cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዲናችንን እንማማር ...

ኣጫጭርና እና ቁምነገር ኣዘል የሆኑ ፅሁፎችን ያነባሉ ። 📖📚 ⬇⬇⬇ @click2Join https://t.me/click2Join , , , " እስልምና ማለት ሁሉንም የህይወት ዘርፍ የሚመለከት የተሟላ ስርዓት ነዉ " Use this bot 👇 to contact us @Click2contactus_bot

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
194
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ዒድ ሙባረክ
إظهار الكل...
*ለይለተል-ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? * እናታችን ዓኢሻ ረዲየ ‐አላሁ ዓንሀ እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለይለተል-ቀድርን ባገኝ (ያቺ ለሊት ለይለተል-ቀድር መሆኖን ባውቅ) ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ብዬ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም:- "አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሂቡ አል-ዓፍው ፈዕፉ ዓኒ " በይ አሉኝ:: ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ ) ማለት ነው። (ቲርሚዚይ፣ኢብኑ ማጃህ፣ ኢማሙ አህመድ እና ሃኪም ዘግበውታል::) ሸይኽ አልባኒም ሀዲሱን ሰሂህ ከማለታቸውም ባሻገር በአንዳንድ የቲርሚዚይ ኪታብ ህትመቶች ላይ የሚታየው "ከሪሙን" የሚለው ቃል ጭማሪ ከአንዳንድ ፀሀፊዎች ወይም አታሚዎች ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል:: (ሲልሲለቱ አል-አሀዲስ አሰሂሃ) ✍ ጣሀ አህመድ ረመዳን 1442 🌐 https//t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
ኢእቲካፍ አንደኛ፡ ትርጉሙና ሸሪዓዊ ድንጋጌው ‘ኢእቲካፍ’ ማለት አምልኮን አስቦ መስጂድ ውስጥ መቆየት ሲሆን ሸሪዓዊ ብይኑ ሱና ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦ وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَ‌ٰهِۦمَ وَإِسْمَـٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَـٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ البقرة: ١٢٥ “ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን” አል-በቀራህ 125 وَلَا تُبَـٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَـٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَـٰجِدِ البقرة: ١٨٧ “እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”፡፡ አል-በቀራህ 187 አዒሻ ረዐ እንዳሉት “ነብዩ(ﷺ) የረመዳንን የመጨረሻዎች አስር ቀናት እስኪሞቱ ድረስ ኢእቲካፍ ያደርጉ ነበር፡፡”ሁለተኛ፡ የኢእቲካፍ መስፈርቶች 1.ኢእቲካፍ ፈፃሚው ሙስሊም መሆን፣ የመለየት እድሜ የደረሰና አእምሮው ጤናማ መሆን አለበት፡፡ በአንፃሩ ከሃዲ የአእምሮ ህመምተኛ ወይም የመለየት እድሜ ያልደረሰ ህፃን ኢእቲካፋቸው ትርጉም አይኖረውም፡፡ ለኢእቲካፍ አቅመ አዳም (ሄዋን) መድረስና ወንድ መሆን መስፈርቶቹ አይደሉም፡፡ የመለያ እድማ (ሰባት አመት) የደረሰ እንዲሁም ሴት ልጅ ኢእቲካፍ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ 2.