት የሚያስት ሆኖ በትውልድን መንገድ የተጋረጠና መረን የሚያስወጣውን ሁሉንአቀፍ የጾታ ትምህርትን ( Comprehensive Sexuality Education/CSE) አጥብቀን አጥብቀን አጥብቀን የምንቃወም ስብስቦች ነን። 6ኛ- እጅግ ርህራሔ በጎደው ሁኔታ ወጣቶችና ህፃናት ስለራሣቸው መምረጥና መወሰን በማበረታታት ያለ ወላጅ እውቅና የተዋልዶ አካላቸውን በህክምና በማስለወጥ የዘለቄታ የአካል የስነልቦናና የአእምሮ በቀውስ የሚያስከትልን የፆታ ማስቀየር (trangender)እንቅስቃሴንና በዚህ ንግድ ዋና ተዋናይ የሆነውን International plan parenthood Federation (IPPF) አጥብቀን እንቃወለን 7ኛ- እኛ በፈጣሪ ማንነት የተፈጠርን እንጂ ማንነታቸው እንደጠፋባቸው ከዝንጀሮ መጣን ወይም አምላክ የለም ብለው በማሰብ እንደሚቸገሩቱ የማናስብ ያልሆነውን ለመሆን የማይመጥነን ልካችንን የምናውቅ የፈጣሪ ልጆቹ ነኝ። ስለዚህ ይህ አቋም አቋማችሁ የሆነ በሁሉም ኃይማኖት የምትገኙ የተከበራችሁ ለዚህ ክብርን ለሚያስጥል አስተሳሰብ የማትንበረከኩ ራሳችሁን ቤተሰባችሁን ማህበረሰባችሁን አገራችሁን ወጋችሁንና እምነታችሁን ለገንዘብ የማትሸጡ የሰው ልጆች ሁሉ ኑና ተቀላቀሉን። አላማችን ኢትዬጲያችንን ከባህል ወረራም (Cultural Imperialism) መታደግና መታደግ ብቻ ብቻ ብቻ ነው። ታሪክ የማይረሳውንና እስከትውልድ ጥግ በመልካሞቹ የሚዘከረውን ይህን movement በደስታ ተቀላቀሉ!!! ሣባ ነኝ
إظهار الكل...
እንዴት ናችሁ ሰሞኑን ጳዉሎስ ሆስፒታል ከአንድ አባት ጋር እያወራን በጨዋታ መሀል አንድ ጥያቄ ጠየቋቸው፡፡ እንዴት ነው ወደ ወጣትነት ዘመኖ ቢመለሱ ምን ያስተካክሉ ነበር? #_አይ_ልጄ_የእግዚአብሔርን_ቃል_አነብብ_ነበር_እንደቃሉም_እኖር_ነበረ ፡፡ ይገረምሀል ያልሞከርኩት ነገር የለም እጠጣለው አጨሳለው ይኸው ሲጋራ ካቆምኩኝ አምስት አመት አለፈኝ እስከ አሁን ድረስ ያስቸግረኛል፡፡ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፡፡ አባቶች እንደዚህ ይሉ ነበር ስለ #መጠጥ ወደ መጠጥ ቤት (🕊 #እንደ_እርግብ_ትገባለህ ) ጨዋታው ይጀመራል (🦧 #እንደ_ዝንጀሮ_ታስካካለህ) ቀጣይ መናደድ ትጀምራለህ (🐅 #እንደ_ነብር_ትቆጣለህ ) መሳደብ መጣላት መደባደብ ትቀጥላለህ (🐖 _ #እንደ_አሳማ_ተጨመላልቀህ_ትወጣለህ) ጠቢቡ ሰለሞን ሊያስተምረን ሲጀምር እንዲህ አለ፡ (መጽሐፈ መክብብ 1 ) ------------ 2 ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል። 3 ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው? ደግሞ ሲጨርስ እንዲህ አለ " #የነገሩን_ሁሉ_ፍጻሜ_እንስማ ፤ #ይህ_የሰው_ሁለንተናው_ነውና ፤ #እግዚአብሔርን_ፍራ፥ #ትእዛዙንም_ጠብቅ ።" (መጽሐፈ መክብብ 12: 13) abeni 24:19 @sexualpurity
إظهار الكل...
ውለታ ወይስ ግዴታ! ለባለትዳሮች . . . ለትዳር አጋራችሁ የምታደርጉትን ነገር እንደ ውለታ ከቆጠራችሁት የትዳር ትርጉሙ አልገባችሁም ማለት ነው፡፡ ለፍታችሁ ገንዘብ ስላመጣችሁ፣ የቤት ውስጥ ስራ ሸክም በጋራ ስለተሸከማችሁ፣ አጋሮቻችሁ በህመም፣ በወሊድ ወይም በመሳሰሉት የሕይወት ግዴታዎች ውስጥ ሲያልፉ እነሱ ያቃታቸውን በመሙላታችሁና አብራችኋቸው በመቆማችሁ፣ ልጆችን በመንከባከባችሁ . . . ከመንገዳችሁ ወጥታችሁ ለአጋራችሁ ውለታ እያደረጋችሁላቸው እንደሆነ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ለትዳር አጋራችሁ፣ ለቤታችሁና ለልጆቻችሁ የምታደርጉት ነገር በሙሉ ግዴታችሁ ነው! ይህንን ዝንባሌ ለማረም ከፈለጋችሁ ለእኔ የሰራልኝን ልምምድ ላጋራችሁ፡፡ የትዳር አጋሬ ለእኔም ሆነ ለቤታችን የምታደርገውን ማንኛውንም ነገር ልክ እንደውለታ በመቁጠር አመሰግናለሁ፤ እኔ የማደርገውን ነገር ደግሞ ልክ እንደ ግዴታ በመቁጠር ሃላፊነቴ ላይ አተኩራለሁ፡፡ ይህ ልምምድ ለአንዳንዶች የማይስማማና ሚዛን-ጎደል ቢመስልም ለተጠቀሙበት ግን የሚሰራ ልምምድ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...