ኒያ፦ ነቢዩ (ﷺ) “ስራዎች የሚለኩት በኒያ ነው” ብለዋል:: 3.መስጂድ ውስጥ መሆን አለበት፦ “እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ” ል-በቀራህ 187 ነቢዩም (ﷺ) ኢእቲካፍ የሚያደርጉት መስጂድ ውስጥ ብቻ እንጂ ቤት ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ኢእቲካፍ አድርገው አያውቁም፡፡ ሶስተኛ፡ የኢእቲካፍ ወቅት ተወዳጅ ተግባሮቹና ኢእቲካፍ ላይ ላለ ሰው የሚፈቀዱ ነገሮች 1.የኢእቲካፍ ወቅት፦ኢእቲካፍ ሊባል የሚችለው አንድ ግለሰብ መስጂድ ውስጥ ለተወሰነ ወቅት ሲቆይ እንጂ ምንም ካልቆየ ኢእቲካፍ አይሰኝም፡፡ ትንሹ የኢእቲካፍ መጠንን በተመለከተ በዑለማዎች መካከል የተለያዩ ሃሳቦች ቢኖሩም ነገር ግን የተሻለው አቋም ገደብ የለውም የሚለው ነው፡፡ ይሁንና ከአንድ ቀን ባያንስ የተሻለ ነው ምክንያቱም ነቢዩም (ﷺ) ሆኑ ከሰሃቦች አንድም ግለሰብ ከአንድ ቀን ያነሰ ወቅት ኢእቲካፍ እንዳደረጉ አልተዘገበም፡፡ ኢእቲካፍ ከሚደረግባቸው ጊዜያት በላጩ የመጨረሻዎቹ የረመዳን አስር ቀናት ናቸው፡፡ ይህን በተመለከተ አዒሻ እንዳሉት “ነብዩ(ﷺ) እስኪሞቱ ድረስ የረመዳን የመጨረሻ አስር ቀኖችን ኢእቲካፍ አድርገዋል፡፡” አል ቡኻሪ (2ዐ2ዐ) ሙስሊም (1172) የረመዳን አስር ቀኖችን ኢእቲካፍ ማድረግ የፈለገ የሃያ አንደኛውን ቀን ንጋት ሱብሂ ሰላት ኢእቲካፍ ያሰበበት መስጂድ ውስጥ በመስገድ ይጀምርና የመጨረሻው የረመዳን ቀን መግሪብ ከሰገደ በኋላ ያጠናቅቃል፡፡ 2.የተወደዱ ተግባሮቹ፦ኢእቲካፍ ከሌሎች ጉዳዮች ራሱን አግልሎ መስጂድ ውስጥ የሚቆይበት ተግባር በመሆኑ በኢእቲካፍ ጊዜ ሰላት፣ ዚክር፣ ዱዓ (ፀሎት)፣ ቁርአን ማንበብ፣ ምህረትን መማፀንና ሌሎችንም አምልኳዊ ተግባራት በብዛት መፈፀም ይወደዳል:: 3.ኢእቲካፍ ለሚፈፅም ሰው የተፈቀዱ ነገሮች፦ኢእቲካፍ ላይ ያለ ሰው ምግብ የማይቀርብለት ከሆነ ለመመገብ ለመፀዳዳት ለጀናባ ትጥበትና ውዱእ ለማድረግ ከመስጂድ መውጣት ይፈቀድለታል፡፡ እንዲሁም በጠቃሚ ጉደዮች ከሰው ጋር ማውራት የተፈቀደ ሲሆን ነገር ግን በማይጠቅሙ አሉባልታ ወሬዎች ጊዜውን ማጥፋት ከኢእቲካፍ ዓላማ ጋር ተፃራሪ ነው::ኢእቲካፍ በመፈፀም ላይ ያለን ሰው መጥቶ መጎብኘትና በአንዳንድ ጉዳዮች ማውራት እንግዳውንም ለመሸኘት መውጣት ይፈቀዳል፡፡ ሶፊያ ረዐ እንዲህ ይላሉ “ነቢዩ(ﷺ) ኢእቲካፍ ላይ ባሉበት በምሽት መጥቼ ሰላም ብዬ ትንሽ ካጫወትኳቸው በኋላ ስመለስ ለመሸኘት ተከትለውኝ ወጡ”:: አልቡኻሪ (2ዐ35) ሙስሊም (2175) ኢእቲካፍ ላይ ያለ ሰው የመስጂዱን ንፅህና ጠብቆ መስጂድ ውስጥ መመገብ መጠጣትና መተኛት ይችላል፡፡ አራተኛ፡ የኢእቲካፍ አፍራሾች 1.ያለ ምክንያት ከመስጂድ መውጣት የኢእቲካፍ ዋናው መሰረት መስጂድ ውስጥ መቆየት በመሆኑ ያለምክንያት ትንሽ ለመቆየት ቢሆንም እንኳን ሆን ብሎ ከመስጂድ ውጭ መውጣት ኢእቲካፉን ያበላሻል:: አዒሻ እንዳሉት “ነቢዩ(ﷺ) ኢእቲካፍ ላይ ሆነው ለጉዳይ እንጂ ቤት አይገቡም ነበር፡፡” አል ቡኻሪ (2ዐ29) 2.የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የግብረ ስጋ ግንኙነት በሌሊትና ቤት ውስጥም ቢሆን ኢእቲካፍን ያፈርሳል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦ وَلَا تُبَـٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَـٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَـٰجِدِ البقرة: ١٨٧ “እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”፡፡ አል-በቀራህ 187 ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጭ የዘር ፈሳሽ እንዲፈሰው ማድረግም ኢእቲካፍን ያፈርሳል:: 3.የአእምሮ ጤና ማጣት፡- በእብደት ወይም በስካር አእምሮን ማጣት ኢእቲካፍን ያበላሻል:: 4.የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መምጣት ኢእቲካፍን ይበላሻል፡፡ 5.ከእስልምና መውጣት፡- ከእስልምና መውጣት ስራን ሙሉ በሙሉ ያበላሻል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ الزمر: ٦٥ “ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል”፡፡ አል-ዙመር 65 ምንጭ፦አል ፊቅሕ ሙየሰር ------------*********------------- © ዝክረ ረመዳን አፕ ሸዕባን 2010 Ibnu Mas'oud Islamic Center
إظهار الكل...
〰〰〰〰〰〰 🌙 ከረመዳን የመጨረሻዎቹ ➓ ቀናት🌙 የእነዚህን አስርት ቀናት እና ለሊቶች ታላቅነት የሚያሳየን በውስጣቸው ‹‹ለይለተል ቀድር›› የተባለችው ለሊት መኖሯ ነው፡፡ ይህች ለሊት ከሌሎች የምትለይበት ብዙ መለያዎች ያላት ስትሆን ከነርሱም መካከል ኢንሻ አላህ በጥቂቱ:- ↓ ↓ ↓ ↓ ↓ ↓ ↓ ↓ ↓ ↓ ↬ቁርዓን የወረደባት ለሊት መሆኗ ↬ከ1ሺህ ወራት የምትበልጥ መሆኗ ↬የተባረከች መሆኗ ↬ጅብሪል ዐ.ሰ በመልዕክት በብዛት የሚወርድባት መሆኗ ↬ሰዎች በከፍተኛ አምልኮ ውስጥ የሚገቡ ከመሆኑ አንፃር ከእሳት ነጃ ወይም ነፃ የሚወጡባት ለሊት መሆኗ! በእነዚህ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ መግባት የመልዕክተኛው ሱና ነው፡፡ ኢዕቲካፍ ማለት እራስን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ መዘውተር ነው፡፡ እናታችን ዓኢሻ [ረ.ዐ] እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹ነብዩ {ሰ.ዐ.ወ} እስኪሞቱ ድረስ ከረመዳን የመጨረሻዎቹን አስርት ቀናት እራሳቸውን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ ይዘወትሩ ነበር፡፡›› ✍ ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውተል ይቀላቀሉን 🔽 @click2Join @click2Join @click2Join
إظهار الكل...
----------------- ረመዳን -- ቁርአን የወረደበት ወር -- የጀነት በሮች የሚከፈቱበት የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት -- ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር -- ከሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት የያዘ ወር -- ከምንጊዜውም በበለጠ ዒባዳ የሚደረግበት ወር -- አንድ ባሪያ አላህ ከፈቀደለት ነገሮች ራሱን በማቀብ አላህን ፍራቻ 'ተቅዋ' የሚያገኝበት በረመዳን -- ምንዳቸው ገደብ ከሌላቸው ሰራዎች መካከል አንዱ የሆነው ፆም ወር ሙሉ ይከናወናል። • እነዚህና ሌሎች መልካም ነገሮችን የያዛ ወር ስለሆነ ይህንን የተከበረ ወር ለአመታት ደጋግመው ከሚያገኙትና መልካም ነገርንም ከሚሸምቱበት አሏህ ያድርገን.... አሚን ------------- @click2Join @click2Join @click2Join
إظهار الكل...
7.36 MB
#ጌታዬ_ሆይ! ይቅር ካልካቸው፣ ስራቸውን ከወደድካላቸው፣ ወንጀላቸውን ከማርክላቸው፣ ከእሳት ነፃ ካልካቸው፣ ጀነተን ከ ፃፍክላቸው፣ ባሮችክ አድርገን!🤲
إظهار الكل...
___________________________ ዉዱ ነቢያችን ﷺ ምን ይላሉ የ 3ት ሰዎች ዱዓእ ተቀባይነት ኣላቸዉ #የፆመኛ #የተበዳይ #የመንገደኛ ስለዚ ረመዳን እንጠቀምባት ዱዓ እናብዛ ... '' ኣለህ ሆይ በዱንያም በኣኺራም ጥሩ ነገር ግጠመን '' ----------------------- @click2Join @click2Join @click2Join
إظهار الكل...
ይህ ነው የኛ ኢስላም! =========== ሁላችንም ሼር እናድርገው ስለ አንድ ሀይማኖት እውነተኛ ይዘት ለመረዳት ወደ ትክክለኛ መዛግብቱና ምንጮቹ መመለስ አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። ይህ ሲሆን ግን መመሪያዎቹንና አንቀፆቹን በቁንፅል እይታና በጥራዝ ነጠቅ መዘዛ እየገመገሙ ለፍርድ መቻኮል ታላቅ ስህተትን ያወርሳል፤ ለበደልም ያበቃል። የእምነቱን ሁለንተናዊ ይዘትና አስተምህሮት መገንዘብ የሚቻለው አናቅፁን በታትኖ ሳይሆን ሰብስቦ፣ አራርቆም ሳይሆን አቀራርቦ ነውና። በአንድ ቦታ ያልተብራራው በሌላ ቦታ ይብራራል፤ እዚህ ጋር ያልተገደበውም እዚያ ጋር ሊገደብ ወይም መስፈርቱ ሊገለፅ ይችላል። ከዚህም ጋር ቃሉ የተነገረበትን አገባብና አኳያ ማስተዋል የግድ ነው። በጥናት ሂደት ላይም በአሻሚ ገለፃዎች ላይ ከመንጠልጠል ወደ ግልፅ መመሪያዎች መመለስ ይገባል። ይህን መተግበር የአንድ ዘርፍ ምሁራን ከሰርጎ ገቦች ከሚለዩባቸው ነጥቦች አንዱ ነው። ይህን እንደመግቢያ ከተረዳን ዘንድ ወደ አንድ ሁነኛ ምሳሌ እንሸጋገር፦ ሙስሊሞች ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በሚኗኗሩበት ሂደት ሊከተሉት ስለሚገባቸው አጠቃላይ ስርዓት ኢስላም ያሰፈረውን ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው በጦረኛ ጠላቶች ላይ ውጊያ በታወጀባቸው አንቀፆች በኩል አይደለም። እነዚህ በውስን የጦርነት ሂደት ላይ ብቻ ሊተገበሩ የሚችሉና በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች የተከበቡ ህግጋት እንጂ የሁልጊዜ ደንቦች አይደሉም። -› ይህንን ከሚያብራሩት አንቀፆች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፦ لَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُمْ مِنْ دِيَارِكُمْ أَنْ تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ * إِنَّمَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ قَاتَلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَأَخْرَجُوكُمْ مِنْ دِيَارِكُمْ وَظَاهَرُوا عَلَى إِخْرَاجِكُمْ أَنْ تَوَلَّوْهُمْ = {ለእነዚያ በሀይማኖታችሁ ላልተጋደሏችሁና ከአገራችሁ ላላስወጧችሁ በጎ ብታደርጉና ፍትህን ብትውሉ አላህ አይከለክላችሁም፤ አላህ ፍትኸኞችን ይወዳልና። አላህ የሚከለክላችሁ እነዚያ በሀይማኖታችሁ (የተነሳ) የተጋደሏችሁንና ከአገራችሁ ያስወጧችሁን እናንተን በማስወጣትም ላይ ያገዙትን እንዳትወዳጇቸው ነው።} [አል-ሙምተሒነህ 60 ፡ 8-9] ይህ ሌሎችን ሙስሊም ስላልሆኑ ብቻ መግደል እንደማይቻል ያሳያል፤ በየትኛውም የታሪክ ማህደር ሙስሊሞች ሌሎችን ኢስላምን ስላልተቀበሉ ብቻ ገድለው አያውቁም። በኢስላማዊ አስተዳደር ውስጥ ለምዕተ አመታት የኖሩት ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ተገድደው ኢስላምን እንዳልተቀበሉ ተጨባጩ አለም ይመሰክራል። ይህም ማለት የግዛቱ መተዳደሪያ ህግ ቁርኣናዊ ሆኖ ሳለ መብታቸው በጥቅሉ ተጠብቆ ነበር ማለት ነው። አደራ! እንደነ isis ያሉትን ቡድኖች እዚህ ርዕስ ላይ ማስገባት ራሱ ስህተት ነው! እነርሱ ከማንም ይልቅ የገደሉት ሙስሊሞችን ነውና! በዚህ ላይ ደግሞ ስለማንነታቸው የምንለው፦ ውስጡን ውስጠ-አዋቂ ይወቀው፤ ነው! እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ጥቂት ግለሰቦች በኢስላም ስም ለሚፈፀም የደም መፍሰስ ሁሉ ክቡሩን ቁርኣን ተጠያቂ ያደርጋሉ፤ ወይም ሀማኖቱን ራሱ ይኮንናሉ። ይህንን የሚያናፍሱት አብዛኛዎቹ ሙግተኞች መረጃዎችን ከላይ በጠቆምነው መልኩ ለማገናዘብ ብቃቱ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱም የላቸውም! . . . . ይህ ነው የኛ ኢስላም!! በኢልያስ አህመድ ሙሉውን ያንብቡት! የኢስላም ጠላቶች ለሚነዙት ውዥንብር አርኪ ምላሽ ያገኛሉ። በሚከተለው አስፈንጣሪ በዚሁ በቴሌግራም ያንብቡ... https://t.me/iv?url=https%3A%2F%2Ftewhidfirst.blogspot.com%2F2015%2F06%2Fblog-post_15.html&rhash=e0afe308584546 👍🏻👍🏻 SHARE 👍🏻👍🏻 ፌስ ቡክ ላይ አንብቦ ሼር ለማድረግ https://www.facebook.com/397552227770329/posts/446515572873994 የፌስቡክ አድራሻችን https://www.facebook.com/ustathilyas
إظهار الكل...
ይህ ነው የኛ ኢስላም!

Ilyas Ahmed *** ይህ ነው የኛ ኢስላም! *** ================= ስለ አንድ ሀይማኖት እውነተኛ ይዘት ለመረዳት ወደ ትክክለኛ መዛግብቱና ምንጮቹ መመለስ አማራጭ የሌለው እርምጃ...

✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏ እችን ወር በ ረመዳን ብርሃን ኣረግክልን ተጠቅመን ሰዎችንም ምንጠቅምም እንድታረገንም እንማፀንሃለን። ብዙ ሰዉ ቸግሮታል እሚበላዉም ኣጥቶዋል ... ያለንን እናካፍል ጠፊ በሆነዉ ብር ዉብ የሆነችዉን ጀነትን እንግዛ። ሓቢባችን ምን ይላሉ '' ከናንተ ኣነዳቹም ኣላመነም ለራሱ ሚወደዉን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ '' ጥሩ ነገር እንወድ የለ ? ስለዚ ስንሰጥ የተበጣጠሰና ትርፍራፌ ነገር ኣንስጥ ደህና የሆነ ነገር ኣላህ ደሞ ምንዳን ሚያሳጣ ኣይደለም ✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏ ኣንብቡ መልካም ስለ ሆነም ሼር ያድርጉ @click2Join @click2Join @click2Join
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.